ባባ ቫንጋ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2025 ምን ይከሰታል ብለው ተነበዩ?ታዋቂዋ የቡልጋሪያ ጠንቋይ "ሶሪያ በአሸናፊዎች እጅ ትገባለች፤ በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል" ብለዋል‼️
ከ28 አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈው ባባ ቫንጋ እስከ 2030 ድረስ አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተቶች ተንብየዋልቫንገሊያ ፓንዴቫ ጉሽቴሮቫ ወይም በተለምዶ ባባ ቫንጋ እየተባሉ የሚጠሩት ቡልጋሪያዊት ጠንቋይ አዲስ አመት ሲቃረብ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ይስባሉ።
አይነስውሯ ባባ ቫንጋ በ85 አመታቸው በፈረንጆቹ 1996 ህይወታቸው ቢያልፍም እስከ 2030 አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተት ተንብየዋልና አሁንም ድረስ ይነሳሉ።
በ12 አመታቸው የአይን ብርሃናቸው ካጡ በኋላ የወደፊቱን የመተንበይ ብቃት እንዳዳበሩ የሚናገሩት ባባ ቫንጋ የመስከረም 11ዱን የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎች ጥቃት፤ የሶቪየት ህብረት መፈራረስና ካንሰር የተባለ በሽታ ቀጣይ ስጋትነትን አስቀድመው ተንብየዋል።
ከ16 ቀናት በኋላ በሚገባው 2025ም በአለማችን የሚከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከህልፈታቸው በፊት ተንብየዋል ብሏል ዴይሊ ታር በዘገባው።
የአውሮፓ ጥፋትባባ ቫንጋ የፈረንጆቹ 2025 ምዕራባውያንን ክፉኛ የሚጎዳ አስከፊ ጦርነት የሚከሰትበት መሆኑን ተንብየዋል። በሶሪያ ጉዳይ አስቀድመው ተናገሩት የተባለውም የቡልጋሪያዊቷን እንስት የመተንበይ ችሎታ በጉልህ አሳይቷል። "ሶሪያ በመጨረሻ በአሸናፊዎች እጅ ትወድቃለች፤ አሸናፊው ግን አንድ አይሆንም" ያሉት ባባ ቫንጋ፥ "በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛ የአለም ጦርነት ይጀመራል" ሲሉ ተንብየዋል።
ከዮፎ ጋር ግንኙነትባባ ቫንጋ "በ2025 የሰው ልጆች ምንነታቸው ከማይታወቁ በራሪዎች (ዮፎ) ጋር ግንኙነት ይጀምራሉ፤ ይህም ምናልባትም አለማቀፍ ቀውስ ያስከትላል" ይላሉ።
የአሜሪካዋ ኒው ጀርሲ ከአንድ ወር በላይ ዩፎ ይሁኑ ድሮኖች እስካሁን በውል ያልተለዩ በረሪ አካላት በሰማይ እያንዣበቡባት ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ካሸነፉ የአሜሪካ መንግስት በዩፎዎች ዙሪያ ያለውን ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የትራምፕ መመረጥም የባባ ቫንጋ ትንበያ እውን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ነው ተብሏል።
#Alain #Vanga
=====================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉
@Akiyas21bot @ET_SEBER_ZENA@ET_SEBER_ZENA