ቅ/ጽ/ቤቱ ከደንበኞች ጋር ታቀራርቦ በመስራቱ አገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳየ ተገለጸ
***************************************
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከላኪዎች፣ ከአስመጭዎች እና በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ አምራቾች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮነን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን በመንግስት የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነቶች በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱም በ2017 የበጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት በገቢ አሰባሰብ፣ በህግ ተገዥነት ስራዎች እና በአገልግሎት አሰጣጥ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገቡን አስረድተዋል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ በርካታ ደንበኞች ያሉት መሆኑን ያስታወሱት ስራአስኪያጁ ዘመኑን የዋጀ እና የደንበኞችን ክብር የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎችም እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ተፈሪ አክለውም፣ ቅ/ጽ/ቤቱ ከደንበኞች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ተቀራርቦ በመስራቱ አገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ መሻሻል እንዳሳየ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት 36 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ ይዞ እየሰራ ሲሆን ባለፉት አራት ወራት 12 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም ስራአስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
”የንግዱ ማህበረሰብ ለሀገር ብልጽግና የማይተካ ሚና አላቸው“ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ በቅ/ጽ/ቤቱ እና በደንበኞች በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች እና ችግሮቹን ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በመድረኩ የተገኙ ደንበኞች አገልግሎት አሰጣጡ መሻሻሉን ገልፀው በቀጣይም መሰል ውይይቶች እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/ecczenaበድረ ገጽ፦
www.ecc.gov.etበቴሌግራም፦
https://t.me/EthiopianCustomsCommission