እናት ባንክ ‹‹አዳዲስ የቢዝነስ ሥራ መሪዎችን ማሳደግ›› በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ በአሜሪካን ኢምባሲ በተካሄደው መድረክ ልምድና ተሞክሮውን አጋራ ፡፡
መድረኩ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ የተካሄደ ሲሆን፤በዚሁ መድረክ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች፣ኢንቨስተሮችና ወጣት ሴቶች ተሳትፈዋል፡፡
በመድረኩ ሴቶች ያለቸውን የፋይናንስ አያያዝ፣የሴት የቢዝነስ ሥራ መሪዎችን አቅም በማጎልበት፣የንግድ ሥራን ማሳደግ፣የኢኮኖሚ ዕድገትን በማፋጠን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ ልምዳቸውን አጋርተዋል፡፡
የእናት ባንክ የማርኬቲግ ኮሙኒኬሽንና የደንበኞች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወይዘሮ አክሊል ግርማ፤እናት ባንክ የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ለማጎልበት እየሰራቸው ያሉ ተግባራትን በተመለከተ በማብራራት ያለውን ልምድ አጋርተዋል፡፡
የሴቶች አቅም ለመገንባትና ብቁ ሴት የቢዝነስ ሥራ መሪ ለማፍራት ቀጣይነት ባለው መልኩ በትብብር መስራት እንደሚያሰፈልግ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልበት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
——————***——————
Follow us:
https://tiktok.com/@enatbank_tikhttps://youtube.com/@enatbankhttps://instagram.com/enatbank_inshttps://t.me/EnatBank_officialhttps://www.facebook.com/enatbank.ethhttps://twitter.com/bankenathttps://www.linkedin.com/company/enat-bank-s-chttps://whatsapp.com/channel/0029Va5THJVKAwEhqj4NB40EWebsite:
https://enatbanksc.com