🎄💥እንቁ ᴛᴜʙᴇ™💥🎄


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


🎀..ችግሮችህ በሙሉ ሰው ሰራሾች ናቸው ስለዚህም በሰው ይፈታሉ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ችግሮች ከሰው አቅም በላይ ሊሆኑ አይችሉም••🎀

For any comment & cross👇
@KERODINA
ከቆያችሁ ብዙ ነገር ታገኛላችሁ
If you stay, you will find a lot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: DT Promotion
'https://t.me/addlist/37N4EgSzRtU3YjA0' rel='nofollow'>❓ Fakkicha Hubannoodhaan Ilaali!
☁️              ☁️                       🛰
         ☁️              ☁️      ☁️             ☁️
                                    ☁️
☁️     ☁️ ☀️  
           ☁️             ✈️
☁️              ☁️☁️  ☁️
     ☁️           🚁      📡 ☁️
🏡🏬🏥🏡🏭.    🏨🏣🏦
                     / | \
     _🚂🚃  /   |   \ 🚩___
       👬🚦 /    |     \ 🚦🚶
        🌳   /      |        \  🌳
              /        |          \    🐐         🎡
     🌳  /  🚔   |  🚔     \ ⛽️       🏟
          /            |             \
  🌵 /      🚖   |  🚘          🚴
      /                |       🚔     \
    /         🚍    |                   \
  /                    |                    
» Konkolaataa diimaa fakkicha irra jiru tuqii garam akka deemu ilaali! Itti Gammadda! Irraa baratta! Just «JOIN» Now!


Waver @FastVipProm


Репост из: DT Promotion
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
⏰ከ15 ደቂቃ በዋላ ይጠፋል ⏰

💵የ100 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ?

10+10*0+10=???

✍Comment your answer below👇


ሊጠናቀቅ 23 ቀናት የቀሩትን ZOO ያልጀመራችሁ አሁንም ጊዜ አላችሁ ጀምሩ 👋

✅|| Task ውስጥ የነሱን ቻናል Join በማድረግ ሌሎችም አሉ እነሱን ሰርታችሁ ብዙ ቶክኖችን መሰብሰብ ትችላላችሁ በሱ ነጥብ animal ገዝታችሁ እሱ በየ ሰዓቱ ቶክን ይሰጣቹዋል አሰራሩ ምንም አያለፋም እንዳያልፋችሁ። በተጨማሪም 1 ሰው ስትጋብዙ 10,000 animal feed እየሰጡ ነው አሁን ላይ በዚህ animal feed token per hour በደምብ ማሳደግ ነው እሱ በየ ሰዓቱ የነሱን token ይቆጥርላቹዋል።

✅|| እዛው ላይ የሰበሰባችሁትን ቶክን ነው ወደ ዋሌታችሁ የምትቀበሉት ብለዋል Convert አይደረግም real token እየሰበሰብን ስለሆነ።

ቀሪ 23 ቀናት ብቻ አሉ ሊጠናቀቅ 🔥

ለመጀመር 👉 http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref923788743


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣2️⃣

ቦታውጋ ስንደርስ ከመኪናው እንድወርድ ጋበዘኝና ወረድኩ:
የባለፈው እራሱ ቦታ ላይ ሄደን ተቀመጥን አቀማመጣችን ግን የዛሬው ዝም ብሎ ፊት ለፊት ነበር::
ልዑሌ እንዲህ ግን ስትሆኚ ታስጠያለሽ እሺ አያምርብሽም አለኝ ለማሳቅ መሞከሩ ነው ግን አልተሳካም
የበለጠ ልቤ እየመታ ነው ልቤ የሆነ በቃ ወጥታ ልትበር ያህል እያስጨነቀችኝ ነበር  አይን አይኔን እያየ እእ ንገሪኛ አለኝ።
ለመስማት እንደጓጓ ግልፅ ነው በሱ ቤት ጥሩ ዜና የምነግረው መስሎታል በመጀመሪያ የሆነ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ በጣም እድለኛና ልዩ ሰው እንደሆንክ እንድታውቅ እፈልጋለሁ።

ፈጣሪ እንዳንተ ሁሉን ነገር አሟልቶ የሰጠው ሰው የለም .......አቋረጠኝ ተሳስተሻል ፈጣሪ አንድ በጣም የምፈልገውን ነገር ነጥቆኛል እሱን የሆነ ቀን ታቂው ይሆናል አለኝ::

ምንድነው ንገረኝ ድጋሜ ላንገናኝ እንችላለን ስለው በጣም ደነገጠ ማለት አለኝ ከመቀመጫው እየተስተካከለ መጀመሪያ አንተ ንገረኝ አልኩት የኔንማ ታቂዋለሽ ያው ፍቅር ነዋ እናትና አባቴ ሞተዋል 2 ወንድሞች አሉኝ::

እነሱም ስለገንዘብ እንጂ ሌላ ነገር ግድ አይሰጣቸውም::
በጣም ብቸኝነት ይሰማኛል  ከስራ ውዬ ስገባ ከገንዘቤና ከመኪናዬጋ አላወራም  በዛን ሰአት እቤት ቁጭ ብላ ውሎዬ እንዴት እንደነበር ምን እንዳስደሰተኝ : ምን እንዳስከፋኝ ምትጠይቀኝ እናት ብትኖረኝ ግን ደስ ይለኝ ነበር።

ሲለኝ በጣም አሳዘነኝ የሚከፈለውን መስዋትነት ከፍዬ አብሬው ብቆይ ደስ ይለኝ ነበር ግን ከአቅሜ በላይ ነው።

ገና ላወራ ስጀምር እንባዬ ቀደመኝ ልዑሌ ደንግጦ  ወደ እራሱ አስጠግቶ እቅፍ አደረገኝና ከኪሱ ሶፍት አውጥቶ እንባዬን እየጠረገ ምን ሆነሽ ነው ሰላሚና ንገሪኝ  እንጂ በፈጣሪ ስም በጣም እያስጨነቅሽኝ ነው ።
እንዴ ምንድነው እንዲህ መሆን  አለኝ።

እኔም ታሪኩን እንዲህ ብዬ ጀመርኩለት ከማክቤልጋ ከመለያየታችን በፊት አብረን አድረን ነበር ባሌ የሚሆን መስሎኝ ነበር የሚያፈቅረኝ መስሎኝ ነበር እሱ ግን አንድ በቂ ምክንያት እንኳን ሳይሰጠኝ እንደቆሻሻ አውጥቶ ጣለኝ::

      እና እሱን አሁን ምናመጣው ሰላም?? አለኝ ::

እንዳታቋርጠኝ አስጨርሰኝ አልኩት እየተቆጣሁ ::
አሺ በቃ አላቋርጥሽም ቀጥይ ብሎ ዝም አለ ::
ምን  እንደተፈጠረ ሳላውቅ አልፈልግሽም አለኝ ።
ማለቴ አንተን የተዋወኩ ሰሞን ከዛም አንተጋ ደውዬ ላግኝህ አልኩህ አገኘሁህ አወራን ተግባባን በህይወቴ ውስጥ አንተ ስትመጣ ሁሉም ነገር ያበቃ መስሎኝ ነበር ድጋሜ ስለ ማክቤል ላለመሳብ ወስኜ ነበር ከውስጤ አውጥቼ እንደቆሻሻ ጥዬው ነበር ።
በሱ ቦታ አንተን ተክቼ በውስጤ አንግሼህ ነበር የምር ልዑሌ ወድጄህም አፍቅሬህም ነበር። በዚህ አጭር ጊዜ እንዴት እሱን እረስቸሽ እኔን አፈቀርሽኝ ልትለኝ ትችላለህi ግን እኔጃ አላቅም እኔ ላንተ እመጥንሀለሁ ብዬ አደለም ግን በቃ እንዲሁ የምትለይ ሰው ነህ::
ግን በቃ ፈጣሪ ለሰራሁት ሀጥያት ሊቀጣኝ ፈልጎ ነው መሰለኝ ይሄን ዱብዳ አወረደብኝ።
እኮ ዱብዳው ምንድነው ንገሪኛ ?? አለ

እሺ እኔ ባለፈው ሆዴን በጣም እያመመኝ ሲያስቸግረኝ ወደ hospital ሄድኩ ከዛ ምርመራ ሳደርግ  እርጉዝ መሆኔን ነገሩኝ አቃለሁ በጣም ያሳፍራል ሳላገኝህ ዝም ብዬ ለሰጠፋ ነበር ግን ልቤ እንቢ ብሎኝ ነው (እንባዬ ይፈሳል)

ልዑሌ የጠበኩትን ያህል አልደነገጠም 

 እናም ላስወርድ ስሄድ   ማስወረድ አትችይም አሉኝ በቃ ልዑሌ ምን አይነት የማረባ ሰው እንደሆንኩ የገባኝ አሁን ነው ከዚህ ቡሀላ ድጋሜ ላታየኝ ትችላለህ::.
ከሰው በታች ሆና ያሳደገችኝን እናቴን ማሳፈር አልፈልግም ።በሰፈሩ ሰው መጠቋቆሚያ አላደርጋትም ይሄን ከማደርግ ሞቴን እመርጣለሁ ...........እኔ እያወራሁ ልዑሌ ቃል ሳይናገር ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ መኪናው አመራ ::
ደንግጬ እኔም ቆምኩ ዞር ብሎ እንኳን ሳያየኝ መኪናውን አስነስቶ እዛው ጥሎኝ ሄደ ...

🔻ክፍል አስራ ሶስት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌       ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣1️⃣

በቃ እኔ ማቀው ቤት አለ እዛ ሄደ ምሳ እንብላ ።
ስንጨርስ ባለፈው የሄድንበት ቦታ እንሄዳለን አለ ።
የትኛው ቦታ አልኩት ባለፈው የምጠይቅህ ጥያቄ አለ ብለሽኝ የሄድንበት ቦታ አለኝ እሺ በቃ እንሂድ ተስማምቻለሁ ብዬው ወደ ትካዚዬ ገባሁ ከሀሳቤ ያነቃኝ የልዑል ድምፅ ነበር በቃ ደርሰናል ውረጂ መኪናዬን አቁሜ መጣሁ አለኝ ።
እኔም ወርጄ ቆምኩ መኪናውን አቁሞ መጣ ወደ ውስጥ ገብተን ተቀመጥን ምግብ አዘዝን እኔ ግን ምግቡ ምንም ሊበላልኝ አልቻለም እሱ እንዳይደብረው ብዬ ነው ያዘዝኩት እሱ ሲበላ አይን አይኑን አየዋለሁ ቀና ሲል አጎነብሳለሁ ሁኔታዬ ለሱም ግራ እንዳጋባው ከፊቱ ላይ ያስታውቃል አስሬ ብይ እንጂ ብይ እንጂ ይለኛል አይ በቃኝ ምሳ በልቼ ስጨርስ ነው የደወልከው አሁንም አንተ እንዳይደብርህ ነው ያዘዝኩት እንጂ ልበላ አይደለም አልኩት አረ የሆነ ነገርማ ሆነሻል በቃ እኔም በቃኝ አስደበርሽኝኮ አለኝ ።

እሺ በቃ እንውጣ ግን የኔን ምግብኮ አልነካሁትም ለምን ቴካዌ አስደርገን ጎዳና ላይ ለተኛ አንድ ሰው አንሰጠውም ችግር የለውማ ስለው አረ የምን ችግር ሌላም አስጨምረን እናስደርግና ስናልፍ ላገኘነው ጎዳና ተዳዳሪ እንሰጠዋለን ብሎ አስተናጋጇን ጠራና ነገራት ትንሽ ቆይታ አስተናጋጇ በጥቁር ፌስታል ይዛ መጥታ ሰጠችው ሂሳቡን ከፍሎ ወጣን።

እየሄድን እያለ ተደርድረው የተቀመጡ ጎዳና ተዳዳሪዎች አይተን መኪናውን አቁሞ ወረድን።
ምግቡን የያዝኩት እኔ ነበርኩ ከተቀመጡት ውስጥ አንድ ህፃን ልጅ ጠራሁና ምግቡን ሰጠሁት ኪሴ የነበረውን 50 ብርም ጨምሬ ሰጠሁት።

ልጁ በጣም ነበር ደስ ያለው ልክ ሎተሪ እንደደረሰው ነገር እየሮጠ ተሰብስበው ወደ ተቀመጡት ሰዎች ሄደ ፌስታሉ ውስጥ ምግብ እንዳለ እርግጠኞች ነበሩ መሰለኝ ገና ልጁ ወደነሱ ሲመጣ ነበር እጃቸውን የሰበሰቡት በቃ ሁሉም እየተሳሳቁ እየተሻሙ መብላት ጀመሩ ልዑሌ ምስጥ ብሎ እያያቸው ነበር

ሳየው አረ ሰውዬ ነቃ በል ወይ ሂድና ተቀላቀላቸው ብዬ ወደ መኪናው ገባሁ እሱም ተከትሎኝ ገባና መንዳት ጀመረ።

ታቃለህ ልጁ ግን በጣም ነው ያሳዘነኝ ይሄኔ የሱ እኩዮች ትምህርት ቤት ገብተው እየተማሩ  ነው ያሻቸውን ለብሰው ያሻቸውን በልተው እሱ ግን ገና በጨቅላ እድሜው የሰው ፊት ይገርፈዋል
የሰው እጅ ይጠብቃል። አንዳንዶች በሱ እድሜ ምን አነሳችሁ ምን ጎደላችሁ አፈር እንዳይነካችሁ ተብለው ያድጋሉ አንዳንዶች ደሞ እንደሱ ገና በልጅነታቸው የችግር ጅራፍ ይገርፋቸዋል
አሁን ይሄ ልጅ ምንን ተስፋ አድርጎ ነው የሚኖረው አልኩት።
እንባዬ እየተናነቀኝ ልዑሌ ፈጠን ብሎ ነገን  ተስፋ አድርጎ ነው የሚኖረው
እሱ ፈጣሪ ያደለው ጤና አለው ሰው በተለያየ በሽታ  ነገ እንደሚሞት እያወቀ ይኖር የለ እንዴ።
የልጁን ህይወት ደሞ ብሩህ ማድረግ የምንችለው እኛ ነን ለምሳሌ አንቺ ለምን ብር ሰጠሽው ለሱ ብር መስጠት ማለት ልጁ የበለጠ እየጎዳሽው ነው ይሄ ልጅ በእርግጠኝነት የሆነ ሱስ አለበት እሱ እንኳን ባይኖርበት ጓደኞቹ ይኖርባቸዋል ስለዚህ ይሄን ብር ለሱሳቸው ማስታገሻ አዋሉት ማለት ነው።
ነገም መቶ ሌላው ሰው ብር ሲሰጣቸው እሱንም ለሱስ ያውሉታል ስለዚህ ሱሳቸውን እያስፋፉ ይሄዳሉ ማለት ነው።

ይሄን ብር ከምሰጫቸው ይልቅ የ5 ብር ዳቦ ገስተሽ ብሰጫቸው ግን ከርሀብ ነው ምታስታግሻቸው ገባሽ አለኝ ።
ወደኔ እያየ ሲያወራ በጣም ስሜታዊ ሆኖ ነበር ንግግሩ ደሞ ምንም ሀሰት የለውም እስከዛሬ ግን አስተውዬው አላቅም ነበር።

ለጎዳና ተዳዳሪዎች ብር ስሰጣቸው ትልቅ ውለታ የዋልኩላቸው ይመስለኝ ነበር ለካ እየጎዳኋቸው ነበር ስለው አይ ከዚህ ቡሀላም ካወቅሽ አንድ ነገር ነው በይ እየደረስን ነው ወሬውን ለመናገር ተዘጋጂ አለኝ እኔ ግን በውስጤ አልንገረው እንዴ! ቢያንስ ለትንሽ ቀን አብሬው ልቆይ እንዴ? እላለሁ አንዱ ልቤ ደሞ ወደፊት ነገሩ እየከፋ እንደሚሄድና ካሁኑ ንገሪውና  ወደ አንዱ ቤተክርስቲያን ትጠፊያለሽ ይለኛል ብዙ አሰብኩበት ግን ለልዑሌ መናገር ግድ ሆኖ አገኘሁት በቃ ሁሉንም ነግሬው ካሁን ቡሀላ ባላገኘው ይሻለኛል.......


🔻ክፍል አስራ ሁለት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማዕበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰1️⃣0️⃣

ከሆስፒታል ወጣሁ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ምን እንደማስብ አላውቅም ።

ብቻ መንገድ ላይ ግራ ተጋብቼ ስጓዝ ልዑሌ ደወለ ገና ስልኬ ላይ ስልኩ ሲጠራ እደነግጣለሁ ድምፁን ስሰማ የውስጤ ጭንቀት ሁላ ነው ሚጠፋው: ስልኩን ሳየው ፈገግ እንዳልኩ እንኳን ሳይታወቀኝ ፈገግ እላለሁ  :

ስልኩን  አንስቼ ሄሎ አልኩት እንዴት ነሽ የኔ ቀውስ ምነው ጠፋሽ ለመናፈቅ ባልሆነ አለኝ እየሳቀ ::
ወይ መናፈቅ እያልኩ በውስጤ ለመረሳት ነው እንጂ አልኩት አይ አንቺማ እንዴት ትረሻለሽ እሺ ዛሬስ አንገናኝም እንዴ ? ሲለኝ በጣም ነው የደነገጥኩት ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ እሱን ማየት አልችልም እንዴት ብዬ ነው አይኑን የማየው በሌላ በኩል ደግሞ ቢያንስ አይኑን ባየው ሰላም እንደሚሰማኝም አቃለሁ እሺ በቃ ከፈለክ አሁን ከፈለክ ማታ ካፌ ሳልጨርሰው አይ አሁን ይሻላል እስካሁን ምሳ አልበላሁም  እሺ የት እንገናኝ አለኝ ::
አንተ ደስ ያለህ ቦታ በቃ ሰፈር ጠብቂኝ እና መጥቼ እወስድሻለሁ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው::
የተለመደችው ቦታዬጋ ሄጄ ቁጭ አልኩኝ መጮህ ማልቀስ ተመኘሁ ግን አቅም አነሰኝ ።።
እናቴ እኔን በድህነት አሳደገችኝ እኔ ደሞ ልጄን በድህነት ላሳድገው ነው ?እንደዛ የለፋችልኝ እናቴ ለስራዋ ምከፍላት ይሄንን ነው 😢 እዛ ትንሽ  ከተቀመጥኩ ማበዴ ስለማይቀር ተነስቼ  እስከ አስፋልቱ በእግሬ መራመድ ጀመርኩ።

ትንሽ እንደተራመድኩ ማክቤል ከሆነች ልጅጋ ተቃቅፈው እየተሟዘዙ ከፊት ለፊቴ መጡ ሳየው ደሜ ነው የፈላው ሄጄ ባንቀው ደስ ይለኝ ነበር ።
ልጅቷ የባለፈዋ ልጅ መስላኝ ነበር ግን አይደለችም ሌላ ናት ልክ ሲያየኝ  አንዴ ይስማታል አንዴ ያቅፋታል ብቻ የሚያደርጋትን ነበር ያሳጣው እኔ አንገቴን ደፍቼ ወደፊቴ መራመዱን ተያያዝኩት
አነሱም እኔን እየተከተሉ በሚመስል መልኩ ፍጥነታቸውን ጨምረው ተራመዱ  አጠገቤ ሲደርስ ሰላም ነው ሰላሚና አለኝ እያገጠጠና እያፌዘ መልስ ሳልሰጠው ወደፊቴ ሄድኩ።
ትንሽ እንደተራመድኩ ልዑሌ ደውሎ እንደደረሰና እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ  ቶሎ ቶሎ ወደፊት መራመድ ጀመርኩ ልክ አስፋልቱጋ ስደርስ ልዑሌ መኪናውን አቁሞ ከመኪናው ወርዶ እየጠበቀኝ ነበር ሲያየኝ ፈገግ አለና ወደኔ መቶ አቀፈኝ ሲያቅፈኝ የሚነዝረኝ ነገር ነው ማይገባኝ ኤሌትሪክ ይዞ የሚዞር ይመስል።

እውነት ለመናገር ስላየሁት በጣም ነው ደስ ያለኝ ግን ፊቴ አሁንም እንደተዘፈዘፈ ነው እጄን ይዞኝ ወደ መኪናው ሊያስገባኝ እያለ    የድሮ ፍቅረኛሽን ቦዲይ ጋርድነት ቀጠርሽው እንዴ አለኝ እየሳቀ
ማለት አልኩት ግራ ገብቶኝ እና ለምንድነው ከኋላ ከኋላሽ የሚከተልሽ አለኝ ዞር ስል አቶ ማክቤል 2 እጁን ኪሱ ከቶ ከኋላዬ እየተከተለኝ ነበር እንዴ ጉድ ፈላ ልጅቷን ምን ውስጥ ከተታት አሁን አብራው አልነበረች እንዴ ለራሴም ጥያቄ ፈጠረብኝ ቢሆንም  ከልቤ ነበር የሳኩት ልዑሌ የመኪናውን በር ከፍቶልኝ በክብር ካስገባኝ ቡሀላ ወደ መኪናው ገባ።

ማክቤል ቆሞ እያየኝ ነበር በውስጤ እሰይ ቅጥል በል እያልኩኝ እየሳኩ ሳየው ነበር መኪናው መቀሳቀስ ሲጀምር ማክቤልም ተንቀሳቀሰ የትን የምንሄደው አልኩትን  ልዑሌን በቀዘቀዘ ድምፅ የት መሄድ ትፈልጊያለሽ ደስ ያለሺን ቦታ ምረጪ አለ አይ አንተ ደስ ያለህ ቦታ ከቻልክ ብቻችንን የምንሆንበት ቦታ ቢሆን ደስ ይለኛል ምሳ ከበላን ቡሀላ የምነግርህ ነገር አለኝ አስቸኳይ ነው አልኩት ።
እና ለምንድነው ድምፅሽ የቀዘቀዘው ዛሬ የደበረሽ ነገር አለ እንዴ ነገሩስ አስቸኳይ ነው እንዴ በጥያቄ ሲያጣድፈኝ እሱን ስነግርህ ታቀዋለህ መጀመሪያ ምሳውን እንብላ መቼስ በጣም እርቦሀላ ......

🔻ክፍል አስራ አንድ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌
‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰9️⃣

ምን ማለት ነው ድንገት ተነስቶ ተለያይተናል ማለት እ እኔ ስለሰርጋችሁ ቀን መርዘምና ማጠር ነበር ሳስብ የነበረው እቃቃ ጨዋታ ነበር እንዴ የያዛችሁት እእ ለምንድነው የተለያያችሁት ንገሪኝ????
እማ ደሞ አሁን ስለሱ ማውራት አልፈልግም ስለ አዲሱ ልጅ መስማት ከፈለግሽ ልንገርሽ ካልፈለግሽ ደሞ በቃ ልተኛ አንቺም ሂጂና እረፍት አድርጊ አልኳት ፊቴን እያዞርኩባት 😒😒
አይ ልጄ በቃ ስለማክቤል አልጠይቅሽም ንገሪኝ ስለ አዲሱ ልጅ ።
ለምድነው እንዲህ ምታለቅሽው ለምን ከፋሽ ፍቅር ሲይዝሽ የመጀመሪያሽ አደለምኮ የማክበል ጊዜኮ እንዲህ አልሆንሽም ልጄ አሁን ምን ተፈጥሮ ነው ንገሪኝ ግልፁን ።

እሱማ አዎ እማዬ የማክቤል ጊዜኮ መጀመሪያ የፍቅር ጥያቄ ስላቀረበልኝ የኔ እንደሚሆን አውቄ ነበር ይሄ ግን ስሜቱ ምን እንደሆነ አይገባኝም አንዳንዴ አውቆ የራቀኝ ይመስለኛል በእርግጥ ገና ከተዋወቅን 3 ወር ምናምን ነው ግን በጣም ነው የምወደው አንዳንዴ በጣም ሀብታም ስለሆነ እኔ እንደሱ ሀብታም ስላልሆንኩ እየናቀኝ ይመስለኛል ።
አይኑ ውስጥ የፍቅር ስሜት አያለሁ: ሲያየኝ ደስ እንደሚለው አቃለሁ :
ግን እሱ ምንም እናዳልመሰለው ያስመስላል በቃ ግን ሳስበው አይወደኝም አልኳት እያለቀሰኩ ውስጤ ያለው ስሜትና ከህክምና ማስረጃውጋ ተደማምሮ  እንባዬ ሲፈስ ወደር የለውም ነበር ;::
ቀና ብዬ እናቴን ሳያት ፍጥጥ ብላ እያየችኝ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ስጭኝ አለችኝ እስተያየቷ ያስፈራል::
በጉጉት እየጠበኩ የናቴን አይን አይኗን ሳያት ኮስተር ብላ እውነት ልጁን ሀብቱን መልኩን አይተሽ አይደለም ያፈቀርሽው አለችኝ ::
አረ ማሚ ሙች በሱ አይደለም እኔ ስለሱ ሀብትና ንብረት ምናገባኝ ብለሽ ነው ወደፊት ድንገት ባሌ ቢሆን ከሱና ከፀባዩጋ እንጂ ከገንዘቡጋ አልኖር ማሚ ሁሌ ሲገባ  ሲወጣ ጨቅጫቃ ከሆነ ለኔ የሚገባኝን ፍቅር ካለገሰኝ የሱ ገንዘብ ለኔ ምን ያደርግልኛ እማ እኔ ደሀም ሆነ ሀብታም የማገባው ባል ከቤት ወቶ እስኪመጣ እንዲናፍቀኝ እፈልጋለሁ ።
ሁሌ ደስታ ሳቅ ጨዋታ የነገሰበት ቤተሰብ እንጂ በሀብት የታጠረ ፍቅር የሌሌለው ሰው አልፈልግም  አልኳት ።
ንግግሬ ከልቤ ነበረ ማሚም ደስ ብሏት በቃ ታገሺው ልጁ ያንቺ ነው።
ቢዘገይም አይቀርም ብላ በተስፋ ሞልታኝ መች እንደማስተዋውቃት ጠየቀችኝ እኔም አንድ ቀን ነበረ ምላሼ።

እሺ በቃ እረፊ ብላኝ ከክፍሌ ወጣች እሷ እንደወጣችልኝ የክፍሌን በር ከውስጥ ቆልፌ አልጋ ላይ ተዘረርኩና  ያለችኝን ማሰብ ጀመርኩ ምናለ እውነት በሆነ ብዬ ተመኘሁ።
ግን ደሞ ልዑሌ የኔ እንደማይሆን ከመቼው በላይ አረጋግጫለሁ አረ እንደውም ድጋሜ ሁላ አጠገቡ ላልደርስ ወስኛለሁ እኔ ያን ያህል ጨካኝ መሆን አልፈልግም በተለይ ደግሞ ልዑሌ ላይ ሁሉንም ነገር ልንገረው ወይስ ዝም ብዬ ስልኬን አጠፋፍቼ ልጥፋ አላቅም ብቻ በጣም ግራ ገብቶኛል ምን እንደማረግ ጨቆኛል በዚህ ሰአት ሚስጥሬን የማማክረው ጓደኛ ቢኖረኝ ደስ ይለኝ ነበር ግን መናገር በራሱ ያሳፍራል ውርደት መስሎ ታየኝ በቃ ምሽቱን ሙሉ ሳስብ ሳለቅስ አመሸሁ በዛው እንቅልፍ ጣለኝ ጠዋት ስነሳ ከጠዋቱ 4 ሰአት ሆኗል ።
እናቴ የማታውን ነገር ስላየች ሳትቀሰቅሰኝ ነው ወደስራ የሄደችው ።

ተነስቼ ተጣጥቤ ለባብሼ ቀጥታ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ ለማስወረድ ፈልጌ ነበር ያው የገመትኩት አልቀረም ማስወረጃ ጊዜው አልፏል (አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ ሳንፈልግ ጭካኔን ሀጥያትን አስተምረውን የሚያልፉ ብዙ ሰዎች አሉ)

በቃ ምን እንደማደርግ ነው የጨነቀኝ ለማንም ሳልናገር ብን ብዬ ልጥፋ እንዴ እላለሁ


🔻ክፍል አስር ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰8️⃣

ብቻዬን ቁጭ ብዬ ማብሰልሰል ጀመርኩ ::
   ማክቤል   ከኔ የበለጠች ቆንጆ ስለያዘ የሆነች ቅናት ብጤ ተሰምታኛለች እኔምኮ ከሱ የበለጠውን ይዣለሁ ብዬ እራሴን ላፅናና ሞከርኩ ግን ልዑሌ የኔ  እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም ።።


ትንሽ ቆየሁና ተነስቼ ወደሆስፒታል ሄድኩ ይቅርታ ተራዬ አልፎኛል መሰለኝ ውጤቱ አንቺጋ ስለሆነ ብትነግሪኝ አልኳት ውጤት ለመናገር ስትጣራ የነበረችዋን ዶክተር
ኦኦ አንቺ ነሽ ስምሽ ሲጠራ የጠፋሽው
ነው ግቢ አለችኝ ።
ገባሁ ቁጭ አልኩኝ
መጀመሪያ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀችኝ ከማንጋ ነው ምትኖሪው ስራ አለሽ ፍቅረኛ አለሽ ወይ የኑሮ ሁኔታሽ እንዴት ነው ብቻ ብዙ ከጠየቀችኝ ከመለስኩላት ቡሀላ ወጤቱን ነገረችኝ .....

የምርመራ ውጤቴን ሳየው እዛው ነበር እራሴን የሳትኩ ስነቃ ዶክተሮቹ ከበው ደህና ነሽ ደህና ነሽ ይሉኛል መልሴን እራሴን ከፍ ዝቅ በማድረግ መልሼላቸው ካላጋ ላይ ወረድኩ እንባዬ ዝም ብሎ ይፈሳል አንዷ ዶክተር ሶፍት ሰታኝ እንድረጋጋ ነገረችኝ መረጋጋት ግን አቃተኝ:: ደና እንደሆንኩኝ ነግሪያቸው
ዝም ብዬ ወደቤቴ ሄድኩ እቤት ታናሽ እህቴ ብቻ ነው ያለችው ስታየኝ ደንግጣ  እሮጣ  መታ አቀፈችኝ ዝም እንድትል  አስጠንቅቂያት ወደ ክፍሌ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ::

ክፍሌ ተጠቅልዬ ሳስብ ሳለቅስ ስገላበጥ አመሻሽ ደረሶ እናቴ ወደ ቤት መጣች እቤት ስትገባ ከሳሎን ስታጣኝ ወደ ክፍሌ መጣች ብታንኳኳ ብታንኳኳ ዝምታ ነበር መልሴ የበሩ ድብደባና ድምጿ በጣም ሲረብሸኝ ተነስቼ ከፈትኩላት ስታየኝ ደነገጠች ምነው ልጄ ምን ሆንሽብኝ እያለች ፊቴን ስታሳሸኝ እንባዬን መቋቋም አቃተኝ ፊቴን አዙሬ ወደ አልጋዬ ሄድኩ ተከትላኝ ገባችና  አልጋዬ ላይ አረፍ ካለች ቡሀላ ወደሷ ጎትታ  ጉልበቷ ላይ አስተኛችኝ በይ አሁን በርጋታ የሆንሽውን ሁሉ ንገሪኝ አለች ከናቴ ምንም ነገር አልደብቃትም ከልጅነቴ ጀምሮ እንደ ልብ ሚስጥረኛ ጓደኛ ሆና ነው ያሳደገችኝ ሌላው ቀርቶ ትምህርት ቤት እንኳን የፍቅር ደብዳቤ ሲሰጠኝ ከናቴጋ ነበር ከፍቼ ማነበው የሚጠቅመኚንና ማይጠቅመኝን ከሷ የተሻለ የሚያውቅ ሰው አለ ብዬ ስለማላስብ ነው ምንም ነገር ማልደብቃት አሁንም ሁሉንም አፍረጥርጬ ልነግራት ነበር ግን እንደማልችል ገባኝ እናቴ ይሄን ብትሰማ ምን ያህል እንደምታፍር ሳስበው ሰቀጠጠኝ እናቴ በቀላሉ እንደማትፋታኝ ስለገባኝ የሆነ ታሪክ ፈጥሬ ልነግራት እያሰብኩ እያለ ድንገት ልኡል አይምሮዬ ውስጥ ብልጭ አለ ።
እእእ ....ንገሪኛ..
ልጄ አለች በለሆሳስ ድምፅ ጠየቀችኝ ምን መሰለሽ ማም ፍቅር ያዘኝ አልኳት እየተቅለሰለስኩ ::
አላመነቺኝም 💀ፍቅር ስለያዘሽማ እንዲህ አትሆኚም ።ደሞስ ዛሬ ነው እንዴ ፍቅር የያዘሽ እእእ ይሄን ያህል ጊዜ ከማክቤልጋ ስትቆይ ፍቅር እንደያዘሽ ነበር ማቀው እኔ እናትሽ ስታይኝ ህፃን ልጅ ነው እንዴ ምመስልሽ በይ አሁኑኑ እውነቱን ተናገሪ ብትዋሽኝ አውቅብሻለሁ እሺ አፋጠጠችኝ።
  እኔም ድርቅ ብዬ እማዬ ከማክቤልጋ ተለያይተናል ከሌላ ሰው ነው ፍቅር የያዘኝ ....
     ይቀጥላል

🔻ክፍል ዘጠኝ ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰7️⃣

ምክንያቱም እኔ የብር ችግር የለብኝም ይሄንን ጥያቄ ለ1 የኔ ቢጢ ብታቀርቢለት መልሱ ገንዘቡን ይልሻል እኔን ስጠይቂኝ ደሞ ሰውዬውን አልኩሽ ሰው የሌለውን ነገር ነው የሚመኘው እኔ ገንዘብ አለኝ ፍቅር ግን የለኝም ባሁን ሰአት ከገንዘቡ ይልቅ አንድ የልቤን ማማክረው እውነተኛ ሰው ባገኝ ነው ምመርጠው እኔ ሚስት ማግባት ብፈልግ ገንዘቧን አይቼ አይደለም
ማገባት ለምን መሰለሽ በቤት ላይ ቤት በመኪና ላይ መኪና በገንዘብ ላይ ገንዘብ እንጂ ፍቅርን አትሰጠኝም አንዲት ሴትን ሳፈቅራታ ክፍተቴን እንድትሞላልኝ እፈልጋለሁ የኔ ክፍተት ገንዘብ አይደለም የኔ ክፍተት እውነተኛ ፍቅር ነው ገንዘብ ሳላጣ ጤነኛ ሆኖ በሚኖረው ሰው እቀናለሁ :ሁሌ እየሳቀ በሚኖረው እቀናለሁ :የልቡን ሁሉ ዝርግፍ እያደረገ ለልብ ጓደኛው ሲያማክር ሳይ እቀናለሁ: ምክንያቱም አሁን የጠቀስኩልሽ ነገሮች ሁሉ የለኝም እነዚህ ነገሮች ያሏቸው ሰዎች ግን ለነሱ እንደተራ ነገር ናቸው እነሱ በእጃቸው የሌለውን እሩቅ አሻግረው ሲያዩ የተሰጣቸው ነገር ሳያመሰግኑበት  ሳይጠቀሙበት ያልፍበታል ተመለሰልሽ ብሎ ጉንጬን ነካ ነካ እስኪያደርገኝ ድረስ አፌን ከፍቼ ነበር ምሰማው
አንዳንድ ጥያቅዎችን ተፈጥረውብኛል ግን ዝም አልኩኝ ።
ልኡሌ አነጋገሩ ውስጤ ነበር የገባው እውነት ፈልጎ ያጣውን ክፍተቱን እኔ  ብሞላለት ብዬ ተመኘሁ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ እሱን ለማስደሰት ለራሴ ቃል ገባሁ  ።
ሳየው ሁሉ ነገሩ ነው የሚያሳሳኝ ከንፈሩ አይኑ ብቻ አላቅም ወደሱ የሚጎትተኝ ብዙ ነገር አለ በጭራሽ መቋቋም የማልችለው ።

አንዳንዴ በጣም ያመኛል ምግብ እራሱ አይረጋልኝም በልቼው ወዲያው ይወጣል ያጥወለውለኛል ብቻ ሀኪም ቤት ለመሄድ እነሳና ምን እንዳስቀረኝ ሳላቅ እቀራለሁ። ዛሬ ግን በጣም ሲብስብኝ ሄድኩ ምርመራ አድርጌ ጨርሼ ልወጣ ስል  ማክቤል ደወለ ግራ እየተጋባሁ አነሳሁት ሄሎ የኔ ውድ አለኝ አቤት አልኩ በመኮሳተር ድምፅ🎈😡😡 ፈልጌሽ ነበር ከቻልሽ አስቸኳይ ነው እባክሽ አለ። እኔም ምን ሊለኝ ነው ብዬ እያሰብኩ  እዛው ከግሮሰሪያችሁ   ፊት ለፊት ያለው ሆስፒታል ነኝ አልኩት ትንሽ እንኳን አልደነገጠም አስቸኳይ ነው ትመለሻለሸ ቶሎ ነይ አለኝ  እኔም ውጤት ለመስማት ተራዬን እየጠበኩ ስለነበር ዝም ብዬ ወጥቼ ሄድኩ ።
ውጤቱን እስክሰማም ጨንቆኛል ግን ለምን ወጥቼ እንደሄድኩ እንጃልኝ።
ልክ  አስፋልቱን ተሻግሬ  በር ላይ ስደርስ ማክቤል በር ላይ ቆሞ በፈገግታ ተቀበለኝ የኔ ፊት ግን ጭራሽ አልተፈታም።
አቤት ምንድነው አልኩት ከፊት ለፊቱ ቆሜ: አትኮሳተሪ እንጂ ጉዳዩን ደግሞ ግቢና እነግርሻለሁ በናትሽ አልገባም እንዳትይኝ ብቻ መቼም እዚህጋ ቆመን እናውራ አትይኝማ አለ የመማፀን ፊት እያሳየኝ እሺ ብዬ አልፌው ገባሁ ከፊቴ ቀደመና የሆነ ወንበር ስቦልኝ ተቀመጥኩ ምን ልታዘዝ አለችኝ አስተናጋጇ ነበረች አይ ምንም አልፈልግም በቃኝ ስል.. ማኪያቶ አምጭላት አለ ማክቤል ::
እሺ ምን ፈልገህ ነው ንገረኝ አሁን እቸኩላለሁ አልኩት።
ተረጋጊ እንጂ እስቲ የሆነ ነገር ቅመሺ አለኝ እየሳቀ ነበር
ወዲያው አስተናጋጇ ማኪያቶውን ይዛ መጣች እንደዛ የምወደው ማኪያቶ ገና ሲሸተኝ አቅለሸለሸኝ ፉት ለማለት ወደ አፌ  እንኳን ማስጠጋት አቃተኝ አጎንብሼ ልውጣ አልውጣ እያለ የሚታገለኝ ነገር እየከበደኝ  አፌን በሶፍት አፍኜ ስጠባበቅ ትንሽ መለስ ሲልልኝ
በቃ ንገረኝ ልሄድ ነው ብዬ ቀና ስል በጣም የምታምር የደም ግባት ያላት ልጅ የማክቤልን ትከሻ ተደግፋ ቆማለች ተዋወቁ ፍቅረኛዬ ነች አለ
በማፌዝ አስተያየት እያየኝ ልጅቷ ፈገግ ብላ እጇን ዘረጋችልኝና መርሀዊት እባላለሁ አለች ስትስቅ ድፕሏ ጎላ ብሎ ይታያል ውበቷንም በእጥፍ ይጨምርላታል ውስጤ ቅጥል እያለ ሰላም እባላለሁ ብዬ ጨበጥኳት እጇን ለቀኳትና በጣም እንደምታምር ነግሪያት ተነስቼ ወጣሁ ማክቤል መጣሁ ብሏት ተከተለኝ በህይወቴ እንደሱ ወራዳ ሰው አይቼ አላቅም በጣም ጠላሁት ከኋላዬ መጥቶ እየሳቀ ቆንጆ ናት እንዴት አየሻት ሲለኝ ድምፁ ሊያስታውከኝ ምንም አልቀረውም ነበር ዝም ብዬ ወደፊቴ ሄድኩ እሱ እየተከተለኝ ይለፈልፋል እንዴት ነው ፍቅረኛሽ ሸመጠጠሽ እንዴ አብራችሁm አትታዩም  ወይስ ተከራይተሽው ነበር ብቻ ምላሱን ብቆርጠው በምን እድሌ መጨረሻ ላይ ትግስቴ ሲሟጠጥ በርጋታ ወደሱ ዞርኩና ፍቅረኛህ በጣም ቆንጆ ናት በጣም ደስ ትላለች ግን ደሞ ታሳዝናለች እንዳተ አይነት ሰው ላይ ስለጣላት ለማንኛውም ያዝልቅላቺሁ እኔን ግን ተወኝ እኔኮ በቃ እርግፍ አድርጌ ትቼሀለሁ እኔ የራሴን ህይወት ጀምሬሀለሁ አንተን ከሰው እኩል እንኳን መቁጠር ካቆምኩ ሳምንታቶች አልፈዋል ሰርግህን እንዳትረሳኝ ከቀደምኩህ አረሳህም ብዬው በቆመበት ጥዬው ሄድኩ ልክ ልኩን ስለነገርኩት አልተከተለኝም ብቸኝነት ሲሰማኝ የምሄድበት የሆነ ቦታ አለ እዛ ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ የምርመራ ውጤቱም አለ ለካ .....
ይቀጥላል


🔻ክፍል ስምንት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
  💔 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰6️⃣

ስለዚህ በሆነ ነገር ልፈትነው አሰብኩ ልክ እንደተገናኘን በመጣደፍ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህማ አልኩት መቼም አንዴ ሲፈጥረኝ እርጋታ ብሎ ነገር አልፈጠረብኝም እሺ ሞልቃቂት አለ እየሳቀ ሲስቅ አንዳች ሰውነትን ስንጥቅ የሚያደርግ ምትሀት ነገርማ አለው )
በቃ ተወው ስንወጣ መኪና ውስጥ እነግርሃለሁ ብቻችንን ስንሆን አልኩት እሺ እንደተመቸሽ አለኝ ደሞኮ ሲያወራ ቃላቶቹ አንቺ ቅደሚ አንቺ የሚባባሉ ነው የሚመስለው አቤት እርጋታቸው ።
ልክ መኪና ውስጥ ስንገባ ወደፊት ንዳው አልኩት የት እንደሚሄድ ባያቅም ይነዳዋል ብቻ ዞር ስል ትንሽዬ ቦታ አየሁ አቁመው አቁመው ሳይታወቀኝ አንባረኩበት እሺ ተረጋጊ እንጂ ሰላም አለ ።
እሺ ወደ ታች ታጠፍ አልኩት ታጠፈ  ትንሽ ተጉዘን ከመኪናው ወረድን ለሁለታቺንም በደንብ እየተያየን ለማውራት የሚመቸንን ቦታ ከመረጥን ቡሀላ ቁጭ አልን እሱ ትንሽ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ እግሩን ከፍቶ ተቀመጠ እኔ በእግሮቹ መሀል  ገብቼ ቁጭ ልል አልኩና ድፍረት ይሆንብኛል ብዬ ከጎኑ ወደሱ ዞሬ ቁጭ አልኩኝ
እሺ አጂሪት ቀጥይ አለ። ለመስማት እንደጓጓ  የሆነ ነገር ሹክ ብሎኛል ።
ምን መሰለህ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር አልኩ ምን ብዬ እንደምጀምር ግራ እየገባኝ እኮ ነው ። ጠይቂኛ ብቻ አፈቅርሀለሁ እንዳትይኝ እንጂ አለ አነጋገሩ የቀልድ አይመስልም ማለት አልኩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም ቀጥይ አለ።
እሺ ብዬ የራሴን ጥያቄ ልግባው 😂😂😂😂😂😂 በቃ ለምሳሌ መንገድ ላይ እየሄድክ አንድ የኔ ቢጤና አንድ ሚሊየን ብር ብታገኝ ቀድሞ ልብህ የትኛውን ይከጅላል አልኩት ::
መልሱን እስክሰማ   ተጨነኩ
እእእ በቃ ለዚህ ነው እዚህ ድረስ ያመጣሺኝ ብሎ አፍንጫዬን ጎተተኝና
ወደ መልሱ ስገባ እኔ የኔ ብጤውን እመርጣለሁ ምክንያቱም ይቀጥላል .....................



🔻ክፍል ሰባት ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 🟰5️⃣

ልብሴን ለባበሼ ስወጣ ልኡልጋ ደወልኩ አነሳውና እዛው እየጠበቀኝ እንደሆነ ነገረኝ ሄድኩ ውስጥ ስንገባ ማክቤል የለም ለነገሩ አይኑን ማየት እራሱ ነበር ያስጠላኝ ልክ ስንገባ የሆነ ምግብ ሸተተኝ እና በጣም አማረኝ ለልኡል ልነግረው ነበር ግን ይታዘበኛል ብዬ ተውኩት ።
አስታናጋጇ ትንሽ ቆይታ ስገባ የሸተተኝን ምግብ ባጠገቤ ይዛ አለፈች መቋቋም እስኪያቅተኝ ድረስ አማረኝ ስትመለስ አስተናጋጇን በእጄ ጠርቻት አሁን ባጠገቤ ይዘሽ የሄድሺውን ምግብ ይዘሽልኝ ነይ አልኳት ልኡልንም ምን እንደሚፈልግ ጠይቃው ሄደች
ምግባችንን ጨራርሰን እየተጎነጨን ዝም ብለን እያወራን ነው ልኡል በጣም ተጨዋች ነው ።
አጉል እንደሀብታም አያካብድም በጣም እየገረመኝ ነው ጨራርሰን ልንወጣ ስንል ማክቤል ከፊት ለፊት መጣ አየተሳሳቅን ባጠገቡ አለፈን በግልምጫ አንስቶ አፈረጠኝ ቦታም አልሰጠሁትም የወደድኩትን ያህል ነው ያስጠላኝ ብቻ በቃ ከልኡሌጋ በጣም እየተቀራረብን ነው አንዳንዴ ሳስበው በጣም ነው ሚገርመኝ ፈጣሪ እንዴት ሁሉን ነገር አሟልቶ ለ1 ሰው ይሰጣል ብዬ አሰብኩ ከመልክ መልክ በሀብት ላይ ሀብት በፀባይ ላይ ፀባይ አላቅም ብቻ ይሄ ጎሎታል ማይባል እንደስሙ ልኡል የሆነ ሰው ነው አንዳንዶቹ ሀብት  ካላቸው በጎነት ይጎላቸዋል በሀብታቸው ምንም ነገር ማድረግ የሚችሉ የሚመስላቸው ተራ ሰዎች በዚች አገር ላይ እልፍ ሰዎች አሉ አንዳንዶቹ ደሞ መልክ ካላቸው ፀባይ ይነሳቸዋል ብቻ ልኡሌ ከማቃቸው ሰዎች በብዙ ነገር ተለየብኝ አሁን አሁንማ ሳላገኘው ማደር እራሱ በጣም ጭንቅ ክፍት ይለኝ ጀምሯል አረ እንደውም በጣም ነው የሚያነጫንጨኝ ማክቤልን ከልዑልጋ ማወዳደር እየከበደኝ መጣ።
ማክቤልን ማስታወስም ማየትም ስለማልፈልግ የነሱ ግሮሰሪ እግራችን ደርሶ አያቅም ::
ከልኡልጋ በደንብ ማውራት ከጀመርን አንድ ወር አልፎናል ይመስለኛል የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ነው ነገር ግን እሱጋ ስደርስ አላስነቃም አንዳንዴ ልኡሌ እየተደበረብኝ  ይመስለኛል ምክንያቱም ማክቤል ያለኝን ሳስታውስ እውነት እንደሱ ሀብታም ስላልሆነኩ ባይወደኝስ ብዬ አስባለሁ:

🔻ክፍል ስድስት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


ታሪኩን እየወደዳችሁት ነው?

አዎ ❤️
አይ😔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 4️⃣

አዎ ላወራሽ ፈልጌ ነበር አለ ከተመቸኝ እሺ አልኩት በቃ ቻው ደህና ደሪ ስልኩ ጆሮዬ ላይ ተዘጋ ከትንሽ ደቂቃዎች ቡሀላ ወደ ልኡል ጋ ደወልኩ አያነሳም ልረብሸው ስላልፈለኩ ዝም አለኩ እንቅልፌ ሸለብ ከማድረጉ ስልኬ ጮኸ ልኡል ነበር አነሳሁትና በሰላም ገባህ አልኩት አዎ እየነዳሁ ስለነበር ነው ያላነሳሁት ይቅርታ አለኝ የተወሰነ ካወራን ቡሀላ ቻው ተባብለን ተኛሁ ጠዋት ከእንቅልፌ የተነሳሁት 3 ሰአት ላይ ነበር ቁርሴን በላልቼ ስጨርስ ወደ ጓደኛዬጋ ልወጣ ልብሴን ስለባብስ ስልኬ ጮኸ ማክቤል ነው አነሳሁት ሄሎ አለኝ አቤት አልኩት ዛሬ እንገናኛለን ተባብለን አልነበር ከተመቸሽ አሁን ላግኝሽ በራቺሁ ጋ ነኝ አለ ጠብቀኝ ብዬው ከ10 ደቂቃ ቡሀላ ወጣሁ ተኮሳትሮ ነበር የጠበቀኝ ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ምንድነው ልታናግረኝ የፈለከው አልኩት በውስጤ ይቅርታ ሊጠይቀኝ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ እኔም ትንሽ ከለመነኝ ቡሀላ እሺ እንደምለው ወስኜ ነበር እሱ ግን የትናትናው ልጅ ፍቅረኛሽ ነው አለ ተኮሳትሮ ለምን ጠየከኝ አልኩት አይ እኔ እንድትጎጂ አልፈልግም ላስጠንቅቅሽ ብዬ ነው ማለት አልኩት ውስጤ ግራ ግብት ብሎታል እሱኮ በጣም ሀብታም ነው በጣም ታዋቂ መኪና አስመጪና ላኪ ድርጅት አላቸው ከወንድሞቹጋ በዛ ላይ የራሱ የሆነ ምን የመሰለ ሆቴል አለው ስታስቢው ዝቅ ብሎ ካንቺጋ የሚሆን ይመስልሻል እኔ እንኳንኮ የራሴ የምለው ምንም ነገር ሳይኖረኝ ባባቴ ጎሮሰሪ  ተኩራርቼ ነው አንቺን ደሀ ነሽ ብዬ የተውኩሽ ?።እስኪ እራስሽን ተመልከቺ አንቺም ሆንሽ ቤተሰቦቺሽ ከዚህ ከቆመ የጭቃ ቤት በቀር የራሴ የምትሉት ምን አላቺሁ እና ተጠቀቂ ብሎኝ  በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ ብቻ አላቅም በስለት እንደተወጋሁ ነገር ሰውነቴን ሁላ ደነዘዘኝ የማቀው ማክቤል አልመስልሽ አለኝ ለአይኔ አስጠላኝ በጣም ቀፈፈኝ እስከዛሬ ፍቅረኛዬ መሆኑን ሳስብ ሰቀጠጠኝ ፈዝዤ በቆምኩበት የሆዴን ህመም መቆጣጠር አቅቶኝ መሬት ላይ ወደኩ ከየት መጣ ሳልለው የሆነ ሰውዬ መቶ አነሳኝ እራሴን ለማረጋጋት ከሞከርኩ ቡሀላ ወደ ቤት ገብቼ ተኛሁ ያለኝን በሙሉ ማሰብ ጀመርኩ ግማሹ ልቤ እውነቱን ነው አንቺ ተመርቀሽ እንኳን ስራ የለሽ የራሴ የምትይው የግል ቤት የለሽ ይለኛል ግማሹ ልቤ ግን ለፍቅር ገንዘብ መስፈርት እንደማይሆን እየነገረኝ ነው ብቻ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ደርሷል ሳወጣ ሳወርድ ከራሴጋ ስጣላ ስታረቅ ብቻ ክፍሌ ሆኜ በሀሳብ ሀገሪቷን ሳስስ ከሀሳቤ ልኡሌ ነበር ደውሎ የቀሰቀሰኝ እንደከፋኝ እንዲያቅ ስላልፈለኩ እንደመሳቅ ብዬ ሄሎ አቶ ልኡል ምን ነበር ስለው አይ ዛሬስ ፍቅረኛሽን አታስቀኚውም ወይ ልልሽ ነበር አለኝ ::በዛ እረጋ ባለ ድምፁ አይይ ታውቆብሀል በቀጥታ ላግኝሽ ነው ሚባለው አልኩት እየተፍለቀለኩ እሺ የት እንገናኝ እዛው የባለፈው ቤት ነዋ አልኩት እየተፍለቀለኩ ወዲያው ተነስቼ ከሌላ ጊዜው በተሻለ የሚያሳምረኝን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ
``


🔻ክፍል አምስት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል 3️⃣


ቀኑ እየመሸ ሄደ ከ10 ሰአት ጀምሮ ስልኬን ሳነሳ ስጥል ቆየሁ ልክ 11.50 ሲል ደወለልኝ ውጪ ሰፈር መጥቻለሁ🙄
ክው አልኩ እንዴ ልብስ ሳልቀይር ሳልዘጋጅ ከራሴጋ እያወራሁ በፍጥነት ከሌላ ጊዜው በላይ ቆንጆ ሚያደርገኝን ልብስ መርጬ ለበስኩ : ፀጉሬ ከመጀመሪያውም ተሰርቼው ስለነበር ያን ያህል አላስቸገረኝም ።
ይቅርታ አስጠበኩህ አደል??
የሴት ነገር የታወቀ ነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ ??? ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ
ቀለል ያለ ሰው እኔም ቀለል አድርጌ እዚህ ነው እንዴ ምናወራው ባይሆን እኔ ከፍላለሁ ሻይ ቡና እንበል እንጂ !!
ሳቀብኝ ምናልባት ከቸኮልሽ ብዬ ነው እንጂ እሺ ምታቂው ቤት አለ እዚህ አካባቢ ወይስ በኔ ምርጫ ልውሰድሽ ???
አይ እኔ ማቀው ቤት አለ አዛ ልውሰድህ አልኩት ። ቀጥታ እነ ማክቤልጋ ወሰድኩት ገባን ቁጭ አልን እሺ ለምን እንደፈለግሽኝ ንገሪኝ ከማዘዛችን በፊት አለኝ ።
በቃ አጠር ቀልጠፍ አድርጌ እንባ እየተናነቀኝ የ6 አመት ፍቅረኛዬ ምን እንደተፈጠረ እንኳን ሳይነግረኝ ከመሬት ተነስቶ እንለያይ አለኝ 
ሳላስበው እንባዬ ካይኔ ዝርግፍ ብሎ ፈሰሰ።
አይዞሽ ብሎ ሶፍት ሰጠኝ ቀና ስል ማክቤል እያየኝ ነበር እሱ ፊት እንደዚህ መሆኔ በራሴ እየተናደድኩ ለመሳቅ ሞከርኩ እንዴ ምነው አለኝ ፍቅረኛዬኮ ፊት ለፊት እያየኝ ነው እንዴ እዚህ ምን ይሰራል እዚህ እንደሆነ አውቀሽ ነበር እንዴ ብሎ ተከታታይ ጥያቄ ጠየቀኝ።
አዎ ይሄ ቤት ያባቱ ነው እሱ ደሞ ከዚህ አይጠፋም ይቅርታ ግን ላናድደው ፈልጌ ነው እሱ ከማያቀው ሰውጋ ሆኜ ለሱ ደሞ ካንተ የተሻለ ሰው አላገኘሁም ማለቴ ላስቀናው ከፈለኩ ከሱ የተሻለ ቆንጆ ሰው መሆን አለበት ብዬ ሳስብ አንተ መጣህልኝ !!ቁጥብ ፈገግታውን ለገሰኝ ሲስቅ የሆነ ብቻ የሚያስደነግጥ ነገር አለው እኔ ምልሽ  ካንቺ ምን አጥቶ ነው የተጣላሽ ????? መጀመሪያ ከኔ ምን ጎድሎት ነው የተጣላኝ ብለሽ እራስሽን ጠይቁ አለኝ።
ማወቅ ምፈልገው እሱን ነው አልኩት እና ምግብ እንዘዝ አለኝ አስተናጋጁን ጠራነው እሱ የራሱን ምርጫ ሲያዝ እኔ የቀድሞ ፍቅረኛዬ አብዝቶ ሚወደውን ምግብ አዘዝኩ እየተመገብን እያለ ላጉርስህ ማለቴ ካልደበረህ??? አልኩት ምነው እያየሽ ነው እንዴ አለኝ አዎ አይኑን ከኛ ላይ መንቀል አልቻለም አልኩት እሺ አለኝ በዙም ደስ እንዳላለው ያስታውቃል ግን የኔ አይና አውጣነት አጎረስኩት በልተን እንደጨረስን በቃ እንሂድ አለኝ እሺ ብዬ ተነሳሁና እጁን ያዝኩት የሆነ የገባው ነገር ነው ወደ እራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ ልክ ከበሩ እንደወጣን ልሸኝሽ አለኝ ካላስቸገርኩህ አልኩት ደርሰን ልወርድ ስል ለካ እስካሁን ስሙን አላቀውም እውይ እረስቼው ስምህንኮ አልነገርከኝም አልኩት የዛኔ ከት ብሎ ሳቀብኝ እንዴት ስሜን እንኳን ሳታቂ የጋበዝኩሽን ምግብ ትበያለሽ ደሞ ጭራሽ መኪናዬ ውስጥም ገብተሻልኮ አለኝ ከደበረህ ይቀራላ አትንገረኝ ተወው ብዬ ፊቴን ዘፈዘፍኩት ባክሽ አታኩርፊ  ልኡል እባላለሁ አለኝ ስምን መለአክ ያወጣዋል ማለትኮ እንዳንተ ነው  በቃ ቻው አልኩት እሺ ብሎ ሄደ መኪናው ካይኔ ሲሰወር ወደ ቤቴ ገባሁ ልክ ሰገባ ማዘር ምነው ቶሎ መጣሽ ብላ ሙድ ያዘችብኝ ሰአቱን ሳየው2 ሰአት አልፏል ትንሽ ካወራን ቡሃላ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጋደም ከማለቴ ስልኬ ጮኸ ሳየው ማክቤል ነው ።ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ አላነሳውም ትንሽ ይበሳጭ ብዬ ዝም አልኩት ድጋሜ ደወለ አሁንም ዝም   በ4ኛው  አነሳሁት ሄሎ አልኩ በመኮሳተር ድምፅ ምነው ስልክ አታናሺም አለ ::
መጀመሪያ ሰላምታ አይቀድምም ስልክ ያላነሳሁት ደሞ ከፍቅረኛዬጋ ነበርኩ ምነው በሰላም ነው የደወልከው??
ይቀጥላል

🔻ክፍል አራት ከ2️⃣5️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
      
  💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል2️⃣

ምሽቱን ሙሉ አይኔ ደም እስኪመስል ሳለቅስ አመሸሁ አንድም ቀን ካፉ ክፉ ቃል አውጥቶ አስቀይሞኝ አያቅም ይሄ ነው የምለው መጥፎ ፀባይ የለበት በድንገት እንደዚህ ያደረገው ነገር ግራ ገባኝ አልቅሼምም አልወጣ አለኝ::

  ማታ መሽቶ እናቴ ወደቤት መጣች ከእህቴጋ ሲያወሩ እየሰማኋቸው ነው እህትሽ ምን ሆና ነው በጊዜ ወደመኝታ ቤት ያመራችው ??
እኔጃ እማዬ ከመጣሁ ጀምሮ አላናገረችኝም እስቲ አንቺ አናግሪያት አለቻት።
እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እናቴ አይታኝ ተያት በቃ እንቅልፍ ወስዷታል ብለው ከክፍሌ ወጡ።
   ሌሊቱን ሙሉ አንዴ ስነሳ አንዴ ስቀመጥ አንዳንዴም እንደ ህንድ አክተር ልግደለው እንዴ እላለሁ አንዳንዴ ደሞ በድንገት ቢሊየነር ሆኜ በየቲቪው ብታይኮ እራሱ እየለመነ ይቅርታ ይጠይቀኛል ብቻ ሌሊቱ እንዲሁ ነጋልኝ በሀሳብ ስብሰለሰል ።
  
   በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ ስነሳ ቤት ማንም የለም ከነጋ ቡሀላ ስለሆነ እንቅልፍ የወሰደኝ አርፍጄ ነው የተየሳውት ቀጥታ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ድፍት ብዬ አለቀስኩ የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ እንደቀለለ ነገር ተሰማኝ ወደ ቤቴ ተመልሼ ምሳ ሰአት ሳይደርስ ቤቱን ፏፏ አድርጌ እናቴን ጠበኳት ተጨዋውተን ወደ ስራዋ ተመልሳ ሄደች ።
እኔም ለባብሼ ወደነማክቤል ሬስቶራንት ሄድኩኝና አስጠራሁት ገና ሲያየኝ ፊቱን ቅይይር አደረገው ።

ምንድነው??
ማክቤል መለያየታችን ይሁን እሺ  ቢያንስ ግን ይሄ ነው ጥፋትሽ በለኝና ልወቀው እኔም ጭንቅላቴ እረፍት ያግኝ አልኩት።
        በቃ መለያየት ፈለኩ ተለያየን ሌላ ምክንያት መደርደር አያስፈልገኝም እየመጣሽ እንዳትበጠብጪኝ ክብርሽን ጠብቂ ።   
ይሄን ተናግሮ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ
እንባ እየተናነቀኝ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ሄድኩኝኝኝ ምሽቱን በሙሉ ከራሴጋ ሳልሆን መምሸቱም መንጋቱም ስለማይቀር መሽቶ ነጋ ዛሬም በጠዋት ተነስቼ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ።
ቅዱስ ሚካኤል አባቴ ለኔ ካላልከው በቃ ከልቤም ከህይወቴም አውጣልኝና አንተ የተሻለውን እንደምታዘጋጅልኝ ስለማምን አንተን እጠብቅሀለሁ የራሴን ሰው እስክሰጠኝ አሱን ግን አባቴ ከነትዝታዎቹ ከሀሳቤም ከኔ ህይወት አውጣልኝ ብዬ ፀለይኩ።።
ወደ ቤቴ ተመልሼ እንደተለመደው እናቴን ምሳዬን ሰርቼ ቤቴን አፀዳድቼ ጠበኳት ከሷጋ ተሳስቀን የልብ የልባችንን አውርተን ወደስራዋ ሄደች ።
  ልክ እናቴ ሄዳ ለብቻዬ ቁጭ ስል ቀጥታ ሀሳቤ ውስጥ ይመጣል ። አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ እንዴት ነው እሱን መበቀል ምችለው ????????
ከብዙ ሀሳብ ቡሀላ ጭንቅላቴ ውስጥ 1 ሰው መጣ ነዛሬ ሳምንት ሆዴን በጣም እያመመኝ ተቸግሬ ነበር ።
ለመታየት ወደ ሆስፒታል አመራሁ ልክ ከtaxi ወርጄ የሆስፒታሉ በር ላይ ስደርስ ከአንድ ልጅ ይሁን ሰውዬ ብቻ አላትሞ መሬት ላይ ዘረረኝ ። በጣም ደንግጦ ወይኔ ይቅርታ በሀሳብ ተውጬ ነው ተጎዳሽ የኔ እናት እእ በፈጣሪ ስም ደና ነሽ  ብቻ ምን ልበላችሁ ተርበተበተ ከወደኩበት አነሳኝ ለጊዜው ትንሽ ቢያዞረኝም ያን ያህል ህመም አልተሰማኝም ነበር። ወዴት ነሽ እ ምን ልርዳሽ አለኝ ወደ ሀኪም ቤት ልገባ የነበርኩት ልጅ ወደ ቤቴ ነኝ አልኩት ።
እሺ ነይ እኔ ልሸኝሽ  አለኝ እንኳን ለመንዳት ለማየት ወደምታታሳሳው መኪናው ውስጥ አስገባኝ ።
ይቅርታ አላየሁሽም ነበር እሺ ካመመሽ ወይ የሆነ የጉዳት ስሜት ከተሰማሽ ደውይልኝ ብሎ ቁጥሩን ሰጠኝ ወደ ቤቴ ሸኝቶኝ ተመለሰ ። ይኸው 1 ሳምንት ሙሉ ትዝ አላለኝም ነበር ዛሬ ግን ማክቤልን ለማስቀናት ለአንድም ይሁን ሁለት ቀን ይተባበረኝ ይሆናል ብዬ አሰብኩ።
 
በሰአቱ ስሙን አልነገረኝም ነበር ስልኬ ላይ የገፈተረኝ ልጅ ብዬ ነው save ያደረኩት ያ በደንብ ለማስታወስ ያህል ማለት ነው😂😂   

   ስልኬን አነሳሁ ደወልኩ አያነሳም 😣
  ወዲያው ስልኬን ከጄ ላይ ሳላስቀምጠው መልሶ ደወለ ።
     ሄሎ!!!
ሄሎ ጤና ይስጥልኝ ሰላም ነህ (ምን እንዳርበተበተኝ ፈጣሪ ይወቀው)።
   አብሮ ይስጥልን ሰላም ነኝ ማን ልበል?
(ወይኔ ድምፁ ደስ ሲል ከዛ ከርከሮ ማክቤል ተብዬ አንፃርማ ይሄ)....
እእእእ ይቅርታ ሰላም ነኝ እእ ባለፈው ሆስፒታል በር ላይ ገፍትረህ የጣልከኝ ልጅ።
   እእእ አወኩሽ ምነው አመመሽ እንዴ እእ???
አረ አደለም ሰላም መሆኔን ልንገርህ ብዬ ምናልባት ተጨንቀህ ከነበር አልኩት ቀልድ ማውራቴ ነው በኔ ቤት እሱ ግን በስሬስ
እውነት ለመናገር አስቤሽ ነበር ግን በሰአቱ ስልክሽን አልወሰድኩም እና ቢያማት ትደውል ነበር ብዬ ዝም አልኩ።
   አለኝ።
አረ አላመመኝም ደና ነኝ ግን ከይቅርታጋ 1 ነገር ላስቸግርህ ነበር ማለቴ ከተመቸህ ዛሬ ላገኝህ ነበር 1 ጉዳይ ላወራህ ነበር ። (አይና አውጣነቴን ከየት እንዳመጣሁት አላቅም) 
እእ ምነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ???
አዎ በሰላም ነው ግን ካልተመቸህ ችግር የለውም ተወው በቃ ።  አልኩት
አረ እንደዛ አላልኩም ወደማታ አካባቢ ስራ ከጨረስኩ አገኝሻለሁ ሰፈርሽ ባለፈው ያደረስኩሽ ቦታ ነው አደል???

   አዎ አዎ እዛ ነው ደውልልኝ ቀደም ብለህ ማለቴ ከተመቸህ አልኩት ።
 እሺ እደውልልሻለሁ መልካም ቀን።
ስልኩ ተዘጋ
       

🔻ክፍል ሶስት ከ2️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 💔
@FEGEGTA_BCHA 💔
💔 
@FEGEGTA_BCHA 💔


🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
        💗የፍቅር ማእበል💗   


ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟

          ⭐️ክፍል1️⃣

ሰላም እባላለሁ።   ብዙዎች እንደ ስሜ ሰላም የሆንኩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል...
ቅብርር ያልኩ የድሀ ልጅ ነኝ እናቴ እንደወንድም እንደሴትም ሆና ነው ያሳደገችኝ ፈጣሪ ይመስገን እንደማንኛውም ኢትዮጽያዊ ተመርቄ ስራ ይለኝም ።
     በወጣትነት እድሜ ቤተሰብ ለፍቶ ስንት መስዋትነት ከፍሎ አስተምሮ ሲጨርስ ስራ አቶ ቤት ቁጭ ብሎ የነሱን እጅ እንደመጠበቅ የሚያም ነገር የለም ።
    በዚህ ህይወት ውስጥ ብቸኛ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ፍቅረኛዬን ማክቤልን ነው ።
 
  ከልጅነታችን ጀምሮ አብረን ነው ያደግነው የፍቅር ስሜት በመላችን አልነበረም  እኔ 12 ስገባ እሱ ቀድሞኝ ተፈትኖ ውጤት አልመጣለትም ነበር 
እና የዛን አመት ነው አፈቅርሻለሁ አፈቅርሀሉ ሳንባባል እራሳችንን relationship ውስጥ ያገኘነው ።
 
  ይኸው አሁን 5 አመታችንን ጨርሰን ወደ 6 እየሄድን ነው ፈጣሪ ከፈቀደው እኔ ልክ ስራ እንዳገኘሁ እናቴን የተወሰነ የሰርግ ወጪ ማገዝ ከቻልኩ ለመጋባት ነው እቅዳችን 
ቢያንስ ካገባሁ ቡሀላ ከናቴ ላይ ሸክም ከመሆን እድናለሁ በራሴም እፍጨረጨራለሁ ብዬ አምናለሁ።
    

ከናቴጋ  ቡናችንን እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ እያለን ማክቤል ደወለ አነሳሁት
ሄሎ ሰላም

ወዬ ማክ 
ሰፈር ነኝ የተለመደው ቦታ እየጠበኩሽ ነው ቶሎ ነይ !!!
እሺ መጣሁ ብዬ እናቴን መጣሁ ቆይ ማክቤል ፈልጎኝ ነው ከቆየሁብሽ ወደ ስራሽ ሂጂ እሺ እናቴ
ስሚያት በዛው በለበስኩት ቱታና በነጠላ ጫማ ወደ ማክቤል አመራሁ  (ነፍቅር አጋራችሁን በጣም ስትቀርቡት ስለለበሳችሁት ልብስ ግድ አይሰጣችሁም እዚጋ ዋናው ነጠብ እሱን ማግኘታችሁ ማውራታችሁ ለናንተ ከበቂ በላይ ነው)
ማክ የተለመደው ቦታችንጋ ቁጭ ብሏል እንደለመድኩት ከኋላው ሄጄ ጥምጥም ብዬበት ሳምኩት ፍፁም የማቀው ማክቤል አልነበረም እጄን ከሰውነቱ ላይ መንጭቆ አነሳው በስማም እንዴ ምናባህ ሆነሀል መነጨከኝኮ አልኩት 😒
  ካሁን ቡሀላ መተዛዘሉ አስፈላጊ አደለም ለትልቅ ጉዳይ ነው የፈለኩሽ አለኝ ፊቱ ደም መስሏል ደም ስሩ ሁላ ተወጣጥሯል አረ እያስጠነከኝ ነው የተፈጠረ ነከር ካለ በቀጥታ ተናገር ምን ሆነሀል ቆይ??

ከዛሬ ጀምሮ እኔና አንች መለያየት አለብን ካሁን ቡሀላ አጠገብሽ አልደርስም አጠገቤ እንዳትደርሺ  አለኝ።
   ከት ብዬ በረጅሙ ሳኩበት አንተ ያምሀል እንዴ እኔኮ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ ደነገጥኩ አንተ ትቀልዳለሀ ደነዝ ጌታን ፊትህ ሁላኮ ተቀያይሯል እጄን ወደጉንጩ እያስጠጋሁ  
በደጋሜ አጄን ከፊቱ ላይ አነሳና መስፍን ይሙት አልቀለድኩም ለምን ብለሽ እንዳጠይቂኝ ዝም ብለሽ ከህይወቴ ውጭልኝ አለ አይኑ አዝሎት የነበረውን እንባ አፈሰሰው
  

ምን አልክ መስፍን ይሙት እእ በአባትህ ማልክኮ እንዴ ምንድነው የተፈጠረው ያምሀል እንዴ ቆይ ምን አጠፋሁ ንገረኝ እንዴ ቆይ አቶደኝም አታፈቅረኝም 6 አመት ይቅርና 6 ወር የለፉበት ፍቅርኮ ያሳዝናል እእእ እንዴት ከመሬት ተነስተህ እንለያይ ትለኛለህ እናቴ የሰርጋችንን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እኔ የምንጋባበት ቀኑ እርቆብኝ ሳለ እንደቀላል እንለያይ ትለኛለህ እእእእ ።( ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ነበር ልቤ ተከፍታ ለመውጣት ምንም አልቀራትም አንድ ቀን እንኳንኮ በመሀላችን አስታራቂ ገብቶ አያቅም ከፍ ያለ ፀብ ተጣልተን አናቅም አንድም ቀን ስለመለያየት አስበን አናቅም የመጀመሪያው ነኝ የመጀመሪያዬ ነው)
  
  የተፈጠረውን ነገር እንኳን አላብራራልኝም ፊቴን ቀና ብሎ አላየውም መናገር ሚፈልገውን ተናግሮ ሲጨርስ ሄደ ጥሎኝ እራሴን ችዬ መቆም እንኳን ስለከበደኝ እዛው ደገፍ ብዬ ቁጭ አለኩ
መጮህ አማረኝ ማልቀስ አማረኝ አነዱ ልቤም አውቆ ነው አሁን ይመጣል ይለኛል አንዱ ልቤ ደሞ መቼም የውሸት በአባቱ አይምልም ይለኛል ግራ ገባኝ እንደምንም ተሟሙቼ ቤቴ ደረስኩ እናቴ ወደስራዋ ሄዳለች ማንም የለም እህቴም ብትሆን ውሎዋ ትምህርት ቤት ነው ቀጥታ ክፍሌ ገበሁ በቁም አልጋው ላይ ወደኩኝ አፌን በትራሴ አፍኜ ጮኩ ትራሴን ነከስኩት ምንም መፍትሄ የለም ስልኬን አነሳሁ ደወልኩኝ በሁለቱም ስልኩ block አድርጎኛል ...

🔻ክፍል ሁለት ከ2️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
 


እንዴት ናቹ ቤተሰቦች የ forward ምልክቱን ነክታቹ ቻናሉ ላይ post የተደረገውን ግጥም ተመልከቱት ትወዱታላችሁ ❤️


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


🔥እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቻችን አዲስ ታሪክ እነጀምር እንዴ?😁🤗

በ LIKE እና COMMENT ንገሩኝ👇


Hello guys❤️

Показано 20 последних публикаций.