ESAT (ኢሳት🇪🇹)®


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኤምባሲዎችን የመሬት ጥያቄን የሚመልስ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ሲል ገለጸ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታወቀ።ካቢኔው ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከልም የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን ማስተናገድ የሚለው እንደሚገኝበት አመላክቷል።

ካቢኔው የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን የሚመልስ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ቢልም መሬት የጠየቁትን ኤምባሲዎች በዝርዝር አላሳወቀም።ከኤምባሲዎች በተጨማሪም የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን ምላሽ የሚሰጥ ውሳኔ አሳልፊያለሁ ብሏል።

የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ ተቋማትም መሬት ለመስጠት የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ከአስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

📌 📍.. THE EASIEST PLACE TO SELL AND BUY CARS

📌 📍.. VERY RELIABLE AGENT

📌 📍.. FULLY TRUSTWORTHY


📌.. ALL YOU NEED TO DO IS JOIN OUR TELEGRAM CHANNEL

https://t.me/Poppycarmarket

☎️ 0911407105   👈 ይደውሉልን


🌟 በ4 ዓመት ውስጥ 5 ሳይት ማስረከባችንን ያውቃሉ ?
✨ አዎ አሁን ደግሞ 6ኛ ፕሮጀክት የሆነው ሳርቤት ቫቲካን ኢንባሲ አጠገብ
Jenboro real estate
     በጊዜ ግቡ
የጋራ መጠቀሚያ ሙሉ በሙሉ የተማሟላለት፦
የከርሰምድር ውሀ
ባክአፕ ጀኔሬተር
ፓርኪንግ (4 ቤዝመንት)
ቴራስ
ጅም ስፓ እና የልጆች መጫዎቻ
15 ሊፍት እና 2 escaleter lift
electric charge station
Security camera ....
በዓል ምክንያት በማድረግ በ1% ቅደመ ክፍያ ሽያጭ ላይ ነን!!!
ሰፊ የካሬ አማራጭ  ከምቹ አከፋፈል ጋር

ባለሁለት  መኝታ
106 ካሬ =>125,610ብር
123 ካሬ => 145,755ብር
,136 ካሬ=> 161,160ብር

ባለ ሶስት መኝታ
150 ካሬ =>177,750ብር
157 ካሬ =>186,045ብር
176ካሬ =>208,560ብር
181 ካሬ =>214,485ብር

የሱቆች አማራጭ
ከ17 ካሬ  => 36,890ብር
38  ካሬ  =>82,460ብር
52  ካሬ =>112,840ብር
78  ካሬ =>169,260ብር
84  ካሬ  =>182,280ብር
125 ካሬ =>271,250ብር ብቻ
ልብ ይበሉ ከላይ የተጠቀሱት 1% ቅድመ ክፍያ ናቸው
ለበለጠ መረጃ 0960-7777-79 ሀሎ ይበሉ
https://t.me/apartmentandshopinfo


በእስክንድር ነጋ የሚመራዉ የፋኖ ሀየረል ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ‼️

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል።

የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ አልያም በአሜሪካ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

መንግስት በዋናነት በእስክንድር ከሚመራው የፋኖ ክንፍ  ጋር በቅርቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ እንደተወያየ እስክንድር ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልፆ ነበር። አክሎም በድርድሩ ላይ የኢጋድ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች መገኘታቸውን ገልፆ ነበር።

በውይይቱ ላይ በፋኖ ክንፉ በኩል የተነሱ ነጥቦች መከላከያ አካባቢውን በግዜያዊነትም ቢሆን ለቆ መውጣት፣ ክልሉን ማስተዳደር፣ በፌደራል መንግስቱ በስልጣን መወከል፣ የድሮን ጥቃት ማቆም፣ ለተጎዳው ህዝብ ለህይወት ሳይቀር ካሳ መክፈል እና የመሳሰሉት ናቸው ተብሏል።

በመንግስት በኩል ደግሞ ትጥቅ በመፍታት ወደ ማሰልጠኛ መግባት፣ ጎጃም አካባቢ ላይ ያለውን ነገር ማስተካከል፣ በየከተማው ያለውን አደረጃጀት መረጃ መቀበል፣ ተጠያቂ የሚሆኑ አባላቱን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም በምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ መካተት ናቸው ተብሏል።

"በመንግስት ዝግ ስብሰባ ላይ ሲያጨቃጭቅ የነበረው የነእስክንድር ክንፍ አቅም ጉዳይ ሲሆን ግምገማውም በሀገር ውስጥና በውጭ ተቀባይነትን ለማግኘት መነጋገሩ እንደ  አማራጭ ተወስዷል" ያሉን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጫችን ሸዋ ላይ ድርጅቱ የተሻለ አቅም እንዳለው፣ ነገር ግን ጎጃም ላይ የለም የሚባል ደረጃ ላይ እንደደረሰ መረጃ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል ብለዋል።

"ቢያንስ ሸዋን ማቃለሉ እንደ ጥሩ እድል በመታየቱ እና የድርድር ዝርዝር መረጃም የሚቀበሉ አለም አቀፍ ተቋማትም በመንግስት የንግግሩ ቦታ ስለተጓጓዙ ውይይቱ ተደርጓል" በማለት ሂደቱን አስረድተዋል።

"ነገር ግን አሳሳቢው ጉዳይ አሁንም ልክ እንደነ ጃል ሰኒ እንዳይሆን ነው፣ ሙሉ ሰላም ለማምጣት የተወሰነ ቡድን ሳይሆን ሁሉንም አካታች መሆን አለበት" ያሉን ደግሞ በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት የሰጡን ተንታኝ ናቸው።

"መንግስት ነገሮችን ያቀሉልኛል ብሎ እየሄደበት ያለው ይህ ነው። ሁሉም ወደ ንግግሩ መግባት አለበት፣ አልያ እንደ  ኦሮምያ አይነት ሁኔታ ይፈጠራል፣ ይባስ ብሎም በቀረው ፋኖ ታጣቂ እና በመንግስት መካከል የሚኖረው ሁኔታ ይባስ ሊካረር ይችላል" በማለት ለሚድያችን ተናግረዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል‼️

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን፤ ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1


በዛሬው ዕለት በመላው የትግራይ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጀ ሰልፎች እየተደረጉ ነው‼️

ስልፎቹ ገሚሶቹ ሰሞኑን "የትግራይ ሰራዊት የበላይ አመራሮች" ያስተላለፉትን ውሳኔ የሚቃወሙ ገሚሶቹ ደግሞ የሚደግፉ መሆናቸው ከማህበራዊ ትስስር ገፆች ለመመልከት ተችሏል።

መቐለ፣ተምቤን ዓብይ ዓዲ፣ ጣንቋ ምልሽ፣ ኮረም፣ ዓዲ ግራት፣ አኽሱም፣ ውቅሮና እንትጮ ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል ይጠቀሳሉ።

በሰልፎቹም በአንድ በኩል ከፍተኛ የጦር አመራሮቹ የወሰኑት ውሳኔ እንዲተገበርና ጊዝያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተጠየቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የጦር አመራሮቹ ውሳኔን የሚቃወም ብሎም ትግራይ ላይ ዳግም ጦርነት እንዲነሳ አንፈልግም የሚሉ ድምፆች ተሰምተዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እንደሰጉ ነዋሪዎች ገለጹ‼️

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ትላንት በሰጡት መግለጫ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ለሚመራው ህወሓት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፣ ትግራይ ክልል ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናገሩ። ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩን ወደ ሕዝብ አቅርበው “ይዳኙ” ብለዋል።

በሌላ በኩል ሦስት የክልሉ ፓርቲዎች በሰጡት መግለጫ፣ የወታደራዊ አመራርን በፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባት እንደሚቃወሙ በመግለጽ፣ “ወታደራዊ አዛዦቹ ከኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ያላቸው ናቸው" በማለት ወንጅለዋል።

ከከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራሎች አንዱ፣ ኮልኔል ገብረ ገብረ ጻድቃን፣ “የትግራይ የፀጥታ ሁኔታ ከትግራይ ሕዝብ እና የፀጥታ አካል ውጭ ባለመኾኑ የውጭ ኃይል አንሻም" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። አክለውም "ጉዳዩ ስም ማጥፋት ነው” ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


ባለቤቱን ገድሎ ስጋዋን ከትፎ መጸዳጃ ቤት ዉስጥ የከተተዉ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት‼️

ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠውን እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

©ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ

@Esat_tv1
@Esat_tv1




"የትግራይ ሐይል አዛዦች" መንግሥትና ምርጫ ቦርድ ህወሓትን ለማፍረስ አመራሩን ለመበተን እያሴሩ ነዉ አለ‼️

የትግራይ ሐይል አዛዦች በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አስታወቁ። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል። በሌላ በኩል ፓርቲውን ለማፍረስ እና አመራሩን ለመበተን እያሴሩ ነው በማለት ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትን እና የምርጫ ቦርድን ወንጅሏል። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራዉ የህወሓት ክንፍ ቁጥጥር ኮምሽን ትላንት ባወጣው መግለጫ በአስቸኳይ የህወሓት ሕጋዊነት ሰውነት ሊመለስ ይገባል ብሏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ አቅራቢያ አዲስ ሰደድ እሳት ተቀሰቀሰ‼️

በአሜሪካ ካፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል ትናንት አዲስ የሰደድ እሳት መቀስቀሱ ተነግሯል።

በሰዓታት ውስጥ ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት የሸፈነው ይህ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ስፍራቸው እያፈናቀለ መሆምኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎም 31 ሺህ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ለ23 ሺህ ሰዎች ደግሞ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ደረቅ አየርና አደገኛ ንፋስ ለሰደድ እሳቱን መዛመት ምክንያት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋም ተሰግቷል።

በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ሰደድ እሳት ለማስቆምም በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩn የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።

በሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢው ከ16 ቀናት በፊት ከተቀሰቀሰው እሳት ውስጥ ከባድ የተባሉት የኢቶንና ፓላሲደስ እሳቶች አሁንም እየነደዱ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል‼️

🗣IOM

መነሻውን ከጅቡቲ በማድረግ 35 ኢትዮጵያውያንን አሳፍሮ ወደ የመን ሲያቀና የነበረ የስደተኞች መርከብ በኃልኛ ንፋስ ተመቶ በደረሰው አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል

አደጋው ቅዳሜ ዕለት (ጥር 10) መድረሱን፤ የ9 ሴቶች እና የ11 ወንዶች ህይወት ማለፉን የጠቀሰው ድርጅቱ በመርከቡ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን ዜግነት ያላቸው መርከበኞች ደግሞ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


"🔥 ከ Shein.com የሚፈልጉትን መርጠው ይዘዙ ! 🔥
ከጂም ልብሶች እስከ የዕለት እለት ልብሶች
👔 የወንዶች ጂም ሱሪዎች🏋️‍♀️፣ ቲሸርቶች👕፣ ጂንሶች👖፣ ቦክሰሮች🩳፣ ቀበቶዎች እና

👗 የሴቶች ልብስ፣ ቦርሳ👜፣ ጫማ 🥿፣ ቀሚስ💃፣ሰዓት⌚፣ ጌጣጌጦች ማንኛውም ያሻዎትን እቃዎች።

ሌሎች ማህበራዊ የሚመረጡ ልብሶች ሁሉንም እዚህ በአንድ ቦታ ያገኛሉ የምርጫዎን
🤙 ይዘዙ ባሉበት እናደርሳለን።
🎀በጥራት የተሰሩ አስተማማኝ እና የዘመኑን

📩 አሁኑኑ ይዘዙ 👉 @lina_ahme / @muniti
📞0964350845
🔗 ይህን ሊንክ ይጠቀሙ!👇

https://t.me/mooncollections


በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ቦሉ ግዛት በሆቴል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ 66 ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ‼️

በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ቦሉ ግዛት በሆቴል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ቢያንስ 66 ሰዎች ሞተው 55 ሰዎች መጎዳታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናትን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል።

"በአደጋው የ66 ዜጎቻችንን ሕይወት አጥተናል፤ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነን" ሲሉ የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ከማል ሜሚሶግሉ፥ ከተጎጂዎቹ መካከል ቢያንስ አንዱ በአስጊ ሁኔታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገሪቱ የፍትሕ ሚኒስትር ይልማዝ ቱንክ፥ ከአደጋው ጋር በተያያዘ የሆቴሉን ባለቤት ጨምሮ 4 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው በዋና ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል።

የቦሉ ግዛት አስተዳዳሪ አብዱልአዚዝ አይዲን በበኩላቸው፥ እሳቱ በባለ 11 ወለሉ ሆቴል 4ኛ ፎቅ ላይ ከሌሊቱ 9:30 ገደማ መነሳቱን ተናግረዋል። 4ኛው ፎቅ የሆቴሉ ምግብ ቤት መሆኑንም አክለዋል።

በአደጋው ከሞቱት ሰዎች መካከል ሁለቱ ከሕንፃው ወደ ውጭ ከዘለሉ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ጠቅሰዋል።

የእሳት አደጋው በተከሰተበት ወቅት 234 እንግዶች በሆቴሉ ውስጥ እንደነበሩ አስተዳዳሪው አብዱልአዚዝ አይዲን ለአናዶሉ የዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

የአደጋው ምስሎች የሕንጻው ጣሪያና የላይኛዎቹ ወለሎች በእሳት ሲጋዩ ያሳያሉ።

በወቅቱ የሆቴሉ የአደጋ ጠቋሚ ሥርዓት ከጥቅም ውጭ ሆኖ እንደነበር የዓይን እማኞችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ፕሬዚዳንት ሬሺፕ ታይፕ ኤርዶዋን መንግሥታዊ ተቋማት የአደጋውን መንስዔ ለማጣራት እየሰሩ ነው ብለዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1




በሆሳዕና ከተማ ከእናት እጅ ታዳጊውን ነጥቆ ሊበላ የሞከረው  ጅብ በእናትየው ተጋድሎ ልጁ ማትረፍ ተቻለ‼️

በሀዲያ  ዞን በሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናራሞ ቀበሌ መንደር 16 ነዋሪ  ወይዘሮ  ደንባሌ አሥራት ጥር 11ቀን 2017  ዓ/ም  ከጧት 3 ሰዓት አከባቢ ሽላንሻ  ወንዝ ልብስ ለማጠብ  የ12 ዓመቱን ታዳጊ አሥከትላ ትሄዳለች።

ስራዋንም በመከወን ላይ እያለች አንድ ጅብ ወደ እነሱ  ይመጣል። በአጠገባ ከነበረች  ከሌላ ሴት  ጋር  በመሆን ይህንኑ ህፃን በመሀል አሥገብተዉ ቆመው  ጅቡን በፍርሀትም መመልከት ይጀምራሉ ።

ይህ ጅብ ማለፉ  ይቀርና በሁለቱም ሴቶች  መካከል  ያለውን ህፃን ዘሎ ቀኝ እግሩን ነክሶ በመያዝ ሊውሰድ ይሞክራል  የልጁ ወላጅ  እናትም ቀኝ እጁዋን  በጅብ  አፍ  ውሥጥ በመክተት የጅቡን ጓሮሮውን  በግራ እጇ አንቀ በመያዝ በላዩላይ ትወድቃለች።

በዚህ ሰአት  አብራቸው የነበረችው  ሴትም ከጅብ አፍ ህፃኑን  ነጥቃ በመውጣት ልጁን ታተርፈዋለች ።በጩኸት የወጡ ስዎች ህፃኑን ሊበላ  የቋመጠውን ጅብ  ብዙም  ሳይሄድም ደርሰው  ተባብረው ገድለውታል።እናት ለልጅ እራሷን አሳልፋ  በመሥጠት የልጁን  ህይወት ለመታደግ መቻሏን ከሀዲያ ዞን  ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


በቁጥጥር ስር ውለዋል‼️

🗣የአምቦ ከተማ አስተዳደር

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር በአንቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩና የሃይማኖት ስም በማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተማሪዎቹ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበረው የጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በታቦት እና በሃይማኖቱ ላይ ሲሳለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ቲክቶክ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ከለቀቁ በኋላ እጅግ በርካታ ሰዎች ጋር ደርሶ ቁጣን ፈጥሯል።

የአምቦ ከተማ አስተዳደር በድርጊቱ የተሳተፉ እና በማህበራዊ ገጾች ላይ የለጠፉ 3 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ (እንደታሰሩ) ገልጾ የአምቦ ዩኒቨርሲቲም የዲሲፕሊን ቅጣት ለማስተላለፍ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተውቋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1


ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች‼️

🗣ነዋሪዎች

በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ የሚቃወም ሠልፍ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 13/2017 እየተካሔደ ይገኛል።

ከሚሰሙ መፈክሮች መካከል:-

ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት መአድ ይመለሱ !

ህገ-መንግስት ይከበር !

የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይከበር !

ሰላም እና ፍትህ ለትግራይ !

@Esat_tv1
@Esat_tv1

Показано 18 последних публикаций.