🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በእንቁ TUBE የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💟
⭐️ክፍል 🟰9️⃣
ምን ማለት ነው ድንገት ተነስቶ ተለያይተናል ማለት እ እኔ ስለሰርጋችሁ ቀን መርዘምና ማጠር ነበር ሳስብ የነበረው እቃቃ ጨዋታ ነበር እንዴ የያዛችሁት እእ ለምንድነው የተለያያችሁት ንገሪኝ????
እማ ደሞ አሁን ስለሱ ማውራት አልፈልግም ስለ አዲሱ ልጅ መስማት ከፈለግሽ ልንገርሽ ካልፈለግሽ ደሞ በቃ ልተኛ አንቺም ሂጂና እረፍት አድርጊ አልኳት ፊቴን እያዞርኩባት 😒😒
አይ ልጄ በቃ ስለማክቤል አልጠይቅሽም ንገሪኝ ስለ አዲሱ ልጅ ።
ለምድነው እንዲህ ምታለቅሽው ለምን ከፋሽ ፍቅር ሲይዝሽ የመጀመሪያሽ አደለምኮ የማክበል ጊዜኮ እንዲህ አልሆንሽም ልጄ አሁን ምን ተፈጥሮ ነው ንገሪኝ ግልፁን ።
እሱማ አዎ እማዬ የማክቤል ጊዜኮ መጀመሪያ የፍቅር ጥያቄ ስላቀረበልኝ የኔ እንደሚሆን አውቄ ነበር ይሄ ግን ስሜቱ ምን እንደሆነ አይገባኝም አንዳንዴ አውቆ የራቀኝ ይመስለኛል በእርግጥ ገና ከተዋወቅን 3 ወር ምናምን ነው ግን በጣም ነው የምወደው አንዳንዴ በጣም ሀብታም ስለሆነ እኔ እንደሱ ሀብታም ስላልሆንኩ እየናቀኝ ይመስለኛል ።
አይኑ ውስጥ የፍቅር ስሜት አያለሁ: ሲያየኝ ደስ እንደሚለው አቃለሁ :
ግን እሱ ምንም እናዳልመሰለው ያስመስላል በቃ ግን ሳስበው አይወደኝም አልኳት እያለቀሰኩ ውስጤ ያለው ስሜትና ከህክምና ማስረጃውጋ ተደማምሮ እንባዬ ሲፈስ ወደር የለውም ነበር ;::
ቀና ብዬ እናቴን ሳያት ፍጥጥ ብላ እያየችኝ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ስጭኝ አለችኝ እስተያየቷ ያስፈራል::
በጉጉት እየጠበኩ የናቴን አይን አይኗን ሳያት ኮስተር ብላ እውነት ልጁን ሀብቱን መልኩን አይተሽ አይደለም ያፈቀርሽው አለችኝ ::
አረ ማሚ ሙች በሱ አይደለም እኔ ስለሱ ሀብትና ንብረት ምናገባኝ ብለሽ ነው ወደፊት ድንገት ባሌ ቢሆን ከሱና ከፀባዩጋ እንጂ ከገንዘቡጋ አልኖር ማሚ ሁሌ ሲገባ ሲወጣ ጨቅጫቃ ከሆነ ለኔ የሚገባኝን ፍቅር ካለገሰኝ የሱ ገንዘብ ለኔ ምን ያደርግልኛ እማ እኔ ደሀም ሆነ ሀብታም የማገባው ባል ከቤት ወቶ እስኪመጣ እንዲናፍቀኝ እፈልጋለሁ ።
ሁሌ ደስታ ሳቅ ጨዋታ የነገሰበት ቤተሰብ እንጂ በሀብት የታጠረ ፍቅር የሌሌለው ሰው አልፈልግም አልኳት ።
ንግግሬ ከልቤ ነበረ ማሚም ደስ ብሏት በቃ ታገሺው ልጁ ያንቺ ነው።
ቢዘገይም አይቀርም ብላ በተስፋ ሞልታኝ መች እንደማስተዋውቃት ጠየቀችኝ እኔም አንድ ቀን ነበረ ምላሼ።
እሺ በቃ እረፊ ብላኝ ከክፍሌ ወጣች እሷ እንደወጣችልኝ የክፍሌን በር ከውስጥ ቆልፌ አልጋ ላይ ተዘረርኩና ያለችኝን ማሰብ ጀመርኩ ምናለ እውነት በሆነ ብዬ ተመኘሁ።
ግን ደሞ ልዑሌ የኔ እንደማይሆን ከመቼው በላይ አረጋግጫለሁ አረ እንደውም ድጋሜ ሁላ አጠገቡ ላልደርስ ወስኛለሁ እኔ ያን ያህል ጨካኝ መሆን አልፈልግም በተለይ ደግሞ ልዑሌ ላይ ሁሉንም ነገር ልንገረው ወይስ ዝም ብዬ ስልኬን አጠፋፍቼ ልጥፋ አላቅም ብቻ በጣም ግራ ገብቶኛል ምን እንደማረግ ጨቆኛል በዚህ ሰአት ሚስጥሬን የማማክረው ጓደኛ ቢኖረኝ ደስ ይለኝ ነበር ግን መናገር በራሱ ያሳፍራል ውርደት መስሎ ታየኝ በቃ ምሽቱን ሙሉ ሳስብ ሳለቅስ አመሸሁ በዛው እንቅልፍ ጣለኝ ጠዋት ስነሳ ከጠዋቱ 4 ሰአት ሆኗል ።
እናቴ የማታውን ነገር ስላየች ሳትቀሰቅሰኝ ነው ወደስራ የሄደችው ።
ተነስቼ ተጣጥቤ ለባብሼ ቀጥታ ወደ ሆስፒታል ሄድኩኝ ለማስወረድ ፈልጌ ነበር ያው የገመትኩት አልቀረም ማስወረጃ ጊዜው አልፏል (አንዳንዴ በህይወታችን ውስጥ ሳንፈልግ ጭካኔን ሀጥያትን አስተምረውን የሚያልፉ ብዙ ሰዎች አሉ)
በቃ ምን እንደማደርግ ነው የጨነቀኝ ለማንም ሳልናገር ብን ብዬ ልጥፋ እንዴ እላለሁ
🔻ክፍል አስር ከ3️⃣0️⃣0️⃣Vote💝 በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💔 @FEGEGTA_BCHA 💔
💗የፍቅር ማእበል💗