ZENA LIVERPOOL


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Спорт


እንኳን ወደ ዜና ሊቨርፑል ቻናል በሰላም መጣችሁ◦
____________________________________

➠የክለባችን የዝውውር መረጃዎች.
➠የክለባችን የእያንዳንዱ ጨዋታ በቀጥታ.
➠የተለያዩ የክለባችን ትንታኔዎች.
➠የተጫዋቾች ግለ ታሪክ ሌሎችም...

༆ ለ አስታየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ @virgil_vandik

| ❷⓪❷❹| ዜና ሊቨርፑል ቻናል !

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Спорт
Статистика
Фильтр публикаций


🚨ጊዜው የዝውውር ነው።

ዛሬ ጠዋት የተደረጉ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች ለመመልከት የትም ሳሄዱ #TRANSFERNEWS የሚለውን መንካት በቂ ነው።👇




የእንግሊዝ አሰላለፍ ! 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

04:00 | እንግሊዝ ከ ስሎቬኒያ

ልክ እንደ ተጠበቀው ኮነር ጋላገር የአሌክሳንደር አርኖልድን ቦታ ተክቶ በመሀል ሜዳ ላይ የሚጫወት ይሆናል።በዚህም መሰረት አሌክሳንደር አርኖልድ እና ጆ ጎሜዝ ጨዋታውን ከተጠባባቂ ወንበር በመነሳት የሚያከናውኑ ይሆናል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀዉ የኔዘርላንድ እና የኦስትሪያ ጨዋታ የክለባችን ተጫዋቾች ኮዲ ጋክፖ እና ቨርጅል ቫንዳይክ ለሀገራቸዉ ኔዘርላንድ ሙሉ 90 ደቂቃ መጫወት ሲችሉ ርያን ግራቨንበርክ ዛሬም ምንም ደቂቃ ሳይጫወት ቀርቷል።

ጋክፖ ለሀገሩ ግብ ቢያስቆጥርም ኔዘርላንድ 3-2 መሸነፏን ተከትሎ ምድቧን በ3ኝነት በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል የሌሎች ሀገራትን ዉጤት የመጠበቅ ግዴታ ዉስጥ ገብታለች ! 🇳🇱

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


በአንፊልድ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ምሽቶችን መመልከት የናፈቀው😍🔥

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ሊቨርፑል በርከት ያሉ የተከላካይ አማራጮችን እየተከታተለ ቢሆንም በአሁኑ ሰአት የመሀል ተከላካይ ማስፈረም አስፈላጊ እንዳልሆነ አስረግጠው ተናግረዋል። በመጪው የዝውውር መስኮት የክለቡ መሪዎች ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ 6 ቁጥር አማካይ መግዛት ነው።

[ ጄምስ ፒርስ ]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ሉዊስ ዲያዝ እና ካኦሚኔህ ኬህለር በሊቨርፑል የአርኔ ስሎት ስኳድ ቡድን ይሆናሉ። ተጫዋቾቹ ሊሸጡ የሚችሉት ከ50 ሚሊዮን ፓውንድ እና 25 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ባለው ዋጋ ጥያቄ ከቀረበላቸው ነው።

[ ጄምስ ፒርስ ]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


እንዲሁም በተመሳሳይ 1:00 ላይ ፈረንሳይ ፖላንድን የትምትገጥምበትን አሰላለፍ ይፋ ስታደርግ የክለባችን ተጫዋችን የሆነው ኢብራሂማ ኮናቴ ጨዋታውን ከተጠባባቂ ወንበር በመነሳት የሚጀምር ይሆናል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


1:00 ላይ ኔዘርላንድ ኦስትሪያን የምትገጥምብትን አሰላለፍ ይፋ ስታደርግ የክለባችን ተጫዋች የሆኑት ቨርጂል ቫንዳይክ እና ኮዲ ጋክፖ በቋሚነት የሚጀምሩ ሲሆን በአንፃሩ ሪያን ግራንቭበርች ከተጠባባቂ ወንበር በመነሳት የሚጫወት ይሆናል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ዋታሩ ኤንዶ በፓሪስ ኦሎምፒክ የጃፓን ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሊቨርፑል በቅድመ ውድድሩ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ የማይገኝ ይሆናል። እንዲሁም የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ሞሃመድ ሳላህን በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ቡድናቸው ውስጥ ለማሰለፍ ጓጉቷል።

[ዴቪድ ሊንች]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


በአሰልጣኝ ጋሬዝ ሳውዝጌት የምትመራው እንግሊዝ ዛሬ ከስሎቬኒያ ጋር ለምታደርገው ጨዋታ በመሀል ሜዳው ላይ ከአሌክሳንደር አርኖልድ ይልቅ ኮነር ጋላገርን ልትጠቀም ትችላለች።

[ ROB DORSETT ]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


ሊቨርፑል ስፔናዊውን የአትሌቲክ ቢልባኦ የመስመር አጥቂ ኒኮ ዊልያምስን በዚህ ክረምት ለማስፈረም ሀሳብ ውስጥ አይደለም።

[ JAMES PEARCE 🥈]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


ላይፕዚግ በአሁኑ ሰአት ታይለር ሞርተንን ለማስፈረም ፉክክሩን እየመራ ነው ነገርግን ከሳውዝሃምፕተን ፣ኢፕስዊች ታውን ፣ቦርንማውዝ እና አታላንታ ጋር መወዳደር አለበት። ሊቨርፑል ወጣቱ አማካዩን ለመሸጥ 20 ሚሊየን ፓውንድ ይፈልጋሉ።

[ሌዊስ ስቲል]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


OFFICIAL✅

ክለባችን ሊቨርፑል ከJAPAN AIRLINES ጋር አዲስ የወዳጅነት ስምምነት ተፈራርሟል !

በዚህ ስምምነት ላይ ክለባችን ወደ የትኛውም ስፍራ ተጫዋቾችን ይዞ ሲሄድ የጃፓኑ ኤርላይን ይዞ ይጓዛል ፤ ስምምነቱም ለአንድ አመት የሚቆይ ይሆናል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


ኮስታስ ሲሚካስ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን ቢለቅ ብዙም አያስደንቅም ነገርግን ግሪካዊው ተከላካይ ሊለቅ የሚችለው ሊቨርፑል ለእሱ ተስማሚ የሆነ ጥያቄ ሲያገኝ ነው። ሊቨርፑል ሲሚካስ እንዲለቅ አያስገድደውም ተጫዋቹ ራሱ በሁኔታው ከተስማማ እና የመጀመሪያ ምርጫ በክለቡ መሆን ከሆነ በሊቨርፑል መቆየት ይችላል።

[ሌዊስ ስቲል]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


📆 ከዛሬ አራት አመት በፊት ልክ በዛሬዋ እለት ነበር ክለባችን ሊቨርፑል ከ30 አመት ቆይታ በኃላ የ19ነኛ የፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ከፍ ማድረግ የቻለው።🥳🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿🏆

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club


ሊቨርፑል ናቲ ፊሊፕስን በ8 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ ለመሸጥ ገምግሟል። ፊሊፕስን ከሚከታተሉት ቡድኖች መካከል አዲስ የፕሪሚየር ሊግ አዳጊ የሆነው ኢፕስዊች ታውን እንግሊዛዊውን ተከላካይ ማስፈረም ይፈልጋል።

[ሌዊስ ስቲል]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ሪካርዶ ካላፊዮሪ ሊለቅ የሚችልበት አጋጣሚ ከሆነ ቦሎኛ ጣሊያናዊውን ተከላካይ ለመተካት የክለባችንን ተጫዋች [ በውሰት ለሌላ ክለብ የሚጫወተውን ] ሴፕ ቫንዴንበርግን የማስፈረም ፍላጎት አለው።

[ሌዊስ ስቲል]

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ዛሬ ሀገራቸውን ወክለው ጨዋታ የሚጫወቱ ተጫዋቾቻችን :-

1:00 | 🇫🇷 ፈረንሳይ ከ ፖላንድ 🇵🇱
            ° ኮናቴ

1:00 | 🇳🇱 ኔዘርላንድ ከ ኦስትሪያ 🇦🇹
            ° ቨርጂል
            ° ጋክፖ
            ° ግራንቭበርች

4:00 | 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 እንግሊዝ ከ ስሎቬኒያ 🇸🇮
           ° ትሬንት
           ° ጎሜዝ

መልካም ዕድል ለሁላችሁም ! ❤

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club


ሌሊት ላይ ሀገራቸዉን ወክለዉ ጨዋታ ያደረጉ የክለባችን ተጫዋቾች :-

የሉዊስ ዲያዝ ሀገር የሆነችው ኮሎምቢያ ፓራጓይን 2-1 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ልጃችን ዲያዝ ለሀገሩ ድንቅ የሚባል እንቅሰቃሴን አስመልክቷል።

የአሊሰን ቤከር ሀገር የሆነችው ብራዚል ከኮስታሪካ ጋር 0-0 መለያየት ስትችል ልጃችን አሊሰን ክሊንሺት በማስመዝገብ  ሙሉ ደቂቃን መጫወት ችሏል።

𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚|| @zena_Liverpool_club
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚||
@zena_Liverpool_club

Показано 20 последних публикаций.