በወቅቱ የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ዳይሬክተር የነበረው አህመድ ሃሰን ሳላህ ለሀገሩ በእግር ኳሱ እያደረገ ያለውን እና ሊያደርግ የሚችለውን ነገር በመግለፅ ሀገርን ከዚ በላይ ማገልገል አይጠበቅበትም ሲል ከሳላህ ጎን ቆሟል።
የወቅቱ የሀገሪቷ እግር ኳስ ዳይሬክተር አህመድ ሃሰን ለሳላህ የተናገሩት ከ10 አመታቶች ቡሃላ ልክ መሆናቸውን አለም መመልከት ቻለ ፤ ሳላህ ምንም እንኳን ለሀገሩ የአፍሪካ ዋንጫን ባያመጣም በ2017 እና በ2021 ለፍፃሜ አብቅቷቸው ዋንጫውን ቢያጡም በአለም ላይ ግብፅ ስትነሳ መሃመድ ሳላህ መሃመድ ሳላህ ሲነሳ ግብፅ መነሳቷ አይቀሬ እንዲሆን ማድረግ ችሏል።
በቡድን ለሀገሩ ስኬትን ያላመጣው ሳላህ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ከስሙ ጋር ሃገሪቷን ከፍ ማድረግ ችሏል። ሳላህ ከሀገሩ ግብፅ አልፎም በየሽልማት ስነስርአቱ በየ ትልልቅ ግጥሚያዎች ሳይቀር አፍሪካንም ማስጠራት ችሏል።
#ክፍል_7
@Ethioliverpool143@Ethioliverpool143