Фильтр публикаций


ሐማስ ከሚለቃቸዉ ታጋቾች ኢትዮጵያዊ እንደሚገኝበት ተሰማ

እስራኤልና ምዕራባዉያን መንግሥታት በአሸባሪነት የሚወነጅሉት የፍልስጤም ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሐማስ በቅርቡ ከሚለቃቸዉ ታጋቾች አንዱ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊ ነዉ።

እስራኤልና ሐማስ ባለፈዉ ጥር ባደረጉት ሥምምነት መሠረት በመጀመሪያዉ ዙር ከተለቀቁና ከሚለቀቁ ታጋቾች 6ቱ በመጪዉ ቅዳሜ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከሥድስቱ ታጋቾች አንዱ ኢትዮጵያዊ-እስራኤላዊ አቬራ መንግሥቱ ነዉ።አቬራ መንሥቱ እንደ ሌሎቹ ታጋቾች ሐማስ መስከረም 29፣ 2016 ደቡባዊ እስራኤልን በወረረበት ወቅት የታገተ አይደለም።

ጀሩሳሌም ፖስት የተባለዉ የእስራኤል ጋዜጣ ምንጮችን ጠቅሶ ባለፈዉ ጥር በኢንተርኔት እንደዘገበዉ የ38ት ዓመቱ ጎልማሳ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር መስከረም 7፣2014 በራሱ ፈቃድ ጋዛ ገብቶ እጁን ለሐማስ ሰጥቷል። በዘገባዉ መሠረት ያኔዉ የ28 ዓመት ወጣት የእስራኤል ወታደር እንደነበር ሐማስ አስታዉቋል።

ይሁንና ሑዩማን ራይትስ ወች የተባለዉ የመብት ተሟጋች ድርጅትና ቤተሰቦቹ የሐማስን አባባል አልተቀበሉትም።ወጣቱ የአዕምሮ ሕመምተኛ ነዉ ይባላል። ጋዛ ከመግባቱ በፊት ከእናቱ ጋር ተጣልቶ እንደነበረም ጋዜጣዉ የመብት ተሟጋቹን ድርጅት ጠቅሶ ዘግቧል።


የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በከፈተው ጥቃት በርካቶች ተገደሉ


የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር በሁለት የደቡባዊ ሱዳን መንደሮች በከፈተዉ ጥቃት በትንሹ 200 ሠላማዊ ሰዎች መግደሉን አንድ የመብት ተሟጋች ቡድን አስታወቀ።የሱዳን መንግስት በበኩሉ ፈጥኖ ደራሹ ጦር የገደላቸዉ ሠላማዊ ሰዎች ቁጥር ከ400 ይበልጣል ባይ ነዉ።




የትራምፕ የልደት ቀን ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ረቂቅ ህግ ቀረበ

ሪፐብሊካን የኮንግረንስ አባሏ ክላውዲያ ቴኒ የትራምፕ ልደት ቀን (ሰኔ 14) ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር የሚጠይቅ ረቂቅ ህግ ማቅረባቸውን ዘ ሂል ዘግቧል።

የትራምፕ የልደት ቀን ከአሜሪካ የሰንደቅ አላማ ቀን ጋር በተመሳሳይ ቀን የፌደራል የህዝብ በዓል ሆኖ መከበር እንዳለበት ነው ረቂቁ የሚጠይቀው።

የአሜሪካ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን የልደት ቀን ብሄራዊ በዓል ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።


88ኛው የሰማዕታት መታሰቢያ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

88ኛው የየካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት በመከበር ላይ ይገኛል።

በመታሰቢያ ሥነ ስርዓቱ ላይ አቡነ እንጦስ የምስራቅ ሀረርጌ ሀገር ስብከት እና የሲኖዶስ አባል፣ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የሐይማኖት አባቶች እንዲሁም አርበኞችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዕለቱ ፋሽስት ጣሊያን ከየካቲት 12/1929 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ከ33 ሺሕ በላይ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በነበሩ ንፁሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተገደለበትን ቀን በማሰብ የሚከበር ነው።


የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።

በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት ተራዘመ

የሕዝብ እነደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኮሚሽኑ የስራ ዘመን እንዲራዘም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሶስት ዓመታት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከቀረበለት በኋላ ነው፡፡




የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች እየሸሹ መሆናቸው ተሰማ

በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን ጥቃት እያየለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አሥር ሺሕ የሚሆኑ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዜጎች ባለፉት ሦስት ቀናት ድንበሯን አቋርጠው መግባታቸውን ቡሩንዲ አስታውቃለች፡፡

ወታደርቶችን ከሲቪሎች ለመለየትና በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አማካይነት መጠለያ ለመስጠት ጥረት በመደረግ ላይ መኾኑን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።


ትራምፕ እና ፑቲን መከሩ

የዩክሬኑን ጦርነት ለመቋጨት ያለመዉ የሰለም ንግግር በሳዉዲ አረቢያ መዲና ሪያድ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የሰላም ንግግሩ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ከተወያዩ በኋላ ነዉ እየተካሄደ የሚገኘዉ፡፡

በመድረኩ ላይ የሩሲያን ልዑክ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ሲመሩት በአሜሪካ በኩል ደግሞ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮና የደህንነት አማካሪዉ ሚካኤል ዋልትዝ ይገኙበታል፡፡

ይሁን እንጅ የግጭቱ ባለቤት የሆነችዉ ዩክሬን በመድረኩ ላይ አለመጋበዟ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ፡፡
ከአዉሮፓ አገራትም የተጋበዘ እንደሌለ አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡


የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃማስ መጥፋ አለበት አሉ

ማርኮ ሩቢዮ “ሃማስ እንደ መንግስትም ይሁን ወታደራዊ ኃይል መቀጠል አይችልም” ብለዋል። ሃማስ ትራምፕ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል የያዙትን እቀድ “ዘር ማጽዳት” ነው ሲል አውግዞታል።


በጋምቤላ ክልል በወረርሽኝ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

የጋምቤላ ክልል የጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር አቶ ኝኪዎ ጊሎ እንደተናገሩት፤ለክልሉ አጎራባች በሆነው ደቡብ ሱዳን በሽታው ተከስቶ እንደነበር ተናግረዋል።

በክልሉ ኑዌር ብሔረሰብ ዞን በአኮቦ፣ ዋንቱዋ፣ ማኩዌይ እና ላሬ ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት መከሰቱን እና ኮሌራ መሆኑን ለማረጋገጥ ዉጤቱ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በበሽታው ከተያዙት 1መቶ36 ሰዎች መካከል የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤31 ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙም ነዉ አቶ ኝኪዎ የገለጹት፡፡
96 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው ማገገማቸውንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡




የሶማሊያ እና የኬኒያ መንግስታት በጫት ንግድ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

የሶማሊያ እና የኬኒያ መንግስታት በጫት ንግድ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ኬኒያ ወደ ሶማሊያ በምትልከው ጫት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማደረጉን ተከትሎ ንግዱ ሙሉ ለሙሉ ታግዷል። በዚሁ በአወዛጋቢ ጉዳዩ ላይ የየሀገራቱ አመራሮች ተገናኝተው ሊመክሩ መሆኑን የሶማሊያው ሻቤል ጋዜጣ አስነብቧል።


ሳፋሪኮም የተቋረጠው አገልግሎት መመለሱን ገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ በጥቂት አከባቢዎች ተቋርጦ የነበረው አገልግሎታችን ወደነበረበት ተመልሷል ሲል ሳፋሪኮም አስታወቀ። ስለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ ጠይቋል።


ሃማስና እስራኤል ታጋቾች እና እስረኞችን ተለዋወጡ

ሀማስ 3 ታጋቾችን ሲለቅ፤ እስራኤል ደግሞ 369 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች። የታጋቾችና እስረኛ ልውውጡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ ያንዣበበውን የመፍረስ ስጋት ቀንሷል።


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አጥር የሌላቸው የማረሚያ ተቋማት መኖራቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አጥር የሌላቸው የማረሚያ ተቋማት መኖራቸው ተሰምቷል።
በዚህም ታራሚዎች ወጥተው የሚጠፉበት ዕድል መኖሩን የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በግንባታ ላይ 10 እና ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ 4 ማረሚያ ቤቶች እስካሁንም አለመጠናቀቃቸው ተጠቅሷል፡፡

በክልሉ ለሚገኙ ታራሚዎች ምህረት በሚደረግበት ወቅትም፣ በሀሰተኛ ማስረጃ የሚወጡ ታራሚዎች በርካታ ናቸው ተብሏል፡፡




ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ ተሰማ

በየዕለቱ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ አረብ ሀገራት ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የሚጓዙ ወጣቶች በሠሜን ወሎ በርካቶች ናቸዉ። ምንም እንኳን በአካባቢዉ ወደ አረብ ሀገር በባህር መጓዝ ከዚህ በፊት የተለመደ ቢሆንም አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ያልተረጋጋ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወጣቶች ይህን አስከፊ መንገድ ምርጫ አድርገዋል ሲል ዶቼቬሌ በዘገባው አመልክቷል።


የትራምፕ ውሳኔ የኤችአይቪ ቁጥጥር ላይ ስጋት መደቀኑ ተሰማ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በወሰዱት ጊዜያዊ የርዳታ ማቆም ርምጃ በሃምሳ ሀገራት የኤች አይቪ ሕክምናን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በቢሊዮን የሚቆጠሩ የኤች አይ ቪ፣ የፖሊዮ፣ ኤምፖክስ እና የወፍ ጉንፋን በሽታን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት መስተጓጎላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከበዓለ ሲመታቸው ጀምሮ አነጋጋሪ ውሳኔዎችን ሲወስኑ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የዚህ ውሳኔ አካል ከሆነው ውስጥ የዩኤስ ኤይድ ርዳታ ማቆም አንዱ ነው፡፡ ትራምፕ በርዳታ ድርጅቱ ውስጥ የሚሠሩ አስር ሺህ የሚደርሱ ሠራተኞችን ከመቀነስ ጀምሮ ተቋሙ ይሰጣቸው የነበሩ ዓለም አቀፍ ርዳታዎችን እንዲያቆም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው አይዘነጋም፡፡

Показано 20 последних публикаций.