EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


"የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጠናዊ፣ አኅጉራዊ እና የልማት ቀዳሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር።

ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል።

ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶቻችንን ለማጠናከር ተወያይተናል።

ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ ተወያይተናል።

ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል።

ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና ውይይት አድርገናል።

በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


ማህሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
**************

የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለመሆን ሶስት እጩዎች ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በዚህም በስራ ላይ ያሉትን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ለመተካት በተካሄደው ምርጫ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ 33 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈዋል።

በ7 ዙር በተካሄደው ምርጫ እጩ ሆነው የቀረቡት የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 21 ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ወርቅነህ ገበየሁ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ማህሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በመታሰቢያ ደረጀ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና እና ከአለም የእርሻ ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሬዮ ጋር ያደረጉት ውይይት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢኳቶሪያልጊኒ ፕሬዚዳንት ጋር ያደረጉት ምክክር


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ
****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዚዳንት ኦቢያንግ ኑጌሚያ ባሶንጎ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ ከ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገፃቸው ባጋሩት ፅሁፍ፤ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ኦቢያንግ ኑጌሚያ ባሶንጎ ጋር በቁልፍ ዘርፎች አጋርነታችንን የምናጠናክርበትን መንገዶች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድረገናል ብለዋል።

ለጋራ ዕድገትና ለጋራ ብልጽግና የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።


ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች ነው -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
************************

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን በተሳካ መልኩ እያስተናገደች መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎችን በክብር ተቀብላ እያስተናገደች መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ እንግዶችን ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጓን አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ መጎልበት እንዲሁም ለአፍሪካ ሕብረት መጠናከር ጉልህ ሚና ማበርከቷንና ይህንን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማንሳታቸውን ገልጸዋል።

በተለይ እርስ በእርስ የተባበረና በመሰረተ ልማት የተሳሰረ አህጉር ለመፍጠር ከሌሎች ውንድም እና እህት አፍሪካውያን ጋር እንደምትሰራ እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገበችው ውጤት ለአፍሪካውያን ምሳሌ እንደሚሆን መግለጻቸውንም ጠቅሰዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ
*****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮ እና ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲረል ራማፎሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ እና የሀገራቱ መሪዎች በቀጣናዊ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ስለመግለጻቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡


''ዘላቂ ፍትህ፣ ሰላም እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቅኝ ግዛት ድንበሮች ከተጣሉብን መልክዓ ምድራዊና ፖለቲካዊ ውጥረቶች እና ታሪካዊ ክፍፍሎች በላይ ልቀን መገኘት ይኖርብናል። በሁሉም ሀገሮቻችን መካከል ኅብረትን በማሳደግ የጋራ እጣፈንታችንን በጋራ በመጨበጥ ኃብቶቻችንን እና ተስጥኦዎቻችንን በማስተባበር የአኅጉራችንን ሙሉ አቅም ልንጠቀም እንችላለን።''
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ
*******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሱሉሁ ሳሚያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንቶቹ ጋር በቀጣናዊ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

Показано 9 последних публикаций.