Deacon Chernet


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን
2ኛ ጴጥ 3፡18
በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን እንኑር !
ጥቆማ ወይም ጥያቄ ካላቹ በዚህ የተለግራም ቦት👉🏽https://t.me/Cher2112bot ይጠቀሙ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ክፉ ሰዎች ፣ አጋንንትና ዲያብሎስ በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ለምን አንደ ኾነ?

“እነዚህ ኹሉ እንዲኖሩ ለምን እንደ ፈቀደ ብትጠይቅ ፣ ስለማይነገረው የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ቦታ ባትሰጥ ፣ ኹሉንም ነገር እጅግ አጥብቀህ ብትመረምር ፣ ይህንንም ብትዘልቅበት ሌሎች ብዙ ነገሮችን ታጣለህ፡፡

ለምሳሌ ፦ መናፍቃን በዚህ ዓለም ላይ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ለምን ፈቀደ ? ለምን ዲያብሎስ እንዲኖር ፈቀደ ? ለምን አጋንንትስ ? ብዙ ሰዎች እንዲሰናከሉ የሚያደርጉ ክፉዎች ሰዎችስ ? ከዚህ ኹሉ በላይም ጌታችን ክርስቶስ እንደ ተናገረ ፥ ቢቻለውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ ኃይል ያለው የክርስቶስ ተቃዋሚ የሚመጣው ለምንድን ነው? [ማቴ.፳፬፥፳፶]

ስለማይመረመረው የእግዚአብሔር ጥበብ ኹሉን ነገር መተው እንጂ እነዚህን ነገሮች ልትጠይቅ አይገባህም፡፡ አስቀድሞ በእውነትና በጽኑ መሠረት ላይ የቆመ ሰው ብዙ ሞገዶች ቢያላትሙት እንኳን ፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ማዕበላት ሲነሣሡበት እንኳን አይጎዳም ብቻ ሳይኾን እንዲያውም የበለጠ ብርቱ ይኾናል፡፡

ደካማ ፣ ልፍስፍስና ግድ የለሽ ሰው ግን ምንም መከራ ባይገጥመውም እንኳን አዘውትሮ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱ ምን እንደ ኾነ ማወቅ ከፈለግህም በኹላችንም ዘንድ በደንብ የታወቀውን አድምጠው፡፡ በብዙና ልዩ ልዩ በኾነ መንገድ በእኛ ላይ የሚኾነውን እያንዳንዱን ነገር የሚያዝዘው እግዚአብሔር ሌሎች ብዙ ግልፅ የኾኑ ምክንያቶችም አሉትና፡፡

እስከዚያው እኛ የምናውቀው ይህንን ነው ፦ እነዚህ መሰናክሎች እንዲመጡ የፈቀደው ቅዱሳን የሚያገኙት ክብር እንዳይቀንስ ነው ብለናል። እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር ሲነጋገር ግልፅ ያደረገው ይህንን ነው ፦ “ ጽድቅህ እንድትገለጥ እንጂ እኔ በሌላ መንገድ የምፈርድብህ ይመስልሃልን? ” እንዲል። [ኢዮ.፵፥፰]

እንደዚሁም ቅዱስ ጳውሎስ ፦ “በእናንተ ዘንድ የተፈተኑት [የተመሰገኑት የተመረጡት] እንዲገለጡ ፥ በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” አለ [፩ኛ ቆሮ.፲፩፥፲፱] “በመካከላችሁ መለያየት [ምንፍቅና] ደግሞ ሊኾን [ሊኖር] ግድ ነውና” የሚለውን በሰማህ ጊዜ ግን ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የተናገረው እንደ ትእዛዝ ወይም እንደ ሕግ አድርጎ እንደ ኾነ አታስብ፡፡ በጭራሽ አይደለም ! ይልቅ ፥ ሊመጣ ያለውን ነገር ትንቢት እየተናገረና ትጉሃን ከዚያ እንደሚያተርፉ ነው እያመለከተ የነበረው፡፡

“ከዚያም ያልተታለላችሁ የእናንተ ሃይማኖታችሁ ምግባራችሁ ይገለጣል” አለ፡፡"

[#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ]

@deaconchernet
@deaconchernet
@deaconchernet


#ጾመ ነቢያት ነገ እሑድ ኅዳር 15 ይገባል

መልካም ጾም ይሁንልን!

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#መልስ: ሰይጣን ሰዎችን ከሚጥልበት መሰናክሎች አንዱ ውዳሴ ከንቱ፣ ያልሆኑትን አድርጎ ማሳየት ነው።

በዚህም ብዙ መንፈሳውያን ተሰነካክለው ወድቀውበታል። አንድ ሰው ከሰዎች ሙገሳ ቢቀርብለት ''አቦ አቦ ካላንተ ሰው የለም" ቢባል ይህንን አመለካከት ለማቆም አይችል ይሆናል። ነገር ግን የራሱን ኃጢአት በማሰብ ሰዎች እንደገመቱት ጻድቅና ቅዱስ አለመሆኑን በመረዳት ራሱን ለንስሓ ማዘጋጀት ግን ትልቅ ጥበብ ነው።

ወንድማችን፦ የሰዎችን የውዳሴ ከንቱ ንግግር ለጆሮህ ስማው እንጂ ወደ ልብህ እንዲገባ አትፍቀድለት። ሰዎች ምንም ይበሉ ምን አንተ ቦታ ካልሰጠሃቸው በውዳሴ ከንቱ ተጠልፈህ ልትወድቅ ስለማትችል የምትሰማው ነገር ከልኩ ካለፈ ቦታ አትስጠው። በሌላ በኩልም ያልሆንከውን ነህ ብትባልም ለመሆን መጣር እንጂ ተስፋ ቆርጠህ መቀመጥ አይገባህም። ኃጢአትህ ባለመገለጡ ያልገለጠህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ለአለም ያልተገለጠውን በደልህን ለንስሓ አባትህ ተናዘዝ!

እግዚአብሔር ራሳችንን ወቅሰን እንጸጸት ዘንድ ይታገሰናል፤ በዚህ ትዕግስቱ ካልተመለስን ግን በደላችንን ለፍጥረታት ለፍጥረታት ሁሉ ይገልጥብናል። ኋላም የሚሸፍነው ማንም አይኖርም። የሆነው ሆኖ በአጉል ትኅትና አይገባኝም፣ እኔ ለዚህ አልበቃሁም እያልክ ራስህን ከቅድስና ሕይወት እንዳትለይ ተጠንቀቅ!

ሰይጣን ከንቱ እንደሆንክና ለምንም ነገር እንደማትበቃ አድርጎ በማሳየት የልብህን ሰላም ነሥቶ በውስጥህ ጭንቀት ፈጥሮ ከንሰሓና ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቅህ ይችላልና። ስለዚህ "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" የሚለው ስሜትህ ከገደብ አልፎ ከእግዚአብሔር ቤት እንዳይለይህ ትኅትናህን በልኩ አድርገህ በንስሓ ራስህን አስተካክል!

አቤቱ እኔስ እውነተኛውን እራሴን ሳውቀው ምንም ዋጋ በማያሰጠው ከንቱ ውዳሴ ለምን እጠለፋለሁ፤ አንተ የእውነት ጠራኸኝ እኔስ የእውነት መምጣት ለምን አቃተኝ፤ ሰዎች የደረቡብኝ የውዳሴ ካባ ጎተተኝ፤ እነሱስ ለክፋት አልነበረም ለኔ ግን ለጥፋት ሆነብኝ፥ ጌታ ሆይ አንተን ዘንግቼ ይጠቅሙኛል ብዬ በእጄ የያዝኳቸው፣ ያበረቱኛል ብዬ የተደገፍኳቸው፤ ለውበትም ያጌጥኩባቸው እንደ ባለማዕረግ በእራሴ የደፋኋቸው ለልቤ ስብራት መጠገኛ ለዕንባዬም ማባበሻ የማይጠቅሙ ከንቱ ናቸውና አቤቱ ከዚህ ክፉ ደዌ አድነኝ!

ምሥጢሬን ላካፍላችሁ የተወሰደ

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#እግዚአብሔርን ያታለልኩ እየመሰለኝ እጨነቃለሁ።

#ጥያቄ: እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ምን ያህል ኃጢአተኛ እንደነበርኩ ራሴን አውቄለሁ። በአካባቢዬ ያሉት ሰዎች ግን እኔን በጣም ጥሩ ክርስቲያናዊ ሕይወት ያለው ራሱን ለእግዚአብሔር ያስገዛ ሰው አድርገው ይመለከቱታል!

በመሆኑም እዉነተኛው ሕይወቴና ሰዎች ለእኔ ያላቸው አመለካከት እየተጋጨብኝ፣ ኅሊናዬ እየተረበሸ፣ እግዚአብሔርንም እያታለልኩ ያለሁ እየመሰለኝ ነውና ምን ትመክሩኛላችሁ ?


#ኦርቶዶክሳውያን ደናግል መልኣካዊ ኑሮን ሲመኙና እርምጃቸው ወደ ሰማያዊው መንግስት ሲሆን፥ አስቀድመው ዐይነ ልቦናቸውን ከሰማያዊው ንጉሥ በቀኝ ወደተቀመጠችው፤ ከወርቅ በተሠራና በተለያዩ ኅብረ ቀለማት ባሸበረቀ መጋረጃ ወደተጋረደችው፤ በላይ በሰማይ ወዳለችው ወደ ቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያም ይሰቅላሉ። ባይነቷንና ፍቅሯን፤ ያንጸባርቃሉ፣ ምርጫቸው እርሷን መከተል ነውና የሕይወትን ቃል ያስተጋባሉ። ጆሮኣቸውን ወደ እርሷ አቅንተው ወገናቸውን፣ የኣባታቸውንም ቤት ይረሳሉ። እርሷ ወደ ንጉሡ መዳረሻ መሰላላቸው እንደ ሆነች በኣግባቡ ተረድተዋልና፥ መከተላቸውም ከንጉሡ ዘንድ እደሚያደርሳቸው ያውቃሉና፤ በመንፈስ ከእርሷ ጋር በመሆን የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ሆነው ይኖራሉ።

ጣዕመ ፍቅራቸውን በልቦናችን ያሳድርብን። አሜን።

ምንጭ: ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋሕዶ ፩ ( ውርስ ትርጉም በአዜብ በርሄ)

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#በዓለ_ደብረ_ቁስቋም

ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቊስቋም ላይ ያረፉበችበት ኅዳር ፮ ቀን ይከበራል፡፡

የቁስቋም ተራራ ጌታችን ኢየሱስን ለመግደል ከሚፈልጉት ሸሽተው መጠጊያ ያገኙበት እንዲሁም ቅዱስ ገብርኤል ንጉሥ ሄሮድስ መሞቱን ለቅዱስ ዮሴፍ በሕልሙ የገለጸበት ስፍራም ጭምር ነው፡፡ ‹‹የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሞተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ›› እንዲል። (ማቴ.፪፥፲፱-፳)

ቁስቋም ተራራ ጌታችን ብዙ ተዓምራት የፈጸመበት በመሆኑ ተባርኳል፤ ተቀድሷልም፡፡ ይህ ተራራ የተቀደሰ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ ብሏል፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፤ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

ሊቁም በመቀጠል ሙገሳውን እንዲህ ሲል ገልጿል፤ ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በዚህም ተራራ ስድስት ወራት ዐርፈዋል፡፡ (ድርሳነ ማርያም)

በየዓመቱ ኅዳር ፮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡ ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ጌታችን ኢየሱስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

እመቤታችን ቅድስት ማርያም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር ከመሰደዷ አስቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብፅ እንዘ ይጼዐን ዲበ ደመና ቀሊል፤ ጌታችን በፈጣን ደመና (በእመቤታችን ጀርባ) ተጭኖ ወደ ግብፅ ይወርዳል›› ተብሎም በተናገረው መሠረት ትንቢቱ ተፈጽሟል፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩)

ኅዳር ፮ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ ጌታችንም ካረገ ከብዙ ዘመናት በኋላ በኅዳር ፮ ቀን ‹‹አስተጋብኦሙ እግዚእነ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ውስተ ዝንቱ ደብረ ቊስቋም ወቀደሰ ታቦተ ወቤተ ክርስቲያን ወሠርዐ ቊርባነ ወመጠዎሙ ሥጋሁ ቅዱሰ
ወደሞ ክቡረ፤ በዚህ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው፤
ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ
ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል›› ይላል፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፮)

እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም በመምህር ተስፋ ሚካኤል፤ ፳፻፫ ዓ.ም፣ ስንክሳር ኅዳር ፮

@deaconchernet
@deaconchernet
@deaconchernet


#ምጽዋት ፍፁም ናት ለሚሰራትም ጠባቂው ናት!!'

#እኔስ ሀብቴን ብልና ዝገት በማያጠፉት፣ ሌቦችም አጥሩን ጥሰው፣ ግድግዳውን ወይም አጥሩን አፍርሰው፣ ጉድጓዱን ምሰው በማይወስዱበት ስፍራ፤ ህልፈትና ጥፋት በሌለበት በሰማያዊ መዝገብ አከማቻለሁ።

እናንተስ??

#ለጽጌ የነዳያን ምገባ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲን በአሁኑ እሁድ በሚደረገው በጎ አድራጎት ተሳተፉ ችላ አትበሉት የምትችሉትን ሞክሩ ዋጋው ብዙ ስለሆነ!

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ፡ ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፣
የሐና አበባ እዘምርልሻለሁ ፡ የደስታንም መንገድ አስተውላለሁ፣

ማእከለ ማኀበር እዜምር ፡ ማእከለ ማኀበር።
በማኀበር መካከል እዘምራለሁ።

ወረብ ዘማኀሌተ ጽጌ (ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን) ዘኀዳር 1

#ናሁ ተፈጸመ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር።
እነሆ ተወዳጁ የጽጌ ማኀሌት ተፈጸመ።

በረድኤት፣ በጠብቆቱ ያልተለየን፣ ቸር፣ መሐሪ ፣ ይቅር ባይ፣ ሰውን ወዳጅ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ በሁሉም ቦታ ያለ፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ፣ ዘመናትን እያሳለፈ ለዘለዓለም የሚኖር፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው አልፋና ኦሜጋ ፤ ለዛሬዋ ዕለት ያደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁንልን።

ለዛሬዋ ዕለት ያደረሰን እግዚአብሔር አምላካችን በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅር፣ በአንድነት ጠብቆ ለከርሞውም እንዲያደርሰን ቅድስት ቸርነቱ ትርዳን።

እመቤታችን አትለይን፣ ጸሎቷ ፣ ፍቅሯ ፣ ምልጃዋ አይለየን፣ የቅዱሳኑ ሁሉ ረድኤት፣ በረከት ምልጃ አይለየን።

አሜን!

@deaconchernet
@deaconchernet
@deaconchernet


#ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና

እንቅልፍ ሲበዛ የስንፍና ምልክት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: "ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ" ፤ "የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳል" የሚሉት ጥቅሶች ለዚህ ምስክር ናቸው:: (ምሳ. 20:13 ፤ 23:21)

#ሆኖም በእንቅልፋቸው የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችም አሉ:: አንቀላፍቶ ሚስቱን ያገኘው አዳም እንዴት ይረሳል? ከኤሳው ጋር ሲታገል የኖረው ያዕቆብ ሲባረክ ያደረውስ በእንቅልፉ አልነበር? ያዕቆብማ ምነው ባልነቃ ያሰኛል:: ሰማይ ድረስ መሰላል ወጥቶ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየው በእንቅልፉ ምክንያት ነበር:: በባቢሎን ምርኮ ዘመን የነበረው አቤሜሌክ ደግሞ የእንቅልፋሞች ንጉሥ ቢባል አያንስበትም:: የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ብሎ ሲጸልይ የነበረው ይህ ሰው በፈጣሪ ፈቃድ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ያህል ተኝቶ ነበር:: ከእንቅልፉ ሲነሣም እንቅልፍ ሳይጠግብ እየተበሳጨ ነበር:: ማንቀላፋቱ ግን ብዙ ጉድ ከማየት አዳነው:: (ተረፈ ኤርምያስን ይመልከቱ)

ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአቤሜሌክን የእንቅልፍ ክብረ ወሰን የሰበሩ ሰባቱ እንቅልፋሞች (The Seven Sleepers) የተሰኙ ቅዱሳንን እንተዋወቅ:: ወቅቱ የሮም ነገሥታት አላውያን የነበሩበት ክርስቲያኖች በግፍ እየተገደሉ የነበረበት ዘመነ ሰማዕታት ነው:: ክርስቲያን መሆን ወንጀል በነበረበት በዚያ ወቅት ክርስቲያኖች ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በመስቀል እየተሰቀሉ በሰይፍ እየተቀሉ እየሞቱ የነበረበት ዘመን ነው::

በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት (249-251) ታዲያ በንጉሣዊ ምክር ቤቱ ውስጥ አባል የነበሩ ሰባት ወጣት ልዑላን ድንገት ክርስትናን ተቀብለው "ለጣዖት መሥዋዕት አንሠዋም" ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ይህን በማድረጋቸው የሚከተለውን ጽኑ ቅጣት ያውቁ ነበረና ፈርተውም በቅርብ ወዳለ አንድ ተራራ ሸሽተው በዋሻ ውስጥ ተደበቁ፡፡

በዚያ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው እያሉ ታዲያ ሰባቱንም እንቅልፍ ይጥላቸዋል፡፡ ንጉሥ ዳክዮስ አሳድዶአቸው ሲመጣ ተኝተው እንዳሉ ያያል:: አውሬው ንጉሥ ሁኔታውን ሲያውቅ እዚያው ዋሻ ውስጥ ይሙቱ ብሎ የዋሻውን መግቢያ በር በግንብ አስደፍኖት ሔደ፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ወጣቶቹ እንቅልፍ ላይ ናቸው::

ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ከሆነ በኋላ እነዚህ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው ይነቁና የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከእነርሱ አንዱን ወደ ከተማ ሔዶ ምግብ እንዲገዛላቸው ይልኩታል፡፡

ዋሻው የተዘጋበት በር ከዘመን ብዛት ፈርሶ ነበርና የተላከው ወጣት ከዋሻው በቀላሉ ወጥቶ ወደ ከተማ አቀና፡፡ ወደ ከተማ ገብቶ ለሰባቱም የሚበቃቸውን ምግብ አገኘና ሂሳብ ሊከፍል ከኮሮጆው ሳንቲም አወጣ፡፡ ያወጣው ገንዘብ ግን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት መገበያያ የነበረውን ‘የጣዖት አምላኪዎቹን’ ነገሥታት የወርቅ ሳንቲም ነበር፡፡ ሰባቱ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከእንቅልፍ የነቁበት ያ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ የኤፌሶን ከተማ ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊት ከተማ በሆነችበት ደግ ዘመን ነበር፡፡

የሰባቱ ወጣቶች ዝና ወዲያው በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያን ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ደረሰ፡፡ ወጣቱ ወደ ዋሻው ከተመለሰ በኋላ ግን ሰባቱም ቅዱሳን ድጋሚ እንቅልፍ ጣላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲተኙ ግን እስከወዲያኛው በክብር አሸለቡ፡፡ ለእነዚህ ሰባት ሰማዕታት በሥፍራው ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠርቶላቸዋል፡፡

"እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ" መዝ.3:5

ደግሞ ይህችን አገኘን ብላችሁ እንዳትተኙ! ለእንቅልፍ ፍቅር ያለው ወዳጅ ካላችሁ ግን Mention በማድረግ ይህን ጽሑፍ አጋሩት!

"የኤፌሶን ወንዝ" ገፅ 64 የግርጌ ማስታወሻ ላይ የተወሰደ

ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እድሳት የሚውለው የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ የመጀመሪያ እትም እያለቀ ነው:: እርስዎ እጅ ገብቶ ይሆን?

~ አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
~ ሰርዲኖን መጽሐፍ መደብር/ Sardinon Book Store

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም፦
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር

በብዙ መልካም የሆነ ሰውን አንድ ክፉ ነገር ብናይበት ብዙ መልካም ነገሩን ሳይሆን ክፉ ነገሩን አይተን ጉድለት ይሰማናል። አእምሯችን ነጭ ወተት ላይ አንዳረፈ ዝንብ ክፉውን ትኩረት ሰጥቶ ያያል፤ ልባችንም መውደድ ይከብደዋል። ይህ ግን የሥጋ እውቀትና ግብር ነው።

እግዚአብሔር እንደዚህ ቢሆን ኖሮ መወደድ እና መዳን አይገኝም ነበር። በእርሱ ዓይን ብዙ ክፋታችን የተገለጠ ነውና። ነገር ግን እርሱ መልካም ስለሆነ በኃጢአት እየኖርን ጠላቶቹ እያለን ወደደን፤ ያውም እስከ ሞት በሚያደርስ ፍቅር። ለዚህ ቸርነትና ፍቅር አንክሮ ይገባል! (ሮሜ. 5፥10)ይህ አምላካዊ ቸርነት በእኛ ዘንድ ለእምነት፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ምንጭ ነው።

እምነት ማለት ሳይገባን ክፉዎች ሆነን የወደደን እና ቀድሶ እና አክብሮ መልካም ልጆቹ ያደርገን ዘንድ ወደ እርሱ የጠራን አምላክ መኖሩን ተረድቶ በእርሱ ታምኖ መኖር ነው። ከዚህም ምሥጋና እና ደስታ ይወጣል። (ዮሐ. 14፥1)

ፍቅር ደግሞ በሥራ እግዚአብሔርን መምሰል ነው፤ እሱ ያለ ጥቅም እና ማዳላት ሁሉን ይወዳልና፤ ጠላቶች ሆነን ሳይቀር ወዶናልና። በእኛ ውስጥ ያለውን ክፋት አይቶ ሳይተወን መልካም አድርጎ መፍጠሩን አስቦ ሊያድነን መጥቷልና።

ተስፋ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ርስትን እየጠበቁ መከራን መታገስ እና የክርስቶስን መምጣት መጠበቅ ነው። እኛን ያድን ዘንድ አንድያ ልጁን ለመከራ አሳልፎ የሰጠ መልካሙ እረኛችን እና አባታችን የማይሰጠን ምን ነገር አለ?የሚጠቅመንን እና ቃል የገባልንን ሁሉ ይሰጠናል። (ሮሜ. 8፥32) ፍቅር ግን ከሁሉም ይበልጣል አለ ሐዋርያው። እውነተኛ ፍቅር ያለው ሰው ሕግን ሁሉ ፈጽሟልና። (1ኛ ቆሮ. 13፥13)

@deaconchernet
@deaconchernet
@deaconchernet


#ስለ ሐሜት መጥፎነት" 

" የመፍረድ ስልጣን ሳይኖረው በሰው ላይ የሚፈርድ ሰውን በተመለከተ ጌታችን ፦ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋሁ በምትሰፍሩትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋልና” በማለት አስተምሮናል፡፡ [ማቴ.፯፥፩]

እንዲሁ የጌታ ወንድም ያዕቆብ ፦ “ወንድሞች ሆይ ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል” [ያዕ.፬፥፲፩] ብሎ ጽፎልናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! ከጌታ ቃልና ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ ምን ተማራችሁ? ጻድቁ ሎጥ በሰዶም ተቀምጦ ነበር ፤ ነገር ግን  “ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበር ” [፪ጴጥ.፪፥፯] ተብሎ እንደተጻፈልን ራሱን በጽድቅ አስጨንቆ ይኖር ነበር እንጂ በማንም ላይ እጁን አልጠቆመም ነበር፡፡ ሐሜት በሰው ላይ መፍረድ ነውና፡፡

ነገር ግን ሐዋርያው ይህን ከጻፈልን በኋላ “ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን ፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል” [፪ጴጥ.፪፥፱] በማለት ፍርድን መስጠት የእግዚአብሔር ድርሻ እንደሆነ እርሱም በኃጢአተኞችና በዓመፀኞች ላይ አንደሚፈርድባቸው ጽፎልናል፡፡ ስለዚህ ራስን በመግዛትና በትሕትና መመላለስ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ፤ ጊዜውም ዛሬ ነው፡፡"

[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ]

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#ከአበው ሕይወት

+ አንድ መነኩሴ ለሌላው መነኩሴ እንዲህ ብሎ ጠየቀው "የምጸልየው ጸሎት የቃሉ ኃይል አይታወቀኝምና ምን እጠቀማለሁ?" አለው። ያ መነኩሴም ሲመልስለት "የቃሉ ኃይል ለአንተ የማይታወቅህ ቢሆንም ሰይጣናት የቃሉን ኃይል ያውቃሉና ይደነግጣሉ ፤ ስለዚህ ነገር ትንሽ ትንሽ እያልክ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር አጋዥነት እስከምትደርስ ድረስ እና ከልብህ መደንደን እንድትለመልም ፣ ከዘወትር ድካምም እንድትድን ጸሎትን አታቋርጥ" አለው።

+ አባ አጋቶንን "የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማግኘት የትኛው ሥራ ይሻላል? በጌታችን ፊትስ በዝቶ ጥቅም የሚሰጠው ማንኛው ሥራ ነው?" ብለው ጠየቁት። እርሱም "የዋህ ልብ እና በመፍራት በመንቀጥቀጥ የሚቀርብ ንጹሕ ጸሎት ነው" አላቸው።

+ ኹል ጊዜ ልቡ ንጹሕ የሆነለት ሰው እግዚአብሔርን ያየዋል ፤ ኹል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚመለስ ሰው አጋንንትን ያባርራቸዋል። ፍላጎቱን የሚንቅ ሰው በልቡ ውስጥ ጌታን ያያል። ንጽሕናን የሚወድ ሰው በመንግሥተ ሰማይ የኹሉ አባት ጌታን ያያል።

ምንጭ: መጽሐፈ ገነት ዘውእቱ ዜና አበው ፤ 2ኛ ዕትም 2010 ዓ.ም

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#ሥራን_አስመልክቶ_የተሰጠው_ትምህርት!

ወደጄ ሆይ ! በምትሠራው ሥራ ምክንያት አትዘን፡፡

“በምትሠራው ሥራ ላይ በፍጹም ስኬታማ ልሆን አልቻልኩም፡፡ እኔ ስንፍናን የተሞላሁ ፣ የደነዘዝሁ ነኝና በፍጹም ይህን ተግባር ልፈጸም አልችልም፡፡ እጆቼ ያለ ፍሬ ከሥራው ብዛት የተነሣ ዝለዋል፡፡ ሥራውን ለመሥራት አሁን አቅሙ የለኝም ስለዚህ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ ... የሚል ሐሳብ በአእምሮህ ውስጥ ከቶ አይመላለስ::

እንደ አንድ አማኝ በእግዚአብሔር ታመን ፥ እንዲህ ባለ ነገርም ተስፋ አትቁርጥ፡፡ ነገር ግን ወደ መንግሥቱና ወደ እርሱ ደስታ ስለጠራህ ስለ ጌታችን ስለ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ መከራውን ሁሉ ታግሠህ ኑር፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “እውነት እላችኋለሁ ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ፥ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል ፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም፡፡” [ማቴ.፲፯፥፳]

ስለዚህ ተወዳጆች ! ሆይ እምነት ይኑረን ፤ እኛ ተስፋ ያደረግናቸው ከቶ ሊያድኑን የማይችሉ ሰዎችን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው::” [መዝ.፻፳፬፥፩] የኃያላን ጌታ ሆይ በአንተ ተስፋ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡፡ "

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ


@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#ከመዝሙረ ዳዊት ልብን የሚያረጋጉ ጥቅሶች

“አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።”
መዝሙር 27፥8

“እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።”
መዝሙር 28፥7

"መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።"
መዝሙር 37፥5

"ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤ ለዘላለምም ትኖራለህ።"
መዝሙር 37፥27

"አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።"
መዝሙር 51፥10

"እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።"
መዝሙር 34፥18

"መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።"
መዝሙር 62፥7

“አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።”
መዝሙር 39፥7

"ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።"
መዝሙር 62፥10

“ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።”
መዝሙር 42፥5

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


#በፈተናህ ላይ ልትሰለጥን ትፈልጋልህን?!

" የዓይን አምሮትህንና የሥጋ ፍትወትህን ሁሉ ከአንተ ቆርጠህ ጣላቸው። በጌታህ ዘንድ ዋጋ የሚያሰጥህ በጎ ሥራ እንዳለ ካሰብህ በእርሱ እንዳይፈረድብህ መልካሙን ሥራ በፍጹም ታዛዥነት ፈጽም፡፡

ጠብን በመውደድ የራስን ፈቃድ ብቻ ተከትሎ መጓዝ ትልቅ ጥፋትን ያመጣል፡፡ ወጣኒ ተሐራሚ ሆኖ ለቃሉ ታዛዥ ያልሆነ እርሱ የቍጣ ልጅ የሚል ስምን ያገኛል። ይህን በተመለከተ ዳዊት ፦ “ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና፡፡ በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፡፡ " [መዝ.፪፥፲፪] በማለት መክሮናል፡፡

ነገር ግን ከስህተቱ መታረም የማይወድ ሰው ራሱን ያጠፋል፡፡

አዲስ ወይንን አሮጌ አቁማዳ እንዳይዙት ቢይዙት ግን አቁማዳው እንዲጠፋ ወይኑም እንደሚፈስ ፥ በትሕርምት ሕይወት ውስጥ ሳሉ ከስህተት አለመማር ለከፋ ጥፋት ይዳርጋል፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ፦ “ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መሰማማት አለው? " [ ፪ቆሮ.፮፥፲፬ ] በማለት በዓመፃ ሥራችን እንዳንጸና ይመክረናል፡፡"

[ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፡፡ ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው?  የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ  የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet


ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን
ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ
ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ
እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥
አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት
ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ
እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ
እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ
አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት
እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ]
ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና
ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች
በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡

[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]

@Deacochernet
@Deacochernet
@Deacochernet


#ሊቁ_አባ_ሕርያቆስ

ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል:: አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል:: ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት::

አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ብየ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብደኛል:: ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን 4ኛው: ወይ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል::

ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው:: ገና ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን: የዋህና ገራገር ነበረ:: መቼም እመቤታችንን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን:: ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ: ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ::

የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር:: ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም:: የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ::

ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው:: ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን: አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር::

በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ: መላልሶ ያመሰግንበት ነበር:: ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝ. 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር:: ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው:: የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው::

አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ: ቁሞም ተቀምጦም: ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቋረጥ ይላት ነበር:: እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር:: በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ::

ምንም አለመማሩ ቢያሰጋቸውም "በጸሎቱ: በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል" ብለው ሾሙት:: ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት: ይንቁትም ነበር:: እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው: እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር::

አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::

በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር::

"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::

የሚገርመው ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር:: እመቤታችን አነጋገረችው: ባረከችው:: ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ: ምግብም ሳይበላ: እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ1 ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል::

በኋላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም አንድ ፈተና ገጠመው:: አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት 1 ቀን ቅዳሴ "ማን ይቀድስ" ሲባል ሰዎቹ "አባ ሕርያቆስ ይሁን" አሉ::

እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም: እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ" አላቸው:: "አይሆንም" ብለው እርሱኑ አስገቡት:: ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር:: ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ እርሱ "እግዚእን (የጌታ ቅዳሴን) ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት::

ይህንን ያሉት እርሱ የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው:: እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት:: አባ ሕርያቆስ ግን እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ:: ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን: መገፋቴን ተመልከች" አላት::

ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ ቀጸበችው (ጠራችው):: በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው:: ደጉ ሰው ደስ ብሎት "ጐሥዐ ልብየ" ሲል ሁለቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ:: እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው::

ሕዝቡና ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ: አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ:: ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ መካከል ድውይ ፈወሰበት:: እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ::

መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር 1 ሊቅ ሆነ:: ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ (10,000) ናቸው:: ሊቁ እንዲህ በንጹሕ ተመላልሶ ዐርፏል::

ታላቁ ሊቅና የእመቤቴ ወዳጅ የሆነው አባ ሕርያቆስ ዘብሕንሳ የተወለደውም ያረፈውም ጥቅምት 2 በዚህች ዕለት ነው።

© ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

@Deaconchernet
@Deaconchernet
@Deaconchernet



Показано 20 последних публикаций.