ባጃጅ የሠራው የ14 ዓመት ታዳጊ
የ14 ዓመት ታዳጊና የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አብዱልሃፊዝ ጸጋዬ የሚኖረው በጉራጌ ዞን ሙኽር አክሊል ወረዳ ነው።
የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች የሠራው አብዱልሃፊዝ እስካሁን ወደ አምስት የሚጠጉ የፈጠራ ሥራዎች መሥራቱንም ገልጿል። ከእነዚህም ውስጥ በኤሌክትሪክ እና በፀሐይ ብርሃን የሚሰራ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ይገኝበታል።
ከቴክኖሎጂው ጋር የተዋወቀው የሰባት ዓመት ልጅ እያለ መሆኑን የሚገልጸው የፈጠራ ባለሙያው÷ የመብራት እና የመኪና ፈጠራ እጅግ እንደሚያስደስተው ተናግሯል።
ታዳጊው ወደ ፈጠራ ሥራ የተሳበው ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ መጠየቅ እና መመራመር ስለሚወድ መሆኑንም ይገልጻል።
የታዳጊው እህት አምሪያ ጸጋዬ የወንድሟን የፈጠራ ሥራዎችን በተመለከተ በሰጠችው አስተያየት የመጀመሪያ ሥራው የምግብ ማቅረቢያ ትሪን እንደመሪ በመጠቀም በእንጨት እና በሌሎች ቁሳቁስ መኪና መስራቱን ታስታውሳለች። ከዛ በኋላ ግን በተለያዩ የትምህርት ቤት ውድድሮች ላይ እየተሳተፈ ማሸነፍ መቻሉን ትናገራለች።
አብዱልሃፊዝ ወደ ፈጠራ ሥራዎች የገባው በአካባቢው ያሉ እናቶችን ችግር በመመልከት በተለይም እናቶች ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ በአቅሙ መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነም ገልጿል።
ታዳጊው በፀሐይ ብርሃን የምትሄድ ባለሦስት እግር ወይም በተለምዶ ባጃጅ የምትባለውን ተሽከርካሪ፣ መለስተኛ አይሱዚ እና እሳት ማቀጣጠያ ከሠራቸው የፈጠራ ሥራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
አብዱልሃፊዝ በፈጠራ ሥራዎቹ ምክንያት በወረዳ እና ዞን ደረጃ በተደረጉ የተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ወደ ፊት የሠራትን ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪውን ወደ ገበያ ለማውጣት እና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ድጋፍ እንዲደረግለትም ጠይቋል።
@Ethionews433@Ethionews433