Фильтр публикаций




ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)

"...መጀመሪያ የሌለው እርሱ ሰው ሆነ!..."
1 ወደ ጢሞቴዎስ 3:16 አማ05
[16] የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤..."

✍️ በክርስትና ሕይወት ውስጥ አሳዛኝ ሰው የምንለው ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትክክለኛ እና ልክ የሆነ እውቀትና እምነት የሌለውን ሰው ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማወቅ የክርስትናችን መሠረት እና እግዚአብሔርን መምሰል የምንችልበት ሚስጥር ነው።

ክርስቲያን የምንሆነው ጌታን የተቀበልን ዕለት ሳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርሰቶስ ላይ ባለን መገለጥ ላይ ተመስርቶ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ማንኛውም ሰው የሰው መልክና ቁመና ነበረው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሰው ተጸነሰ እንደ ሰውም የመወለጃው ወራት በደረሰ ጊዜ ተወለደ።
እንደ ማንኛውም የሰው መልክና ቁመና ይዞ ዕድሜ እየተቆጠረለት በጥበብ፣ በቁመት፣ በሞገስ በእግዚአብሔር እና በሰው ፊት አደገ።
ጌታ ኢየሱስ በዲያብሎስ ተፈተነ፣ በላ፣ ጠጣ፣ ደከመው፣ ታመመ፣ ሞተ እንዲሁም ተቀበረ። ማንኛውም ሰው የሚሆነውን ሁሉ ሆኗል ተፈትኗል ነገር ግን ከኃጢአት በቀር። ከላይ የዘረዘርናቸው ኢየሱስ ምንም እንኳን ዘላለማዊ አምላክ ቢሆንም ፍጹም ሰው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ሁሉንም የኃጢአታችንን ዕዳ እንደ እኛ ሰው በመሆን መክፈሉን የሚያስረዳ ነው።

በመጨረሻም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከ2017 አመት በፊት መሆኑ አምላክነቱ መጀመሪያ ያለው መሆኑን አያስረዳም። እርሱ መጀመሪያ የሌለው ከዘላለም በፊት የነበረ፣ ያለና የሚኖር አምላክ ነው።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15 አማ05
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 25/05/2017
⛪️ የክብር ሕይወት ቤ/ክ
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም ምሽት!
























Репост из: Rev. Tezera Yared (GloriousLifeChurch)
ጥሩ ባለ አደራ መሆን ማለት ጊዜን፣ ችሎታን ወይም ውድ ሀብትን እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር ሁሉ እንዴት እንደተጠቀምንበት መልስ የምንሰጥ መሆናችንን ማወቅ ማለት ነው!!!
የተባረከ ቀን!!!!
ሬቨ ተዘራ ያሬድ

Being a good steward means recognizing that we are answerable for how we use what God has given us, whether it be TIME, TALENT or TREASURE!!!
Blessed day!!!!
Rev Tezera Yared


Репост из: Rev. Tezera Yared (GloriousLifeChurch)
.....የጌታ ልደት ማለት...!!!

ትንቢተ ኢሳይያስ 9:6-7

የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን
የኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ መወለድ የአለምን ታሪክ የቀየረና የሰው ልጆችንም ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሀን ያሻገረ ታለቅ ክስተት ነው፤ ኢየሱስ ተወለደ ማለት ..
God Literally become a human being. “with out controversy” ማለት ነው!!!

1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3 (05)
16 የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።

1Tim 1 (NKJV)
16 And without controversy great is the mystery of godliness: God was manifested in the flesh, Justified in the Spirit, Seen by anger

Incarnation:- A central doctrine of the Christian faith which affirms that God took human form in the body of Christ. In other words God was incarnated in human flesh. Glossary definition
የጌታ ልደት ማለት ትርጉሙ ከበአል ባለፈ ......

Christmas means the invisible has become visible!!!

Christmas means God has become human!!!

The absolute has become particular!!!
መልካም በዓል ቤተቦች!!!











Показано 20 последних публикаций.