ሰላም!
ከላይ ባለፈው ያጫወትኩዋቹን የMark Douglasን
Trading in the Zone የተሰኘ የTrading Psychology መጽሐፍ አያይዤላቹሀለው::
ባለፈው በነገርኩዋቹ መሰረት ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ይህን መጽሐፍ የማንበብ Challenge ይኖረናል:: ይህን Challenge ሁላችሁም እንድትሳተፉ አበረታታለው:: የእውነት ይህን መጽሐፍ ማንበብ ከፈለግን ምንም አይነት ሰበብ ያስቀረናል ብዬ አላስብም::
ብዙዎቻቹ ያነሳቹልኝ ምክንያት "
English በደንብ አልችልም" ነው:: ግን ይህ መጽሐፍ የተለየ የእንግሊዝኛ እውቀት አይጠይቅም:: Trading ላይ ያለን ነገር ከተረዳቹ ይህን መጽሐፍ አንብቦ መረዳት ያን ያክል ከባድ አይሆንም:: ምናልባት የሚከብዱ ቃላቶች ካሉ Translate እያረቹ በደንብ ለመረዳት ሞክሩ::
ሁለተኛው የሚነሳልኝ ምክንያት ደግሞ "
ጊዜ የለኝም" ነው:: ይህ መጽሐፍ ምንሸመድደው መጽሐፍ አይደለም:: ይህ መጽሐፍ ደግመን ደጋግመን በማንበብ ውስጣችን እንዲቀር ምናደርገው መጽሐፍ ነው ስለዚህ ለፈተና እንደምናነበው መጽሐፍ በጣም ተጨናንቀን እናነበውም:: በማንኛውም ቦታ ትንሽ ደቂቃ ስናገኝ ማንበብ እንችላለን - ታክሲ ውስጥ, ካፌ ውስጥ, Trade እያደረግን ብቻ ትንሽ ክፍተት ባገኘንበት ሰዓት ስልካችንን አውጥተን የተወሰነ ለማንበብ እንሞክር የዛኔ ሳናስበው ራሳችንን የመጽሐፉ የመጨረሻ ገጽ ላይ እናገኘዋለን😁:: እንዲህ ሲሆን ምንም ጥልቅ የሆነ የማንበብ ፍቅር ራሱ አያስፈልገንም::
ስለዚህ ምንም አይነት ምክንያት ብትሰጡኝ አልሰማሁም:: ማንበብ ከፈለግን እናነበዋለን::
ስለዚህ Challengeአንች:
1. ይህ መጽሐፍ ወደ 200 ገጽ አለው እኛም Challangeኡን ለማቅለል
በሳምንት ከ60 - 70 ገጽ እናነባለን::
2. አንብበን ብቻ አናበቃም ከቻልን አንድ አፍታ የተረዳነውን ትንሽ ነገር እንጽፋለን:: ካልቻልን ደግመን ደጋግመን ያነበብነውን እናስባለን::
3. ሳናነብ ምንውልበት ቀን አይኖርም አንድም ገጽ ቢሆን እናነባለን::
ቻሌንጃችን ይሄ ነው:: ከነገ እንጀምራለን እንዲሁም የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ ላይ ሁላችንም መጨረስ ይኖርብናል:: እኔም በየጊዜው Summarize አደርግላቹሀለው:: ይህን መጽሐፍ አንብባቹ ለምትጨርሱ የሆነ ነገር አመቻችተን Giveaway ይኖራል::😊
ለሁላችሁም መልካም የንባብ ጊዜ እመኛለሁ!!
@ICT_Yohannes 🤑