Hello Doctor


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


በዚህ channel ላይ በያሉበት ሆነው ጤና ነክ የሆኑ መረጃዎችንና የተለያዩ ተፈጥሯዊ ውበት መጠበቂያ ዘዴዎችን ያገኛሉ።
ጥያቄ እና አስታየት ካሎት https://t.me/HelloDoctor1 ወይም hellodoctor163@gmail.com ላይ ያስቀምጡ።
join as on YouTube channel
https://youtu.be/3Ku9JybN3LQ
የዚህ channel ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን 🙏🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций




የማንኮራፋት ችግር | Snoring disorder
    
የማንኮራፍት ችግር ማህበራዊ ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ጤና ላይ የሚያመጣዉ መዘዝ የጎላ ነው።

የማንኮራፋት ችግር የሚከሠተዉ አየር ከሳንባ ወይም ወደ ሳንባ በሚወጣበት እና በሚገባበት ጊዜ በሚያልፍባቸው የአየር ቱቦ በቂ የሆነ ክፍተት ካላገኘ ወይም የሚያልፍበትን የተመቻቸ መስመር የሚያስቀይር ችግር ካጋጠመው የሚፈጥረው የተዛባ ድምጽ (turbulent air flow) ነው።
   
ይህን የማንኮራፋት ችግር የሚያስከትሉ ምክነያቶች በህጻናት እና አዋቂዎች ላይ የተለያዩ ቢሆንም የሚከሠቱበትን ቦታ በ 4 ከፍሎ ማየት ይቻላል።

1. ከአፍንጫ እስከ ላንቃ ያለው የአየር መተላለፊያ ሲሆን ህጻናት ላይ በአብዛኛው አዴኖይድ የምንለው የቶንሲል ክፍል መጠን መጨመርና በአፍንጫ የሚያልፈውን አየር ሲዘጋ የሚከሠት ነው። አዋቂወች ላይ ከዚህ ቦታ በሚነሳ ችግር ማንኮራፋት ከተከሠተ ካንሠርን ጨምሮ ሌሎች እብጠቶችን ማሠብ እና ምርመራ ማድረግ ግድ ይላል።

2. ከምላስ የኋለኛው ክፍል እና በጎኑ ከሚገኙ ቶንሲሎች (posterior tounge and palataine tonsilar hypertrophy) ጋር ተያይዞ የሚከሠት ማንኮራፍት ነው። የዚህ ከምላስ ጎን የሚገኘው ቶንሲል የማንኮራፍት ችግር ከመፍጠሩ በላይ በ ተደጋጋሚ የቫይረስ እና የባክቴሪያ ኢንፌክሽን በመፍጠር ተጨማር የጤና እክል ያስከትላል።

3. በአፍና መንገጭላ አካባቢ የሚከሠቱ የአፈጣጠር ችግሮች እንዲሁም ከነዚህ ቦታወች ተነስተው የኅለኛውን የአየር መተላላፊያ ሊዘጉ የሚችሉ እብጠቶች እንደ ምከንያት ይጠቀሳሉ።

4. የኋለኛው የአየርና የምግብ የጋራ መተላለፊያ ግድግዳን የሚሠሩ ጡንቻወች መዛል ፣ በስብ መሞላት ፣ በእብጠት መጠቃት ወይም መግል መቋጠር ከተፈጠረ የሚከሠት ይሆናል።

ማንኮራፍት የሚከሠትባቸውን ምክነያቶች በወፍ ዘረር ካየን የዚህ ችግር መጠን ከሠው ሠው እንደተፈጠረው የአየር መተላለፊያ መስመር መጥበብ መጠን ይለያያል። ይሔም ከልማዳዊ ማንኮራፍት (habitual snorer) እስከ ሳንባ ከረጢቶች መጠን መቀነስ (pulmonary alveolar hypoplasia) ብሎም የሳንባ ደም ስሮች ግፊት እና የልብ ችግር ሊፈጥር ይችላል።

በተጨማሪም አካላዊና አእምሯዊ የእድገት ችግር ፣ የጸባይ ችግር (በተለይም ህጻናት ላይ) ፣ ቀን አብዝቶ የመተኛት ችግር ፣ በስራ  የመዛልና ውጤታማ ያለመሆን እና የመሳሠሉ ተጽኖወችን ይፈጥራል።

በትዳር አጋር ላይ የሚፈጥረው ጫና እና ማህበራዊ ቀውሡም ሌላው ጉዳቱ ነው። ማንኮራፍት የፈጠረውን የጤና ችግር ደረጃ ለማወቅ አይነተኛ የሚባለው መሣሪያ (polysomnography ) ሲሆን በሀገራችን የለም ማለት ይቀላል። ነገር ግን ይሔንን ለመተካት የሚፈጠሩ ስሜቶችን እና ምልክቶችን በማየት እና የልብ ፣ የአተነፋፈስ ምርመራወችን በማድረግ ደረጃውን ማወቅ ይቻላል። የዚህን ጀረጃ ማወቁ ጥቅሙ ለእያንዳንዱ ደረጃ የሚሠጠው ህክምና የተለያየ መሆኑ ነዉ።

ወደ መፍትሔው ስንመጣ ፤ መፍትሔው የሚወሠነው ማንኮራፍቱን በፈጠረው ችግር እና የችግሩ መጠን ሲሆን

1. በአብዛኞች ህጻናት ላይ ከአፍንጫ ጀርባ እና ከምላስ ጎን ያለውን ቶንሲል በሠርጀሪ በማስወገድ የሚስተካከል ይሆናል።

2. በአዋቂወች ደግሞ እባጮች (እጢወች) እንደሌሉ ከተረጋገጠ በኋላ ክብደት መቀነስ ፣ የኦክስጅን ህክምና (CPAP) ብሎም የአየር መተላለፊያን ቱቦ ለማሥፍት የ ሚደረጉ ሠርጀሪወች (uvuloplalatopharyngoplasty
,uppp እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ሠርጀሪወች) የህክምና አማራጮች ናቸው።

ስለዚህ፦ ማንኮራፋትን እንደ ቀላል ችግር በማየት አንዘናጋ፤ቢያንስ ያለንበት የማንኮራፍት ጀረጃ በምን መሥተካከል እንደሚችል ሀኪሞችን እናማክር።
    
ዶ/ር አለማየሁ እሸት


የፀጉር ቀለም የጎንዮሽ ጉዳት

በአሁን ጊዜ ጸጉርን ለማሳመር ሲባል ብዙዎች ቀለም ይቀባሉ ወንድም ይሁን ሴት ሆኖም ግን ያለውን የጎንዮሽ ጉዳ ያተዋሉት አይመስልም እኛም እንደጤና ባለሙያ ግዴታችን ነውና እስኪ አውቃችሁ ትጠነቀቀቁ ዘንድ እነሆ አልን።

📌 ሽበት፡- የጸጉር ቀለሞች በብዛት አሞኒያ እና ፐርኦክሰሳይድ ንጥረ ነገሮች ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ የጸጉር ተፈጥሯዊ ቀለምን በማሳጣት ሽበት እንዲከሰት እንዲሁም ጸጉር ሳስቶ እንዲሰባበር ያደርጋል፡

📌 የቆዳ አለርጂ፡- የጸጉር ቀለሞች ፓራፌናይልዲአሚን የሚባል አለርጂ አምጪ ንጥረ ነገር ይይዛሉ ይህ ደግሞ ቆዳን እንዲቆጣ፣ እንዲያሳክክ እንዲሁም ቀልቶ እንዲያብጥ ያደርጋል፡፡

📌 በእርግዝና ወቅት፡ ነብሰጡር ሴት በፍጹም የጸጉር ቀለም መጠቀም የለበትም ምክንያቱም ጽንሱን ከማስወረድ ጀምሮ እስከ ካንሰር መከሰት ስለሚዳርግ

📌 አስም፡- ልክ እንደአስም አይነት የመተንፈሻ አለርጂ ችግር ያለባቸው ሰዎች የጸጉር ቀለምን ማሶገድ የግድ ይላቸዋል ምክንያቱም በውስጣቸው የሚይዙት ኬሚካሎች ሳንባን በከባድ ሁኔታ ስለሚጎዳ ነው፡

📌 እርግዝናን ማዘግየት፡- በእርግጥ በዚህ ዙሪያ ብዙ የተደረጉ ጥናቶች ባይኖሩም ነገር ግን እንዳንዶች እንደሚያሳዩት የጸጉር ቀለም እርግዝና ለሚጠብቁ ጥንዶች የማዘግየት ሁኔታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

📌 የአይን ደም ስሮች መቆጣት፡- አይናችን በብዙ ነገር የተከለከለ ቢሆንም ግን አሁንም ቢሆን ከሰደጋ የጸዳ አይደለም በመሆኑም የአይናችን ደም ስሮች ከሚጎዱበት ዋነኛም ምክንያቶች መሀከል የጸጉር ቀለም ዋነኛው ነው፡፡

📌 ካንሰር፡- አንዳንድ የጸጉር ቀለም የቆዳ ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በውስጣቸው ስለሚይዙ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

@hellodoctor11


✍ #የጆሮ #ማሳከክ (#ear #

#ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው፤ ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት ሲጎዳ ከሚከሰቱ ምልክቶች አንዱ የማሳከክ ስሜት ነው። የጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችን ማወቅ በቶሎ መፍሄዎቻቸውን እንድንፈልግ ይረዳናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችም ናቸው፡-

👉👉 #የጆሮ #ኩክ #መከማቸት

📌 የጆሮ ኩክ (Ear wax) የምንለው ሰውነታችን የሞቱ ሴሎችንና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳበት መንገድ ሲሆን በብዛት በሚገኝበት ወቅት ግን የማሳከክ ስሜትን ይፈጥራል።

📌 ጆሮን ለማጽዳት መሞከር ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ይህን ከማድረግ መቆጠብ የተሻለ ነው። ወደ ሀኪም በመሄድ ከታዪና ትክክለኛ ምክንያቱ የኩክ መጠራቀም ሆኖ ከተገኘ በጠብታ መድሀኒት ወይንም በህክምና ባለሞያ እርዳታ እንዲወጣ ይደረጋል።

👉👉 #ኢንፌክሽን

📌 የጆሮ ማሳከክ አንዳንዴ ደግሞ የኢንፌክሽን መኖር ምልክት ይሆናል። ጉንፋንን ወይንም ቶንሲልን የሚያስከትሉ ባክቴርያና ቫይረስ በደም ተዘዋውረው ወደ ጆሮ በመሄድ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናሉ ።

📌 ውሀ ዋና የሚዋኙ ሰዎችም ውሃው በጆሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እና ተፈጥሮአዊ የሆነውን በሽታ አምጪ ተዋሲያንን የመከላከል አቅም በእርጥበት ምክንያት እንዲያጣ ስለሚያድርግ ሌላው የኢንፌክሽን መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል ።የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ ወደ ሀኪም በመሄድ ጸረ ባክቴርያ የሆኑ የጆሮ መድሀኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው።

👉👉 #የቆዳ #አለርጂ

📌 በጆሮዎ ውጨኛው ክፍል የሚገኘው ቆዳዎ በአለርጂ ምክንያት የማሳከክ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል። የመዋቢያ ቅባቶች ወይንም ቁሳቁሶች አለርጂን ሊይስከትሉ ይችላሉ ። የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ አለርጂው የተከሰተበትን ምክንያት ተከታትሎ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛም መጠቀም ማቆም ተገቢ ነው።

👉👉 #ጆሮን በሹል እና ጎጂ በሆኑነገሮች ማጽዳት

📌 ጆሮን በሹል እና ጎጂሊሆኑ በሚችሉ እንደ ጸጉር ማበጠሪያ ፣ የክብሪት እንጨት፣ ቁልፍ ፣ የእስኪብርቶ ክዳኖች በመሳሰሉት ማጽዳት የጆሮ ቆዳን ለመሰንጠቅ ስለሚችል ለኢንፌክሽን ይዳርጋል ከዚህም ባለፈ የጆሮን ውስጣዊ ክፍል በመጉዳት የመስማት ችሎታችንን ሊያሳጣን ይችላል።

@hellodoctor11


ብጉር | Acne vulgaris

◈ ብጉር በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቅ፤ ወዝ አመንጪ እጢዎች ተከማችተው በሚገኙባቸው የአካል ክፍሎች ላይ (ፊት ፣ ደረት ፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል) የሚወጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው።

◈ ብጉር ከጨቅላ ህጻናት ጀምሮ የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ከ12-25 የእድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ይታያል።

◈ ብጉር አብዛኛውን ጊዜ ወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከወጣትነት የእድሜ ክልል በኋላ (30 እና 40ዎቹ) የሚከሰተው የብጉር አይነት ግን በብዛት ሴቶች ላይ ይታያል።

➡ ለብጉር መከሰት አራት መሰረታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ናቸው

1- Follicular hyperkeratinization; ይህም የሞቱ ህዋሳት ተጠራቅመው የወዝ መተላለፊያ ቱቦ እንዲዘጋ ያደርጋል

2-የወዝ በብዛት መመረት (increased sebum production)

3-Propionibacterium acne የሚባለው የባክቴሪያ አይነት

4-ብግነት (Inflammation)

➡ ብጉርን እና ብጉር መሰል ሽፍታዎችን (Acneiform eruption) የሚያባብሱ ነገሮች

👉ጭንቀት (stress)
👉ከመጠን ያለፈ ውፍረት
👉በወር አበባ አካባቢ
👉የሚዋጡም ሆነ የሚቀቡ መድሀኒቶች (steroids, phenytoin...)
👉በስራ ሁኔታ የሚያጋጥሙ ኬሚካሎች

👉በቆዳችን ላይ በሚከሰተ መፈጋፈግ (friction) ወይም ጫና (pressure) ፤ ለምሳሌ በህመም ሆነ በሌላ ምክንያት ለረጅም ግዜ በጀርባው የሚተኛ ሰው ጀርባው ላይ ብጉር ሊወጣ ይችላል ወይም የጡት ማስያዣ ገመድ የሚያርፍባቸው ቦታዎች ላይ ሊወጣ ይችላል
👉 ለረዥም ሰአት የፊት ማስክ ማድረግ
👉በውስጣቸው comedogenic ingredients የያዙ የፊትና የጸጉር ቅባቶች

➡ ብጉር እንዴት ይታከማል?

✔️ ብጉር በአብዛኛው ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የቆዳ ህመም በመሆኑ በራሱ የሚጠፋውም ከእድሜ ጋር ተያይዞ ነው ፤ ስለዚህም ምልክቶቹን መቆጣጠር እንጅ በህክምና ማዳን (በአንድ ህክምና እስከ መጨረሻው እንዳይመጣ ማድረግ) አይቻልም።

በዚህም ምክንያት የብጉር ህክምና ወራትን የሚፈጅ በመሆኑ ታካሚዎች ከቆዳ ሐኪማቸው ጋር እየተመካከሩ ህክምናውን መከታተል ይኖርባቸዋል።

✔️ እዚህ ጋር ብጉር በራሱ ጊዜውን ጠብቆ የሚጠፋ ከሆን መታከም ለምን ያስፈልጋል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ፤ብጉር ከሚያሳድረው የስነ-ልቦና ጫና በተጨማሪ ሳይታከም በቆየ ቁጥር ፊታችን ላይ ጠባሳ የመፍጠር እድሉ የሰፋ ስለሆነ በጊዜ መታከሙ ይመከራል።

✔️ የብጉር ህክምና እንደ ጥንካሬው መጠን በሚቀባ ፣ በሚቀባና በሚዋጥ ወይም በሚዋጥ መድሀኒት ሊታከም ይችላል

✔️ ከዋናው ህክምና በተጨማሪ በውስጣቸው Salicylic acid, Benzyle peroxide የያዙ መታጠቢያ ሳሙናዎች መጠቀም ያስፈልጋል

➡ ከህክምናው በተጨማሪ ማድረግ የሚጠበቅብን

👉እንቅስቃሴ ማድረግ (ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳል)
👉ብጉሮቹን ለማፍረጥ አለመሞከር (ጠባሳ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ)
👉ለቆዳ ጤና መጠበቂያም ሆነ ለውበት የምንጠቀማቸው ምርቶች Oil-free & non-comedogenic መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉ፀሐይ መከላከያ (sun-screen) መጠቀም (መጠቀም ያለብን የፀሐይ መከላከያ እንደ ቆዳችን አይነት ስለሚለያይ የቆዳ ሐኪም ያማክሩ)
👉ቆዳችን ላይ ጫና (pressure) የሚፈጥሩ ነገሮችን (helmets, ስልክ, የቦርሳ/የጡት ማስያዣ ገመድ, የፊት ማስክ) መቀነስ
👉ሰውነታችንን ካላበን መታጠብ

✔️ በመጨረሻም ከቆዳ ሐኪም ውጪ የተሰሩ ቪድዮችን አይተን ወይም የቆዳ ሐኪም ሳናማክር መድሀኒቶችን ገዝተን ባለመጠቀም ቆዳችንን ከተጨማሪ ጉዳት እንከላከል‼️

ዶ/ር ዮሐንስ ታደሰ ፤ የቆዳና አባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት


Join us
@hellodoctor11


#6_አእምሮን_የሚጎዱ_ልማዶች

#አንደኛ ጨለማ ቤት ውስጥ ብዙ መቆየት። አንዳንዴ ወደ ውጪ ብቻህን ወጣ ብለህ 'ወክ' ማድረግ እና ተፈጥሮን ማድነቅ ያስፈልግሃል።

#ሁለተኛ ስለሀገርም ሆነ ስለማንኛውም ነገር አሉታዊ የሆነ ዜና ማንበብ፣ መስማት፣ ማየት... አእምሮህን የሚጎዳ ድርጊት ነው። ወዳጄ ሀገርህም፣ አህጉርህም፣ አለምህም እጅግ ሰፊ ነው። የራስህን ሰላም ካልፈለግክ፤ ይሄ ሁላ ህዝብ ባለበት፤ የሆነ ቦታ ብጥብጥ ሌላም ሌላም ነገር ሳይከሰት ውሎ አያድርም።

#ሶስተኛ ኤርፎን በሁለት ጆሮ ከቶ በከፍተኛ ድምጽ ዘፈን ሌላም ሌላም ነገር መስማት፤ ጤናማ አያደርግም። ሁሉም በመጠኑ... ከመጠን ያለፈና ሁሌም ተደጋግሞ የሚደረግ ነገር ሁሉ ጎጂ ነው!

#አራተኛ ከህብረተሰቡ የተገለለ መሆን። የብቻ ጊዜ ማሳለፍ ጥሩ ሁኖ ሳለ -ሙሉ ለሙሉ ከማህበረሰብ የተነጠለ መሆን አዋቂነትም አይደለም።

#አምስተኛ ስኳር ያለባቸውን ምግቦች መመገብ...

#ስድስት በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ። ሰውነትህ ለፍቶ ማረፍን ይፈልጋል። እንቅልፍ ባይወስድህ እንኳ አይንህን ጨፍነህ ማረፍ ይጠበቅብሃል።

Join
@hellodoctor11


✍️ #በባዶ #ሆዳችን #ልንመገባቸው #የማይገቡ #ምግቦች #ምን #እንደሆኑ #ያውቃሉ?

🔹 ብርቱካን እና ሎሚ፡- ከልክ ያለፈ የአሲድ መመንጨት ያስከትላል
🔹 ጣፋጭ ምግቦች (ቸኮሌት፣ ከረሜላ…)፡- ለስኳር በሽታ ይዳርጋሉ
🔹 ቲመቲም፡- የጨጓራ ቁስለትን ይፈጥራል
🔹 ዝኩኒ፡- የሆድ መነፋት፣ ቃር፣ የሆድ ጋዝ መብዛት ያስከትላል
🔹 እርጎ፡- በሆዳችን ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን ይገላል
🔹 ሙዝ፡- የልብ ችግር ያስከትላል
🔹 ለስላሳ መጠጦች፡- ስርአተ-ልመትን ያዛባል፡፡

Join
@hellodoctor11


✍️ #ህይወትህና #ብክነት!

•ምርጥ ሃሳቦች በአእምሮህ ዉስጥ እየመጡ በተግባር ካላዋልካቸዉ።
• እራስህን ከሌሎች ጋር የምታነጻጽር ከሆነ።
• የሚጠቅምህ ነገር ላይ ሳይሆን የማይጠቅምህ ላይ ጊዜህን ካቃጠልክ።
• ሰዎች ስለኔ ምን ያስቡ ይሆን ብለህ መጨነቅ ከጀመር።
• ትላንት ስላሳለፍከዉ ህይወት ሁሌ የሚቆጭህ ከሆነ።
• ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ።
• እቅድህ በጣም ከበዛ።
• ሰዉን ለመለወጥ ሁሌ የምትሞክር ከሆነ።
• ምንም የማይጠቅም ክርክር ዉስጥ እራስህን ካገኘህ።
• ለምትሰራዉ ነገር ደንታ ቢስ ከሆንክ ህይወትህን በጣም እያባከንከዉ ነዉና ንቃ!

#join
@hellodoctor11


የአጥንት ኢንፌክሽን (osteomyelitis) ምንድን ነው?

[በዶ/ር ቃልኪዳን አያሌው…የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት]

> ኦስቲኦሜይላይትስ አብዛኛውን ጊዜ የኢንፌክሽን ውጤት ሲሆን የአጥንት ሕብረ ሕዋስ መቆጣት ወይም እብጠትን ያስከትላል። የአጥንት ኢንፌክሽን በብዙ የተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ሲሆን በልጆችም ሆነ በአዋቂዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፡፡
> ኦስቲኦሜይላይትስ በባክቴሪያ የደም ሥር ኢንፌክሽን ምክንያት ሊከሰት ይችላል ፡፡ ይህ ዓይነቱ ኢንፌክሽን በሕፃናት እና በልጆች ላይ በጣም የተለመደ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ረጃጅም አጥንቶቻቸውን ያጠቃል ። ኦስቲኦሜይላይትስ በአዋቂዎች ላይ በሚከሰትበት ስአት ብዙውን ጊዜ በአከርካሪው አምድ በኩል የአከርካሪ አጥንትን ያጠቃል ፡፡
> ምንም እንኳን በተለያየ ባክቴሪያ ወይም የፈንገስ አካላት ምክንያት የሚከሰት ቢሆንም የደም ኢንፌክሽኑ ምንጭ ግን ብዙውን ጊዜ ስታፊሎኮከስ አውሩስ (staphylococcus aureus) የሚባል ባክቴሪያ ነው፡፡
> ኦስቲኦሜይላይትስ በተለያዩ ምክንያቶች እና በአቅራቢያ ካለው የሰውነት አካል ኢንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጣ ይችላል፡፡ ከነዚህም መካከል በድንገተኛ ጉዳት ፣ በተደጋጋሚ ከሚሰጡ የመድኃኒት መርፌዎች ፣ ከቀዶ ጥገና ጋር ተያይዞ ወይም በሰውነታችን ውሰጥ የተቀበረ ሰው ሰራሽ መሣሪያን ተከትሎ ሊከሰት ይችላል፡፡ በተጨማሪም በእግር ላይ ቁስለት ያላቸው የስኳር በሽታ ያለባቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ፡፡
> በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ ተሕዋስያን ወደ ተጎዳው አጥንት ለመግባት ቀጥተኛ መግቢያ በር ይኖራቸዋል ፡፡
> የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ግለሰቦች በኦስቲኦሜይላይትስ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ ነው ፡፡ እነዚህም የታመመ ሴል በሽታ ፡ኤች.አይ.ቪ (HIV) ፡እንደ ኬሞቴራፒ ወይም ስቴሮይድ ያሉ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳክሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎችን ያጠቃልላል፡፡
> ኦስቲኦሜይላይትስ እንደ ኢንፌክሽኑ ምንጭ ላይ በመመርኮዝ ድንገተኛ ክስተት ሊኖረው ይችላል ፣ ዘገምተኛ እና ቀላል ጅምር ወይም ሥር የሰደደ ችግር ሊሆን ይችላል፡፡

ኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ምንድ ናቸው?
> የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች እንደ መንስኤው እና እንደ በሽታው ይለያያሉ፡፡ የሚከተሉት በጣም የተለመዱ የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ናቸው; ሆኖም እያንዳንዱ ግለሰብ የሕመም ምልክቶችን በተለየ መንገድ ሊያጋጥመው ይችላል-
- ትኩሳት (ኦስቲኦሜይላይትስ እንደ ደም ኢንፌክሽን ውጤት ሲከሰት ትኩሳቱ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል)
- በተጎዳው አካባቢ ህመም ይኖረዋል
- ህመምን መግለጽ በማይችሉ ሕፃናት ላይ መነጫነጭ አና በቀላሉ መበሳጨት ይታያል
- የተጎዳው አካባቢ ላይ እብጠት ሊኖር ይችላል
- በተጎዳው አካባቢ ላይ መቅላት እና ሙቀት ሊኖረው ይችላል
- በተጎዳው አካባቢ አቅራቢያ የሚንቀሳቀሱ መገጣጠሚያዎች ማንቀሳቀስ ያስቸግራል
- ክብደት የመሸከም ወይም የመራመድ ችግር ሊኖረው ይችላል
- ማስነከሰ ሊኖር ይችላል
- የኦስቲኦሜይላይትስ ምልክቶች ከሌሎች የሕክምና ሁኔታዎች ወይም ችግሮች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፡፡ ለምርመራ ሁልጊዜ ዶክተርዎን ያማክሩ ፡፡

ለኦስቲኦሜይላይትስ በሽታ የሚደረግ ሕክምና
> ለኦስቲኦሜይላይትስ የሚደረግ ልዩ ሕክምና ከታች የተዘረዘሩትን በመመርኮዝ በዶክተርዎ ይወሰናል ፡፡
o የእርስዎ ዕድሜ ፣ አጠቃላይ የጤና እና የህክምና ታሪክ
o የበሽታው ስፋት
o ለተወሰኑ መድሃኒቶች, ቀዶ ጥገናዎች እና ህክምናዎች የመቻል አቅምዎ
o ለህክምናው ውጤት ያለዎት ግምት
o የእርስዎ አስተያየት ወይም ምርጫ
ለኦስቲኦሜይላይዝስ የሚደረግ ሕክምና ዓላማው ኢንፌክሽኑን ለመፈወስ እና ማንኛውንም የረጅም ጊዜ ውስብስብ ችግሮች ለመቀነስ ነው ፡፡ ሕክምናው የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል
o መድሃኒቶች መስጠት፡-በደም ስር ወይም ደግሞ በአፍ የሚወሰዱ መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ. ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ወይም የተመላላሽ ታካሚ መርሃግብር ሊሰጥ ይችላል፡፡ ህክምናው ለብዙ ሳምንታት ሊቆይ ይችላል፡፡
o ተከታታይ የራጅ እና የደም ምርመራዎች ቁጥጥር ይደረጋል
o የህመም ማስታገሻ ይሰጣል
o የአልጋ እረፍት (ወይም የተጎዳው አካባቢእንቅስቃሴ መቀነስ ) ያስፈልጋል
o ቀዶ ጥገና፡- አንዳንድ ጊዜ የተጠራቀሙ ፈሳሾችን/መግል ለማፍሰስ ወይም የተጎዱትን ሕብረ ሕዋሳት እና አጥንቶች ለማስወገድ የቀዶ ጥገና ህክምና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ፡፡

የኦስቲኦሜይላይትስ የረጅም ጊዜ ችግሮች
> ኦስቲኦሜይላይትስ የሚከተሉትን ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ለመከላከል የረጅም ጊዜ እንክብካቤን ይፈልጋል ፡፡እነዚህም፡-
- የተጎዳው አጥንት ስብራት
- በልጆች ላይ የተዳከመ እድገት (ኢንፌክሽኑ የእድገቱን ንጣፍ የሚነካ ከሆነ)
- በተጎዳው አካባቢ የጋንግሪን ኢንፌክሽን
- ኢንፌክሽኑ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል መሰራጨት
- ካንሰር ሊያመጣ ይችላል
የሕክምና ባለሙያየን መቼ ማናገር አለብኝ

#join

@hellodoctor11




Hello Doctor

#በመርፌ #የሚሰጥ #የወሊድ #የመከላከያ #ዘዴ (depo Provera)


በመርፌ የሚሰጥ የወሊድ የመከላከያ በየሶስት ወሩ በክርን የሚወጋ ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ ደም ስር በመግባት ፅንስን ይከላከላል። በውስጡ ፐሮጀስትሮን ሆርሞንን ይይዛል፡፡

#Depo #የሚሰራው #በሚከተለው #መንገድ #ነው:-


📌 እንቁላል ማኩረትን በማዘግየት(እንቁላሉ ከእንቁላል እጢ ሲወጣ)
📌 የማዕፀን በር(cervix ) ውስጥ የሚገኘውን ንፋጭ(የሚያጣብቅ ፈሳሽ) በማወፈር ነባዘር(የወንድ የዘር ፍሬ) ወደ ማሕፀን ውስጥ እንዳይገባ በመከልከል
📌የማሕፀን የውስጠኛው ሽፋን ላይ ለውጥ በማምጣት ፅንሱ እንዳይመቸው በማድረግ ነው።


#በመርፌ #የሚሰጥ #የወሊድ #የመከላከያ #ዘዴ (#depo #Provera) #ጠቀሜታዎች


📌 ልክ እነደ ወሊድ መከላከያ እንክብሎች ሁሌ መውሰድን አይጠይቅም
📌 ለሚያጠቡ እናቶች ተመራጭ ነው፣ለአንድ እናት ከወለደች ከ 6 ሳምንት ጀምሮ ሊሰጥ ይችላል፡፡
📌 የጡት ወተትን አይቀንስም፡፡
📌 በማጥባት ወቅት ያልተፈለገ ጽንስ እንዳይከሰት ይረዳል
📌 Estrogen(ኢስትሮጂን) ያለበትን የእርግዝና መከላከያ እንክበል መውሰድ ለማይችሉ

#የጎንዮሽ #ጉዳት፡-

📌 የወር አበባን ማዛባትና ማብዛት/ጠብታ ብቻ መታየት፡፡ ይህ ችግር በተለይ በመጀመሪያዎቹ ሶስት እና ስድስት ወራት የሚታይ ሲሆን እስከ 50 ፐርሰንት የሚደርሱ ሴቶች ደግሞ ይህን ዘዴ ለአንድ አመት ከተጠቀሙ የወርአበባ ዑደት ጭራሹኑ ላያዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን መከላከያዉን ካቋረጡ የወር አበባ ዑደታቸዉ የመጨረሻዉን መርፌ ከተወጉ በ6 ወራት ዉስጥ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል፡፡
📌 የክብደት መጨመር
📌 ራስ ምታት
📌 የሆድ ህመም
📌 ድብርት
📌 የድካም ስሜት እና የመሳሰሉት ሊከሰቱ ይችላል፣ ለጤና ግን አያሰጋም በመጀመሪያው ወራቶች ውስጥ ሊጠፉ ይችላሉ፡፡


#በመርፌ #የሚሰጥ #የወሊድ #የመከላከያ #ዘዴ (#depo #Provera) #መጠቀም #የሌለባቸው


📌 የጡት ካንሰር ህመም ካለ
📌 የጉበት በሽታ ካለ
📌 የአጥንት መሳሳት ችግር ካለ
📌 ከመጠን በላይ ክብደት ካለዎት፣
📌 በዘር የሚተላለፍ የደም መርጋት ችግር፣
📌 የስኳር ህመም፣
📌 ከፍተኛ የደም ግፊት፣
📌 ከፍተኛ የስብ ክምችት፣
📌 ከፍተኛ የሆነ ድብርት ካለ
📌 ለ ፕሮጀስትሮን (allergy) ከሆኑ


#join👇🏼

@hellodoctor11


ጥያቄ




❓eshi yena teyake betam lekes sew yemiyawefer kinin yenoral?

#ክብደት_ለመጨመር_የሚመከሩ_ምግቦች_ዝርዝር

ልከኛ የሰውነት መጠን ጥሩ ነው። ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ቅጥነት በሰውነታችን ላይ ችግር ያስከትላል። ከዛም ባለፈ ለድካም ፣ ለደም ማነስ እንዲሁም ለሀይል ማጣት ይዳርገናል፡፡

እነዚህ በሰውነታን ላይ ክንደት የሚጨምሩልን ምግቦች ናቸው፡፡

1. ጣፋጮች፦ እንደ ኬክ፣ ቸኮሌት፣ አይስክሬም ያሉ በስኳር እና በወተት የተሰሩ ምግቦችን መብላት ከመጠን ያለፈ ቅጥነትን ላላቸው ሰዎች የሚመከር ነው፡፡

2. ኦቾሎኒ፦ ኦቾሎኒ ጤናማ እና በቫይታሚን፣ ቅባት እና ፋይበር ሚኒራሎች የበለፀገ ነው፡፡ ለልብ ጤንነትም ከመጥቀሙ ባሻገር ተፈጥሮአዊ ዘይት ስላለው በፍጥነት ሰውነታችን ክብደት እንዲጨምሮ ያደረጋል፡፡

3. ጥራጥሬ፦ ቡናማ ሩዝ፣ ገብስ፣ አጃ እና ስንዴ ካርቦሀይድሬታቸው ከፍተኛው ስለሆነ ጡንቻዎቻችንን ይገነቡልናል፡፡

4. የእንስሳት ተዋጽኦ፦ ወተት፣ አይብ እና ቅቤ የካልሺየም ፕሮቲን እና ቅባት ስብስብ አላቻ፡፡ እነዚህም ተፈጥሮአዊ የክብደት መጨመሪያ መንገዶች ናቸው፡፡

5. የእንስሳት ቅባት፦ የእንስሳት ቅባት እንደ ጮማ እና ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ በፕሮቲን እና ካርቦሀይድሬት የበለጸጉ ናቸው፡፡ እነዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክብደት እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡

6. ሙዝ፦ ሙዝ ክብደት ለሚፈልጉ ሰዎች ሁነኛ መፍትሄ ነው። አንድ ትልቅ ሙዝ 120 ካሎሪ ሀይል ይይዛል። በተጨማሪም ፓታሺየም እና ሚኒራል ያካተተ ነው፡፡ የሙዝ እና ወተት ውህድ ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

7. የፍራፍሬዎች ጭማቂ፦ ፍራፍሬ ጤናማ ቫይታሚን ከመስጠቱን ባሻገር በአንድ ብርጭቆ 57 ካሎሪ እናገኝበታለን።

8. ስኳር ድንች፦ ድንች ጣፋጭም ሆነ የተለመደው በካርቦ ሀይድሬት የበለፀገ በመሆኑ የተስተካከለ ቅርፅ ለሚፈልጉ ሰዎች መፍትሄ ነው፡፡

9. እንቁላል፦ እንቁላል በካሎሪ፣ ሚኒራል፣ ፕሮቲን እና ቅባት የበለፀገ በመሆኑ፡፡ ክብደት ከመጨመር ባለፈ ለአዕምሮ እና አጠቃላይ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የምግብ ዝርዝሮች ሲጠቅሙ ከስፖርት ጋር ቢሆን ተመራጭ ይሆናል።

Join 👇🏼
@hellodoctor11










❓ህፃን ልጄ አንድ አንዴ የእራስ ቅሉ ይግላል።
እድሜ 6 ወር ነው። ምክያቱ ምንድነው?

#በልጆች~ላይ~ከፍተኛ~ሙቀት~(ትኩሳት)


በትናንሽ ልጆች ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት በጣም የተለመደ ነው. የሙቀት መጠኑ ብዙውን ጊዜ በ 3 ወይም 4 ቀናት ውስጥ ወደ መደበኛው ይመለሳል።

ከፍተኛ ሙቀት ምንድን ነው?

በህፃናት ያለው መደበኛ የሙቀት መጠን 36.4C ነው, ነገር ግን ይህ ከልጅ ወደ ልጅ ትንሽ ሊለያይ ይችላል.
ከፍተኛ ሙቀት 38C ወይም ከዚያ በላይ ነው.
ከፍተኛ ሙቀት እንደ ሳል እና ጉንፋን ያሉ ኢንፌክሽኖችን ለመዋጋት የሰውነት ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው።

ብዙ ነገሮች በልጆች ላይ ከፍተኛ ሙቀት ሊያስከትሉ ይችላሉ, ከተለመዱት የልጅነት በሽታዎች እንደ #ኩፍኝ እና #ቶንሲሊየስ, #ክትባቶች ነው


ልጅዎን ቤት ውስጥ መንከባከብ ይችላሉ. የሙቀት መጠኑ ከ 3 እስከ 4 ቀናት ውስጥ መቀነስ አለበት.

#ማድረግ-ያለቦ

✅ብዙ ፈሳሽ ስጧቸው

✅በቂ ምግብ ይስጧቸው

✅በሌሊት ልጅዎን በየጊዜው ሙቀቱን ያረጋግጡ

✅ቤት ውስጥ ያስቀምጧቸው



✅ስለልጅዎ የሚጨነቁ ከሆነ የህክምና ምክር ያግኙ

✅ከፍተኛ ሙቀት እስኪያገኝ ድረስ ልጅዎን እቤት ውስጥ ለማቆየት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ላለመገናኘት ይሞክሩ

#ማድረግ-የሌለቦ-ነገር

❌ልጅዎን ለማቀዝቀዝ ልብሶቹን አያወልቁ ወይም ርጥብ ስፖንጅ ያድርጉ, ከፍተኛ ሙቀት ለበሽታው ተፈጥሯዊ እና ጤናማ ምላሽ ነው

❌በጣም ብዙ ልብሶችን ወይም የአልጋ ልብሶችን አትሸፍናቸው

❌ከእድሜ ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት አስፕሪን አይስጡ

❌በዶክተር ካልተመከረ በስተቀር ibuprofen እና paracetamol አንድ ላይ አይስጡ

❌ከ 2 ወር በታች ለሆኑ ህጻናት ፓራሲታሞልን አይስጡ

❌ከ 3 ወር በታች ወይም ከ 5 ኪ.ግ በታች ለሆኑ ህጻናት ibuprofen አይስጡ
join👇🏼
@hellodoctor11


Hello Doctor

❓Hello selam nachu fit lay miweta bgurn endet matfat yechalal ken wedeken eyebeza ena getstayen eyabelashew slehone meftehe btsetugn des ylegnal❔


ጤና ይስጥልኝ ውድ የHello Doctor ተከታታዮቻችን እደምን አመሻችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁን እየተመኘን ለእናተ ይጠቅማል ብለን ያሰብንውን የኛን መረጃ እንሆ ይከታተሉን።

#ቡግር ምንድነው?

ቡግር በቆዳ ላይ የሚገኙ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች ሲሞሉ ወይም ሲደፈኑ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ ቡግር ነጭ ወይም ጥቁር አናት አንዳንዴም ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡
ነጠባጣቦቹ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፤ ህመም ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡
ብዙውን ጊዜ ቡግር በፊት ላይ ይወጣል፤ እንዲሁም በአንገት፣ ደረት፣ ትከሻ እና ጀርባም ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡
ቡግር በማንኛውም ሰው ላይ ሊታይ ይችላል፡፡
እንደሚስተዋለው ከሆነ ግን ቡግር በጉርምስና ወይም በወጣትነት እድሜ ውስጥ ያሉት ላይ ይበረታል፡፡
በዚሕ ጊዜ የመጣ ከሆነ እድሜ በጨመረ ቁጥር እንዲቀንስ ይጠበቃል፤ ጥቂቶች ላይ ግን አብሮአቸው ይኖራል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዳንድ ጊዜ ቡግር በሆርሞን ችግር ምክንያት ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፡፡
በእርግዝናም ወቅት የመከሰት እድል አለው፡፡

#ምልክቶቹ_ምንድናቸው?

· ነጭ አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
· ጥቁር አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
· ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች
· ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች
· ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች
· ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች

#ቡግር በምን ምንክንያት ይመጣል?

- ለቡግር መከሰት ዋና ዋና የሚባሉት ምክንያቶች፤
- ቅባትማ የቆዳ አይነት
- የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ ሴሎች መዘጋት
- ባክቴሪያዎች
- የአንዳንድ ሆርሞኖች ስራ መጨመር (ለምሳሌ Androgen)
ከላይ እነደጠቀስነው ብጉር ቅባት አመንጪ እጢዎች (Sebaceous gland) በሚበዙበት የቆዳ ክፍል አካባቢ ነው፡፡
እነዚህም ፊት፣ ግንባር፣ ደረት፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል እና ትከሻን ያጠቃልላል፡፡
የፀጉር ቀዳዳዎች ከቅባት አመንጪ እጢዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
የእነዚህ ቀዳዳዎች ግርግዳ ሲያብጡ ነጣ ያለ አናት ይኖራቸዋል፤ ወይም ደግሞ አናታቸው ክፍት ከሆነ ሲጠቁር ይችላል፡፡
በዚህ ጊዜ ቀዳዳዎቹ በባክቴሪያ እና ቅባት ይሞላሉ፡፡
ቀያይ ከፍ ከፍ ያሉ ውስጣቸው ነጭ የሆኑ ነጠብጣቦች የሚፈጠሩት ደግሞ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት ከመዘጋታቸው በላይ በባክቴሪያ ሲጠቁ ነው፡፡

#ቡግርን ምን ሊያባብሰው ይችላል?

· የሆርሞን መለዋወጥ ወይም መዛባት
· አንዳንድ መድሐኒቶች
· አመጋገብ (የተጠበሱ ምግቦች፣ በካርቦሀይድሬት የበለፀጉ ምግቦች)
· ጭንቀት ወይም ውጥረት
· ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም
· የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሚያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ከሆነ

#ተጋላጭነት

- የጉርምስና የእድሜ ክልል
- የሆርሞን መዛባት
- የዘር ተጋላጭነት
- ቀባትማ ነገሮችን በቆዳ ላ መጠቀም
- ቆዳን የሚፈገፍጉ (የሚፈትጉ) ነገሮች
- ጭንቀት

#ቡግርን መከላከል ይቻላል?

ቡግርን በዘላቂነት መከላከል ባይቻልም እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች ግን አሉ።

ከነዚህም መካከል ፦

· በዝግታ ወይም በጣም ሳያሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም።
· በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ።
· ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ
· ጭንቀትን አለማብዛት
· አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም፤ እንደ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት
· ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ
· ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም፤ በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው ከሆነ
· ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ ለምሳሌ እንደ ፔትሮሊየም ያሉትን

#ሀኪም ጋር መቼ መሄድ አለቦት?

በቤት ውስጥ ማድረግ የሚመከሩ መንገዶች የማይሰሩ ከሆነ የቆዳ ሀኪሞት ጠንከር ያሉ መድሐኒቶችን ያዝሎታል፡፡
ሴቶች ላይ ቡግር ለብዙ አመታት ሊቆይ ይችላል፤ በአባዛኛው የወር አበባ ከመምጣቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ይመለሳል፡፡ እንዲህ አይነቱ ቡግር ብዙውን ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱ ሴቶች ላይ በራሱ ይጠፋል፡፡
አዋቂዎች ላይ በድንገት የሚወጣ፣ በፍጥነት የሚበዛ ቡግር ተጓዳኝ የጤና እክልን ሊያመላክት ስለሚችል ምርመራዎች መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡

Hello Doctor

ለወዳጆ ያጋሩ

Join 👇

@Hellodoctor11👩‍⚕
@Hellodoctor11👩‍⚕
@Hellodoctor11

Показано 20 последних публикаций.

721

подписчиков
Статистика канала
Популярное в канале