Fauda (chaos)
ፋውዳ በ 2015 በ HOT (በእስራኤል የኬብል ቻናል) ለእይታ የበቃ ታዋቂ የእስራኤል ተከታታይ የቴሌቭዥን ፊልም ነው።
አቪ ኢሳቻሮፍ እና ናዳቭ ላፒድ የተባሉ እስራኤላውያን በጋራ የተወኑበት ፊልም ሲሆን፣ በአሳዛኝ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ እና በጠንካራ የትወና ብቃት አለም አቀፍ እውቅናን ያገኘ ፊልም ነው።
ፋውዳ በእስራኤል ሲቪሎች ላይ ለሚሰነዘረው ጥቃት ተጠያቂ የሆኑትን የፍልስጤም ታጣቂዎችን የመከታተል እና የማስወገድ ኃላፊነት የተሰጠው በእስራኤል መከላከያ ሃይል (idf) ውስጥ የሚታወቀውን የዶሮን ሳሊንገርን ታሪክ የሚያሳይ ፊልም ነው።
ፊልሙ ዶሮን ስለተባለው የቀድሞ የእስራኤል ልዩ ሃይል ኦፕሬቲቭ ስለነበረው ግለሰብ ታሪክ የሚያጠነጥን ሲሆን፣ ችሎታውን የሚጠይቁ ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን ተልእኮዎች (mission) ሲከውን የሚያሳይ ፊልም ነው።
ታድያ ለዶሮን የተሰጠው ሚሽን በእስራኤል እና በጋዛ ድንበር ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ያለውን ፋይሰል የተባለ ታዋቂ የፍልስጤም ታጣቂን መከታተልን ያካትታል።
@MOVIE_NEWS12@MOVIE_NEWS12