ከመጽሐፍ ገጽ 📚😍


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


"There is no friend as loyal as a book"
Ernest Hemingway
unlimited quotes💭
Daily book recommendation 📚
Music to vibe to 🎶
Deep dives into the epic novels📖
Short stories🖋 and thoughts🤔
We forever live between the pages💖

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


Good morning loves


"ብዙ ነገር ይረሳል።
በተለይ አቅመ ቢስ ከሆንን ብዙ ነገር እንረሳለን።
ካልረሳን እናብዳለን።
ካበድን፤ እብድ ተብለን ልንሰደብ ነው ደ'ሞ።

ጤንነት ያምራል
ጤንነት ይሻላል"

#ግራጫ_ቃጭሎች
#አዳም_ረታ


አንድ ዘመን ላይ ይህ ላለመፈጠሩ ምን ዋስትና አለን?🥺


𝔱𝔥𝔢 𝔤𝔬𝔬𝔡 𝔫𝔢𝔴𝔰 𝔦𝔰… 𝔶𝔬𝔲 𝔡𝔬𝔫’𝔱 𝔥𝔞𝔳𝔢 𝔱𝔬 𝔟𝔢 𝔦𝔫𝔳𝔦𝔫𝔠𝔦𝔟𝔩𝔢




Good morning loves 🥺😊


"....ዛሬ ዛሬ ሙሉ በሙሉ የተረዳሁት የሐበሾች ስር ነቀልነት መሰረቱ ስሜት መሆኑን ነው።

ከዐሥረኛ ፎቅ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሆሆሆ ብለው እርስ በእርስ ተነዳድተው እየተንበለበሉ ይወድቃሉ።

ለእነሱ ዋናው ጉዳይ መውደቁ ሳይሆን ከፋም ለማም እጅ ለእጅ መያያዙ ነው። በሰው የደረሰበት ቢደርስባቸው ስህተት አይደለም።

ማሰብ የሚጀምሩት በመዋግደ ሕሊና ግፊት በመውደቅ ጎዳና ላይ ስምንተኛው ፎቅ ሲደርሱ ነው።

ወደ የት እየሄድን ነው? ይላሉ
ፓራሹቱን ይዘሃል ወይ? ይባባላሉ።

አምስተኛ ፎቅ ጀምሮ ወሬአቸው ጭቅጭቅና ፀፀት ነው። እስከ ዜሮ ፎቅ የሚቀጥለው ጉዞ በጸሎት የታጠረ ምሬት ነው። በየደጀሠላሙ መንበርከክ ነው። ነጫጭ ለብሶ በክራላይሶ መንደድ ነው። ለ'ተለመነኝ' በሚያጤሱት ዕጣን መታፈን ነው። እግዜር በምሬት ይገጠምበታል፣ የሚረገም ይረገማል፣ ስለት ይገባል፣ ጥንቆላ ይጠነቆላል።የሚታማ ማሰስ ነው። እጃቸውን የያዘው ደባል ዘላያቸውን ሰው መርገም ነው። ወደ ኋላ እየተመለሱ በአጀማመራቸው ማሳበብ ነው።

መሬት ወድቀው በትዕንግርት ከመሰባበርና ከመሞት ቢድኑ፣ የአወዳደቃቸው ዚቅ ሊያርሙ እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ተያይዘው ወደ ፎቁ ይወጣሉ።

ስህተቱ መውደቁ ሳይሆን አወዳደቃቸው ይመስላቸዋል። ይሄ የማያቋርጥ ክብ የእኛ ነው።

#የስንብት_ቀለማት
#አዳም_ረታ


Good night loves 🧐


"I'm on the edge of the abyss, but the view from here is exceptional."

- Tracey Emin... 🖋️


" . . .  ሲጋደም ሀበሻ የሚያስበው ትላንትናን እና ነገን ነው። ብዙ ግዜ ያለፈ አመቱን ነው። ሲወለድ እናቱ ያላሰችውን ቅቤ ነው።

ሀበሻ ከማንም ዜጋ የበለጠ ታሪካዊ እንስሳ ነው።

ታዲያ "ዛሬ" የተባለች የጊዜ መለያ በአጠገቡ እያፉዋጨች ስታልፍ አያያትም። እንደገናም፡ ነገን ላገኝ ብሎ፡ ለሆነ ቆራጣ ራእይ ዛሬ ሸር ሲሰራባት፡ ሲጠልፍባት፡ በፖለቲካ ሲናከስባት፡ ሲብጠለጠልባት የሚመኛት ነገን በዛሬ ሲያፈርስ ጊዜ ያልፋል"

#ይወስዳል_መንገድ_ያመጣል_መንገድ
#አዳም_ረታ






A DAILY REMINDER

Andrew good morning loves❤️


"ልጆች ደስ ትሉኛላችሁ።

አሮጌዎቻችሁ ያስጠሉኛል።

እናንተንም እንደነሱ እንድትከፉ ያስጠኑአችኋል።

ያስተማሩ እየመሰሉ ያጠፏችኋል . . .

እስኪ ሕፃናት እንኳን አዲስ አይን አውጡ"

#ማሕሌት

#አዳም_ረታ


'ጥናት ከሌለ ዕውቀት የለም።
ዕውቀት ከሌለ መለወጥ የለም።

ልበሙሉነት ብቻውን ያለ ትክክለኛ መረጃ ምንም ነው።

ሳታውቅ 'አውቀሃል' ካለህ አገልግሎትህ መስዋዕት መሆን ብቻ ነው።

ማወቅ ሲገባህ ካላወቅህ ደደብ ነህ'

መረቅ
-አዳም ረታ
#አዳም_ረታ


Have a good night loves


Sometimes it is okay to lose, to give in , and let it consume you.




ሀ..ሁ የምትችል ከሆነ በፅሁፍ ፤ የማትችል ከሆነ በወሬ ታሪክህን ንገር።

ዘመናት ያቆራኛል። አየህ፤ ሁሉ ነገር ይደጋገማል።

ነገር በወሬ ከጠፋ፤
ነገር ለምን በወሬ አይነሳም?

ግራጫ_ቃጭሎች
-አዳም ረታ
#አዳም_ረታ


Good morning 🎆
#Aesthetic

Показано 20 последних публикаций.