♥️ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ ትቆዪና መንገድ ዳር ቆመው ተሳፋሪ ከሚጠብቁ ታክሲዎች ወደ አንዱ ዘው ብላ ትገባለች። የገባችበት ታክሲ ቻይናዊ ሹፌርም ግራ በመጋባትና በመገረም ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በጥያቄ ስሜት መላልሶ ማየት ይጀምራል።
አጅሪት ግን ምንም ያልተፈጠረ በማሥመሰል መሄድ የምትፈልግበትን ተናግራ እንዲንቀሳቀስ በዓይኗ ምልክት ትሰጠዋለች። ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር ግን ያልተመለሠለት ጥያቄ ነበርና አሁንም ከእግር እስከራሷ መላልሶ ማየቱን ይቀጥላል።
ይኼኔ ቆንጂት በሷ ብሶ በስጨት እንደማለት እያደራረጋት " ልብስ ያልለበሰች ሴት አይተህ አታውቅም???" ብላ ታፈጥበታለች። ይኼኔ ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር እንዲህ በማለት በትህትና መለሠ "🤔... የኔ እህት... እኔ ግራ ተጋብቼ የማይሽ እርቃንሽን መሆንሽ ገርሞኝ ሳይሆን... ለአገልግሎቴ ልትከፍዪኝ የሚገባኝ ገንዘብ የቱጋ እንዳለሽ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው።"
እየውልህ ወንድሜ በዚህች ዓለም ስትኖር ልክ እንደ ቻይናዊው ሹፌር ማተኮር ያለብህ ሰለሚመለከትህ ጉዳይ ብቻ ነው። ስለማያገባህ ጉዳይ ስትፈተፍት በመዋልና በማደር ለራስህ የምትጨምረው ነገር የለም። አቅምህ እስከቻለው ለሌሎች መልካም አድርግ የሌሎችን ግላዊ ህይወት ግን ለባለቤቶቹ ተውላቸው።
✅️@HahuCryptoet