Фильтр публикаций


Festivaalli Dorgommii tapha kubbaa miilaa Yunivarsiitii Bulee Horaan qophaa'e jalqabe.


ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አከባቢ ያሉ እና በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች መሠረታዊ የኮፒዩተር ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ። ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡ https://web.facebook.com/BuleHoraUniversity/


ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለዋናው ግቢ እና ለማስተማሪያ ሆስፒታል ፖሊስ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡ https://web.facebook.com/BuleHoraUniversity/


ሚያዝያ 25/2017 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህብረሰብ ጋር ውይይት አካሄዱ።
**************************************************************
በውይይቱ ላይ ከትምህርት ሚኒስትሩ በተጨማሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ፣የትምህርት ሚኒስቴር የክትትልና ግብረ-መልስ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ፣ም/ፕሬዝዳንቶች፣መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ተሣታፊ ሆነዋል።

ውይይቱን የመሩት የፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የውይይቱን ዓላማ በሚመለከትት ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር በመማር ማስተማር፣በምርምርና በማህብረሰብ አገልግሎት ሥራ እና በሌሎች ጉዳዮች እያከናወነ ያለውን ሥራ በሚመለከት ቀደም ሲል የትምህርት ሚኒስቴር ሱፔርቭዥን ቡድን ግምገማ ባደረጉት መሠረት ግብረ መልስ ለመስጠትና ተጨማሪ ውይይቶችን በማድረግ ዩኒቨርሲቲውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ታሳቢ ያደረገ ውይይት መድረክ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በተነሱት ጥያቄዎች አስተያየቶች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በዶ/ር ብርሃኑ ለማና የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተጀመረው የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑና ይህንንም ከማረጋገጥ አኳያ ዩኒቨርሲቲዎች ዋነኛ ተዋናይ እንዲሆኑ የጠየቁ ሲሆን የሚነሱትን በርካታ የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ የመምህራንን ባንክ ለማቋቋም የተጀመረው ሂደት በጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ስለመሆኑ አፅኖት ሰጥቶ አስረድቷል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
በአሁኑ ሰዓት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ``Mineral Resource Exploitation፡ for Economic and Environmental Impacts``በሚል ዎርክሾፕ እየተካሄደ ይገኛል።



Показано 6 последних публикаций.