እውን መረጃ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


📌#ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች የምታገኙበት ቻናል
ጥቆማ ለመስጠት
👉 @ewun_mereja_bot
#እውነተኛ እና #ትኩስ #መረጃዎች
#እውንነት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


የኤሌክትሪክ ዋጋ ጭማሪ ዳግም እንዲከለስ አለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማት እየጠየቁ ነው


ለዉጡን ተከትሎ ከግምት ዉስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ

መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ተረድታለች።

የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ዉስጥ 122 በመቶ ደርሷል።

ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ አለም ባንክና የአለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ አለምአቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሬ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸው ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

#CapitalNews

#እውን_መረጃ


የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸው ዛሬ ይከናወናል

የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት ከ2016 - 2020 የመሩ ሲሆን በ2020 በተደረገው ምርጫ በጆ ባይደን ተሸንፈው ከስልጣን መውረዳቸው ይታወሳል።

ትራምፕ በ2024 በተደረገው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራቷን ዕጩ ካማላ ሀሪስን በሰፊ ድምፅ አሸንፈው፤ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸው ይታወቃል።

በዚህ እጩው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ዛሬ የሚያደርጉ ሲሆን በበዓለ ሲመታቸው የበርካታ ሃገራት መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#እውን_መረጃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አዲስ አበባ‼

አሁን ከመሸ ቂርቆሰ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 10 ከጨርቆስ ወደ ለገሀር መውጫ ላይ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰ ቃጠሎ ነው:: የተቃጠለው ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሲሆን መነሻው ምን እንደሆነ ለጊዜው ማወቅ አልተቻለም።(wasu)

11/05/2017

#እውን_መረጃ


ሃማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን መልቀቅ ጀመረ

እስራኤል እና ሃማስ ያደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ ሃማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን ዜጎች  መልቀቅ ጀምሯል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር  እንዳስታወቀው እገታ ላይ ከነበሩ ዜጎቻቸው መካከል ሶስት ሴቶች ዛሬ ተለቀዋል።

ሶስቱ ሴቶች ሃማስ በፈረንጆች ኦክቶበር 7 2023 እስሬኤል ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ጥቃት አግቶ የወሰዳቸው  ናቸው።

ያለፉትን 471 ቀናት በሃማስ እገታ ስር ቆይተው ዛሬ ነፃ ወጥተዋል።

ከጋዛ ተለቀውም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

ሃማስ እና እስራኤል በደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያው ምዕራፍ ሃማስ ያገታቸውን 35 እስራኤላውያን ይለቃል። እስራኤል ደግሞ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ያሰረቻቸውን 1 ሺህ ፍልስጤማውያን እስረኞች ለመፍታት ተስማምተዋል።

የስምምነቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከዛሬ ጀምሮ ለስድሰት ሳምንታት የሚቆይ ይሆናል።

#እውን_መረጃ


አሞሪም መራሩን እውነት በይፋ ተናገሩ

እየመሩት ያለው ቡድን በማንችስተር ታሪክ እጅግ መጥፎው ቡድን መሆኑን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በይፋ ተናገሩ።

ቡድናቸው ዛሬ በሜዳው በብራይተን 3ለ1 ከተሸነፈ በኋላ በሰጡት አስተያየት እየመሩት እንዳለው አይነት መጥፎ ቡድን ማንችስተር ዩናይትድ በታሪኩ ኖሮት እንደማያውቅ ገልፀዋል።

አሞሪም ቡድናቸውን ሲገልፁ " በማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ እጅግ መጥፎ ቡድን ሆነናል "ብለዋል።

" ይህንንም ልንቀበል ይገባል " በማለት በሽንፈቱ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በቡድናቸው አቋም የተሰማቸውን ስሜት ገልፀዋል።

“We are being the WORST team maybe in the HISTORY of Man United, we have to acknowledge that”.

#እውን_መረጃ


310 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 310 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በተመሳሳይ 99 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢው እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተከናወነ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 89 ሺህ 898 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

#እውን_መረጃ


በአማራ ክልል የከተራና የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር መጠናቀቁ ተገለጸ

በአማራ ክልል የከተራና የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ  በድምቀት መከበሩን   የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የሚዲያ ዋና ከፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር መሳፍንት እሸቴ ፤ በዓሉ ሃይማኖታዊ ዕሴቱን በጠበቀ አግባብ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በድምቀት መከበሩን ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በአሉ  ያለችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከሀይማኖት አባቶች ፣ወጣቶችና ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ቀደም ብሎ በመወያየት ዝግጅት ማድረጉን አስታውሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ ታቦታት  ከማደሪያቸው ወደ መንበራቸው መመለሳቸውን  አስታውቀዋል።

#እውን_መረጃ


የአብኑ ደመወዝ ካሴ ከአራት ወራት እስር በኋላ ዛሬ ከእስር ተለቋል!

#እውን_መረጃ


የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች አልዐይን ከተማ

የጥምቀት በዓል በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአልዐይን ከ በዛሬው ዕለት በድምቀት መከበሩን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

#እውን_መረጃ


📌አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ አረፈ

አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት እንቁስላሴ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ 30 በሚሆኑ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አገኝቷል፡፡

#እውን_መረጃ


የኢትዮጵያ ጂዲፒ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ምክንያት ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ተገለጸ

የአገሪቱ  የውጭ ዕዳ የጂዲፒ ጥመርታ ለደሃ ሃገራት ከተቀመጠው ጣሪያ አልፏል

የኢትዮጵያ ኖሚናል ጂዲፒ (የዋጋ ንረትን ታሳቢ ያላደረገ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት) በዶላር ሲተመን፣ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 207 ቢሊዮን ዶላር በሦስት ወራት ውስጥ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ተገለጸ፡፡

የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት በገንዘብ (በዶላር) ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከተደረገ በኋላ በ2017 ዓ.ም. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱን የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ አስታውቋል።

የአገሪቱ ጂዲፒ በዶላር ሲተመን ያሽቆለቆበት ምክንያትም ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ተግባራዊ በመደረጉ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል።

በዚህና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. የአገሪቱን ጂዲፒ 32.9 በመቶ ይዞ የነበረው አጠቃላይ የመንግሥት የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ (Public Debt) በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም. ወደ 50.3 በመቶ አሻቅቧል።

የመንግሥት (የአገሪቱ) የውጭ ዕዳ መጠን ለብቻው ተነጥሎ ሲታይ፣ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 28.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 31 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ሲሆን፣ ለዚህም ሁለት ምክንያቶች ተጠቅሰዋል።

አንደኛው ምክንያት ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተግባራዊ መደረጉ ሲሆን፣ ሌላው በተጠቀሱት ሦስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት (IMF) እና ዓለም ባንክ በድምሩ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተለቀቀለት መሆኑ ናቸው። 

በዚህ ምክንያት የውጭ ብድር ክምችቱ በ7.5 በመቶ ከመጨመሩ ባለፈ፣ የውጭ ምንዛሪ ለውጡን ተከትሎ የአገሪቱ ጂዲፒ በዶላር ሲተመን፣ በሰኔ ወር ከነበረበት 207 ቢሊዮን ብር በመስከረም ወር 2017 ወደ 100 ቢሊዮን ብር በማሽቆልቆሉ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ዕዳ ከጂዲፒው ጋር ያለው ጥምርታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። 

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. የአገሪቱ የውጭ ዕዳ (የአገር ውስጥ ዕዳን ሳይጨምር) ከጂዲፒው ጋር የነበረው ጥምርታ 13.9 በመቶ ሲሆን፣ በመስከረም 2017 ዓ.ም. ላይ ግን ወደ 30.9 በመቶ ማደጉን ሰነዱ ያመለክታል።

በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከጂዲፒው ያለው ጥምርታ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) እና የዓለም ባንክ ለደሃ አገሮች ካስቀመጡት 30 በመቶ እንዳለፈ ከዚሁ መንግሥታዊ ሰነድ ለመረዳት ተችሏል።

በተመሳሳይ የመንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ ከጂዲፒው ያለው ጥምርታም ለደሃ አገሮች ከተቀመጠው ጣራ ማለፉን ሰነዱ ያመለክታል።

ይሁን እንጂ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከተደረገ በኋላ የመንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ መጠን በዶላር ሲሰላ በከፍተኛ ደረጃ አሽቆልቁሏል።

የመንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 2.29 ትሪሊዮን ብር ወደ 2.3 ትሪሊዮን ብር ያደገ ቢሆንም፣ በዋናነት በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ምክንያት የአገር ውስጥ ዕዳው በዶላር ሲተመን በሰኔ ወር ከነበረበት 39.9 ቢሊዮን ዶላር ወደ 19.8 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን መረጃው ያመለክታል።

#እውን_መረጃ


#Update

ቆሟል‼

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ "ጎቱ ኦኖማ" በተባለው አከባቢ ትላንትናው ዕለት ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ ተነስቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን ወረዳው አስታውቋል።

#እውን_መረጃ


በቁጥጥር ስር ዋሉ❗️

የደቡብ ኮርያ ኘሬዝደንት ዮን ሱክ ዮል ዛሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በኘሬዝደንቱ ላይ ክስ የመሰረተው የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስር ትዕዛዝ በማስተላለፉ ፓሊስ በቁጥጥር እስር አውሏቸው ወደ ማረፊያ ቤት ወስዷቸዋል።

ኘሬዝደንቱ እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት ያዘዘው መረጃዎችን ያጠፋሉ በሚል ምክንያት ነው።

በደቡብ ኮሪያ ታሪክ ኘሬዝደንት ዮን ሱክ ዮል በስልጣን ላይ እያሉ የታሰሩ የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል።

ፓሊስ ኘሬዝደንቱን በይፋ ማሰሩን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው በዋና ከተማዋ ሁከት ቀስቅሰዋል።

ኘሬዝደንቱ በፓለቲካዊ ምክንያት የአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወቃል።

#እውን_መረጃ


እውነተኛው የመካከለኛው ምስራቅ ትርምስ ሊጀመር በቋፍ ላይ ይገኛል !!

የአሜሪካው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ  እስራኤል የኢራንን የኒውክለር ጣቢያ ለማጥቃት የወሰነች ሲሆን የትራምፕ አስተዳደር እና እስራኤል እንዲህ ዓይነቱን ኦፕሬሽን ለመፈጸም እየተነጋገሩ ነው።

#አል_አረቢያ #እውን_መረጃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#ጎንደር

በጎንደር ምዕመናን ወደ ጥምቀተ ባሕሩ መግባት ጀምረዋል

#እውን_መረጃ


ለመላዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

#እውን_መረጃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ቤተሰቦች #ቲክቶክ በአሜሪካ "እንዲህ ነው የተዘጋው" ሲሉ ስክሪን ሪከርድ ልከውልናል

በተጨማሪም ቲክታክ ከፕለይ ስቶር ጠፍቷል አሁን ያላችሁን ቲክታክ app ከጠፋ የማግኘት እድል የላችሁም ።

#እውን_መረጃ


#እሳትአደጋ

በኦሮሚያ ዞን ምዕራቢ አርሲ ሰደድ እሳት ተነሳ

ጥር 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ በአካባቢው ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ሰድድ እሳት ዛሬ ከቀኑ አስር ሰዓት አከባቢ አባሮ ተብሎ የሚጠራው ተራራ ላይ መነሳቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

አሁን ላይ ቮልካኖ ፈንድቴ ነው ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክል አለመሆኑንም አመላክቷል።

ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ማህበረሰብ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ዞኑ በማህበራዊ ድህረ ገፁ አስታውቋል።


Via:መናኸሪያ ሬዲዮ

#እውን_መረጃ


የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት  የቀድሞ  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር  ቲቦር ናጊ  የትራምፕን መምጣት  ተከትሎ  ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መመለሳቸውን   አስታውቀዋል።

ቲቦር ናጊ  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ  መወገድ አለበት በሚል የሚታወቁ ሲሆን  በቅርቡ  የሶሪያው መሪ በሽር አልአሳድን መውደቅ ተከትሎ   ኢሳያስም የአሳድ እጣፈንታ ይጠብቀዋል በማለት በማህበራዊ ሚዲያቸው መለጠፋቸው ይታወሳል። 

የቀድሞ በ ኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር   ቲቦር ናጊ   እንደ ህዳሴው ግድብ በመሳሰሉ   በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ  በተደጋጋሚ  ከኢትዮጵያ  ጎን በመሰለፍ የሚታወቁ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ውዴታም በአደባባይ   የሚገልፁ  ጉምቱ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሲሆኑ  ከወዲሁ ኢሳያስና ግብፅን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ዜና መሆኑ ተዘግቧል ።

#እውን_መረጃ


የአሜሪካው ተመራጭ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሌጋሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በመምራት በበዓለ ስመታቸው እንዲገኙ መጋበዛቸው ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የምታደሙ የአፍሪካ መሪዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአዘጋጆቹ በኩል ይፋ ተደርጓል።

እንደ ደይሊትራስ ዘገባ ግብዣው በጥር 13 ቀን 2025 ለወጣቱ የናይጄሪያ የንግድ ሥራ መሪ ዶ/ር ኡዞቹክ በተላከ ደብዳቤ “ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕን በማክበር የመድብለ ባህላዊ ጥምረት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምረቃ ቦል አስተናጋጅ ኮሚቴን በመወከል እንዲገኙ ስንጋብዝ በታላቅ ክብር ነው ይላል ብሏል።

ይህ ታላቅ ዝግጅት በጥር 20፣ 2025 በዋሽንግተን የሚካሄድ ሲሆን በማዳም ፍራንያ ኢ ካብራል ሩዪዝ መሪነት ከአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት በቀረበው ሀሳብ እንደተገለጸው ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅዖ እና አመራር እውቅና በመስጠት፣ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ በመገኘታችን ታላቅ ክብር እንሰጣለን ብሏል።

በዚሁም የወቅቱን የአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በዩኤስ ፕሬዝዳንታዊ የትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የሚመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሆኑም ዘገባው ጠቅሷል።

WT

#እውን_መረጃ

Показано 20 последних публикаций.