Фильтр публикаций


ለመ/ራን በሙሉ
ውጤት ትንተና ያላስገባችሁ መ/ራን ነገ ማክሰኞ 04/6/2017 ዓ.ም 8:00 ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ


ሰላም ቤተሰብ!!!
ኢዩኤል ተገኝቷል።


የት/ቤታችን 12ኛ F ክፍል ተማሪ ኢዩኤል ዮናስ አርብ በ23/5/2017 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቱ እንደወጣ አልተመለሠም። ያለበትን ያያችሁ ወይም የሰማችሁ 0908138442 መረጃ እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ት/ቤቱ እና ቤተሰቦቹ


የ2017 ዓ.ም 1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና በሰላም ተጠናቋል።
ይህ የፈተና ጊዜ በሰላም እንዲጠናቀቅ እና የኩረጃን ባህልን ለመቀነስ ከጎናችን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን!!!!!








የማጠቃለያ ፈተና ፈረቃ


15/5/2017
ለት/ቤታችን ተማሪወች በሙሉ
ከ16-23/05/2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጠዉ የአንደኛዉ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የጠዋት ፈረቃ ስትሆኑ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የከሰአት ፈረቃ መሆናችሁን ት/ቤቱ ያሳዉቃል፡፡
ት/ቤቱ




🆕እንግሊዝኛ ቋንቋ ማሳደጊያ ፖርታል ጥቆማ
👉🏼የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ተማሪዎችን እንግሊዘኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያግዝ ፖርታል አዘጋጅቷል፡፡ 
🤏🏼ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ጀምሮ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጁ ሁኔታና አውድን ያገነዘቡ እያዝናኑ የሚያስተሩ ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ  በድምጽ በጽሁፍና በምስል የተቀናበሩና የእንግሊዝኛ ቋንቋን የሚያሻሽሉ መረጃዎች ለማግኘት ያስችላል።
🫴🏼ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት ማብራት የሚያስፈልግ ቢሆንም  ኢንተርኔቱ ገንዘብ የማይቆርጥ ሲሆን  በስማርት ስልክ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌትና በኮምፒውተር በማንኛውም ብሮዘር መጠቀም ይቻላል፡፡
🫳🏼ፖርታሉን https://elearn-english.moe.gov.et በመንካት መክፈትና መጠቀም ይችላል፡፡


👎👎👎👎👎👎
#አስቸኳይ #ማሳሰቢያ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤

#ለጥር 01 #2017 ዓ.ም አዳጊ #መምህርራን ።
🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷
#የቆይታ ጊዜ ደረጃ እድገት እየሰራን መሆኑ ይታወቃል በመሆኑም ከላይ ስማችሁ የተገለፀው መ/ራን #PGDT መረጃ ከማህደር ላይ ያላያያዛችሁና #ስልጠና ጀምራችሁ ያላጠናቀቃችሁ #PGDT ወይም ስልጠና የጀመራችሁበትን ማስረጃ እስከ 08/05 /2017ዓ.ም  11:00 ድረስ መም/ትም/አመ/ልቡ/ ቢሮ ቁጥር  3 ድረስ እየመጣችሁ እንድታቀርቡ እያሳሰብን በተገለፀው የጊዜ ገደብ መረጃው ካልቀረበ ግን የደረጃ እድገት የማይሰራላችሁ መሆኑን  እናሳስባለን ።

#የመ/ትም/አመ/ል/ቡድን
     👆👆👆👆👆👆👆👆


6/5/2017
ለት/ቤታችን መምህራን በሙሉ

የጡረታ መለያ ቁጥር እና ቋሚ ቅጥር የሌላችሁ የት/ቤታችን መምህራን ከጥር1-ጥር 30/2017ዓ.ም ድረስ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ እና የሚባዙ ቅፃችን በማባዛት ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በመገኘት የጡረታ መለያ ቁጥር እና ቋሚ ቅጥር እንዲሰጣችሁ ትምህርት መምሪያዉ በአክብሮት ያሳስባል፡፡
ት/ቤቱ


Репост из: Amhara Education Bureau
በተማሪዎች የመማሪያ መጸሃፍት በመጀመሪያ ገጽ ላይ የተጻፈውን የተማሪዎችን የመጸሃፍ አያያዝ የጥንቃቄ መልዕክት ተመልክተው ያውቁ ይሆን? ይህ የጥንቃቄ መልዕክት ተግባራዊ እንዲሆንና በከፍተኛ ወጭ የታተሙ መጸሃፍት ለቀጣዩ ትውልድ ይሸጋገሩ ዘንድ ምንድጋፍ አድርገዋል? በመጸሃፍት አያያዝ ዙሪያ ያለወትን ተሞክሮና ትዝብት ያካፍሉን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ተማሪዎች! ይህን የተማሪ መጽሐፍ በጥንቃቄ ያዙ!
ይህ መማሪያ መጽሐፍ በቀጣይ ዓመት የናንተ ወንድሞችና እህቶች የሚማሩበት የትምህርትቤታችሁ ንብረት ነው! መጽሐፉ እንዳይበላሽ ወይም እንዳይጠፋ በጣም መጠንቀቅ አለባችሁ። መጽሐፉን በጥንቃቄ ለመያዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች ተግባራዊ አድርጉ፤
1. መጽሐፉን ከጉዳት ለመከላከል በላስቲክና በአሮጌ ጋዜጣ ወይም በካኪ ወረቀት ሸፍኑ፤
2. መጽሐፉን ሁልጊዜ ደረቅና ንጹህ በሆነ ቦታ አስቀምጡት፤
3. መጽሐፉን ለመጠቀም ስትዘጋጁ በቅድሚያ እጃችሁ እርጥበት የሌለውና ንጹህ መሆኑን አረጋግጡ፤
4. በመጽሐፉ ሽፋን ወይም የውስጥ ገጾች ላይ አትጻፉ፤
5. መጽሐፉን እያነበባችሁ እያላችሁ ንባባችሁን አቋርጣችሁ እንደገና ለማንበብ ስትፈልጉ ምልክት ማድረጊያ ብጣሽ ወረቀት ወይም ካርድ ተጠቀሙ፤
6. በመጽሐፉ ውስጥ ያሉ ሥዕሎችን ወይም ገጾችን አትቅደዱ፤
7. በመጽሐፉ ውስጥ የተቀደደ ወይም የተገነጠለ ገጽ ሲኖር በሙጫ ወይም በሌላ ንጹህ ማጣበቂያ ጠግኑት፤
8. መጽሐፉን ከቦርሳችሁ ስታስገቡ ወይም ስታወጡ ጥንቃቄ አድርጉ፤
9. መጽሐፉን ለሌላ ሰው ስታቀብሉም ሆነ ከሌላ ሰው ስትቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ። ደህንነቱን አረጋግጣችሁ ተቀበሉ።
10. መጽሐፉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትቀበሉ ሽፋኖቹና ገጾቹ እንዳይገነጣጠሉ መጽሐፉን በጀርባው ጋደም አድርጋችሁ አስቀምጡት፤ ከዚያም ጥቂት ገጾችን ቀስ እያላችሁ በየተራ ግለጡ፤ በግራና በቀኝ እጃችሁ የያዛችሁትን የመጽሐፉን ክፍል በኃይል አትጫኑት (አትመንጭቁት)።
ማሳሰቢያ፤ እነዚህ መመሪያዎች ሳይተገበሩ ቀርተው በመጽሐፉ ላይ አንዳች ጉዳት ከደረሰ በወጣው ሕግ መሠረት ተጠያቂ ያደርጋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ




21/04/2017

ለት/ቤታችን መምህራን በሙሉ

ከጥር 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ እድገት የምታገኙ መምህራን ለመጨረሻ ጊዜ የደረጃ እድገት ያገኛችሁበትን ደብዳቤ እና የሶስት ሴሚስተር ስራ አፈጻጸም እንዲሁም ተሙማ የሰራችሁበትን መረጃ በመያዝ እስከ 22/04/2017ዓ.ም ድረስ ምክትል ር/መምህር ቢሮ ሪፖርት እንድታደርጉ እና የደረጃ እድገት እንዲሰራላችሁ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡


ግልባጭ

-ለት/ቤቱ መምህራን ማህበር

ት/ቤቱ


Репост из: Mado Clinic ማዶ ክሊኒክ
ኮምቦልቻ ሀይስኩል ት/ት ቤት

ማዶ መካከለኛ ክሊኒክ የኮምቦልቻ ሀይስኩል ት/ት ቤት ባፈራቻቸውና አልፎም በሀገሪቱ ታላላቅ የህክምና ተቋማት በሆኑት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና አይደር ሆስፒታል/መቀሌ/ ዉጤት በሆኑ በተጨማሪም በደሴ ሆስፒታል፣ በባቲ ሆስፒታልና ከሚሴ ሆስፒታል ከፍተኛ ልምድ ባፈሩት በእኒሁ ሀኪሞች በቅርቡ በኮምቦልቻ የተቋቋመ የጤና ተቋም ነዉ። ታዳ እስካሁን ለመጣንበት ጉዞ ያገዙንን ማመስገንና ማገዝ ባህልና ወጋችን ለወደፊትም ተባብሮ ዉጤት ለማምጣት ስንቅ እንደሆነ በማሰብ የኮምቦልቻ ሀይስኩል ት/ት ቤት አስተማሪዎች እና አስተዳደር ትዉልድን ለማፍራት የሚያደርጉትን ስራ ማበረታቻ እና ምስጋናም ይሆን ዘንድ ባለን የህክምና ሙያ በት/ት ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት በስፔሻሊስት ሀኪም የነጻ የህክምና ቼካፕ እና ማማከር አገልግሎት እንዲሁም ተማሪዎች በርትተው እንዲማሩ በሰልፉ ላይ አነቃቅተናል። በቀጣይም ተማሪዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ይህም የጤና ተማሪዎች በማእካላችን የተግባር ልምድና ስልጠና እንዲያገኙ ከት/ት ቤቱ ጋር እቅድ ነድፈናል።

ቪድዮ: https://vm.tiktok.com/ZMkB68NNx/

@madoclinic

#Kombolcha #wollo #ኮምቦልቻ #ወሎ


እናመሰግናለን ውድ ልጆቻችን!!!!

Показано 18 последних публикаций.