ልሣነ አምሐራ ሚዲያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ።
ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций








ምዕራብ ጎጃም ከቡሬ ከተማ ወጣ ብሎ ደረቋ ላይ ሀይለኛ ጦርነት በመካሄድ ላይ ሲሆን ከቡሬ ከተማ ታንክ እዬሄደ ይገኛል አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መረጃው በአስቸኳይ ይዛመት።


የጣናው መብረቅ ብርጌድ ከባህር ዳር አፍጫ ስር በምትገኘው መሸንቲ ከተማ ውስጥ ትናትን 8 ሰአት ላይ የተሰካ ኦፕሬሽን ሰርቷል::




🔥🔥የዞዝ አምባ ንጉስ ክ/ጦር አስደናቂ የደፈጣ ኦፕሬሽን🔥🔥

👉የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ የዞዝ አምባ ንጉሥ ክ/ጦር ትንታጎች ጥር 01/2017 ዓ.ም በሁለት ግንባሮች በተጠና ደፈጣ ወራሪ ሠራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

👉 የመጀመሪያ ግንባር ከእብናት በአራት ኦራል ተጭኖ ቋሊሳን ለመያዝ የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊት ልዩ ቦታው ገላ ማጠቢያ የተባለ ቦታ ላይ ደፈጣ የጣሉት የዞዝ አምባ ንጉሥ ክ/ጦር፣ ተከዜ ግንባር ናደው ብርጌድ ባለ ልዩ ተልዕኮ መብረቆች አማካይነት በተወሰደ መብረቃዊ ጥቃት በርካታ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ፈርጥጦ ወደ እብናት ገብቷል።

👉 ሁለተኛው  ግንባር በተመሳሳይ ከእብናት በአራት ኦራል ተጭኖ ቆላ መልዛ ኒቋራ ከተማን ለመያዝ የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊት በሌላኛዋ አግኝቸው ቢተዋ ብርጌድ በተጣለ ደፈጣ ከ20 በላይና በርካታ ቁስለኛውን እያዝረከረከ ፈርጥጦ እንደለመደው እብናት ከተማ ገብቷል።

     ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ


ወሎ ቤተ አምራ ውስጥ አስደናቂ ድል ተመዘገበ:-

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል::
-
ትናንት ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓመተ ምህረት ከወረዳው መቀመጫ ማሻ ከተማ ወደ ኮሬብ በሲኖትራክ ሲንቀሳቀስ የነበረ አድማ ብተና ላይ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት ሲኖትራኩ ላይ ያሉት አድማ ብተናዎችን እሳት በልቷቸዋል::
-
ደምወዝ ተቀብለው ሲገሰግሱ ድስም የምትባል ቦታ ላይ ነው ጭዳ የተደረጉት:: የአማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ፋኖ ሙሀመድ አሊ (ጭንቅየለሽ) እና የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ በለጠ ምትክ (ድሮን) በመሩት በዚህ ኦፕሬሽን አስደናቂ ድል ሊመዘገብ መቻሉን የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ አስታውቋል::
-
በዚሁ በመቅደላ ወረዳ ውስጥ ታህሳስ 28 ቀን አቶ ኢብራሂም የተባለ ግለሰብ ከኮሬብ ወደ ማሻ ከተማ የቤተሰቡን እና የጎረቤቹን የሴፍቲኔት ገንዘብ ለመቀበል እንደመጣ መነሀሪያ ፊት ለፊት ህይወቱን በግፍ ተነጥቋል::

ይህ ግለሰብ ከፋኖ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው ሲሆን ከዚህ ቀደምም አንድ የባጃጅ ሾፌርን ሙዚቃ ለምን ከፈትክ ብለው ህይወቱን ተነጥቋል ተብሏል::

ጥምር ጦሩ በንፁሀን ላይ አሰቃቂ ግፍ መፈፀሙን ቀጥሏል ያለው ፋኖ ቃለአብ ይህን ግፍ የሚፈፅም ጠላት ጋር ንግግር ስለሌለን በምክክር ኮሚሽን ስም ደሴ ተሰባስቦ የሚመክር አካል ወደ እኛ ቢመጣ ቅጣታችን የከበደ እና እስከ ሞት የሚደርስ ነው ብሏል::




ፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው የአማራ ፋኖ በጎጃም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ስራ አስፈፃሚ አባል በመሆን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና ሀላፊ በመሆን ተሹሟል!


ሰበር~ የድል ዜና

ጣርማበር፣ ደብረሲና ፣ ሸዋሮቢትና ራሳ !!

ሳምንት ያስቆጠረው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተጋድሎ

ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም

ከሳምንት በላይ በሸዋ ወደ ራሳ ያለ የሌለ ሀይሉን ለቃቅሞ ወደ ራሳ ለመግባት የሞከረው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት መውጫ ጠፍቶት በራሳ ሸለቆዎች ላይ እየረገፈ ይገኛል። በረሃብና በውሃ ጥም የተዝለፈለፈው ወራሪው ሴት ደፋሪ የአብይ አህመድ ስልጣን ጠባቂ ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ አልሞ ተኳሾቹ ቀዬ ዘው ብሎ ገብቶ መውጫ ጠፍቶት እየተገረፈ ይገኛል።

ድሽቃን እንደክላሽ የሚተኩሱት የመከታው ማሞ ልጆች ዛሬ አድማሱን ባሰፋው አውደ ውጊያ በጣርማበር ፣ደብረሲና ሾላሜዳ ላይ በሞርተር የታገዘ ትልቅ ትንቅንቅ እያደረጉ ይገኛሉ። አርበኛ ስንታየሁ ማሞ(ራንቦ) ክፍለጦር ፤ማንበግር ንጉስ ሻለቃ ከደብረሲና ጣርማበርና ሻላሜዳ የጠላትን ሀይል እየገረፈችው ትገኛለች። በተጨማሪ የአፄ ዘረያዕቆብ ክፍለጦር ጣይቱ ብርጌድ አንድ ሻለቃ በራሳው አውደውጊያ እየተሳተፈች ነው።

በሌላ ግንባር ደጃዝማች ተሳማ አርገጤ ክፍለጦርና 7ለ70 ክፍለጦሮች በሸዋሮቢት ዙሪያ ማፉድና ገደባ የጠላትን ጦር እያረገፉት ይገኛሉ። በአውደውጊያው የጠላት ዙ-23 ከጥቅም ውጪ ሲሆን ከሸዋሮቢት አካባቢ ያለው የጠላት ሀይል መድፍ እያስወነጨፈ ይገኛል። በተመሳሳይ ገደባ ጊዮርጊስ ላይ የጠላት አንድ ኦራል ሲማረክ ከአንድ ሻለቃ በላይ ሀይል ተደምስሷል። 

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!




"እረ አንተ ጎንደሬ፣
እንዴትስ አድርገህ ተኩሰሀት ይሆን:
አለቅን አለቅን አለ ጠላት በራዲዮን"

"አርበኛ ውባንተ ሞተ ያለው ማነው፡
ያ ምሽግ ደርማሹ ሞተ ያለው ማነው፡
ዛሬም ከጉድጓዱ እንደታጠቀ ነው"

የዛ የጦሩ ገበሬ፣ የዛ የጦሩ ጠቢብ፡ የመውዜሩ ዳኛ፣ የምሽጉ ንጉስ፣ የእርሳሱ ሎሌ የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ እስትንፋኖሶች ካለፉት አራት ጀምሮ የጠላት ጦርን የእምብርክክ ሲነዱት ሰንብተዋል።

በህግ ማስከበር ስም በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያወጀው በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የበላይነት የሚዘወረው የአገዛዝ ስርዓቱ ወታደሮች፡ " እርጎ መስሎሽ ከእርሾ ጥልቅ" እንዲሉ አበው ፋኖን አፍናለሁ ብለው በጉና ቀጠና የገቡ ቢሆንም፡ ነገር ግን በሕይወት ተርፎ መውጣት አባይን በማንኪያ ጨልፎ እንደማድረቅ ሆኖባቸው ቀርቷል።

"ወይ መድፍ ብላሽ ወይ ድሮን ብላሽ፡
ወይ ሞርተ ብላሽ ወይ ታንክ ብላሽ፡
ሲደመስሰው ፋኖ በክላሽ።

የውቤ ልጆች ጎራው እያሉ፡
የጉና አርበኞች ጎራው እያሉ፡
ጉና ሰማይ ስር የጠላትን ጦር ሲዎቁት ዋሉ" ብሏል የጠላት ጦር ተቆላልፎ ተቆላልፎ ሲወድቅ የተመለከተ ያገሬው ሰው።

ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክ/ጦር ስር የሚገኙት ፀያይም አናብስቱ የእስቴ ደንሳ ብርጌድ አባላት እና ኃያላኑ የሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ፋኖዎች በጋራ በመሆን በጉና ቀጠና ሸንበቆች፣ ዘምባራ፣ ሾለክት፣ ለበጥ፣ ማሸንት፣ ሊባኖስ፣ አፎጠን፣ መንቆላት፣ ጥናፋ፣ ሩፋኤል፣ ገና መምቻ፣ ዘንጨፍ እና ቁስቋም በተባሉ ቦታዎች ላይ የጦር አውድማ ጥለው የጠላትን ወታደር ሲያበራዩት መሰንበታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ያለፉት ቀናት በሸምበቆች ቀበሌ በተደረገ ትንቅንቅ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ጦር እንደ ደረቀ የዛፍ ቅጠል የረገፈ ሲሆን፡ አርሶ አደሩ ቀብር ምሶ አፈር በማልበስ ፋታ አጥቷል ተብሏል።

በዚህ ስፍራ አሁንም በርካታ የጠላት አስከሬን በየአርሶ አደሩ ማሳ ወድቆ የሰማይ አሞራ እና የዱር አራዊት እየተራኮተበት መሆኑንም መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በተመሣሣይ እነዚኸው ምሽግ ደርማሾቹ የአርበኛ ውባንተ አባተ ልጆች፡ ሙትና ቁስለኛን ለማንሳት በሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና መሪነት ወደ ቀጠናቸው የገባውን አንድ ኦራል እና አንድ አይሱዙ ኤፍ ኤስ አር ሙሉ የአገዛዙን ጦር ወደ አመድነት ሲቀይሩት አፍታ አልፈጀባቸውም ተብሏል።

በዚህ ስፍራ የጠላት ዐብይ አህመድ ጦር፡ በወገን ኃይል ከበባ ውስጥ ገብቶ በአፈሙዝ አለንጋ መገረፍ ሲጀምር "እባካችሁ አድኑኝ" በሚል ትጥቁን እየጣለ በየአርሶ አደሩ መኖሪያ ቤት ለመደበቅ የሚሯሯጠውን ወታደር ለተመለከተ ትዕንግር ነበር ይላሉ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ሁንታውን ሲያስረዱ።

ደብረታቦር ከተማ ተቀምጠው ውጊያውን ሲመሩ የነበሩ የአገዛዙ የጦር መኮነኖች ወታደራቸው የፋኖ አፈሙዝ ሲሳይ ሆኖ ሲቀርባቸው ጊዜ በብስጭት "እናንተናችሁ ቀላል ነው እያላችሁ ያስበላችሁን" በሚል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የወረዳና የዞን ሚሊሻ አስተባባሪዎችን መረሸናቸው ተሰምቷል።

የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች የጦር መኮነኖቹ በሚሊሻ አስተባባሪዎቹ ላይ የወሰዱት እርምጃ ብቻ አልበቃቸውም፡ በየቀጠናው ገብቶ የነበረው ወታደራቸውን ጤና ጣቢያዎችን እያወደመ፡ መድሃኒቶችን እየዘረፈ፡ የጤና ባለሙያዎችን እየገደለነ እና እያሰረ እንዲወጣ ማድረጋቸው ታውቋል።

በአርበኛ ባየ ቀናው በሚመራው አማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክ/ጦር ስር የእስቴ ደንሣ ብርጌድ ቃል አቀባዩ ፋኖ ማረው ክንዱ ከመረብ ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ይከታተሉ👉




ሰበር ዜና!

ሌ/ኮ ተካ መከቦ ተደመሰሰ!

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድን ጨምሮ በመቶዎች የሞቱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ራያ ቆቦ ዞብል ላይ ተፈፀመ::

የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር ራያ ቆቦ ዞብል ከተማ እና ዙሪያዉን ሰፍሮ የሚገኘው 48ኛ ክፍለጦር የጠላት ሃይል ትናትና ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም 10:00 ጀምሮ እስከ ሌሊት 7:00 ድረስ ከባድ ዉጊያ በመክፈት የክፍለጦር ከፍተኛ አዛዡን ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተደመሰሱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ሰርተዋል::

መስከረምና ጥቅምት ላይ ራያ ቆቦ ተኩለሽና ዞብል በበርካታ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም ድሮን ታግዞ የገባ ቢሆንም በተደጋጋሚ አሰልች የደፈጣ ጥቃቶችና ተጋድሎዎች በቅርቡ ተኩለሽን ያስለቀቅን መሆናችን የሚታወቅ ሲሆን ራያ ቆቦ ዞብልና አካባቢው ላይ የመሸገዉን 48ኛ ክፍለጦር ዞብል አምባ ክፍለጦር በበርካታ የደፈጣ ጥቃቶች በማሰላቸትና መፈናፈኛ በማሳጣት ከትናትና ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በቀጠለው ዉጊያ በርካታ ድሎችን ተጎናፅፈዋል::

ዞብል አምባ ክፍለጦር በተጋድሎው

ከቡድን መሳሪያ አንድ ስናይፐር
ከነፍስ ወከፍ 7 ክላሽ፣ ተተኳሽ 2ሺ የክላሽ ጥሬ ገንዘብ 20000 (ሃያ ሺ ብር) ሬድዮ መገናኛዎችን ጨምሮ ጠላት የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት የሚፈፅምባቸውና የሚጠቀምባቸው ሰነዶችን ማርከዋል::

በቀጣይም መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

"በደምና አጥንታችን፤ አማራነታችንን እናስከብራለን::"

የአማራ ፋኖ በወሎ
ወሎ ቤተ-አምሐራ
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም


ቀን 18/2017 ዓ.ም
    
         🔥 አስደናቂ የድል ዜናዎች 🔥

ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም አይበገሬዎቹ የጣና ገላውዴዎስ ረመጦች ከአርብ ገበያ በሁለት አቅጣጫ የመጣን ወራሪ ሠራዊት አሳሩን ሲያሳዩት ውለዋል።

በአርበኛ ማሩ ቢተው አጋፋሪነት የመጀመሪያው ቤላ አቦን ለመያዝ ለመያዝ መነሻውን አርብ ገበያን አድርጎ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ቅስሙም ተሰብሮ እቅዱም ፈርሶ በመጣበት እግሩ ፈርጥጦ ተመልሷል።

ከረፋዱ 3:00 ሰዓት የጀመረው የዚህ ግንባር ዓውደ ውጊያ ልዩ ቦታው "አለቃ ጎራ" የተባለ ቦታ ላይ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት ድረስ ዘልቆ በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ለማድረስ ተችሏል። በዚህም መሠረት ከ80 በላይ የአገዛዙ ጦር እስከ ወዲያኛው ሲሸኝ፣ በርካታ ቁስለኛም የተመዘገበበት ነበር። ሁለተኛው ግንባር ከአርብ ገበያ ተነስቶ ወደ ሳና ከተማ የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊትም በተመሳሳይ በጣና ገላውዴዎስ ነበልባሎች ተለብልቦ ተመልሷል።

በጥቅሉ የአርብ ገበያው አውደ ውጊያ ጠጅ መረር፣ ቅምጦ፣ ሳና ሚካኤል፣ መንታ ውሃ፣ ኪዳነ ምሕረትና ሌሎችም ጎጦች ላይ ሰፊ ዓውደ ውጊያ ተከናውኖ የአማራ ፋኖ በጎንደር ጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር ድንቅ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ሁሉን አቀፍ የበላይነትን መቀዳጀት ተችሏል።

በተመሳሳይ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክ/ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ እና አንዳቤት ብርጌዶች በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል። ከእስቴ ከተማ በ3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በተደረገው ውጊያ የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ነበልባሎች የአገዛዙን ጥምር ጦር በወጉ ሲበልቱት ውለዋል።

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ሳይቀር በመንገድ መሪነት በተሳተፈበት በዚህ ውጊያ አይበገሬዎቹ የፖሊስ አዛዡን አጃቢዎች፣ ከ30 በላይ ሚሊሻ፣ በርካታ ወራሪ ሠራዊቱን እስከወዲያኛው ሲሸኙ የወረዳው ም/ፖሊስ አዛዥና በውል ያልታወቁ ባንዳ አመራሮችም ክፉኛ ቆስለው በማጣጣር ላይ ይገኛሉ። ሌላኛው የአንዳቤት ብርጌድ ክንደ ነበልባሎችም አለም በር እና ቀጭን ሜዳ ላይ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

ሌላው የአማራ ፋኖ በጎንደር ዞዝ አምባ ንጉሥ ክ/ጦር፣ አግኝቸው ብርጌድ ከእብናት ተነስቶ የጀግናው አስቻለው ደሴ መካን የሆነችውን ሰላማያ ከተማን ለመያዝ ከፍተኛ ኃይል ጭኖ ቢንቀሳቀስም የአርበኛ ዮናስ አያልቅበት ልጆች ልዩ ቦታው አድራቆ ላይ በፈጸሙት ፋታ የማይሰጥ መብረቃዊ ጥቃት ወራሪውን ሠራዊት ብትንትኑን አውጥተው ወደ መጣበት መልሰውታል።

በመጨረሻም የአጼ ፋሲል ክ/ጦር እና አሳምነው ብርጌድ ለ2:00 ሰዓታት የቆየ ዓውደ ውጊያን አድርገው በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር ከፍተኛ ኪሳራን አድርሰው ወጥተዋል። በሌላ በኩል የአሳምነው በርጌድ፦ ንሥር ሻለቃ አለም በር ከተማ ላይ አስደናቂ ኦፕሬሽን በመፈጸም በርካታ ሚሊሻን ደምስሳ በጀግንነት ወጥታለች።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ
       አርበኛ ባዬ ቀናዉ

https://t.me/fanozgonder


ሰበር ዜና!

17 ሙትና 29 ቁስለኛ ሁኗል፤ አሁንም በከበባ ውስጥ ይገኛል!

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ላስታ አሳምነው ኮር ተከዜ ክፍለጦር እና ጥራሪ ክፍለጦር በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ላስታ አሳምነው ኮር ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ኩልመስክ ቀጠና ለማጥቃት ሶስት ሬጅመንት ከመካናይዝድ ጋር ያሰለፈው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በፋኖ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ የሚመራው ተከዜ ክፍለጦርና በአርበኛ ሻለቃ ብርሃን አሰፋ የሚመራው ጥራሪ ክፍለጦር ባደረጉት ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ የተመለሰ ሲሆን ጠላት አሁንም ኩልመስክ ላይ ተከቦ ይገኛል::

ከራያ ቆቦ ተኩለሽና አካባቢው በበርካታ ተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት ተሰላችቶና መፈናፈኛ አጥቶ ወደ ጊዳን ወረዳና ኩልመስክ የገባው ጠላት ቀጠናዉን ከአመት በላይ ተቆጣጥረው በሚገኙት የላስታ አሳምነው ኮር አሃዶች ጥራሪ ክፍለጦርና ተከዜ ክፍለጦር ተቀብለው እያስተናገዱት ይገኛሉ::

ኩልመስክና ሃሙሲት አካባቢ በተደረገው ጠንካራ ዉጊያ የጠላት ሰራዊት የተረፈረፈ ሲሆን 17 ሙትና 29 ቁስለኛ ሁኗል፤ ቀሪው የጠላት ኃይልም ኩልመስክ ላይ ከበባ ውስጥ ገብቶ እጅ ስጥ እየተባለ ይገኛል፤ ተጋድሎው ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በጀግኖቹ ተከዜ ክፍለጦር እና ጥራሪ ክፍለጦር ትንቅንቅ የቀጠለ ሲሆን አሁንም የገባው ጠላት በማይወጣበት ሁኔታ ተከቦ ይገኛል::

ቅዱስ ላሊበላ ከተማና ቀጠናው ላይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ድል ለማግኘት የቋመጠው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጦር በተለያየ አቅጣጫ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ሬሽን ለማስገባት ቢሞክርም የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በመጣበት አቅጣጫ ሁሉ እንደ እባብ እየተቀጠቀጠና እየተደመሰሰ ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።




ቀን ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም

በወቅታዊ ጉዳይ ከጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል በርካታ የፈተና ስንክሳሮችን እያለፈ፣ የሴራ ድሮችን እየበጣጠሰ፣ በጽኑ አለት ላይ ራሱን እየተከለ በመጓዝ ላይ ይገኛል።

ትግላችን የሕዝባችን የኅልውናዉ ማረጋገጫ ተምኔቱ ነው፤ ትግላችን በጀግንነትና በአርበኝነት የቆሰሉና የተሰው ጓዶቻችንን አደራ የተሸከምንበት የደም መላሽነት መንገድ ነው፤ ትግላችን እውነትን፣ ፍትሕን፣ ነጻነትንና እኩልነትን መርኁ አድርጎ የሚጓዝ የዐይን ብሌናችን ነው።

በመሆኑም የሕዝባችን ቀጣይነት ማረጋገጫ፣ የታሪካችን፣ የባሕል የእምነታችን ማስቀጠያ ሐዲዳችን የሆነውን የኅልውና ትግል እንደ ነፍሳችን መጠበቅ ሕዝባዊ ብሎም ታሪካዊ ኃላፊነታችንም ግዴታችንም ነው።

ይህ ትግል ቅንጣት ታክል ስህተትን የማይፈቅድ፣ ወቅቱን፣ የፖለቲካ አሰላለፎችንና ስሁት እሳቤ ሸቃጮችንም ጭምር በትግሉ ሜዳ በሚገኙ ሐቀኛ ዐይነ-ንሥር ልሂቃን አማካይነት እየመረመርን መጓዝ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው።

ትግሉ በተለያዩ ቀጠናዎች በጠላት ላይ ሁሉንአቀፍ ድልን እየተቀዳጀ በመጓዝ ላይ ቢሆንም በትግሉ ሜዳ በማወቅም ባለማወቅም የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነትና የእኩልነት ትግላችንን የሚጎትቱ ጥቂት የማይባሉ አካላት መኖራቸውን በውል እንገነዘባለን።

የጣና ገላውዴዎስ ክፍለ ጦር እስካሁን ድረስ የትኛውም አደረጃጀት ውስጥ ሳይካተት ከውጭ ሆኖ የአደረጃጀቶችን አካሄድ እንዲሁም በመርኅ እና በሐቅ አታጋይነታቸው የቆሙትን ሲመረምር ቆይቷል።

ክፍለ ጦራችን ነገሮችን በውል ከመረመረ በኋላ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም የክ/ጦሩ እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት ወቅታዊዉን የትግል ሂደት፣ ነባራዊዉን የፖለቲካ አሰላለፍ፣ የቀጠናውን የአደረጃጀቶች ቁመና በወጉ መርምሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህ መሠረት ክ/ጦራችን እስካሁን ከአደረጃጀቶች ውጭ መቆየቱ ዙሪያ ገባውን ለመመልከት እድል በፈጠረልን መሠረት በመርኅና በሐቅ ታግሎ አታጋይነቱ በአርበኛ ባዬ ቀናው የሚመራው "የአማራ ፋኖ በጎንደርን" ምርጫችን አድርገን ወደተቋሙ ለመግባት በሙሉ ድምጽ አጽድቀን መግባታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

ከዚህ በተጨማሪ የአማራ ፋኖ በጎንደር መሪ አርበኛ ባዬ ቀናው እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ መሪ አርበኛ ሐብቴ ወልዴ እንዲሁም የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞች የጎንደር ሁለቱን ግዙፍ አደረጃጀቶች ወደአንድ የትግል መስመር ለማምጣት የሄዱበትን መንገድ በሙሉ ልባችን እንደምንደግፍ እየገለጽን ለተግባራዊነቱም ከትግል ጓዶቻችን ጋር ሆነን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለንን ጽኑ አቋም ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ስለሆነም የኅልውና ትግላችን የፖለቲካ ደላሎችንና ቁማርተኞችን አጥብቆ ይጠየፋል፤ ይታገላቸዋልም። የኅልውና ትግላችን ፉክክርና ውድድርን ሳይሆን ትብብርን ተደጋግፎትን፣ መለያየትን ሳይሆን በአንድ ተቋም ውስጥ ሆኖ መታገልን የሚሻ በመሆኑ የጎንደር አርበኞች የጀመሩትን የአንድነት መንገድ ለማደናቀፍ መጓዝ ታሪክ ይቅር የማይለው ድርጊት ስለሆነ ሁሉም ታጋይ ለአንድነት ቦታ እንዲሠጥ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም የሚዲያ አካላት ከዛሬ ጀምሮ ሁለቱ ግዙፍ እዞች አንድ የተቋም ስያሜ እስከሚይዙ ድረስ የአማራ ፋኖ በጎንደር ጣና ገላውዴዎስ ክ/ጦር ብላችሁ እንድትዘግቡ እንጠይቃለን።

ትግላችን በክንዳችን
ትግላችን በአንድነታችን
ትግላችን በሐቀኝነታችን
የጣና ገላውዴዎስ ክፍለ ጦር
ጎንደር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ

https://t.me/fanozgonder


የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ የተሳካ ኦፕሬሽን አካሔዷል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአብይ አህመድና የአረጋ ከበደ ጥምር ሀይል በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ውርደትን እየተከናነበ ይገኛል። በዛሬው እለት ነበልባሎቹ የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ሻንበል መማር ጌትነት ሻለቃ በአማሪት ከተማ ሰፍሮ በሚገኘው የጠላት ሀይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ ከተማውን ስታስለቅቀው።

በዚህ የተበሳጨው የጠላት ሀይል በአካባቢው የሚገኙ የአርሶ አደር ሰብሎችን አቃጥሎ በመሄድ የበቀል እርምጃውን ተውጥቷል። የአራት አርሶ አደር የበቆሎና የዳጉሳ ክምር ሙሉ በሙሉ በእሳት አጋይተውታል።

በሌላ በኩል በወተት አባይ ከተማ ሰፍሮ በሚገኘው  የዘራፊ ሀይል ላይ ሌላኛዋ የብርጌዱ ሻላቃ ጊዮን ሻለቃ ጠላት ሰፍሮበት በሚገኘው ካንፕ ላይ በወሰደችው  እርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሳለች። እንዲሁም የወተት አባይን ህዝብ አስገዶ ሊያወያይ የነበረው የጠላት ሀይልም መበተኑን አሻራ ሚዲያ አረጋግጧል።

©ሔኖክ አሸብር የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
ሙሉሰው የኔ አባት የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል አማራ ለፋኖ

ንሥር ብሮድካስት መረጃ 
ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

Показано 20 последних публикаций.