EBS TV NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Get the latest headlines and breaking news in politics, business, technology, sports, entertainment, and cryptocurrency. Join our channel for real-time updates and concise, reliable news delivered straight to your device!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


"በዘንድሮው ምርጫ አለመወዳደሬ ይቆጨኛል" አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ታኅሣሥ 12 እና 13/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂድ ይሆናል፡፡

በዚህ በጉባኤ ላይ ለቀጣይ አራት አመታት የሚያገለግል አዲስ ፕሬዝዳንት እንዲሁም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚመረጥም ይጠበቃል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ከሀገሬ ስፖርት ጋር ቆይታ ያደረገው አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ “የዘንድሮው ፉክክር በተለይ ለፕሬዝዳንት እነ ትራምፕ እንኳን ለአሜሪካ ምርጫ እንደዚህ አልተፎካከሩም፤አሁን ሳስበው እኛ ፌዴሬሽን ውስጥ የሆነ ነገር ስላለ አለመወዳደሬ ይቆጨኛል” ሲል ተናግሯል፡፡


" ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " - ማርክ ጉዬ

➡️ የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ወደ ሜዳ ገብቶ ጨዋታውን አድርጓል !

ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።

ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።

የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።

በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።

ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።

' እኩልነት እና ብዝሃነት ' በሚል ሰብሰብ በዓለም ላይ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እና ሰዎች ጋር ለማድረስ የግብረሰዶማውያን ደጋፊዎች ብዙ አይነት መንገድ ይከተላሉ።

አንዱ ግብረሰዶማውያንን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በተለይም ወጣት ተመልካቾች ያሉትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ነው።

ከነዚህ የእግር ኳስ ፍልሚያዎች አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ / አፍሪካ ሆነ በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነው።

በዚሁ ሊግ የሊጉ አስተዳዳሪ አካላት በ ' እኩልነት እና ብዝሃነት ' ሰበብ የክለብ አምበሎች ክንዳቸው ላይ የግብረሰዶማውያንን ምልክት እንዲያጠልቁ አድርገው ለግብረሰዶማውያን ማስታወቂያ እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የሊጉ ፍልሚያ በሚጋጋልበት ወቅት ነው።

ግብረሰዶማውያን እና የነሱ ደጋፊዎች እጅግ በጣም ተወዳጁን የእግር ኳስ ፍልሚያን ተጠቅመው ግብረሰዶምን የሚያስተዋውቁት በልጆች ፣ ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ዘንድ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና እነሱን ለማነሳሳት ነው።


ትራምፕ ምራጫውን አሸነፉ❗️

ዶናልድ ትራምፕ ዳግም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ተመልሰዋል።


አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።

ዶናልድ ትራምፕም በበርካታ ግዛቶች ድል ቀንቷቸው ምርጫውን እየመሩ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚታወቀው መቼ ነው ?

የምርጫ አሸናፊ በድምፅ መስጫው ምሽት ፣ አሊያም በነጋታው ካልሆነ ደግሞ ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ይችላል።

ያለፈው ምርጫ በአውሮፓውያኑ 2020 ማክሰኞ ኅዳር 3 ነው የተደረገው። ነገር ግን ጆ ባይደን አሸናፊ መሆናቸው የተሰማው ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ነበር።

በወቅቱ አብዛኞቹ ግዛቶች ድምፅ በተሰጠ በ24 ሰዓታት ውስጥ ውጤት ቢያሳውቁም በአንዳንድ ግዛቶች ላይ ቆጠራው ቀናትን ወስዷል።

በ2016 ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤት የታወቀው ከድምፅ መስጫው ቀጥሎ ባለው ቀን ነበር።

በ2012 ደግሞ ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ ውጤቱ ይፋ የተደረገው በድምፅ መስጫው ቀን እኩል ለሊት ገደማ ነው።

ነገር ግን በ2000 በጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና አል ጎር መካከል የተደረገው ምርጫ ከሌሎቹ ለየት ይል ነበር።

ዕጩዎቹ የነበራቸውን ጠባብ ውጤት ተከትሎ ድምፅ ድጋሚ እንዲቆጠር ቢታዘዝም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጣልቃ በመግባት በግዛቲቱ በውጤት እየመሩ የነበሩት ቡሽ አሸናፊ እንዲሆኑ ወስኗል።

ቁልፍ ግዛቶች የትኞቹ ናቸው ?

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት የሚወሰነው በጥቂት ግዛቶች በሚገኝ ድምፅ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ ኢሌክቶራል ኮሌጅ የተባለው ሥርዓት ነው። ይህ ማለት አሜሪካ ፕሬዝደንቷን የምትመርጠው ዕጩዎች በሚያሸንፉት ግዛት መሠረት ነው። አብዛኛዎቹ ግዛቶች ዲሞክራት አሊያም ሪፐብሊካን ናቸው።

ዘንድሮ በጣም ወሳኝ የሚባሉት ግዛቶች ሰባት ናቸው። እነሱም ፦
° አሪዞና፣
° ጆርጂያ፣
° ኔቫዳ፣
° ኖርዝ ካሮላይና፣
° ዊስኮንሲን፣
° ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን ናቸው።

ድምፅ የሚቆጠረው እንዴት ነው ?

ብዙውን ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው በምርጫው ቀን ለሚሰጡ ድምፆች ነው። ቀጥሎ ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት የመረጡ እና በፖስት ድምፃቸውን ያስገቡ ሰዎች ቆጠራ ይካሄዳል።

ከውጭ ሀገራትና ከወታደራዎ ካምፖች የሚላኩ እንዲሁም ድጋሚ እንዲቆጠሩ የተደረጉ ድምፆች ይከተላሉ።

የአካባቢ የምርጫ ባለሥልጣናት አንዳንዶቹ የተሾሙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተመርጠው የመጡ ናቸው። እነዚህ የምርጫ አስተባባሪዎች ናቸው።

አስተባባሪዎች የተሰጠውን ድምፅና የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ያመዛዝናሉ፤ መረጃዎችን ያጣራሉ፤ ጉዳት የደረሰባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ይፈትሻሉ፤ አለመመሳሰል ካለበት ደግሞ ምርመራ ያደርጋሉ።

ወረቀቶቹ ወደ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ገብተው ውጤታቸው እንዲቆጠር ይደረጋል።

አንዳንዶቹ ድምፆች በእጅ ሊቆጠሩ ይችላሉ።

ድምፁ ትክክለኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ መጀመሪያ በክፍለ-ግዛት ቀጥሎ ወደ ግዛት ይሸጋገራል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።


በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አካባቢ የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉ ተገልጿል።

1. መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ
ከመገናኛ - ቃሊቲ
ከመገናኛ - ሳሪስ
ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ ነው።

2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው
ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)

3. ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች
ከመገናኛ - ገርጂ
ከመገናኛ-ጎሮ
ከመገናኛ - አያት እና
ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ ተዘዋውሮ በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።


እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የለም፤ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ ነው ፤ አዋሽ አካባቢ ነው የተከሰተው በሬክተር ስኬል 4.9 ነው " - ዶክተር ኤልያስ ሌዊ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር

@EBS_TV_NEWS


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ።


ቤንዚን ?

በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።

ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።

በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።

በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።

በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።

ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።

በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።

ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።

ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።



@EBS_TV_NEWS


ባለፈው ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቅድመ መደበኛ (ኬጂ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ሊጀመር ነው

ባለፈው ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቅድመ መደበኛ (ኬጂ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በዚህ ሳምንት በተጀመረው የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሳምንት ለአምስት ጊዜ ሊሰጥ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ያዘጋጀው የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተማሪዎች መፅሐፍ እና የመምህራን መምሪያ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች መሠራጨቱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ርዕሰ መምህራን እና መምህራን ገልጸዋል።


Binance የራሳቸዉ Project መሆኑን በ Telegram Channel አሳዉቀዋል ስለዚ እየሰራቹ ያላቹ Keep going

Project Name MOONBIX

BINANCE released it's MINI-APP

Daily check in✅

Task Complete✅

Play The GAME✅

ሰትጫወቱ የ BINANCE LOGO እና GIFT BOX አለ እሱን CATCH አርጉ Except The BLACK ROCK🚫

💥ለመጀመር👇 https://t.me/Binance_Moonbix_bot/start?startApp=ref_7410278692&startapp=ref_7410278692&utm_medium=web_share_copy




እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ደመ የማይፈስበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የማንሰማበት
- በመላ ሀገሪቱ ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የማንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
ያደርግል ዘንድ EBS ይመኛል።

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !


የቴሌ ግራሙ Pavel durove እንደሚታሰር እያወቀ ነው ወደፈረንሳይ የሄደው 🤔...የሚሉ፣ የእሱን የመጨረሻ ፖስት.... አንደ ፍንጭ ይጠቅሳሉ....
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
" እኔ 11 አመት ሲሞላኝ ጠንካራ እና ራሱን የቻለ ነፃ ሰው ለመሆን የወሰንኩበት ቀን ነበር...
ዛሬ ደግሞ ቴሌግራም 11 አመት ሆኖታል ...እናም ጠንካራ እና እራሱን የቻለ መሆን አለበት..." ይላል...


Pavel Durov የሰዎችን Privacy እጠብቃለሁ በማለቱ ምክንያት እየደረሰበት ያለውንእንግልት ለማውገዝ ብዙዎች Telegram Logo ላይ ይህንን ምስል እየተጠቀሙ ነው ።

#Freedurov


Privacy is not a crime.


#FreeDurov


" እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ጸጥ ይላሉ ? " - ዛራኮቫ

የምዕራባውያኑ ለሰብዓዊነትና ነጻነት ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች የቴሌግራም መስራች ፓቨል ዱሮቭ እንዲለቀቅ ይጠይቃሉ ?

የዱሮቭን ፈረንሳይ ውስጥ መታሰረን በመለተከተ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች " ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? ወይስ እንዲፈታ ይጠይቃሉ ? " ብለዋል።

እ.ኤ.አ. በ2018 ፦
- ሂዩማን ራይትስ ዎች ፣
- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፣
- ፍሪደም ሃውስ ፣
- ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች እና ሌሎችን ጨምሮ 26 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቡድን የሩስያ ፍርድ ቤት ቴሌግራምን ለማገድ የሰጠውን ውሳኔ አውግዘው ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።

ዲፕሎማቷ ፤ " አሁን ፓሪስ ደውለው የዱሮቭን መፈታት የሚጠይቁ ይመስላችኋል ? ወይስ ምላሳቸውን ውጠው ዝም ይላሉ ? " ሲሉ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ፅፈዋል።

ዛራኮቫ ፤ በ2018 ቴሌግራም ላይ የሕግ አውጭ ቅሬታዎች ነበሩ፣ ይህም በብዙ የኢንክሪፕሽን ሥርዓቱ ቴክኒካል መለኪያዎች ምክንያት ነው ሲሉ አስታውሰው ፤ ዱሮቭ ግን ነፃ ሆኖ መቆየቱን መተግበሪያውን ማሳገዱን ገልጸዋል።

የዱሮቭ በተያዘበት ቅፅበት በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን መከታተል እንደጀመረ ጠቁመዋል።

" የእኛን ዲፕሎማቶች ስለ ስራቸው ማስታወስ አያስፈልግም " ሲሉም ዛካሮቫ አክለዋል።

ቴሌግራም ሩስያ እንዲሁም በዩክሬን አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለው ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለስልጣናትም ተመራጭ መልዕክት መለዋወጫ አድርገውታል።

ዱሮቭ የሩስያ እና የፈረንሳይ ዜግነት አለው።


የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፈረንሳይ ውስጥ ታሰረ።

➡ በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ የዱሮቭን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ነው።

➡ ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

➡ ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች የተቃውሞ ሰልፍ እየጠሩ ናቸው።

የቴሌግራም መተግበሪያ መስራቹና ዋና ስራ አስኪያጁ ፓቨል ዱሮቭ ትላንት ቅዳሜ ምሽት ፈረንሳይ ፣ በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቡርጌት ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ዱሮቭ በግል ጄቱ ተሳፍሮ ሊጓዝ ሲል ነው የታሰረው።

ለእረፍት ካቀናበት አዘርባጃን ተነስቶ በፈረንሳይ አድርጎ ሊጓዝ በኤርፖርቱ ባረፈበት ወቅት ነው መያዙ የታወቀው።

በፈረንሳይ የመጀመሪያ ደረጃ የፖሊስ ምርመራ አካል በሆነ የእስር ማዘዣ እንደተያዘም ነው የተነገረው።

ምርመራው ያተኮረው በቴሌግራም ሞደሬት / ቁጥጥር የማድረግ ክፍተት ላይ ነው። የፈረንሳይ ፖሊስ " ቴሌግራም የወንጀል ድርጊቶች፣ የአደገኛ እፅ ዝውውር፣ ሽብር፣ መኒ ላውንደሪንግ፣ ማጭበርበር ያለገደብ የሚተለለፉበት ሆኗል " በሚል ምርመራ ያደርጋል ነው የተባለው።

ዱሮቭ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሏል።

ቴሌግራም በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም። የፈረንሳይ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፖሊስም በጉዳዩ ላይ ምንም አላሉም።

የሩስያ ምክትል የዱማ አፈ-ጉባዔ ቭላዲላቭ ዳቫንኮቭ ዱሮቭ እንዲፈታ የሚጠይቅ መልዕክት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ፅፈዋል።

እስራቱ በፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለውና የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለማግኘት መሳሪያ ሊሆን ይችላል ነው ያሉት።

በፈረንሳይ የሩስያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ ነው።

ብሎገሮች በፈረንሳይ ኤምባሲዎች ተቃውሞ እየጠሩ ናቸው።

በርካቶች ቴሌግራም ላይ ያነጣጠረው የሃሳብ ነጻነትን መንፈግ ነው ብለዋል።

ቴሌግራም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠቃሚዎች እጅ በጣም መጨመራቸው ይታወቃል።

በተለይ በሩስያ፣ ዩክሬን አካባቢ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በመላው ዓለም ተጠቃሚዎቹ 1 ቢሊዮን ደርሰዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና ባለስልጣናት ዋነኛ ተመራጭ የመልዕክት ማስተላለፊያ መድረክ ሆኗል።

ዱሮቭ የሩስያ-ፈረንሳይ ዜግነት አለው።


#ኢራን

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በስቅላት ገድላለች።

በማዕከላዊ ኢራን " ዝድ ክልል "አስገድዶ መድፈር መፈጸሙ በፍርድ ቤት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተቀጥቷል።

ግለሰቡ " በጥንቆላ ይተዳደራል " የተባለ ሲሆን ወደሱ የሚመጡ ሴቶችን በማታለል አስገድዶ ሲደፍር እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከ12 በላይ የክስ መዝገቦች የተከፈቱበት ይህ ሰው አሱን ጨምሮ ከነ ረዳቱ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በሞት ፍርድ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ጥፋተኛ የተባሉት ሰዎች ታንቀው እንዲገደሉ ተደርጓል።

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚጥሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

መረጃው የአን አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።


የ7 አመት የተከራዩን ልጅ ደፍሮ ከዛም ባለፈ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው አውሬው ጌትነት የተባለው ወንጀለኛ ግለሰብ 25 አመት የተፈረደበት ሲሆን አሁን ጠበቆቹ ቅጣቱን ለማቅለል ደፋ ቀና እያሉ ነው።

እህቶቹ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች የሟች ህፃን ሄቨን እናትን በየሄደችበት እያስፈራሯት ይገኛል የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ይስጠኝ ያለችው እናት ፍትህ ትፈልጋለች።

ቅጣቱ በቂ እንዳልሆነ ተጨማሪ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚገባ ህዝብ ያንን እንደሚፈልግ ለማሳወቅ የፊርማ ማሰባሰብ እና ለእናቷ የገንዘብ ድጎማ ተጀምሯል።
https://www.change.org/p/justice-for-heaven-and-her-mother?recruited_by_id=94947080-5cca-11ef-af3a-c38f3884f55d&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=signature_receipt&utm_medium=copylink

በዚህ ሊንክ በመግባት ፊርማችንን መስጠት የቻልን ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን።

EBS በህጻኗ ላይ በተፈጠረው የግፍ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

ይህ ጉዳይ በጊዜ ካልተቋጨ ነገ እኔ እና እናንተም ቤት መግባቱ አይቀርም!

#ፍትህለሔቨን
#Justiceforheven

Показано 20 последних публикаций.