Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ቻናል
📨ሃሳብና ኣስተያየት @Philemona7 ወይ @ETCONpBOT ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


👉መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ገንብቻለሁ አለ‼️

መንግሥት ኢሕአዴግ መንግሥት ሆኖ አገሪቷን ሲያስተዳድር ለ14 ዓመታት (ከ1996 እስከ 2010 ዓ.ም.) በአገሪቱ ከገነባቸው ኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአምስት እጥፍ የላቀ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ገንብቻለሁ አለ፡፡

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት መረጃ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊዮን ቤቶች ተሠርተው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ያስታወቁት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ለማፅደቅ፣ ማክሰኞ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ባካሄደው 14 መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በስብሰባው ወቅት ከምክር ቤት አባላት መካከል የቀረበው የንብረት ታክስ አዋጅ፣ የዜጎችን ሕይወት የሚቀይር እንዳልሆነ፣ መንግሥት የጀመረውን የኮሪደር ልማት ለመጨረስ እንጂ ደሃውን ለመደጎም ለሚደረግ የልማት እንቅስቃሴ ላይ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ ያቀደ አለመሆኑን በመጥቀስ ትችት ሰንዝረው ነበር፡፡

በአዋጁ እንደተብራራው በሊዝ ይዞታ ሥሪት በሚተዳደር ማንኛውም የከተማ ቦታ፣ የመጠቀሚያ መብት ከሊዝ ይዞታ ሥሪት ውጪ በሆነ ነባር የቦታ የመጠቀሚያ መብት ላይ የንብረት ታክስ እንዲከፈል ተደንግጓል፡፡

ከንብረት ታክስ ነፃ የሚሆነው ለአንድ ቤተሰብ መኖሪያነት አገልግሎት እየሰጠ ያለ በከፍተኛ የቦታ ደረጃ እስከ 15 ካሬ ሜትር፣ በዝቅተኛ የቦታ ደረጃ እስከ 30 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ መኖሪያ ቤት፣ የሃይማኖት ተቋማት ለአምልኮና ለመካነ መቃብር አገልግሎት የሚጠቀሙበት ቦታና ቤት፣ በከተማ ውስጥ ያለ ሙሉ በሙሉ ለግብርና ሥራ የዋለ መሬት ናቸው፡፡

ከምክር ቤት አባላት መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ ተወካይ አቶ ባርጠማ ፈቃዱ በሰጡት አስተያየት፣ የኮንዶሚኒየም አሠራር ከዚህ በፊት ችግር የነበረበት ቢሆንም ለዜጎች የቤት አቅርቦት በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይቀርብ እንደነበርና ትልቅ ችግር የፈታ አማራጭ ነበር ሲሉ ገልጸውታል፡፡

አሁን ግን የኮንዶሚኒየም ቤት አማራጭ መቋረጡን ጠቅሰው፣ መንግሥት የሚያገኘውን ሀብት የቤት ግንባታ ላይ ለምን አያውልም በማለት ጠይቀዋል፡፡

አክለውም የንብረት ታክስ አዋጅ ለዚህ የቤት ግንባታ መርሐ ግብር የማይውል፣ ከዜጎች በሚሰበሰብው ገንዘብ ተገንብቶ የሚቀርብ ተመጣጣኝ የቤት አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የቤቶች ኮርፖሬሽን ዓላማው ቤቶችን ገንብቶ ለዜጎች ቤት ማዳረስ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በተለየ ቢዝነስ ውስጥ ተሰማርቷል ሲሉ ተችተውታል፡፡

የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ በንብረት ታክስ አዋጅ የሚሰበሰበው ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግሥት ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግና የጀመራቸውን ሥራዎች የሚያጠናክር፣ ብቃት ያለው የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠትና የዜጎችን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየመለሰ ለመሄድ ያግዘዋል ብለዋል፡፡

‹‹ባለፉት አምስት ዓመታት የቤት ግንባታ ሥራ ተቋርጧል የሚባለው በጣም የተሳሳተ መረጃ ነው፤›› ያሉት ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ባለፉት ዓመታት ተገንብተዋል ያሏቸውን 1.5 ሚሊዮን ቤቶች በማነፃፀሪያ ሲገልጹ፣ ‹‹በዚህ አገር ኮንዶሚኒየም ተጀመረ ከተባለበት ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ የተገነባውና አሁን ባለው መንግሥት የተገነባው ሲነፃፀር፣ በአሁኑ ጊዜ ከአምስት እጥፍ በላይ ገንብተናል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹የቤት ግንባታ አልተቋረጠም አጠናክረን ቀጥለናል፤›› ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ዘመን አፈራሽ የሆኑ የኮንስትራክሽን ፈጠራዎችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ 120 ሺሕ ቤችችን ገንብቶ እንደሚያስተላልፍ ኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ አስታውቋል።

ኦቪድ ኮንስትራክሽን በመባል የሚታወቀው ኩባንያ በውስጡ 47 ድርጅቶችን በመያዝ ‹‹ኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ›› በሚል አደረጃጀት መምጣቱን በማስታወቅ፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት እፈጽመዋሁ ያለውን ‹‹ራዕይ 2030›› የተባለ ስትራቴጂ ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ስትራቴጂው በቦሌ ገላን ጉራ በተሰኘ ሳይት ግማሽ ትሪሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ፣ በመንግሥትና በግል ዘርፍ አጋርነት 90 ሺሕ ቤቶችን፣ እንዲሁም በሌሎች ሳይቶች 30 ሺሕ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ገንብቼ ለተጠቃሚዎች አስተላልፋለሁ ብሏል፡፡

የኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ ታደሰ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመኖሪያ ፍላጎት እንዳለ ገልጸው፣ በአሁኑ ጊዜ ቢያንስ ከ600 ሺሕ በላይ ቤተሰቦች የመኖሪያ ፍላጎት እንዳላቸው መረጃዎችን በማጣቀስ አስረድተዋል፡፡

ኦቪድ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ችግርን ለመፍታት አዳዲስ መንገዶችንና አማራጮችን በመፍጠር፣ የቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ፣ አዳዲስ የፋይናንስ ሞዴሎችን በመጠቀም ወገኖች እንዲታገዙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለአብነትም ኩባንያው እያቋቋመው ያለው ኦቪድ ቤቶች ባንክና ኦቪድ ማይክሮ ፋይናንስ የመኖሪያ ቤትን ፋይናንስ ለማድረግ ሰፊ ሥራ እንደሚያከናውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

በመጪዎቹ አምስት ዓመታት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የባለሙያ ክህሎትና የግንባታ አቅምን ለማሳደግ፣ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመተባበር፣ በየዓመቱ 1,000 ባለሙያዎችን በማሠልጠን ወደ ገበያው እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ኦቪድ በዚህ የአምስት ዓመት ዕቅዱ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ተቋምና ሸልተር አፍሪካ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመሆን ስምምነት በመፈጸም፣ በኬንያ ናይሮቢና ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሁለት የሙከራ ፕሮጀክቶችን እንደሚገነባ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ከዩኤን ሀቢታትና ዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በዘላቂ የከተማ ልማትና ተመጣጣኝ የቤት አቅርቦት ላይ እየሠራሁ ነው ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የግንባታ ኢንዱስትሪውን ለመለወጥ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ቅልጥፍናን ማሳደግ ወጪንና የአካባቢ ተፅዕኖን መቀነስ ላይ ይሠራል ያሉት አቶ ዮናስ፣ በግንባታ ሥራ 3D ቴክኖሎጂንና ሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በዘርፉ የማስተዋወቅ ሥራም ይከናወናል ብለዋል፡፡

የቤት ባለቤቶችን ዕርካታ ለመጨመር የቤት ገዥዎች የቤት ባለቤትነት ፕሮግራም በማዘጋጀት ስለቤታቸው ግንባታና የሌሎች አገልግሎቶች መረጃ እንዲያገኙ፣ ከሌሎች የቤት ባለቤቶች ጋር መመካከር እንዲችሉ እንሚደረግም አቶ ዮናስ አስታውቀዋል፡፡
ኦቪድ ሆልዲንግ ግሩፕ በእርሻ፣ ማዕድን በማውጣት፣ በሆቴልና በቱሪዝም፣ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በሎጂስቲክስና በሚዲያ፣ እንዲሁም በቅርቡ ከአሜሪካ ሳይንቲስቶች ጋር በተደረገ ስምምነት በኢትዮጵያ ክትባት ለማምረት እየሠራ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

@etconp


👉ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2.4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁ የ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል መባሉን ሸገር ሬድዮ ዘግቧል።

🚧ግንባታው 97.6 በመቶ እንደደረሰና ጥቂት የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ እንደቀሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ተናግሯል ተብሏል፡፡

🏷ከ 14 ዓመት አመታት በፊት የግንባታው መሰረት ድንጋይ ሲጣል 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል ተብሎ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ የ2.4 በመቶ ስራም ቀርቶት ለምን 80 ቢሊዮን ብር እንዳስፈለገ በብዙዎች ጥያቄን ጭሯል።

⏺በጉዳዩ ዙሪያ የህዳሴ ግድብን የቦንድ ሽያጭ ሲከውን የቆየውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ገበያ ዳይሬክቶርት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት አማረ ከሸገር ሬድዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ የግንባታ ስራው በተለያ ደረጃ ስለሚመራ ስለዚህ ጉዳይ ፕሮጀክቱን የሚመሩት የስራ ሃላፊዎች ናቸው የሚያውቁት ብለዋል፡፡

⏺ይሁንና ልማት ባንክ የቦንድ ሽያጭ ላይ እንደመሳተፉ እስካሁን ከህዝቡ ከ20.2 ቢሊየን ብር በላይ መዋጣቱን መናገር እንችላለን ብለዋል፡፡

⏺ለማጠናቀቂያ ስራው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ልማት ባንክ 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱንም አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

⏺ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ በበኩሉ በዚህ ዓመት እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር ከህዝቡ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

⏺በዚህም ባሳለፍነው ዓርብ 110 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታስቦ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከፋናንስ ተቋማት መሰብሰብ የተቻለው 25.9 ሚሊዮን ብር ብቻ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡

@etconp


#ADVERTISEMENT

🔧📐📐ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት 📐📐  
                 መማምረቻ ድርጅት⚙🔧🛠


🛠🛠🛠የምንሰጣቸው አገልግሎቶች🛠🛠🛠

1 መገለጫችን የሆነው የሞደፊክ ስራዎች

2 እዲሁም ፕሌት ከ 1ሚሊም እስከ 30 ሚሊም እንቆርጣለን እበሳለን

3 በመቀጠል ጄቦልት 12ሚ እስከ 32ድረስ ጥርስ አውጥተን አጥፈን እናቀርባለን

4 የተለያዩ ቦልቶች በፈለጉት መጥን

                መገኛችን


ቁ1በእጆት ባለ ስልክ ለናተ ቅርብ

ቁ2 በታታሪዎች መገኛ ኮርቻ ተራ

ቁ3 አየር ጤና ኪዳን ምህረት ጊቢ ማንኛውም ልሜራ   
      እዛው በዘመናዊ ማሽን እቆርጣለን

ማሳሰብያ

ከጊዜው አንፃር የዋጋ ንረት ካሳሰቦት እኛጋ እሚገርም መፍትሄ አለ በማያስቡት መልክ ስራዎን ይሰራሉ ይደውሉ

ስልክ ቁጥር
0912492727
0913061530
0923764834

መልካም ስራ ለራስ ነው ቸር ይግጠማቹ ፀግሽ   
ፕሌት እና ጄቦልት!


👉ስለ Field Hammer Test

🚧በአሁኑ ሰዓት ያለው የኮንክሬት ቅይጥ አተገባበር (Concrete Mixing Methodology) የተሻሻለ እየሆነ ቢመጣም አንዳድን ችግሮች ይስተዋላሉ።

🏷ለምሳሌ ያህል፦ ወጥ የሆነ የጠጠር እና የአሸዋ አይነት አለመጠቀም፣ በቤተሙከራ የቅይጥ ምጥጥን (Mix Design Ratio) ሳይወሰንላቸው የተለያዩ የሲሚንቶ ምርት አይነቶች መጠቀን፣ ሌላ ቦታ ተቀይጦ የሚመጣ እና የኮንክሬት grade ለባለቤቱ በውል ያልተገለጸ አርማታን ለሙሌት መጠቀም (ready mix concrete) የመሳሰሉት ይገኙበታል።

⏺እነዚህ ሂደቶች ለሕንጻው ወይም ለአርማታ መዋቅሩ ስትራክቸራል ፍላጎት አለመሟላት ሊያስከትል ይችላል።

⏺በመሆኑም በሳይት ላይ የምንጠቀማቸው ሙከራዎች ያሉ ሲሆን በዋናነት ሐመር ቴስት (Hammer Test) መጠቀም አለብን።

⭐️በተለምዶ የመዶሻ ሙከራ በመባል የሚታወቀው Hammer Test ኮንክሪት ከተሞላ በኋላ ባሉት በ7ኛ እና በ28ኛ ቀናት ውስጥ ሊከናወን ይችላል (በእርግጥ በመካከል ባሉ ቀናት እና ከ28ኛ ቀን በኋላም እስከ 3 ወር ድረስ የሚተገብሩ ሀገራት አሉ)።

⏺ይህ Non-Destructive Test ምድብ የሆነ የሙከራ ዘዴ የኮንክሪት ጥንካሬን የሚለካ ሲሆን ይህም ከአርማታ ውቅሩ ጥንካሬ ጋር የተያያዘ ምዘና ነው። በመሆኑም፦

❇️1ኛ) በ7ኛ ቀን የ7ኛ ቀን የመዶሻ ሙከራው የአርማታው መዋቅር (Concrete Structure) ያጎለበተውን የጥንካሬ እድገት የምለካበት ሲሆን እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ከሚጠበቀው ዝቅተኛ ጥንካሬ (Minimum Compressive strength) ውስጥ ከ60% - 70% ድረስ ማጎልበት ይኖርበታል። 

❇️2ኛ) በ28ኛ ቀን፦ በ28ኛ ቀን የሚደረግ ሙከራ የአርማታ ውቅሩ የሚጠበቅበትን 100% ጥንካሬ ማጎልበቱን የምናረጋግጥበት የሜዳ ሙከራ (Field Test) ነው።

⚡️ልብ ሊባል የሚገባው ይህ የሐመር ቴስት የኮንክሪት ጥንካሬን ለመወሰን ብቸኛው ዘዴ ሳይሆን እንደ ተጨማሪ ዘዴ መጠቀም የምንችለው መሆኑን ነው። ለበለጠ ውጤት ደግሞ Core Sampling፣ Cylinder test የመሳሰሉትን የጥንካሬ መፈተሻዎችን መጠቀም አለብን።

🔰የሐመር ቴስት ትግበራ ጥንቃቄ (Cautions during field Hammer test)

~ ቢያንስ 10 ቦታዎች ላይ መሞከርና ማንበብ
~ እያንዳንዱ ናሙና እርስ በእርሱ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ ተራራቁ መሆን አለባቸው
~ ከኮንክሬት መዋቅሩ ጠርዝ ቢያንስ 10ሴ.ሜ መራቅ
~ ሐመር ቴስት መሳሪያው የሚመታበትን አንግል ማወቅ (90° ቢሆም ይመረጣል)
~ የአሥሩን ናሙናዎች አማካኝ ማስላትና እና የመጣውን አማካኝ (Average) ውጤት ለውሳኔ መጠቀም ናቸው።

⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp


#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664


Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall


👉የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የእድሳት ሥራ ተጠናቆ ተመረቀ።

@etconp


👉በጎረቤት መሬት ውስጥ ወሰን አልፎ ግንባታ ስለመፈጸም -- (የሕግ አግባብ)

🚧ከግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ በሀገራችን ፍርድ ቤቶች ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ሰፊውን ቦታ የያዘው «ጎረቤት ወሰን አልፎ አጥር ማጠር፣ እጽዋት መትከል እና በመሬት ውስጥ ወይም በአየር ላይ ግንባታ መፈጸም» በሚሉ ጉዳዮች የቀረቡ አቤቱታዎች ናቸው።

⏺በመሆኑም አንድ ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ከተሰጠበት የይዞታ ድንበር መስመሮች ውጪ በመሬት ውስጥም ይሁን ከመሬት በላይ (በአየር ላይ አንጠልጥሎ) ግንባታ መፈጸም አይችልም።

⏺ግንባታ ይቅርና ባለይዞታው ካልፈቀደ በቀር እና በህግ ትእዛዝ ካልተሰጠ በቀር ማንም ሰው በሌላ ይዞታ ላይ አልፎ መግባት (መራመድ፣ መቆም) አይችልም (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1216)።

⏺አንድ ጎረቤት በራሱ ይዞታ ላይ ዛፍ ቢተክልና ዛፉ እያደገ ሲሄድ የዛፉ ሥሮች በመሬት ውስጥ ወደሌላኛው ባለይዞታ መሬት ውስጥ ቢገቡ አልፈው የገቡትን የዛፉን ሥሮች የመቁረጥ ግዴታ አለበት፣ የዛፉ ቅርንጫፎችም በአየር ላይ በሰው ይዞታ ላይ ከገቡ ወይም ቅርንጫፎቹ ወደሌላ ጎረቤት ይዞታ ውስጥ ከተስፋፉ እነዚያን ቅርንጫፎች የመቁረጥ ግዴታ አለበት (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1212)

📜በመሆኑም በፍትሐብሔር ህግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድ ሰው በጎረቤቱ ይዞታ ላይ ግንባታ የፈጸመ ከሆነ (በመሬት ውስጥ መሰረት ግንባታ Foundation፣ በመሬት ላይ ወለል ወይም በአየር ላይ ተንጠልጣይ ውቅር Cantliver Structure ሊሆን ይችላል) ይዞታ የተጣሰበት አካል የባለቤትነት አቤቱታ በፍትሐ ብሔር /ሕ/ቁ 1206 መሰረት በማዘጋጀት ስልጣን ላለው ፍ/ቤት የማመልከት መብት አለው፡፡

⏺አቤቱታው ይዞታው በሚገኝበት አካባቢ ባለ ፍርድ ቤት ቢሆን የተመረጠ ሲሆን በይዘት ደረጃ የይዞታው ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የተያያዘበት፣ ግንባታ የፈጸመው አካል ምን ያህል ካሬሜትር አልፎ እንደገባ፣ እና ያለአግባብ የተፈጸመውን የግንባታ አይነት በመጥቀስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

⏺የአቤቱታው ፍሬ ነገር (ፍላጎት ደግሞ) ግንባታ የፈጸመው አካል አልፎ የገነባውን የግንባታ አይነት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታውን ቀድሞ በነበረበት ይዘት እንዲያስረክብ ውሳኔ እንዲወሰን የሚጠይቅ መሆን አለበት።

⭐️የቴግራም ቻናላችንt.me/ETCONpWORK

ቴሌግራም ሊጽፉልን ካሰቡt.me/ETCONpBOT

💫የ FACEBOOK ገፃችንም ይወዳጁ👇

https://www.facebook.com/ethioconp

@etconp


ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ከ አባይ ግድብ እስከ ኮሪደር ልማት

ከግለሰብ ቤቶች እስከ ተቋማት እና

መጋዘኖች በሁሉም የኢትዮጽያ ክፍል

አሻራችንን አሳርፈናል

🔰ምን ይፈልጋሉ?

✂️ላሜራ መቁረጫ ÷ ማጠፊያ እና መብሻ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦
                    ቁ.1 መርካቶ
                    ቁ.2 ተክለሀይማኖት
                     ቁ.3 አየር ጤና

0904040477
0911016833


👉አሁናዊ ንድፍ፡ ዘለቀ በላይ፣

💫ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ                 

🏷ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋና መግብያ ንድፍ፡፡

⭐️ይህ በታዋቂው ነዳፊ በ ዘለቀ በላይ  ቀለል ብሎ በሀሳብ በልጽጎ የተነደፈ ንድፍ በቀን እና በማታ የተለያዩ ስሜቶችን ይፈጥራል፡፡

⏺ዘለቀ በቅርጽ ላይ ያለው አትኩሮት እንዴት እንደተሳካለት ማየት እንችላለን፡፡

⏺ንድፎቹ ላይ የብርሀን እና የጥላ ጨዋታዎችን ማየት የሚያስደስት ነው፡፡

Via Dawit Benti

@etconp


👉ፌሮ ብረት Vs የአርማታ
[Reinforcement bar Vs Concrete mix]


🚧የኮንክሬት መዋቅር (Concrete Skeletons) የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም በአብዛኛው የተለመደው የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ያለው መዋቅር ነው።

⏺ይህ አይነቱ ስትራክቸር «Reinforced Concrete Structure ወይም ባለፌሮብረት የአርማታ ውቅር» ተብሎ ይጠራል።

⏺በመሆኑም እነዚህ ሁለት ዋና ዋና የግንባታ ግብአቶች (ፌሮ ብረት እና አርማታ) ለውቅሩ የየራሳቸው የሆነ አስፈላጊ ጥቅም አላቸው።

💫ከዚህ አንጻር፦

🚧የፌሮ ብረት (Reinforcement bar)

⏺በባህርዩ ተለጣጭ አይነት ባህርይ ስላለው በኮንክሬት ውቅሩ ላይ የሚተገበረውን ጫና (load) በቀላሉ እንዳይፈረካከስ በማድረግ እና ባለው ወጥነት የተነሳቭየተወሰነ የመለጠጥ ነጻነትን (Ductile Property) በማበልጸግ የመለጠጥ ጥንካሬን (Tensile Strength) እንዲኖረው ያደርጋል።

በዚህ አግባብ የአርማታ ውቅሩ Tension ላይ ልዩ የመቻል አቅም እንዲኖረው የሚያደርግ ግብአት ነው፡

💫አርማታ (Concrete Mix)

⏺በፌሮ ብረት መዋቅሩ ውስጥ እና ዙሪያ የሚሞላው አርማታ ደግሞ የኮንክሬት መዋቅሩ (Concrete Structure) የመኮማተር አቅም (Compressive Strength) እንዲኖረው የሚያደርግ ነው። በመሆኑም አርማታ በመዋቅሩ ላይ የሚተገበረው ጫና በአንጻራዊ ስፋት ላይ አርፎ ማዕከላዊ የፍሰት ሥርዓትን (Centerline load transfer system) ተከትሎ እንዲፈስ የሚያስችል የመድረቅ ወይም የመኮማተር ሂደትን የሚይዝ ነው።

📜ማጠቃለያ አርማታ ጠንካራ የማይለጠጥ ጸባይ ስላለው ፌሮ ካልገባበት ጫና ሲበዛበት የመሰበር ወይም የመቀንጠስ አደጋ ይገጥመዋል።

⏺ፌሮ ብረትም ብቻውን ቢሆን የመለጠጥ ጸባይ ስላለው አርማታ ባይኖርበት ተጣጥፎ ይተኛል ወይም ጎብጦ ይቀራል እንጂ ራሱን ችሎ ደረቅ መዋቅር የመሆን አቅሙን አያስቀጥልም።

🌟በመሆኑም አርማታ ብቻውን ቢሆን ወይም አርማታው በዝቶ ፌሮ ብረት ካነሰ የመለጠጥ አስፈላጊ ባህርዩን ስለሚያጣ «Tensile Failure» ይገጥማል።

⏺በተቃራኒው ፌሮ ብቻውን ከሆነ ወይም ፌሮ በዝቶ አርማታ ካነሰ "Compressive Failure" ይከሰታል ማለት ነው።

⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO

@etconp


👉የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች

🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።

ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።

⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።

[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል

[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ

[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት

[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ

[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ

[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።

[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡-  ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል

[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት

[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል

[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ -   𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦  የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ

[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ  - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦  በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር

🔰እነዚህ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በዝርዝር እና በጥልቀት ይዘው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል።

@etconp


👉የ "Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}


🚧በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።

💫ከእነዚህ ውስጥ  አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን።

⏺ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።  

ክፍል አንድ  ዋና ዋና ጥቅሙ፦


1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል።

2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦  በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው።

3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት  ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።

ክፍል ሁለት፡ ይዘቱ ምን መምሰል አለበት


ይቀጥላል .....

@etconp


Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall


survey which are carried out to provide a national grid of control for preparation of accurate maps of large areas are known
Опрос
  •   Plane survey
  •   Geodetic survey
  •   Geographical survey
  •   Topographical survey
135 голосов


Q : Which one of the following survey is used to define the property line?
Опрос
  •   A : City Survey
  •   B : Cadastral Survey
  •   C : Land Survey
  •   D : Topographical survey
142 голосов


👉HONEYCOMBS :

⏺Honeycombs are hollow spaces and cavities left in concrete mass on surface or inside the concrete mass where concrete could not reach. These look like honey bees nest.

Honeycombs which are on sides are visible to naked eyes and can be detected easily as soon shuttering is removed.

Honey combs which are inside mass of concrete can only be detected by advanced techniques like ultrasonic testing etc.

Honeycomb is due to non-reaching of concrete to all places due to which cavities and hollow pockets are created, main reasons are :

● Honeycombs are hollow spaces and cavities left in concrete mass on surface or inside the concrete mass where concrete could not reach. These look like honey bees nest.

● Honeycombs which are on sides are visible to naked eyes and can be detected easily as soon shuttering is removed. Honey combs which are inside mass of concrete can only be detected by advanced techniques like ultrasonic testing etc.

● Honeycomb is due to non-reaching of concrete to all places due to which cavities and hallow pockets are created, main reasons are:

1. Improper vibration during concrete.

2. Less cover to reinforcement bars

3. Use of very stiff concrete (this can be avoided by controlling water as per slump test).

4. Places like junction of beam to beam to column and to one or more beams are the typical spots where honey combs are observed.

This is due to jumbling of reinforcement of beams and column rods at one place; special attention is required at such place during concreting and vibrating.

5. Presence of more percentage of bigger size of aggregate in concrete also prevents concrete to fill narrow spaces between the reinforcement rods.

@etconp


👉What are bleeding & segregation of concrete?

🏷ANSWER

■ BLEEDING :

⏺It is the tendency of the water to rise to the surface of freshly laid concrete.

This results from inability of the solid material of concrete to hold the all the water mixed fro preparation of concrete and during the process of material downward settling.

If we resort to surface finish in presence of bleeding it would weaken the top surface. Type of cement used also has influence on bleeding process.

☆☆ Effects of bleeding :

● Concrete loses its homogeneity.

● Bleeding is responsible for causing permeability in concrete.

● It reduces the bond between the reinforcement and concrete when water accumulates below reinforcing bars.

● In the process of bleeding the accumulation of water creates a water voids and reduces bond between the aggregate and cement paste.

● Due to bleeding pumping ability of concrete is reduced.

● Increase in the water-cement ratio at the top.

☆☆ Ways to reduce the bleeding :

● Reduce water content. Use lower slump mix.
● Use finer cement.

● Increase amount of fines in the sand.

● Use supplementary cementitious materials.

● Use air-entraining admixtures.

● Bleeding lowers the cement strength.

■ SEGREGATION :

⏺Segregation is the “Separation of constituent materials in concrete.” In concrete technology, segregation is of three types:-

1. Separation of Coarse aggregate from the concrete mixture.

2. Separation of Cement paste from the concrete during its plastic stage.

3. Separation of water from the concrete mix (Bleeding in concrete)

⏺Concrete is a mixture of Cement, fine and coarse aggregates.

A good concrete is one which all the constituents are properly categorized to form a homogeneous mixture.

The primary cause of Segregation in concrete is the differences in specific gravities of the constituents, Specific gravity of Cement is in between 3.1-3.6g/cc, and for aggregate it lies between 2.6-2.7g/cc due to these differences, the aggregate separates from the matrix and causes segregation in concrete.

☆☆ Some other factors causing segregation in concrete:-

● Transporting concrete mixes for long distances.

● Poorly proportioned mix, where sufficient matrix is not there to bind the aggregates.

● Dropping concrete from more than 1m.

● Vibrating concrete for a long time.

☆☆ How to minimize segregation in concrete:-

1. Segregation can be controlled by maintaining proper proportioning the mix.

2. By peculiar handling, placing, transporting, compacting and finishing,

3. By using air entraining agents, admixtures and pozzolanic materials in the mix segregation controlled to some extent.

⏺In case of segregation, the heavy aggregate particles settle down leaving a sand cement mix on top affecting the quality adversely.

Fine aggregate could be used to overcome the problems.

However; design mix must be such that required strength could be achieved.

Similarly water ratio may be catered for in design mix to avoid bleeding keeping in view the local material specifications.

@etconp


#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664


Architecture of Earthquake Resistance.pdf
23.3Мб
👉ጠቃሚ የመጽሀፍ ጥቆማ

🏷የህንጻ ቅርጽ እና ርዕደመሬት ንድፍ ለ ርዕደ መሬት ተከላካይ ኪነ ህንጻ

ለህንጻ ነዳፊዎች እጅግ የሚጠቅም በርዕደ መሬት እና በህንጻዎች  አጠቃላይ ቅርጽ ንድፍ ላይ ያተኮረ በ1981እኤአ በአሜሪካን አገር በ ናሽናል ሳይንስ ፋውንዴሽን አማካኝነት የታተመ መጽሀፍ ፒዲኤፍ ከታች ተያይዟል።

ይህ ባለ 310 ገጽ መጽሀፍ በምስሎች የበለጸገ መጽሀፍ ሲሆን ህንጻ ነዳፊዎች ህንጻዎቻቸውን ርዕደመሬት በሚያጠቃው አካባቢ  ሲነድፉ ከመጀመርያው የንድፍ እሳቤ አንስቶ የህንጻዎቻቸው አጠቃላይ ቅርጽ ውሳኔ ድረስ አትኩሮት ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ዝርዝሮች ላይ በስፋት ትኩረት ያደርጋል።

Building Configuration and Seismic Design
The Architecture of Earthquake Resistance

Christopher Arnold and Robert Reitherman , May 1981

A study conducted by Building Systems Development, Inc.,
San Mateo, California under a grant from the National Science Foundation, Washington, D.C.

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp

Показано 20 последних публикаций.