ጦብያን በታሪክ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ኖር
— ስለ ኢትዮጵያ የማነባቸውን /አልፎ አልፎም ጉዞዎቼን/ እዚህ አስቀምጣለሁ ደስ ካላችሁ አንብቡ። ሌሎች ከኢትዮጵያ ያልሆኑ ነገሮችን ባጋራም አብዛኛው ከወዲህ ነው፡፡
Predominantly (but not strictly) about Ethiopia and Ethiopian history. @hewansemon

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


ሰላም ጤና ይስጥልኝ፡

ሸዋ ሮቢት አካባቢ ያላችሁ ወዳጆች፡ ሸዋ ሮቢት ውስጥ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም የምትባል ቤተ ክርስቲያን አለች? የምታውቁ ብትጽፉልኝ ወሮታ እመልሳለሁ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ

------------------------
Update:

አመሰግናለሁ። ከንግዲህ አትጨነቁ -- የጻፉልኝ ሰዎች አግዘውኛል






ይኸውላችሁ፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 9 ሰዓት ላይ (CFEE) የፈረንሳይ ኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል (ጃንሜዳ ያለው) ይሄን ውይይት በZOOM ያካሂዳል።

ርዕሱ፡ The Stelae Culture Complex in the Horn of Africa
By Dr. Ayele Tarekegn
 
On presential at the CFEE Library (Jan Meda)
 
Topic: FMSEH - CFEE 2025 Seminar Series (1)
Time: Jan 31, 2025 03:00 PM Nairobi
Join Zoom Meeting
https://univ-grenoble-alpes-fr.zoom.us/j/93176792250?pwd=FKbwRHGsjPAodxfRT1VfVPNDKhBt5y.1

Meeting ID: 931 7679 2250
Passcode: 875984


ለተጨማሪ መረጃ፡ https://cfee.hypotheses.org/10997




ቆንጅዬ ጥምቀት የሀገር ሰው። ❤️

ትዝታችንን፣ ናፍቆታችንን፣ ሰላም እና ፍቅራችንን ይመልስልን።




አባዬ የግጥም መድብል አዘጋጅቶ ዛሬ ታትሞ ተለቋል። በቅርብ ለገበያ ይለቀቃል፡፡ ድንገት መንገድ ላይ ካያችሁት ከቻላችሁ ግዙለት፣ ካልሆነም ገለጥ ገለጥ አርጉለት።

በሰባ ዓመቱ ገጥሞ፣ ታይፕ አርጎ (በቤተሰብ ርብርብም) ያዘጋጀው ነው። (በቀን ቤት ውስጥ ስንት ግጥም እንደሚነበብልን አትገምቱም። አብሶ ያቺ ትርንጎ የምትለው ግጥሙን ሁሌ ሲያነብ የተወለደበት አርማንያ/ሰሜን ሸዋ/ ትዝ እያለው እንባ እንባ ስለሚለው የቤታችን ዓባይ ግጥም ናት።) ታድያ ስብስቡን እኔ ላርምልህ ስለው 'አይሆንም አንቺ ታሪኬን ታርሚያለሽ' ብሎ ኸገጣሚው ኤፍሬም ሥዩም ጋር ነው የከረሙበት። ይመቻቸው። ጨርሰዉት ታትሟል።

እዚህም ቻናል ላይ ስላለ በዛው በሰበቡ ስለሱ ትንሽ ስጎርር እንዲያይ ብዬ ነው 😍 በቅርብ ደግሞ የሕይወት ታሪኩ ይለቀቃል።

ፎቶዎች ይከተላሉ።

መጽሐፍ፡ ጥዱ የአያቴ እኩያ ዛፍ
ደራሲ፡ ስምዖን ማርዬ
ሽፋን ዲዛይን፡ ዮፍታሄ ኃይሉ
ጥር 8 2017 ዓ.ም.


የዛሬ ወር ገደማ ስለተአምረ ማርያም ከHMML አንድ ሌክቸር ይተላለፋል (ጋሽ ጌታቸው ኃይሌ ይሠሩበት የነበረው ተቋም ማለት ነው)። እዚህ ብትመዘገቡ መሳተፍ ትችላላችሁ፡

https://secure.hmml.org/a/winter-lecture-series






የመርስዔ ኀዘን ትዝታዬ መጽሐፍ ሲያልቅ ገና ጣልያን እራሱ አልገባም። እስካሁን ሳነባቸው የነበሩት ሰውዬ ድንገት እዛ ላይ ታሪካቸው ቆሞ ኤዲተሩ ልጃቸው ስለቀረው ሕይወታቸው እና ስለአሟሟታቸው የጻፈውን ሳነብ በቅርብ የማውቃቸው ሰው ድንገት የሞቱብኝ ያህል ነው ያስለቀሱኝ። ያረፉት ደርግ በገባ ባምስት ዓመቱ ነው። አስቡት ኢትዮጵያን በስንት ሞያቸው እና በየትልልቅ ድርጅቱ ሲያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ሀገሪቷ እርስበርሷ ስትታመስ እያዩ ሲሞቱ። አሳዘኑኝ።

ሆነም ቀረም ልጃቸው የጻፈው ማሳረጊያ ምዕራፍ ዉስጥ ይሄን አይቼ ትንሽ አዝናንቶኝ ነው፡

በ1918 ዓ.ም. 14ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ ታትሞ ኖሮ በ1942 የወጣውን ብላታ መርስዔ ኀዘን ናቸው አሻሽለው ያዘጋጁት (እነ ሊጦን፣ መስተብቍዕ እና ዘይነግሥ ተጨምረው) እና ከመጽሐፉ ሽያጭ የተገኘው ጥቅም ለማን ሄደ መሰላችሁ? «የኢጣልያ ጦር በ1929 ዓ.ም. ሕፅዋን (ጃንደረባ) ላደረጋቸው ድኾች ልጆች ለሚያድጉበት መንፈሳዊ ትምህርት ቤት እንዲሰጥ ተደርጎ ነበር» ይለናል መጽሐፉ። (ገጽ 225)

ጃንደረባ በግዕዙ ስልብ አገልጋይ ማለት ነው ፡) -- በየሚዲያው ለሚታየው አዲሱ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ትውልድ ሲባል ምን እያልን እንደሆንን ለማሳየትም ነው። (ያው አሁን ትርጉሙን ለውጠን ይሆናል ግን አመጣጡን ማወቃችን አይከፋም)

--
መርስዔ ኀዘን ያገለገሉባቸውን፣ የሠሩዋቸውን ሁሉ የሚጠቅሰውን ምዕራፍ ፎቶ አንስቼ ከሥር ልኬያለሁ።

አሰላም-አሌይኩም






አጼ ቴዎድሮስ ልደታቸው ዛሬ ነው ይላሉ ብዙ ሰዎች። በርግጥ ሦስቱም ዜና መዋዕሎቻቸው አነሳሳቸው፣ ቤተሰባቸውን እና የትውልድ ቦታቸውን እንጂ መች እንደተወለዱ በውል አይነግሩንም። በገደምዳሜ ወደ 1813/14 ገደማ ተወለደ ነው የምንለው። 200+ ዓመታት ማለት ነው። የአንዳንድ ሰው ልጅ ዕድለኛ ነው፡ ከነበረበት ዘመን ሲርቅ ታሪኩ እያማረለት ይሄዳል። ቴዲም እንዲሁ ነው። ከጥፋቱ ይልቅ ሐሳቡ ይመስጠናል አይደለም? ስለዚህም ዛሬ ተወለደ አልተወለደ ብዙ ለውጥ የለዉም ያ እብድ ገና ሲዘመርለት ይኖራል።

በደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት ላይ እብዱ ገብረኪዳን የአጼ ቴዎድሮስ የሐሜት ስም የምትል ነገር አለች። (see ደስታ ተክለወልድ፤ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 74)

ቢሆንም፣ ዛሬ እያከበራችሁ ላላችሁ ከአንዱ ዜና መዋዕል በደረስጌ ማርያም እንደነገሠ የተናገረው አዋጅ ተብሎ የተጻፈውን ላሳያችሁ።

«አራሽ እረስ የወንድ መኮንን ሴት ወይዘሮ ባለ ጉልት ባለ እርስት እየአባትህ ሰጥቼአለሁ። ነጋዴም ነግድ በተቀማህበት ቦታ ደንጊያ ደርድረህ ወደኔ ና። ተወኝ ሌባ ተወኝ ወምበዴ ግባ። እቀማለሁ እሰርቃለሁ ብትል ለአካልህ እዘንለት። አይዞህ ድሃ አይዞህ ወታደር ደስ ይበልህ በክርስቶስ ኃይል ወጥቼልአለሁ። የኢያሱ ይብቃ።»

ገጽ 12፣ ስሙ ካልታወቀ ጸሐፊ የተጻፈ ያጤ ቴዎድሮስ ታሪክ፣ ፉሴላ ኤዲት ያደረግው።




ጅጅጋ እና የአውሮፕላን ነጂነት ማሠልጠኛ

«አውሮፕላን በ1920 ዓ.ም. በነሐሴ ወር ከጅቡቲ መጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ ከዐረፈ በኋላ የአወሮፕላን ነጅነት ትምህርት አዲስ አበባ ላይ ተጀመረ። እንዲሁ ደግሞ በዚህ ዓመት (1922 ዓ.ም.) በሰኔ ወር ትምህርት ቤቱ ወደ ጅጅጋ ከተማ ተዛውሮ የትምህርቱ ሥራ እንዲቀጥል ተደረገ። ምክንያቱም የአዲስ አበባ ዝናሙና ጭቃው አስቸጋሪ መሆኑን፤ ጅጅጋ ግን የተመቸ ሥፍራ መሆኑን በመመልከት ነው። ስለዚህም አስተማሪው ሙሴ ቤዴልና ሜካኒሲዬው ሙሴ ፒካፔር ክረምቱን ሙሉ ሲያስተምሩና አውሮፕላን ሲያስነዱ ጅጅጋ ላይ ከረሙ። ተማሪዎቹ ብዙዎች ሲሆኑ በእነርሱ መካከል ሚሸካ ባቢቸፍና አስፋው ዓሊ የተባሉ እንደ ነበሩ አስታውሳለሁ።»

ፎቶው ላይ ያሉት፡ ፊታውራሪ ታፈሰ ሀብተሚካኤል የጅጅጋ አገረ ገዥ ነበሩ በሰዓቱ። ሙሴ ቤዴል አስተማሪው ሲሆኑ ካፕቴን ዊድሜር ማን እንደሆኑ እንጃ። (ሙሴ የሚሉት ቃል የፈረንሳይኛው አቶ ሳይሆን አይቀርም፡ ሜስዬ እንደማለት።) ፎቶውን የተነሱት አዲስ አበባ ይሁን ጅጅጋ በርግጥ ባይጠቀስም ፊታ. ታፈሰ የጅጅጋ አስተዳዳሪ እንደመሆናቸው ጅጅጋ ሳሉ የተነሱት ሊሆን ይችላል።

ከመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ትዝታዬ፡ ስለራሴ የማስታውሰው
ገጽ፡ 204-205

Показано 17 последних публикаций.