ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   [  ሦ ስ ተ ኛ   ሳ ም ን ት    ]   🕊


▷         " ም  ኩ  ራ  ብ "

  [    በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን    ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

[                          🕊                         ]

❝ ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ ፥ ሊያነብም ተነሣ። ❞ 

[ ሉቃ.፬፥፲፮ ]


🕊                       💖                   🕊


Репост из: የአእላፍት ዝማሬ | Melody Of Myriads
ኢጃት ለሕፃናት ድጋፍ ለማድረግ ተጨማሪ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረመ።

| ጃንደረባው ሚዲያ | የካቲት 2017 ዓ.ም|

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ  ለጋራ ሥራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስር ካሉት 23 ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ጃን ቂርቆስ ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ እና ከገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 100 ሕፃናት የገንዘብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና፣ የስልጠና እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም የሕፃናቱ አካላዊ እድገት፣ ጤና፣ የአዕምሮ መጎልበት፣ መንፈሳዊ እድገት አንዲሁም ማኅበራዊ ግንኙነት መዳበር ነው፡፡

በእነዚህ ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ ፕሮጀክቱ የሕፃናቱን ሁለንተዊ እድገትን ከማስጠበቅ አኳያ አበረታች ውጤት ስለተገኘበት በያዝነው 2017 ዓ.ም. ደግሞ ተደራሽነቱን በማስፋት ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ለ 230 ሕፃናት ለሶስት አመት የሚቆይ ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባው ትውልድ ማህበር እና በሰንበት ትምህርት ቤቶቹ መሀከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።




በአንድም ወቅት በሀገራችን የእህል መታጣት ሆነና ቅድስት እናታችን ዘወትር እንደምታደርገው የኪዳምሕረትን ዝክር ልታደርግ ብላ ዝክሩን የምታደርግበት እህል አጣች፡፡ ደናግል ልጆቿንም ጠርታ ትንሽ ዱቄት እንዲያመጡላት ነግራቸው አመጡላት፡፡ በዚያችም ትንሽ ዱቄት ላይ ጸሎት አድርጋ ከጨረሰች በኋላ ‹ወደ ቦታው መልሱት› አለቻቸው፡፡ በማግስቱም እንስራው ጋኑ ሁሉ በዱቄት ተሞልቶ አግኝተውታል፡፡ ቅድስት እናታችንና ልጆቿም የየካቲት ኪዳነ ምሕረትን በዓል በታላቅ ደስታ አክብረዋል፡፡

መልአኩም እናታችንን ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኋላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ስትደርስ ከቦታዋ ላይ ዓምደ ብርሃን ተጨማሪ ተተክሎ በቀስተ ደማና ተከቦ አይታ ‹‹ይህች ቦታ ምንታምር›› ብላ ጠራቻት፡፡ በ #መድኃኔዓለምም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታለች፡፡ ቦታዋ ዛሬም ድረስ ‹ምንታምር› እየተባለች የምትጠራ ሲሆን ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ የሠራቻት በስሚዛ (በሰንሰል) እንጨት፣ በአይጥ ሐረግ፣ በነጠላ ማገር አድርጋ የግድግዳ ቤተ መቅደስ በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታ በታኅሣሥ 16 ቀን በዕለተ እሁድ ቅዳሴ ቤቷን አክብራለች፡፡ በዚህም ጊዜ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤልና ቅዱስ መሲፋይል በክንፋቸው አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው በቦታዋ ላይ ቀላቅለውበታል፡፡ #ጌታችንም ከብርሃን እናቱ ከቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር ለፍቅርተ ክርስቶስ ተገልጦላት ቦታዋን ባርኮላት እስከዕለተ ምፅዓትም ድረስ እንደማትፈርስ ቃልኪዳን ገብቶላታል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ከባድ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ጫካውን ሁሉ ሲያቃጥል ከቤተክርስያኗ ላይ ግን ለምልክት ያህል ጫፏ ላይ ያለችውን የሰጎን እንቁላል ብቻ አቃጥሎ ቤተ መቅደሷን አልፎ ሄዶ ጫካውን ሁሉ አቃጥሏል፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በአንዲት ቀን ብቻ በተአምራት የሠራቻት ቤተ ክርስቲያኗ ተሠርታ ባለቀች ጊዜ #ጌታችን ለእናታችን ተገልጦላታል፡፡ ጌታችንም በተገለጠላት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ በአራቱም አቅጣጫ ለ #ጌታችን ሰግዳለች፡፡ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ በአራቱም አቅጣጫ ሆነው ሲመለከቷት በተቃራኒው አቅጣጫ እየሰገደች ትታያለች፡፡ በምሥራቅ አቅጣጫ ሆነው ቢያዩዋት ወደ ምዕራብ ሰግዳ ትታያለች፤ በምዕራብም ሆነው ቢያዩዋት ወደ ምሥራቅ ሰግዳ ትያለች፡፡ በሰሜን አቅጣጫ ሆነው ቢያዩዋት ወደ ደቡብ ሰግዳ ትታያለች፤ በደቡብም ሆነው ቢያዩዋት ወደ ሰሜን ሰግዳ ትያለች፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በተሰጣት ቃልኪዳን መሠረት በገዳሟም ውስጥ መርዘኛ እባብም ቢሆን ሰውን ወይም እንስሳትን ቢነድፍ መርዙ ምንም አይጎዳም፡፡ እንዲሁም ጌታችን ገዳሟን መናፍቃን ወይም ከሐዲያን እንደማይረግጧት ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ለምሳሌ የጣሊያን ጦር በሀገራችን የተለያዩ ገዳማትን እያጠፋ መነኮሳትን እየገደለ ከፍተኛ ጥፋት ባደረሰበት ወቅት ይህችንም ገዳም ለማጥፋትና መነኮሳቶቹንም ለመግደል መጥቶ ነበር፡፡ መነኮሳቶቹም ይህን ሰምተው ለሰማዕትነት ተዘጋጅተው ጠበቁ ነገር ግን የጦር አዛዡና ሠራዊቱ የገዳሟን ክልል አልፈው መግባት አልቻሉም፣ የገዳሟ ክልል ላይ ሲደርሱ በተአምራት እግራቸው ተሳስሮ መቆም መቀመጥ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ የጦር አዛዡም ‹‹ #ክርስቶስ ከዚች ገዳም አለ›› ብሎ ሃምሳ ጠገራ ብር ሰጥቶ ወደመጣበት ተመልሷል፡፡

#መድኃኔዓለም_ክርስቶስ በዚህች ገዳም ላይ ለቅድስት እናታችን ድንቅ ድንቅ ቃልኪዳን ከሰጣት በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በየካቲት 29 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፋለች፡፡ በሥጋዋም ላይ ታላቅ የብርሃን አምድ ተተክሎ የታየ ሲሆን እንደፀሐይም ከጠዋት እስከ ማታ ያበራ ነበር፡፡ በመካነ መቃብሯም ላይ እስከ አርባ ቀን ድረስ ብርሃን ተተክሎ ታይቷል፡፡

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት: በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ
ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም
የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቷም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት 29)


የካቲት 29❤️
#ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (ዕረፍቷ)
✞✞✞


የካቲት ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ታላቋ ሐዋርያዊት እናታችን የእመ ምኡዝ ቅድስት ፍቅርተ #ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት ዕረፍቷ ነው፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ወይም እመ-ምዑዝ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደራ ፎገራ አንበሳሜ በሚባለው ቦታ የአብርሃምና የሣራ ምግባር ካላቸው ከአባቷ ከላባ ከእናቷ ከወንጌላዊት #ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን በታዘዘ መልአክ አብሳሪነት ተወለደች፡፡ በተወለደችም ጊዜ በእግሯ ቆማ ‹‹በማኅየዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለ #አብ ምስጋና ለ #ወልድ ምስጋና ለ #መንፈስ_ቅዱስም ምስጋና ይገባል›› ብላ አምላኳን አመስግናለች፡፡ ቤተሰቦቿ ያገኙዋት በስዕለት ሲሆን ስመ ክርስትናዋም ማርያም ጸዳለ ተባለ፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የሚለው የቆብ (የምንኩስና) ስሟ ነው፡፡ ዕድሜዋ ለትምህርት እንደደረሰ #እግዚአብሔር የላከው አንድ ደገኛ መነኩሴ ወደ እርሷ በመሄድ የዳዊትን መዝሙር፣ የብሉያትና የሐዲሳት መጻሕፍትንና የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ በሚገባ አስተምሯታል፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በነበረችበት ዘመን ዐፄ ሱስንዮስ ‹‹ሁለት ባሕርይ›› የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት የአገራችን ሕዝዝ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ስለተነሣና ከ8ሺህ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖንና ከሌሎችም ቅዱሳንና ቅዱሳት ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነትን ተቀብላ ለሃይማኖቷ መስክር ሆናለች፡፡ ባለቤቷ ዘርዐ ክርስቶስም በሰማዕትነት ዐርፎ ሰባት አክሊላት ወርደውለታል፡፡

ዐፄ ሱስንዮስ ለፖለቲካዊ ጥቅም ብሎ የረከሰች የሮማውያንን ሃይማኖት በአገራችን ላይ እንዳወጀ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖን ካህናትንና ክርስቲያን ልጆቻቸውን አነሳስተው እያስተማሩና እያጠነከሩ እያለ በጦር ተወግተው በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖንም በሰማዕትነት ከማረፋቸው በፊት ግን እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስን፣ ቅድስት አካለ ክርስቶስን፣ ቅድስት እመ ወተትንና ሌሎቹንም ቅዱሳንና ቅዱሳት አነሳስተው ባራ ሄደው ንጉሡን መክረውታል፣ ገሥጸውታል፡፡ ንጉሡ ግን ከፍተኛ ፖሊቲካዊ ጥቅም እንደሚያገኝ ሮማውያን ቃል ገብተውለት ስለነበር ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶች አብዝተው ቢመክሩትም ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይልቁንም ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የሃይማኖቷን ጽናት ስላየ ሥጋዋ እየተቆረሰ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በብረት በትር አጥብቆ ያስገርፋት ጀመር፡፡

በመጨረሻም ምድር እየሰወረቻት ለመግረፍ የማይመቻቸው ቢሆን ከሌሎቹ ሰማዕታት ጋር አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍጹም ጨለማ ሆኖ ምድርም ተነዋወጠች፡፡ ስምንት ሺህ አሥር ቅዱሳንም በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አንገቷን በሰይፍ ቢቆርጧትና በሞት ብታርፍም ነገር ግን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14 ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት አስነሥቶ ወደ ቦታዋ መለሳት፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ከሞት ካስነሣት በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መናኒ ሆና በየገዳሙና በየአድባራቱ እየሔደች ዓለምን ስትዞር ያቀናቻቸው ብዙ ገዳማት አሉ፡፡ ለምሳሌ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ በሆኑት በአባ ጉባ ተመሥርታ በግራኝ ወረራ ጠፍታ የነበረችውን ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳምን አቅንታ የወንድና የሴት ገዳም ብላ ሥርዓት ሠርታለች፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ ሰውን የሚበሉ ፍጡሮች ወደሚኖሩበት አካባቢ ስትደርስ 60 የሚሆኑ አገልጋዮቿን ለመብላት ይዘው ሳር ቅጠል እንዲበሉ በማድረግ ዐይናቸውን በጉጠት በማውጣት 4 ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጉባቸው፡፡ ሰይጣንንም ያመልኩ ነበርና ከ4 ወራት በኋላም በዓል አድርገው ለመብላት ከእሳት ውስጥ ጨመሯቸው፣ ነገር ግን #ጌታችን በቸርነቱ ጠብቋቸዋልና እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን ምንም አልሆኑም፡፡ ያንጊዜም ሰው በላዎቹ ‹‹እናንተ ሰዎች ምንድን ናችሁ?›› ብለው ጠየቋቸው።

ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስም ክርስቲያን መሆናቸውንና እነርሱ የ
#ሥላሴ ሕንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብታስተምራቸው ‹‹ምን እንበላለን?›› አሏት፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምሕረት ስትነሳ የእህል ዘርን ለአገልጋዮቿ አሰይዛ ስለነበር ከዚያ ስንዴ ወስዳ ዘራችው፡፡ ስንዴውም በአንድ ቀን ብቻ ተዘርቶ በቅሎ፣ ታጭዶ፣ ደርቆ፣ ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡ ቅድስት እናታችንም ቀምሳ ስታቀምሳቸው እንደማር እንደወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርታላቸዋለች፡፡ ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ጽፋ አስቀመጠችላቸው፡፡ እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ምን ያህል የከበረች ‹‹ሐዋሪያዊት›› እንደሆነች ከዚህ ልብ ይሏል፡፡

የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ተገልጣላት በልጇ ምክንያት ስለደረሱባት ሀዘኖች አውርታላታለች፡፡ የፈለገችውንም እንድታደርግበት በእጇ ያለውን #መስቀል ለፍቅርተ ክርስቶስ ሰጥታታለች፡፡ በዚህም #መስቀል እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ባሕር ከፍላ ደቀ መዛሙርቶቿን አሻግራለች፡፡ የአባታችን የቅዱስ ኤዎስጣቴዎስን ገድል በማንበብና በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እርዳታ ባህሩን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን ሄዳለች፡፡ እንዲሁም በበትረ መስቀሏም እንደ ዘርዐ ቡሩክ ከባሕር ውስጥ የሠጠሙ የደቀ መዛሙርቶቿን መጻሕፍት ምንም ሳይሆኑ ማውጣት ችላለች፡፡ እናታችን በሁሉም ሀገር እየዞረች ቅዱሳት መካናትን ትሳለም ነበር፡፡

በደብረ ዳሞም ሄዳ ‹‹ሴቶች መውጣት አይችሉም›› ቢሏት በሀዘን ስታለቅስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በሥውር ወስዶ ከዓምባው ላይ አውጥቶ ከቤተ መቅደሱ አድርሷታል፣ አቡነ አረጋዊም ተገልጸውላት ባርከዋታል፡፡ በዚያም ቅዱሰ ሥጋ ወደሙን በእጃቸው ተቀብላለች፡፡ እናታችን ወደ ኢየሩሳሌምም ሄዳ ቅዱሳት መካናትን እየተሳለመች ለ7 ዓመታት ቆይታለች፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በዓምደ ብርሃን እየመራት ተመልሳ ወደ ሀገራችን መጥታ በድጋሚ ከሱስንዮስ ጋር ተሟግታለች፡፡ ሙታንንም እያስነሳች እንዲመሰክሩለት ብታደርግም እርሱ ግን ከጥፋቱና ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ነገር ግን እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ መልእክቷንም በንስር አሞራ አድርጋ እየላከች ትመክረው ነበር፡፡


"ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መድኃኒትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን የመማፀኛ ከተማህ ናት፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ትልቁ ኃጢአት

በሰው ልብ የተተከለው ትልቁ ጠላት ትእቢት Pride ነው።
ትልቁ ኃጢአት ትእቢት።  ትእቢት ራስን ከፍ አደርጎ የማየት፣ ሌላውን የማሳነስ፣ ለእኔ የተሻለው ይገባኛል፣ ሌላውን መናቅ ነው። የሌላው ሕመም የማይገባው፣ የወንድሙ ሳይኾን የራሱ ጥቅምን ብቻ የሚያሰላ ነው። 

ትእቢት ሰው አእምሮውን እያገኘ አዕምሮ እያደገ በመጣ ቁጥር ከመሠረቱ በትንሹ እየበቀለች የምትሄድ ናት። አንዲት ቅንጣት ኾና እንደ ዛፍ ተተክሎ ብዙ ቅርንጫፍ ዘርግቶ ሌሎች አስፈላጊ እጽዋትን እንደሚገድል ዛፍ አይነት ነው። በሰው ሕይወት ውስጥ ትእቢት የተለያየ መገለጫ አለው። 

ይነስም ይብዛም የትእቢት ተክል የሌለበት የለም። እንደ ጥንካሬው እየገደላት እያቀጨጫት ፈጽሞም ያሸነፋትም ይኔራል። አንድ ጊዜ አንዱን ረድእ አበምኔቱ አንተ ትእቢት አለብህ አሉት። እሱም አባቴ በፍጹም ትእቢት የለብኝም አላቸው። በል ተወው  ራስህ ተናገርክ አሉት። ትእቢት የለብኝም ብሎ መናገር በራሱ ትእቢት መኾኑን አስተማሩት። 

የትእቢት መገለጫው አጫፋሪዎቹ ብዙ ናቸው። የተሽቀረቀረ (ፋሽን) አለባበስ፣ ተኳኩሎ ተውቦ መታየት፣ በሌላው በጓደኛው ዘንድ የተሻለ መስሎ መታየት፣ ልጅ በሌላቸው ፊት ልጅ መኖሩ የተባረከ አስመስሎ ማውራት፣ ከሌላው ይልቅ የተማረ መኾኑን ማሳየት፣ የትእቢት መልኬቹ ብዙ ናቸው። ድምጼ አናረልኝ ብሎ ሲዘባነን ማየት፣ ተማርኩ ብሎ አፋን በነጠላ ሸፍኖ ሌላውን የጎሪጥ ማየት፣ ማሽሟጠጥ የመሳሰሉት ኹሉ የትእቢት ቅርንጫፎች ናቸው። 

የማያምኑ የማይጾሙ የማይጸልዩ ሰዎች ስናይ እኛ የተለየ ቅድስና የተሻለ ለእግዚአብሔር ቅርብ የኾንን፣ ከመሰለን ትእቢት ነው። ብዙ ሰው ትእቢት በምን መልክ እንደ በቀለችበት አያውቅም። ስለዚኽም ትእቢቱን እየተንከባደበ ያሳድጋታል። 
አንጀቱ እስኪቆስል ቢጾም፣ ጉልበቱ እስኪላጥ ቢሰግድ፣ እንደ ጊዮርጊስ ብንጋደል፣ ትእቢት እስካለበት ድረስ አይጠቅሙትም። ጽድቅ ያለ ትኅትና አይጠቅምም። 
“ጎልያድ በዳዊት ላይ ታበየ ነገር ግን ለውሻ በሚወነጨፍ ትንሽ ደንጊያ ሞተ። ትሑቱ ዳዊት ግን ለእርሱና ለዘሩ እስከዘለዓለሙ ነገሠ። ትሕትና ከትእግስት ይወለዳልና።” ርቱዓ ሃይማኖት 

ትልቁ ምግባር ትኅትና Humility ነው። “ትኅትና ማለት ክፉ ላደረገብህ በጎ ስታደርግለት ነው።” ይላል።  ዜና አበው 146

ትኅትና ኹሉም ከእኔ ይሻላል ብሎ ማሰብ ነው። ሌላውን ማስቀደም ነው። ትኅትና እስከ መጨረሻው መውረድ ነው። ምንም ሳይኖርኽ ድሃ ነኝ ብትል ትኅትና አይደለም። ምንም ስለሌለኽ ነው። ኖሮኽ እንደሌለኽ ኾኖ ማሰብና መኖር ነው። ክርስቶስ አምላክ ነው። አምላክነቱ ግን በሰዎች መናቅን አላስቀረውም። እመቤታችን የእኛን በደል አልተካፈለችም፣ ሰው አልሰደበች አልተመቀኘች ፣ ገንዘብ አልተበደረች ግን ተሰድባለች፣ ተገፍትራለች። ጸሎቷም 
“የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” አለች። ሉቃ.1:48

እኛን ያዋረደ ኃጢአት ሳይኔርባት በእግዚአብሔር ፊት ራሷን እንደ ባርያ ዝቅ አደረገች። ባርያ የራሱ ፈቃድ የለውም። የጌታው ነው። እመቤታችን እግዚአብሔር ፈቃድን በምልዓት የፈጸመባት ኪዳኑ ናት። ከፍጥረት በላይ ኾና ራሷን ዝቅ ያደረገች፣ የትኅትና አስተማሪያችን ናት። 
አድርገኽ እንዳላደረግኽ ስታስብ፣ ሰጥተኽ እንዳልሰጠኽ ስታስብ፣ ጠቅመኽ እንዳልጠቀምኽ ስታስብ የትኅትናን መንገድ ጀምረሃል። 

ንዋይ ካሳሁን

3.2k 0 53 11 83

ሠላሜ ነህ ፀትታዮ
ወደቤ ነህ ማረፊያዬ
ሁን ከኔ ጋራ አሁን ከጎኔ
ፍቅር እኮ መድህኔ

https://t.me/Ethiopian_Ortodoks




ምርኩዜ🥺
ክፍል ፩
የሰው ልጅ እንደዚህ ሲንገዳገድ አይቼ አላውቅም አንድ ጊዜ ወደግራ ደግሞ ወደቀኝ ብቻ ምን አለፋችሁ ካሁን ካሁን ወደቀ እያለ ሰው ይመለከታል በሁለት ሊትር ሃይላንድ የተሞላ ድራፍት በቀኝ እጁ ይዟል በግራ እጁ ደግሞ ሲጋራውን ጨብጧል በብብቱ መሃል ደግሞ ጫቱን ይዞ እየተወላገደ ይራመዳል ያገኘውን ሰው ሁሉ እግዚአብሔርን አትከተሉት እንደኔ ያሰቃያችኋል እያለ ይመክራል መንገደኛው ሁሉ ወይ ጊዜ ሰው እንዴት በጠራራ ፀሃይ ይሰክራል እያለ ይመፃደቅበታል ድሮ የሚያውቁት ደግሞ አይ እንደዛ እንዳልተከበርክ በሀይላንድ ፀበሉን በፌስታል እምነቱን በክብሪት ጧፉን እንዳለኮስክ እንዲህ ተበላሽተህ ቀረህ እያሉ ከንፈራቸውን መምጠጥ ከጀመሩለት ሰነባብተዋል የሰፈሩ ህፃናት እንኳን ሳይቀሩ ባዶ እጁን ሲያዩት እንደ አበደ ሰው ነው የሚቆጥሩት ደግነቱ እሱ ባዶውን አይሄድም እንጂ ሁልጊዜ አቋራጭ መንገድ እያለ ወደ ቤቱ የሚገባው ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ ነው እንድ ቀን አንድ ሰው ለምን በሚካኤል በኩል አድርገህ በአቋራጭ አትሄድም ሲለው እኔ ሚካኤል በተጠራበት በኩል ማለፍ ስለማልፈልግ ነው እንጂ ዙሪያ ጥምጥም መንገድ ፈልጌ አይደለም ግን እስከለተ ሞቴ በሚካኤል በር አላልፍም አለው ከዚያ ወዲህ ማንም ሰው ጠይቆት አያውቅም ለሰፈሩ አዲስ የሆኑ መጤ ሰዎች አይ ይሄ ሰው በቃ ሁልጊዜ መጠጣት መስከር ነው አይደል የሚያውቀው ሰውስ ቆይ ለምንድን ነው ብር የሚሰጠው አንዳንድ ሰዎች የጠቀሙት እየመሰላቸው በነፍሱ ይጫወቱበታል ወይ ዘመን እያሉ ይማረራሉ ሁልጊዜ ስለሱ መጥፎ ሲወራ የሚያቀጠቅጣቸው አንድ አባት እኔ ምላችሁ ልጆቼ ዛሬ ቅዱስን ያየው ሰው አለ እንዴ አለ አንዷ ቀልጠፍ ብላ ውይ ጋሼ ደግሞ አሁን ቅዱስ እዚህ ይኖራል ብለው ነው ያው እዛው መጠጥ ቤት እየተጋተ ይሆናል እንጂ…

ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ

4.4k 0 36 20 119

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ። [አቡነ ሺኖዳ ]

ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲🌷

4k 0 9 13 174

Репост из: የአእላፍት ዝማሬ | Melody Of Myriads
አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው አምላክ ስም በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
1ኛ ሳሙ 17፡45

ዐድዋ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ገበዘ ኢትዮጵያ




የካቲት 23 ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያረገወ ተዐምር ይኽ ነው፡፡

በዚያን ወራት የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክም ሀገሬ
ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ኹሉ ፈጥኖ ይነሣ፡፡የጦር መሣሪያውን
ተሸክሞ ይከተለኝ ዘንድ በሰመ ማርያም አደራ እላላለሁ ሲል ዐዋጅ አሰነገረ፡፡
ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ በጋሻቸው
እምብርት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ መስቀል
ጠላትን ድር አድራጊ እንደኾነ አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡

ወደ አንዷ የትግራይ አውራጃም ምድረ ዐደዋ ደረሰ
፡፡ የዚኽ ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክ ሚስት እቴጌ ጣይቱ(ወለተ ሚካኤል)በንጉሡ ትእዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስ አስይዞ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ማቴዎስና ከቀሳውስቱና መነኮሳቱ ከንጉሡ ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክም ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዘች፡፡ በዚህም ጊዜ ኹላቸው ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ምኒልኮ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ፡፡
ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ይኸውም ወርኃ የካቲት ኻያ ኹለትቀን ነው፡፡ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ዓፄ ምኒልክም የጦር ልብሱን ለብሶ ከሠራዊቱ ጋር ጦር ግንባር ገባ፡፡ ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ 11ሰዓት ጦርነቱ
ተጀመረ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ቅዶስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት እያደረች ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመሔድ እጅግ በሚያስደንቅ የአነጋገሯ ኃይል ቃል በጦርነቱ መኻል እየተገኘች ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ትሰጣቸው ነበር፡፡
በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ዓፄ ምኒልክ በጦርነቱ መኻል ሳለ ሊቀ
ጳጳሳቱ አባ ማቴዎስና ኹላቸው ካህናትም ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኃላ ቆመው ጸሎተ ምሕላ ያደርሱ ነበር፡፡

ንግሥቲቱ እቴጌ ጣይቱም በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ
አትለይም ነበር፡፡ ኹላቸው ካህናትም በአምላካቸው እግዚአብሐር የሕግ ታቦት
ፊት መለከት ይነፋ ነበር፡፡
በዚህም ዕለት ይኸውም በወርኃ የካቲት 23 ቀን በሮማውያንና
በኢትዮጵያውያን መካከል ከፈተኛ ጦርነት ኾነ፡፡ በሰማይም ታላቅ ተዐምር
ተደረገ፡፡ የቀስተ ደመና ምልክት ታየ፡፡ ከቀስተ ደመና ውስጥ መልኩ አረንጓዴ
የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር እንደ ክረምት ነጎድጎድ ያለ ድምፅም ተሰማ፡፡
ከዚኽ የነጎድጎድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና
ሽብር ሆነ ለመዋጋትም አልቻሉም፡፡

ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተዐምር ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነፋስ ይልቆ እየሀፋጠነ በዓየር ላይ በተገለጸ ጊዜ ሮማውያን በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ፡፡ እንግዲህ ማን ያድነናል አሉ፡፡ ምድር ጠበበቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን ጦር ሠራዊት ፈጇቸው፡፡
የተረፋትንም ማረኳቸው ፈጽመው እስኪያጠፏቸውም በሮማውያን ላይ
የእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያን እጅ እየበረታች ሔደች፡፡
የኢትያጵያው ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ
በእግዚአብሔር ኃይል በገባሬ ተዐምራት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት
የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርጎ የድል አክሊል ተቀዳጀ፡፡

በነቢዩ ዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔር ባለ ዘመኔ ኹሉ አመሰግነዋለሁ ለፈጣሪዬ እዘምራለሁ አለ፡፡
ሕዝቡም ኹሉ በክብር ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና
እናመሰግነዋለን የሮማዉያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም
ሰባብሯልና ሠራዊቱንም ኹሉ በምድር ላይ በትኗልና እያሉ አመሰገኑ፡፡
በፈጣሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መኻል የረዳቸው ቅዱስ
ጊዮርጊስንም በፍጹም አደነቁ፡፡ የሮማ የጦር ሠራዊትም በኢትዮጵያውያን ፊተቀ ተዋረዱ ዳግኛም በኢትያጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም፡፡

ይኽ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክም ከዐድዋ ጦርነት
ከተመለሰ በኃላ የኹላቸው ኢትዮጵያውያን ከተማቸው በኾነች ዋና ከተማ አዲስ
አበባ መኻል በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ሕንፃ ክርስቲያን ተከለ፡፡
ስሟንም ገነተ ጽጌ ብሎ ሰየማት፡፡
ንጉሡ ሚኒሊክን ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታና ሀገሩ
ችግር በገጠማት ጊዜ ኹሉ ይረዳው ነበር፡፡

የኃያሉ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎቱና በረከቱ ከኹላችን
ኢትያጵያውን ጋር ይኹን፡፡

ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያንም በነፃነት ይጠብቅልን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ)

https://t.me/Ethiopian_Ortodoks


በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ። እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ። መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይቆጥርልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ። ብዙ ጠባሳ እኮ  ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

4.2k 0 27 4 112

ውድ የኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ  ቤተሰቦች

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ30ሺ በላይ ቤተሰብ በላይ አፍርቷል ፤ ይህ የሆነው በእኛ ጥረት ብቻ ሳይሆን በእናንተም ጭምር ነው ።

መርጣችሁ ስለምትከተሉን ከልብ እናመሰግናለንእዚህ ለመደረስ ያገዛቹን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን !  

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ያላችሁን አስተያየት። በኮመንት ላይ ያስቀምጡልን ።💬

በቀጣይ 40...K




አቤቱ ተወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
ጌታችን ሆይ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡

እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን፤ ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን፤

ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡

🌷ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን
🙏

5.5k 0 41 4 109

ጥፋት እኮ

ሰም ቢፈልግ ኮርቶ በኔ በተጠራ
ነውር እኮ ቤት ቢኖረው ሰውነቴ የሱ ሥፍራ

ኃጢያት እኮ

አባት ቢሻ ደም አምጬ በወለድኩት
ክፋት እኮ መልክ ቢሆን ቁርጥ እሱን በመሰልኩት 

በደል እኮ

ትግል ቢሻ እኔ እኮ ነኝ ጦር ጉልበቱ
ዝሙት እኮ ውበት ቢሆን መልኬ ነበር ምልክቱ

መራቆቴ

ምህረት አቅፎት በቸር ክንድህ ባመለጠ
እንኳን ልትፈርድ በሸሸከው በመረሳት ዋጋ ቀለህ

ደግ እኮ ነህ

ሁሉን ሸፋኝ ምን በገጼ ተገለጠ
እንደገና ለመከዳት ዛሬም በሬን ታንኳኳለህ
🙏

@Ethiopian_Ortodoks


#ጸልየህ_ልታደርገው_ትችላለህ?

ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ  ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!"

በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው?

5.1k 0 50 3 122
Показано 20 последних публикаций.