MADO NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
🔻ሼር በማድረግ እና ለወዳጆ በማጋራት ተባበሩን!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ

በቅርቡ የቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ታሳሪዎች “ከፍተኛ ሕመም እየተሰማቸው ነው ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩት” ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በተለይ አቶ ዮሐንስ የሚገኙበት ማቆያ ሥፍራ ለጤንነታቸው የሚያሰጋቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልፀዋል፡፡ የቂሊንጦ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ዳይሬክተር ኮማንደር ዓለምሰገድ፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፡፡

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ኬኔዲ አባተ))


የአቶ ክርስቲያን እና የአቶ ዮሐንስ የእስር ቤት አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው ገለፁ

via የአሜሪካ ድምፅ


የኤርትራው ባለሥልጣን የቢቢሲውን ዘገባ “ሃስት” ሲሉ ገለጹ

የቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉና ‘በኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና ሶማሊያ ጉዳዮች አማካሪ’ መሆናቸው የተገለጸ ባለሥልጣን በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ሥምምነት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል የሚል ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎ፣ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል "በተጠቀሰው ስም የሚጠሩ ባለሥልጣንም ሆነ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተባለው ቢሮ አለመኖሩን" ለቪኦኤ አፍሪካ ቀንድ አስታውቀዋል። ቢቢሲ ሶማሊኛ ባለሥልጣኑ “ኢትዮጵያ የምትሻው የባሕር ኅይል መሠረት እንጂ የባሕር አቅርቦት አይደለም” ሲሉ መናገራቸውን ጠቅሷል። “ሶማሊያ ለኢትዮጵያ የባሕር መሠረት የምትሰጥ ከሆነ፣ ኤርትራ ከሶማሊያ ጋራ ያላትን ግንኙነት እንደገና ታጤናለች” ሲሉ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉት ባለሥልጣን...

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))


ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች።

via የአሜሪካ ድምፅ


ረቡዕ፡-ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል። ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

via የአሜሪካ ድምፅ


በኢትዮጵያ ግጭቶችን ለማስቆም እና ለዘላቂ ሰላም ለማስፈን የወጣቶች ተሳትፎ

በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን ግጭቶች ለማስቆም እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ወጣቶችን በግጭት አፈታት ሂደቶች ውስጥ በንቃት ማሳተፍ ወሳኝ እንደሆነ በርካታ ጥናቶች ያመለክታሉ። በአፋር ክልል ተወልዳ ያደገችው እና በክልሉ የተካሄዱ ጦርነቶች በአካባቢዋ ወጣቶች ላይ ያደረሰውን ጉዳት በቅርበት የተመለከተችው የ26 አመቷ ፋጡማ አህመድ ታዲያ፣ በግጭት አፈታት ሂደቶች ውስጥ በመሳተፍ በአደገችበት አካባቢ ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን የሚችልበትን መንገድ በማፍላለግ ላይ ትገኛልች። ስመኝሽ የቆየ ከፋጡማ ጋር ቆይታ አድርጋ፣ ወጣቶች በሰላም እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ያላቸው ተሳትፎ ምን እንደሚመስል ቃኝታለች።

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ስመኝሽ የቆየ))


ከለውጡ በኋላ ከ37 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላልፈዋል- ከንቲባ አዳነች

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከለውጡ በኋላ ከ37 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች መተላለፋቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።…

The post ከለውጡ በኋላ ከ37 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላልፈዋል- ከንቲባ አዳነች appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


ሪፎርሙ ኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ አሰልፏል- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሪፎርሙ በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያን በዓለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ መቻሉን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የፕላንና ልማት…

The post ሪፎርሙ ኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ካስመዘገቡ ሀገራት ተርታ አሰልፏል- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ተከስክሶ 38 ሞቱ

ስድሳ ሰባት መንገደኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አንድ የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን  ካዛኪስታን ውስጥ ተከስክሶ 38 ሰዎች ሲሞቱ 29 የሚሆኑት ተርፈዋል። አውሮፕላኑ ከአዘርባጃን መዲና ባኩ ወደ ሩሲያ ግሮዝኒ ከተማ በማምራት ላይ እንደነበር ታውቋል። አውሮፕላኑ አቅጣጫውን በመቀየር በካዛኪስታኗ አክታ ከተማ በድንገት ለማረፍ በመሞከር ላይ ነበር። የአዘርባጃኑ ፕሬዝደንት ኢልሃም አሊየቭ የአደጋውን ምክንያት ከወዲሁ ለመናገር ባይቻልም፣ በነበረው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ለመቀየር ተገዶ ነበር ብለዋል። የሩሲያው ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በበኩሉ፣ ቀድመው የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አውሮፕላኑ ከወፎች ጋራ በመጋጨቱ ችግሩ ሊፈጠር ችሏል ብሏል። በአውሮፕላኑ ውስጥ 42 የአዘርባጃን ዜጎች፣ 16 ሩሲያውያን፣ ስድስት...

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ኤኤፍፒ AFP))


ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጥረቷን ትቀጥላለች- ፕሬዚዳንት ታዬ

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስታወቁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን መልዕክተኛ ከሆኑት ራምታ…

The post ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጥረቷን ትቀጥላለች- ፕሬዚዳንት ታዬ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


በአማራ ክልል የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችሉ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ነው

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በረሃማ አካባቢዎች ያለውን የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻል የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችሉ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን እየተተገበሩ ካሉ…

The post በአማራ ክልል የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚችሉ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ነው appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


በአማራ ክልል 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማረስ ምርታማነትን ማሳደግ ተቻለ

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የሚታረሰውን መሬት 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር በማድረስ ዓመታዊ የምርት መጠኑን ማሳደግ የሚያስችል አቅም መፈጠሩን የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ርዕሰ…

The post በአማራ ክልል 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሔክታር መሬት በማረስ ምርታማነትን ማሳደግ ተቻለ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


ዋሊያዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ በሱዳን አቻቸው ተሸነፉ

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሱዳን 2 ለ 1 ተሸነፈ፡፡ ጨዋታው ዛሬ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና…

The post ዋሊያዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ በሱዳን አቻቸው ተሸነፉ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


የየመን አማፂያን ሚሳዬል ወደ ቴል አቪቭ አስወነጨፉ

የየመን አማፂያን ወደ ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ዛሬ ረቡዕ ሚሳዬል ማስወንጨፋቸውን አስታውቀዋል። ጥቃቱ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲደወል ሲያደርግ፣ ጉዳት ግን አላደረሰም ተብሏል። የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ ሚሳዬሉ ድንበር ከማቋረጡ በፊት መመታቱን አስታውቋል። ሁቲዎች ሚሳዬል ሲያስወነጭፉ በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። በጋዝ ሰርጥ እስራኤል በምታካሂደው ጦርነት ከፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለማሳየት እንደሆነ የሁቲ አማጺያን አስታውቀዋል። በእስራኤል ላይ ሚሳዬል ከማስወንጨፍ በተጨማሪ፣ ሁቲዎች በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጥቃት በመፈጸማቸው ቁልፍ የሆነው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ ተስተጓጉሏል። የእስራኤል ባለሥልጣናት በበኩላቸው በኢራን በሚደገፉት ሁቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በመዛት ላይ...

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))


የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ወደ አስመራ መጓዛቸዉ ተነገረ

የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ   ለይፋዊ የስራ  ጉብኝት ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ  አስምራ ሲደርሱም በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡

መሪዎቹ  በሁለቱ አገራት፤በቀቀጠናዉና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪይ እንደሚመክሩ    ታዉቋል፡፡

ሶማሊያ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳ የሚታወስ ነዉ፡

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

via Ethio FM 107.8 (author: Ethio Admin)




የሩሲያ መርከብ በሜዲትራኒያን ባህር መስጠሟን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

መርከቧ ሁለት ግዙፍ የወደብ ክሬኖችን ይዛ ወደ የሩሲያዋ ሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላዲቮስቶክ እያመራች ነበር ተብሏል

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በሶሪያ የገና ዛፍ መቃጠሉን ተከትሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ

ተቃዋሚዎቹ አዲሱ በመቋቋም ላይ የሚገኘው መንግስት አነሳ ቁጥር ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ





Показано 20 последних публикаций.