Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


#ማስታወቂያ

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ










የትምህርት ክፍል መረጣን አስመልክቶ ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጥር 01/2017 ዓ.ም የተደረገ ፕሮግራም በፎቶ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ጥር 01/2017 ዓ.ም


#Performance_Contract_Signing_Ceremony

Join us tomorrow at 2:00 PM for a significant Performance Contract Signing Ceremony at Debre Markos University. This event marks the #formal_agreement between the President of Debre Markos University and the Vice Presidents, alongside directors and college deans.

This contract symbolizes our commitment to enhancing accountability, transparency, effectiveness and performance within our institution, ensuring that we meet our educational goals and uphold our responsibilities to our students and the community.

Stay tuned for updates and highlights from this important occasion!

Debre Markos University
January 08, 2025


የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማስተባበር የዕሮብና አርብ ቁርሳቸውን በመስጠት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ለነዲያን ማግደፊያ የሚውል አንድ በሬ፤ ለዘይት መግዣ የሚውል 6000 ብር እንዲሁም በደብረ ማርቆስ ለሚገኘው እናት ደብረ ማርቆስ የህፃናት መንደር ለገና በዓል የሚውል ሁለት በግ እና አምስት ሊትር ዘይት በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት አስተባባሪነት ተሰብስቦ ለበዓል መዋያ ተበርክቷል።

ውድ #ተማሪዎቻችን ላደረጋችሁት በጎ ተግባር ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምስጋነውን ከልብ ያቀርባል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #የልደት_በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ታህሳስ 29/2017 ዓ.ም


#ምደባ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች በአዲሱ መዋቅር አተገባበር እና የምደባ ሂደት ዙሪያ ዛሬ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የተፈላጊ ችሎታ የተዘጋጀበት ሂደትን እና አጠቃላይ በምደባ ሂደት ላይ የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ ተደርጓል። በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን እንደግባት በመውሰድ እንዲሁም አስፈላጊውን ሂደት በማጠናቀቅ የምደባ ስራውን በፍጥነት ተሰርቶ ውጤቱን ለዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞች የሚያሳውቅ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና መዳቢ ኮሚቴው አስታውቋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


#የማህበረሰብ_አገልግሎት #Community_service

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የማህበረሰብ አቀፍ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን ስርዓት በማስተባበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ስልጠና፣ የማማከር አገልግሎት እና የማህበረሰብ ልማት ስራዎችን የመስጠት ኃላፊነት አለበት።

በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲያችን በማኅበረሰብ አገልግሎት በኩል #ለእናት_ደብረ_ማርቆስ_የሕጻናት_መንደር 447,800 ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ግብአት ማለትም 40 ካርቶን ፓስታ፤ 20 ከረጢት መኮረኒ፤ 6 ኩንታል ስኳር፤ 15 ከረጢት ሩዝ፤ 7 ኩንታል የፊኖ ዱቄት፤ 107 የጣሳ ወተት እንዲሁም 70 ፕላስቲክ ወንበር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የምርምርና ማህበረሰብ የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

Показано 11 последних публикаций.