የመንግሥትና የግል ሠራተኞች ከደመወዛቸው ለአደጋ ሥጋት ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ
ባንክና ኢንሹራንስን ጨምሮ በበርካታ አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ይፈጸማል
የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በወቅቱ ገቢ የማያደርጉ ወለድና ቅጣት ይከፍላሉ
የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካል ሆኖ እንዲቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ የመንግሥትና የግል ድርጅት ተቀጣሪ ሠራተኞች ከሚከፈላቸው የተጣራ የወር ደመወዝ ላይ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስገድድ ድንጋጌ ተካተተ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የምክር ቤት አባላት በረቂቁ ላይ ለስምንት ደቂቃ ያህል ከተወያዩበት በኋላ፣ ለምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ ተመርቷል፡፡
በረቂቅ አዋጁ ማብራሪያ ላይ በቅድመ አደጋ፣ በአደጋና በድኅረ አደጋ ወቅቶች ለሚወሰዱ የአደጋ ሥጋት ቅነሳ፣ ምላሽና መልሶ ማቋቋም የሚሆን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ መቋቋሙ ተገልጿል፡፡...
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://www.proworksmedia.com/139426/