ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Психология


Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Психология
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አስረግዞ ላሽ ብሏል ሙሉውን ቪድዮ ሊንኩን ተጭናችሁ እዩ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/shorts/kVSSBgm8Hek?si=-PizmsmQ_ByUMdM6




ኤልዳና ትባላለች ነዋሪነቷ ዱባይ ሲሆን ከቲክታክ ፣ ከቴሌግራም ፣ ከኢሞ ፣ ከዋትሳፕና ከፌስቡክ ከጠፋች 2 አመት ሞላት እባካችሁ ዱባይ ያላችሁና ምታውቋት ሰዎች ካላችሁ መረጃውን ላኩልኝ ።


https://www.chanelvip.online/?rf=244
በዛሬው ዕለት የመጣ አዲስ ስራ ሲሆን እንደከፈታችሁ ወዲያውኑ 70 ብር በነፃ ይሰጣል ። ገና 40 ሰው ነው የገባው እኔም አልሞከርኩትም ሰው ነው የላከልኝ ። ምናልባት እዚህ ስራ ላይ ቀድማችሁ የጀመራችሁ ካላችሁ መረጃ ስጡን ።


ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረበዓል በሰለም አደረሳቹ ❤️


መሳሪያ ታጥቃችኋል!

መሳሪያ ታጥቃችኋል፣ ማንም ምንም ሊቋቋመው የማይችል አንጀት አርስ ብርቱ መሳሪያ። ከተጠቀማችሁበት ህይወታችሁን ያሻግረዋል፣ ካልተጠቀማችሁበት ስቃያችሁን ያበዛዋል። ባሻቹት ልክ ይወነጨፋል፣ እንደፈለጋችሁት ወደፊት ይመራችኋል፣ እንደ ፈቀዳችሁለት ከችግር ያወጣችኋል፣ ህይወትን ቀላልና ግልፅ ያደርግላችኋል፣ ማንም የማይሰጣችሁን ሃይልና ብርታት ያጎናፅፋችኋል። ይህ መሳሪያችሁ ምን ይመስላችኋል? የተረጋጋ አዕምሮ ነው። የሰከነ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የማይበገር፣ የማይደነቅ፣ የማይሸበር የተረጋጋ፣ ሰላሙን የሚያስቀድም፣ ከሁኔታዎች በላይ የሆነ፣ ራሱን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ ራሱንም የገዛ አዕምሮ ነው። ቀላል ነገር የታጠቃችሁ እንዳይመስላችሁ። እጣፋንታችሁ በእጃችሁ ነው። የሰው ልጅ ብርቱ ነው፣ የብርታቱ ምንጭም የተረጋጋ አዕምሮው ነው። ሰሜታዊነት ከራስ አልፎ ዓለምን ሲያፈርስ ተመልክተናል፣ በሁኔታዎች አቅጣጫ መነዳት ብዙ መንገድ ሲያስት ተመልክተናል። በከባባድ የህይወት ፍንዳታዎች መሃል ሆናችሁ ምን ታደርጋላችሁ? እግሬ አውጪኝ ብላችሁ ወደ አገኛችሁት አቅጣጫ ትሮጣላችሁ ወይስ ቆም ብላችሁ የሚያዋጣችሁን አቅጣጫ ትመርጣላችሁ?

አዎ! የትኛውም ከባድ መሳሪያ ሊያመክነው የማይችል፣ ራሱን በራሱ መከላከል የሚችል ትልቅ የህይወት መሳሪያ ታጥቃችኋል። ለትንሽ ነገር አትዋከቡ፣ ለቀላል ነገር ራሳችሁን አታስጨንቁ። በምንም ሁኔታ ውስጥ መረጋጋትን ልመዱ፣ ምንም ይፈጠር ምን በፍጥነት ምላሽ ከመስጠት ተቆጠቡ። ሀሳብ ያለው አዋቂ፣ አቋም ያለው ብርቱ ሰው ለጠለቀው ሀሳቡ ጊዜ ይወስዳል፣ አቋሙን ለማራመድ ፊትለፊቱን ያጠናል። በየጊዜው ፈተና ይምጣባችሁ፣ በየሰዓቱ ነገሮች ይወሳሰቡ፣ በተደጋጋሚ ያላሰባችሁት ክስተት ይፈጠር ራሳችሁን ግዙ፣ አዕምሯችሁን ተቆጣጠሩ፣ ከባድ መሳሪያችሁን ምዘዙ፣ ሁኔታውን እንደ አመጣጡ አስተናግዱት። የዓለም አብዛኛው ህዝብ ሳያስብ የሚወስን፣ ሳያቅድ የሚያደርግ፣ የማይፈልገውን ህይወት መርጦ የሚኖር ቢሆንም እናንተ ግን አስባችሁ ወስኑ፣ አስቀድማችሁ አቅዳችሁ አድርጉ፣ በትክክለኛው መንገድ የምትፈልጉትን ህይወት መርጣችሁ የምትኖሩ አይነት ሰዎች ሁኑ። የሰው ልጅ ጥበቡም እውቀቱም አለው፣ ነገር ግን አጠቃቀሙን የማያውቅ ከሆነ ስላለው ብቻ የሚያገኘው ጥቅም የለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ብዙዎች ቢስቁብህ ተረጋግተህ ተራ በተራ አይን አይናቸውን ተመልከት፣ ብዙዎች ሊተቹህ ቢሞክሩ ተረጋግተህ በቀጭን ፈገግታ ተመልከታቸው፣ ብዙዎች የማይገባህን ስም ቢሰጡህ ተረጋግተህ ፊትህን አዙረህ ጥለሃቸው ሂድ። ለሁሉም ነገር ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት ላይኖርብህ ይችላል። ምላሽህ ተመጣጣኝ ከመሆንም በላይ የሚበልጠው እንደዲሆን የማድረግ አቅሙ አለህ። እልህና ነገርን መብላት የሽንፈት ምልክት ነው። እርጋታን መገለጫህ አድርግ። አሸናፊዎች በነገር አንጀታቸውን አይበሉም፣ አሸናፊዎች ከእነርሱ ፍቃድ ውጪ በሆነ ጉዳይ ሲብሰለሰሉ አይኖሩም። በተረጋጋው አዕምሮህ እንጂ በውጫዊ ጫጫታ አትገዛ፣ በትልቁ ሀሳብህ እንጂ በጥቃቅን የሰፈር ወሬ አትመራ። ከብዙ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ድምፅ ብትሰማም ያንተውን መቼና እንዴት መጠቀም እንዳለብህ በሚገባ እወቅ። መሳሪያህ ስላለህ ብቻ የምትመዘው ሳይሆን እያለህም ቢሆን የምትጠቀምበትን ትክክለኛ ጊዜ የምትጠብቅለት ሊሆን ይገባል።


በረከቶችህን አትግፋ!

ችግሮችህን ስትቆጥር በረከቶችህ አያምልጡህ። የትም ብትሔድ፣ ማንንም ብትጠይቅ የማታጣው ነገር ቢኖር ችግሩን የሚተርክልህ ሰው ነው። "የኔ ችግር ይለያል" የሚልህ ሰው ብዛቱ ያንተን ችግር እንድትረሳ ሊያደርግህም ይችላል። ቸግሩን ሲያወራ በረከቶቹን የሚረሳም ብዙ ሰው አለ። በረከት፣ ፀጋ፣ ስጦታ ተነፍጎ በችግር፣ በመከራና በስቃይ ብቻ የተከበበ ሰው የለም። አንተ አላየሀውም ማለት ስጦታ የለህም ማለት አይደለም፤ አንተ አታውቀውም ማለት ክህሎት አልባ በረከት የተነፈክ ነህ ማለት አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ቸግሮችህን እያጎላህ በረከቶችህን አትግፋ። እንዳለህ ባለማወቅህ ብቻ እንደሌለህ አትናገር። እራስን ላለማወቅ ተጠያቂው እራሱ ባለቤቱ ነው። ፀጋህን አለማወቅህ ያለመኖሩ ማረጋገጫ አይደለም። ሁሉም ሰው ከችግሩ በላይ በረከቶች አሉት። የምናስበውን ያለመለየት ጉዳይ ነው እንጂ መልካሙን የሚያስብ፣ በጎውን የሚመኝ ችግሮቹ ላይ መንገሱ አይቀርም። "ይሔ ችግር አለብኝ" ከማለት በላይ "ይሔ በረከት ተሰቶኛል" ማለት ነገሮችን የማስተካከል አቅም አለው። ከፈለከው ታገኘዋለህ፤ ካተኮርክበት ይገለጥልሃል፤ ጊዜ ከሰጠሀው በእርግጥም ትደርስበታለህ። ያንተ ሆኖ የማታውቀው፣ ተሰቶህ የሚሸሸግብህ ስጦታ አይኖርም።

አዎ! እንኳን የቅርቡን የራስህን ይቅርና የሩቁን፣ በሰዎች ላይ ያለውን መመልከት ትችላለህና ለእራስህ ሲሆን አትስነፍ፤ አትድከም። ችግሩን የሚያወራ ብቻ ሳይሆን ችግሩን የሚፈታ ማንነትም እንዳለህ አስታውስ። ማንም ስለሆክ ችግር አንተጋር ብቻ አይመጣም። ማንኛውም ሰው የእራሱ የግል ሸክም፤ የእራሱ አስጨናቂ ሃሳብ አለበት። የሌላው ጉዳይ ያንተ አይደለም፤ ማንም ሰው የእራሱን ፈተና የመወጣት አቅም አለው። የዚህ ንደፈ-ሃሳብ እውነታ አንተም ጋር ይሰራል። ችግርህን መቁጠር ትርፍ አልባ ነው፤ በረከትህን መቁጠር ግን ሰላም፣ ፍቅር፣ እርካታ አለው። ባታውቀው እንጂ ብታውቀው ከችግር በላይ ነህና ተስፋህን ተንከባከብ፤ አንተነትህን ውደድ፤ ፀጋህን አጎልብት፤ በበረከቶችህ አመስግን፤ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ውብ ስብዕና ከሚያጎናፅፍህ ሰላም አንፃር ከውስጥህ ፈልገህ አግኘው።


ጥረትህን አስመዝግብ!

ፅድቅን ፍለጋ ብዙ ለፍተናል፣ ፍፁም ለመሆን ረጅም ተጉዘናል፣ በየጊዜው ለማደግ ለመሻሻል ያለማቋረጥ ጥረናል። ነገር ግን አንዳንድ ቀናት አሉ ጥረታችንን መና የሚያስቀሩት፣ አንዳንድ ሀሳቦች አሉ ልፋታችንን ትርጉም የሚያሳጡት፣ አንዳንድ ድርጊቶች አሉ በአንዴ ረጅሙን ጉዟችንን ድካም ብቻ የሚያደርጉት። በህይወታችሁ አንድ ነገር እመኑ። ሰዎች ናችሁ የተፈጠራችሁት ከስተት ጋር ነው፤ የምታዩዋቸው ሰዎችም ልክ እንደ እናንተ ሰዎች ናቸው ስህተት ይሰራሉ፣ ይወድቃሉ፣ ነገሮች ይባላሹባቸዋል። ራሳችሁ ላይ ጨክናችሁ ምንም የምታመጡት ነገር የለም። አውቆም ይሁን ሳያውቅ ስህተት ለሚሰራ ሰው ስህተቱን ላለመድገም እስከጣረ ድረስ ፈጣሪ ጥፋቱን ይቅር ማለቱ አይቀርም። ሁለት አይነት ሀጢአት አለ። የልማድና የአጋጣሚ። ከልማድ ሀጢያት፣ በቋሚነት ከሚፈፀም ስህተት የምታመልጡት በፆም፣ በፀሎትና በልባዊ ቆራጥነት ነው። ከአጋጣሚው ስህተት ደግሞ ማንነትን ሙሉ በሙሉ በመቀየር ነው። ዓለም ሁሌም ላዩን ወርቅ ውስጡን እሳት አድርጋ ብዙ የምታቀብላችሁ ነገሮች አሏት። እነዚም እናንተ ጋር ሲመጡ ስህተቶች ሆነው ይፃፋሉ።

አዎ! አትደናገጡ አትረበሹ። ፍፁም አይደላችሁም፣ ፍፁም ለመሆንም አትሞክሩ። እግዚአብሔር የሚጠላው ሀጢአትን አንጂ ሀጢአተኛን አይደለም። ስህተቱን አምኖ፣ ጥፋቱን ተቀብሎ፣ ተፀፅቶ ለተመለሰ ሁሌም በሩ ክፍት ነው። ስህተታችሁን የህይወት ዘመን ሸክም አድርጋችሁ አትኑሩ። ትናንት ብትሳሳቱ ቀሪው ዘመናችሁ ሁሉ የተሳሳተና የተመሰቃቀለ እንዲሆን አትፍቀዱ። ነገ መስራት ያለባችሁ የግል የቤት ስራ አለባችሁ፣ ዳግም እንዳይፈጠር ሊታረም የሚገባ ምግባር አላችሁ። በመጥፎ ለማድ አዙሪት ውስጥ ወድቆ ህይወቱ የጨለመበትና ተስፋ ያጣ ሰው ቢኖር ሁሌም ጨልሞ እንደሚቀር አያስብ፣ ሁሌም ጀምበር እንዳዘቀዘቀችበት እንደምትቀር አያስብ፣ ሁሌም ብሶተኛና የዓለም ተጠቂ ሆኖ እንደሚቀር አያስብ። በራሳችሁና በፈጣሪያችሁ ላይ ተስፋ ቆርጣችሁ ሰይጣንን ባለ ድል አታድርጉት፣ ራሳችሁ ላይ ጨክናችሁ የሰማይ አባታችሁን አታሳዝኑት። ስህተት አልባ ህይወት ለመኖር ራሳችሁን አታስጨንቁት። ተሳሳቱ ነገር ግን ታረሙ፣ አሁንም ተሳሳቱ ነገር ግን አሁንም ታረሙ። ስህተት መገለጫችሁ ሆኖ ፋታ ቢነሳችሁ ዝቅ ብላችሁ ከፈጣሪ ብርታትን ለምኑ።

አዎ! ጀግናዬ..! በራስ ላይ ተስፋ መቁረጥ ሽልማት የለውም፣ ራስን ችላ ብሎ መናቅ ምንም ዋጋ አያስገኝልህም። ምግባርህ ቢያሳፍርህ፣ ስራህ ስህተት ሆኖ ቢታይህ ምግባሩ አልያም ስራው እንጂ ስህተት አንተ ስህተት አይደለህም። እያወቅክም ይሁን ሳታውቅ ብታጠፋ ዳግም ራስህን የምታርምበት ሁለተኛ እድል እንዳለህ አስተውል። ሰይጣን ክፋቱ ክፉ ስራ አሰርቶ በራስህ እንድታዝን ያደርግሃል፣ ዲያቢሎስ መሰሪነቱ ብዙ ፈተና ፈትኖህ በአንዱ ቢጥልህ በዛው በአንዱ ሲኮንንህ ይኖራል። የመጡብህን ክፉ ሀሳቦች አንድ ለአንድ ታግለህ ያሸነፍክበትን ጊዜ አስታውስ። ጥንካሬህ ዛሬም እንዳለ ነው፣ አይበገሬነትህ አሁንም እንደዛው እንደተቀመጠ ነው። አንዲት ተልካሻ ስህተት በራስመተማመንህን እንድትሸረሽር አትፍቀድ፤ አንዲት ያልታሰበች ውድቀት ባዶነት እንዲሰማህ እንድታደርግህ አትፍቀድ። ከነስህተትህ ቀና በል፣ ከነጥፋትህ ደረትህን ነፍተህ ተራመድ። ነገር ግን ዳግም ያንን ጥፋት ሰርተህ የሚወድህንና የምትወደውን ፈጣሪህን ላለማሳዘን የቻልከውን ሁሉ አድርግ። ሌላው ቢቀር በእሱ ፊት ጥረትህን አስመዝግብ
የፍቅር ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ፈልገህ አትረበሽ!

ተረጋግተህ መመሰጥ ስትፈልግ የሚረብሽህ ነገር አታጣም፤ ውስጥህን ለማዳመጥ ስትመቻች ትኩረትህን የሚበትን ነገር አይጠፋም፤ የህይወትህን ከፍታና ዝቅታ፣ ክብደትና ቅለት ለመረዳት ስትሞክር ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች ፋታ ያሳጡሃል። የምርታማነትህ ዋነኛ መሰናክል መረበሽ፣ መረጋጋት አለመቻልና ትኩረት ማጣት እንደሆነ አስተውል። እንኳን ፈልገህ ይቅርና አለም እራሷ መረጋጋትህን አትፈልገውም፤ ተመስጦህ አይመቻትም፤ ከእራስህ ጋር በጥሞና መነጋገርህ አያስደስታትም። ስትረጋጋ ውስጥህን ትመለከታለህ፣ ፍላጎትህን በሚገባ ትለያለህ፣ ለአለም ጫጫታም ጊዜ የሚሰጥ ማንነት አይኖርህም፣ በእራስህ አለም የእራስህን አስደሳች ሁነት ትፈጥራለህ። እራሳቸውን የሚያዳምጡ ሰዎች ሰዎችን የማዳመጥና የመረዳት አቅማቸው ከፍተኛ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ፈልገህ አትረበሽ፤ መርጠህ ጫጫታ ውስጥ አትግባ፤ በፍቃድህ ውስጣዊ ሰላምህን አትጣ። ለአለም ክስተት ትኩረት እንደምትሰጠው ለእራስህም ትኩረት ስጥ፣ ሌላው ሰው ሲያወራ እንደምታዳምጠው ውስጥህን የማዳመጥ ብርታት ይኑርህ፣ ለአለም ጫጫታ ምላሽ ለመስጠት እንደምትሯሯጠው የውስጥ ጥያቄህን ለመመለስ ጊዜ ውሰድ። ከየትኛውም ሃላፊነት የሚበልጠው ሃላፊነት እራስን የማወቅና እራስን የመግዛት ሃላፊነት ነው። በምታየው፣ በምትሰማው፣ በምታደርገው የምትረበሽ ከሆነ የመቀየር ሙሉ መብት አለህ። በተረበሸ አለም አንተም ለመረበሽ እራስህን አሳልፈህ እየሰጠህ እንዴትም እራስህን ልታገኘው አትችልም። ትኩረትህን ለማግኘት አለም ምንያክል ገንዘብ ፈሰስ እንደምታደርግ ብታውቅ ዋጋው በገባህ ነበር። ስትረጋጋ፣ ውስጥህን ስትረዳ፣ ለውስጣዊ ሰላምህ ዘብ ስትቆም ከአለም የእስር ሰንሰለት መውጣት ትችላለህ።

አዎ! ማንም ፈጣሪውን ያውቀውና ይከተለው ዘንድ አስቀድሞ እራሱን ማወቅና መረዳት ይጠበቅበታል። በጠፋች አለም እራስህን ለማጥፋት አትፋጠን፤ በተረበሸ አለም እራስህን በፍቃድህ ለመረበሽና ለማወክ አትንደርደር። ለእራስህ ጊዜ ካልሰጠህ ልትረጋጋ አትችልም፤ ውስጥህን ካላዳመጥክ ወደእራስህ ልትመለስ አትችልም፤ የግል አቋም ከሌለህ፣ በእራስህ አቅጣጫ ካልተመራህ ማንም ሲመራህ የምትመራ፣ ማንም የነገረህን የምታምንና በየትኛውም ጊዜያዊ ጫጫታ የምትሸበር ትሆናለህ። ብዙ ሃላፊነት እንዳለብህ አስብ፣ እንዲሁ እንደ ዋዛ ትኩረትህን አሳልፈህ መስጠት እንደሌለብህ ተረዳ። እራስህን ለማዳን ብለህ ከሚረብሹህ ነገሮች ፈቀቅ በል፣ ለውስጣዊ ሰላምህ ስትል ከእየአቅጣጫው ከሚመጡ ማዕበሎች እራስህን ጠብቅ።


በአምላኬ እታመናለሁ!

ከራስ ጋር ንግግር: "በአምላኬ እታመናለሁ፣ በፈጣሪዬ የማይናወፅ፣ የማይሸራረፍ፣ የማይታወክ እምነት አለኝ። እራሴን የምወደው አንድም የእግዚአብሔር አምላኬ የስስት ልጁ በመሆኔ ነው፤ ሁለትም በእርሱ ህያው መንፈስ በመታነፄ ነው። ለሁሉም ነገሬ መሰረቴ እርሱ እንደሆነ አውቃለሁ፣ የትም ብደርስ፣ የትም ብገኝ የሚያደርሰኝ አምላኬ እንደሆነ አውቃለሁ። ጥፋቴ ቢበዛም፣ ሃጢያቴ ማለቂያ ባይኖረውም፣ ብዙ ብበድል ብዙ ብስትም በይቅርታው ብዛት ግን እስካሁን አለው፣ በርህራሔው ጥግ በምህረት መንገድ እመላለሳለሁ። ወዳጅ ባጣ፣ ሰው ቢርቀኝ፣ ዓለም ፊቷን ብታዞርብኝ፣ ከስኬት ጋር ሆድና ጀርባ ብንሆን፣ ብቸኝነት ቢፈትነኝ፣ የውስጤን የምትነፍስለት፣ የሆዴን የማዋየው ሰው እንኳን ባጣ በቸሩ አባቴ በእግዚአብሔር ግን ሁሌም ሙሉ ነኝ፣ ዘወትር ደስ ይለኛል።

አዎ! በአምላኬ እታመናለሁ፣ ፈጣሪዬን አስቀድማለሁ፣ ለእርሱ እራሴን እሰጣለሁ። በእግዚአብሔር የመታመንን ጥቅም፣ ፈጣሪን የማስቀደምን ትርፍ፣ ህይወትን በእርሱ መንገድ የመምራትን፣ እለት እለት ከእርሱ ጋር የማሳለፍን ሽልማት ከማንም በላይ አውቃለሁ። ፈጣሪውን ይዞ ማን ወደቀ? በአምላኩ እቅፍ ሆኖ ማን ይጨነቃል? ማንስ ውስጣዊ ሰላም ያጣል? ዓለም ከንቱ ነች፤ ከሌለኝ ለእኔ ቦታ የላትም፣ ሰው ለእኔ ከመስጠት በላይ ከእኔ መውሰድን ይመርጣል። የእግዚአብሔር አምላኬ ውለታ ግን በምንም መመዘኛ ከፍጥረታቱ ዓለምና የሰው ልጅ ጋር አይነፃፀርም። ምናልባት ደጋግሞ ይፈትነኝ ይሆናል፣ ምናልባት አውቆ አጣብቂኝ ውስጥ ይከተኝ ይሆናል። ነገር ግን መቼም እንደማይተወኝ፣ እኔእንኳን ፊቴን ባዞርበት፣ ከደጁ ብርቅ፣ ዓለም ውስጥ ብደበቅበት ፈለጎ እንደሚያገኘኝ አምናለሁ። ያደረገልኝን ዘርዝሬ ባልጨርስም በእርሱ ስለመታመኔ፣ በምህረቱ እዚ ስመድረሴ፣ በይቅርታው ብዛት ሙሉ ሰው ስለመሆኔ ሁሌም ምስክር ነኝ።"

አዎ! ፈጣሪያችሁ እያለ አትሰበሩ፣ አምላካችሁ አብሯችሁ ሆኖ አንገት አትድፉ፣ ሁሉን ቻይ የሆነ ቸር አባት እያላችሁ ስለምን ሆድ ይብሳችኋል? የዓለምን ክብር፣ የሰውን አንቱታ፣ የምድሩን ዝናና ንብረት ለአፍታ ተወት አድርጉት። ከዓለም ጌጥ በላይ፣ ከስጋዊ ፍቃድ በላይ ስለ ህያዊት ነፍሳችሁ በትንሹ ማሰብ መጨነቅ ጀምሩ። የሰው ልጅ የታመመች ነፍሳችሁን አያድንላችሁም፣ የምትደርሱበት ከፍታና ስኬት በበደል የቆሰለውን ውስጣችሁን አያክምላችሁም። ከእግዚአብሔር የምታገኙትን ፈውስ ከዓለም አትጠብቁ፣ በፈጣሪያችሁ የሚሰጣችሁን ነፃነት ለማግኘት ሰውን ደጅ አትጥኑ። በአምላካችሁ ለመታመን ቅንጣት አታመንቱ፣ በፈጣሪያችሁ ድንቅ ስራ ተስፋ ከማድረግ እንዴትም ወደኋላ አትበሉ። የሚያዋጣችሁን አስቀድማችሁ እወቁ፣ በገባችሁ ልክ በፍፁም ልባችሁ ፈጣሪን ጠብቁት።
የተባረከ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ከአድናቆትህ ተጠቀም!

ሰዎች በመሆናችን የሚመቸን፣ የምንወደው፣ የምናደንቀው ሰው ይኖራል። ከእርሱ ብዙ እንማራለን፣ እናውቃለን፣ እንደርሱ ለመሆንም እንጥራለን። ነገር ግን አኛ ስለወደድነውና አድናቂው ስለሆንን ብቻ ጥፋቱ ትክክል፣ ስህተቱ ተገቢ፣ ውድቀቱም ጥፋት ሊሆን አይገባም። የምታደንቀው ሰውን እንደሆነ እንዳትዘነጋ። ድጋፍህ ሃይልና ብርታት ሊሆነው ይችላል አንተም ከእርሱ ተግባር መጠቀም ካልቻልክ ግን የዘወትር አድናቂነትህ ይቀጥላል። አንተ ስለምትወደው ብቻ የማይሳሳት፣ አንተ ስለምትጠላው ብቻ ትክክል የማያደርግ ሰው የለም። አድናቂው ያደረገህ የግል ፍላጎትህና የእይታ አቅጣጫህ ነው። ማንንም የመደገፍ ምርጫ ቢኖርህም የምትደግፈውን ሰው እያንዳዱን ተግባር ግን የመቀበል ግዴታ የለብህም። ትወደዋለህ ማለት በአጥፊ ሃሳቦቹ ትስማማለህ ማለት አይደለም፤ አይመችህም ማለት መልካም ሃሳቦቹን አትቀበልም ማለት አይደለም። የሚጠቅምህን መውሰድ ላይ ብልህ ሁን፤ ከማንነቱ በላይ ተግባራቱ ላይ አተኩር።

አዎ! ጀግናዬ..! ከአድናቆትህ ተጠቀም! በልክም አድርገው። ስህተት የማይሰራ የለም፤ የማይታረምም እንዲሁ። ተሳስቷል ብለህ ለተቺት አትጣደፍ፤ ታርሟል ብለህም ለማሞካሸት አትቸኩል። ትልቁን ቁብ ነገር አስታውስ፤ የአድናቂና የተደናቂነትን ልዩነት በመሃላችሁ የፈጠረው ነገር የተፈጥሯችሁ ጉዳይ ሳይሆን የድፍረትና የበራስ መተማመናችሁ ጉዳይ ነው። በእራሱ ስለተማመነ፣ ጠንክሮ ስለሰራ፣ ዘወትር በእድገት ውስጥ ስለሚያልፍ፣ በየጊዜው ክህሎቱን ስለሚያዳብር፣ ለአፍታም በጭብጨባ ስለማይዘናጋ፣ በተቃውሞ ስለማይደናገጥ ያለበት ብታ ላይ ቆየ፣ አንተን የመሰሉ ብዙ የልብ ወዳጆችና አድናቂዎችን አፈራ። አንተስ እንደርሱ መሆን የማትችል ይመስልሃልን? በፍፁም! በእርግጥም መሆን ትችላለህ። እዚም እዛም ከማለት በላይ የሚማርክህንና አርዓያ የሚሆንህን አንድ የምትመኘው ሰፍራ ቀድሞህ የደረሰን ሰው በጥሞና ተከታተል፤ ከአድናቂነት ባሻገር ለመማር ተጠጋው፤ እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ከልብህ መርምር።

አዎ! ከአድናቂነትህ አትርፍበት፣ ከደጋፊነትህ ተጠቀም። በውዳሴ ከንቱና ስለሰው ዝና በማጨብጨብ ብቻ ህይወትህ እንዲቀየር አትጠብቅ። እንድትከተለው ያደረገህ በቂ ምክንያት ካለህ ከእርሱ የምትማረው ነገርም እንደሚኖር እሙን ነው። ለመማር የፈጠነ፣ አድናቆቱን ትርጉም የሚሰጠው፣ ብዙ ተከታይ ስላለው ብቻ ለመከተል የማይሽቀዳደም ሰው በእርግጥም የሚፈልገውን የሚያውቅ ሰው ነው። ህይወትህን በሙሉ ስለ አንድ ሰው ብርታትና ጥንካሬ፣ ስለ ጀብዱ እያወራህ ከምታሳልፍ የተጠቀምከውና በህይወትህ ላይ የፈጠረውን ተፅዕኖ ማስተጋባት ብትችል የተሻለ ነው። ለጊዜው ተከታይ ነህ፣ ከጊዜዎች ቦሃላ ግን ተከታዮች ይኖሩሃል። ለአሁን አድናቂ ብቻ ነህ፣ በቅርቡ ግን አድናቂዎች ይኖሩሃል። በየትኛውም ዘርፍ አድናቂና ደጋፊ ማግኘት ላይከብድህ ይችላል ነገር ግን በምታምንበትና በሚያስደስትህ ዘርፍ ላይ የምታፈራቸው እውተኛ ተከታዮችህ ይሆናሉ። ከምታደንቀው ሰው ተማር፣ ፈጠራህን አክልበት፣ በእራስህ መንገድ እርራስህን ለመሆን ጣር፤ አለም ካንተ ብቻ የምትጠብቀው አንድ ውድ አበርክቶት እንዳለ እመን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ከዛሬ በኋላ!

ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ እይታዎችህ ይቀየራሉ፤ አመለካከትህ፣ እሳቤህ ይቀየራል፤ ስራህ ይቀየራል። ምክንያቱም በእራስህ የፀና እምነት ስላለህና ለውጥ የሚጀምረው እራስን ከመመልከት፣ እራስን ከማሻሻል፣ እራስን ከመለወጥ፣ እራስን ከማንሳት፣ እራስ ላይ በመስራት ስለሆነ። ማወቅ የሚገባህን ማወቅ ይኖርብሃል፤ መማር ያለብህን መማር ይጠበቅብሃል፤ መጀመር ያለብህን መጀመር ይኖርብሃል። ከሁሉም በላይ፣ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ መጠንከር፣ መበርታት ይኖርብሃል። አይኖችህን ትገልጣቸዋለህ፤ እውቀትህን ወደ መሬት ታወርደዋለህ፤ እራስህን ወደ መሆን ትጠጋለህ። ሃሳበህን ወደ መተግበር፣ ህልመህን ወደ መኖር፣ እራስህን ወደ ማብቃት ትሸጋገራለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከዛሬ ቦሃላ! ነገሮች ያበቃሉ፤ ሸክሞችህ ይወርዳሉ፤ ጭንቀትህ ይራገፋል፤ ብሶትህ ይርቃል። ከዛሬ ቦሃላ ነገን ታያለህ፤ ነገ ማለት ትናንት ቃል የገባህለት፣ ትናነት ያቀድክለት፣ ትናንት ያሰብክበት ቀን ነው። ዛሬ ላይ ነገን ስታልም ከርመሃል፤ የቀናቱን ለውጥ በጉጉት ጠብቀሃል፤ የጊዜውን መቀየር፣ የሰዓታትን መክነፍ ከልብህ ተመኝተሃል። ነገር ግን ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ ቢመስልህም ዋናው ጉዳይ ግን ባንተ እምነትና ተግባር የሚገለፅ ነው። ቀናት ስለተየሩ የምትቀየር ከመሰለህ ዛሬን የመጨረሻ ቀንህ አድርገው። የስብራትህ መጨረሻ፣ የጭንቀትህ መጨረሻ፣ የብሶትህ መደምደሚያ። የትናነት ውሳኔዎችህን አስታውስ፣ የትናነት ህመምህን ከግምት አስገባ፤ በቃኝ ያልክበትን ጊዜ ወደኋላ ተመልከት።

አዎ! ህይወትህን እንዴት እየኖርክ ነው? በምን ደረጃ ላይ ትገኛለህ? ስለ እራስህ ምን ታስባለህ? የሚገባህ ምንደነው? የምትሰራው ምንደነው? ከሁሉም በላይ አምነህ የተቀበልከው ትልቁ ህልምህ ምንድነው? በጥቃቅን ሽልማቶችን ትልቁን ህልምህን እንዳትረሳ፤ ዛሬ በሚሰጥህ ጊዜያዊ ማደንዘዣ ደሞዝ መኖር ከምትችለው ህልም እንዳትሰናከል፤ ታይቶ ከሚጠፋው፣ አጓጉቶ ከሚወርደው ጊዜያዊ ስጦታ ለመጠበቅ ምን እያደረክ ነው? ምላሾችህ ሁሉ ዋጋ የሌላቸው፣ ለውጥ የማያመጡ፣ መንገድ የማይጠቁሙህ እንዳይመስሉህ። ጥያቄህ ውስጥ ሁሉም ነገር እንዳለ አስታውስ፤ ምላሾችህም የህይወትህ ቁልፍ እንደሆኑ እወቅ። ከዛሬ ቦሃል የምትልበት የተሻለ ጊዜ የለህምና ከዛሬ ቦሃላ ሁሉም እንዲያበቃ የማድረግ ድፍረትን ተላበስ፤ ለእራስህ በቃኝ ያልከበትን የመጨረሻ ውሳኔ አክብረህ ተገኝ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ሊንኩን ተችናችሁ ዘፈኑን ስሙትና የዘፋኙን ስም በትክክል ኮሜንት ላደረገልኝ ልዩ ሽልማት አለኝ
https://youtube.com/shorts/VcIuspWd7Is?si=6WyXgao1WcosEeEH


ጃኒ ድንገት ላይቭ ላይ ተዋረደች ። እስኪ ሊንኩን ተጭናችሁ ተመልከቷት
https://youtu.be/IDSIBe2m5Lg?si=YMuPJrFuVN8sYe5f


ከዚህ ውጭ ምንም Online ስራ እንዳትሰሩ
https://www.cowkeeper.com/#/pages/register/register?c=34982h


Репост из: ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️
ዩቲዩብ አካውንቴ በመዘጋቱ በጣም ከፍቶኛል ። በፈጣሪ ስም እስኪ ይህንን አዲሱ አካውንቴን ሳብስክራይብ በማድረግ ውለታ ዋሉልኝ ። የናንተ ሳብስክራብ ማድረግ ለኔ ለስራዬ ትልቅ ዋጋ አለው ለምታደርጉልኝ ትብብርም ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/LdXatpSSSvg


በዝቅታህ ታድጋለህ!

ብዙ ብታውቅም እውቀትህ አያመፃድቅህም፤ ዝነኛ ታዋቁ ብትሆንም ዝናህ አያኮራህም፤ ታዋቂነትህ አያስኮፍስህም። ብዙ ጀብድ ብትፈፅም፣ ብዙ ተዓምራትን ብታደርግ፣ በብዙ ውጣውረድ ውስጥ ብታልፍም፤ ፈተናዎችህን ብታልፍም፤ ታግለህ ብታሸንፍም ትህትናህን አላጣህም፤ ከሰውነትህ አልወረድክም፤ ማንነትህን አላጣህም። ምንም እንኳን ታዋቂ ያደረገህ ተግባርህና ጥንካሬህ ቢሆንም እውቅናህ ግን በሰዎች ዘንድ ነውና ሰዎችን ማገልገል አታቆምም፣ ማህበረሰብህን መጥቀም አትተውም። ጀርባህን ስላልረሳህ፣ መንገድህን ስላልካድክ ታማኝነት በውስጥህ ይታያል፤ ታታሪነትህ ይቀጥላል፤ ተወዳጅነትህም እየጨመረ ይሔዳል።

አዎ! ጀግናዬ..! በዝቅታህ ታድጋለህ! አንገትህን ብታቀረቅር ስለማትችል አይደለም፤ ታች ወርደህ ብታገለግል ደረጃህ ታች ሆኖ አይደለም፤ የመጣልህን እድል ለሌሎች አሳልፈህ ብትሰጥ፣ ወንድምህን ብታስቀድም፣ ያለህን ብታካፍል፣ ለሰዎች መኖር ብትጀምር ለእራስህ ባዳ ልትባል አትችልም። ቅንነትን ገንዘቡ ያደረገ፣ በትህትና የተመላለሰ፣ ወንድም እህቱን ያስቀደመ መልካም ሰው በጎ ተግባሩ ብቻ ያሳልፍለታል፤ ሰላም ይሰጠዋል፤ በሃሴት ይሞላዋል፤ በመንፈስ ያበረታዋል፤ አቅሙን ያንፀዋል። ዝቅ ብለህ ስታገለግል፣ በትህትና የሚገባህን የተሻለ ለሚጠቅመው ሰው ስትሰጥ ክብርን በውዴታ ታገኛለህ፤ ፍቅርን በፍላጎት ትቸራለህ፤ በሰዎች ልብ ውስጥ በደማቁ ትፃፋለህ።

አዎ! ትህትናህ ብዙ ሊያሳጣህ ይችላል፤ ዝቅ ብለህ በነፃ ማገልገለህ ብዙ ሊያስብልህ ይችላል፣ ያለህን ማካፈልህ፣ እድልህን አሳልፈህ መስጠትህ፣ ለተቸገሩ ወገኖችህ መድረስህ፣ እነርሱን ማስቀደምህ በአሉታዊ ጎኑ ጫና ውስጥ ሊከትህ፣ እንደ አስመሳይነትህም ሊያስመለክትህ ይችላል። ነገር ግን እራስህን ዝቅ ማድረግህ ማንነትህን አያሳጣህም፤ አንተነትህን አያጠፋውም፤ ችሎታህን አያደበዝዘውም። ማድረግ የምትፈልገውን በማድረግ፣ ማድረግ የምትችለውን አድርጎ በመገኘት ብርቱውን አንተነትህን ትገነባለህ፤ ጠንካራውን ማንነትህን ታጎለብታለህ።

አዎ! ማደግ ከፈለክ በሚገባህ ልክ ማገልገል ይኖርብሃል፤ ደረጃህን ማሻሻል ከተመኘህ ዝቅ ብለህ አስፈላጊ ነገሮችን መመርመር፣ በቻልከው መጠን የእራስህን አስተዋፅዎ ማበርከት፣ ወደሚያስተምርህና ልምድ ወደሚሰጥህ ተግባር መጠጋት ይኖርብሃል። አምነህበት እስካደረከው ድረስ ዝቅ በማለቴ አመለጠኝ የምትለው በረከት አይኖርም፤ በትህትናዬ ምክንያት ተሸሸገብኝ የምትለው ስጦታም አይኖርም። የውስጥ እርካታህን፣ ንፁ ደስታህንና የተጣራውን እድገትህን ታረጋግጣለህና መቼም በአትራፊው ዝቅታህና በልባዊ ትህትናህ አንዳታዝን፤ በፍፁም እንዳትቆጭ።

https://youtu.be/LdXatpSSSvg


ሁሉንም አታስደንቁም!

ዓለምን ብትገዙ፣ ብዙ ድንቅ ነገርን ብታደርጉ፣ የስኬት ማማ ላይ ብትቀመጡ፣ በብዙ መንገድ ራሳችሁን ብትቀይሩ ምንም የማይደነቁባችሁና የማይኮሩባችሁ ሰዎች ይኖራሉ። ምናልባትም እነዚህ ሰዎች የሚደነቁት ምንም ውጤት ሳይኖር ጠንቅራችሁ ስትሰሩ ይሆናል፣ ይበልጥ የሚገረሙት ተስፋ ትቆርጣላችሁ ብለው በሚያስቡበት ወቅት ጥረታችሁን በመቀጠላችሁ ይሆናል። የለውጥ ሂደታችሁን በሚገባ ይመለከታሉ፣ አካሔዳችሁን ይከታተላሉ፣ ጥረታችሁን እግር በእግር ያስተውላሉ ነገር ግን እንዴት እንደምትሰሩ፣ በምን መንገድ ወደፊት እንደምትጓዙ አያውቁም። ትወድቃላችሁ ብለው ሲጠብቁ እናንተ ፍጥነታችሁን ጨምራችኋል፣ ይሳሳታሉ ብለው ሲጠብቁ እናንተ ይበልጥ ተምራችሁና ተሻሽላችሁ ወደፊት እየተጓዛችሁ ነው። እናንተ ላይ እንከን በመፈለግ ተጠምደዋል ነገር ግን ይሔን ያህል ትልቅ እንከን አያገኙም። በዚህ ሰዓት በጣም ይደነቃሉ፣ የእነርሱ ምቀኝነትና ክፉ ሀሳብ እንደማያስቆማችሁ ሲረዱ ይበልጥ ይገረማሉ። ከጉዟችሁ ሊያስተጓጉሏችሁ ቢሞክሩም ግን አልቻሉም፤ ጭብጨባቸውን በመንፈግ ስሜታችሁን መጉዳት ቢፈልጉም አይችሉም።

አዎ! ሁሉንም አታስደንቁም! ሁሉም ሰው በእናንተ ለውጥና እድገት አይገረምም፣ ሁሉም ሰውም ለጥረታችሁ እውቅና ለመስጠት አይመጣም። "እኔ ህይወቴ እንዲቀየር፣ ስኬታማና ደስተኛ እንድሆን ሰዎች ሊያምኑብኝ ይገባል፣ እነርሱም የግድ ሊደግፉኝ ይገባል።" ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ አትሳሳቱ። ምንም ለማድረግ ከሰው አመኔታ ይልቅ የሚያስፈልጋችሁ የራሳችሁ በራስመተማመን ነው፤ ከሰው ድጋፍና ጭብጨባ በላይ የራሳችሁ ተነሳሽነትና ወኔ ነው። ስኬትና ጥንካሬ ለሰዎች እንደምትችሉ ማሳየት ሳይሆን ለራሳችሁ እንደምትችሉና አቅሙ እንዳላችሁ በተግባር ማስመስከር ነው። አንዳንዴ ብዙ ታዛቢና ደጋፊ ያላችሁ ቢመስላችሁም መጀመሪያ ግን የሚታዘባችሁ የገዛ ማንነታችሁ ነው። ራሱን ያላኮራ በምንም መንገድ ሰዎችን ሊያኮራ አይችልም፣ ራሱን ያላስደነቀ ሰው እንዴትም ሰዎችን ሊያስደንቅ አይችልም። "ከአሁን ከአሁን ሰዎችን አስደንቃለሁ፣ ከአሁን ከአሁን ሰዎችን አስደስታለሁ" ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ አትሸወዱ። መጀመሪያ ራሳችሁን አስደስቱ፣ በቅድሚያ በራሳችሁ አቅም ተማመኑ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከማንም ምንም ያለመጠበቅን ጥበብ ተማር፤ ከፈጣሪ እገዛ ውጪ የማንም ድጋፍ እንደማያስፈልግህ እመን። ውስጥህ ያለው ፅኑ ፍላጎት ትልቁ ብርታትህ ነው፣ ሰዎች የሚጥሉብህ እያንዳንዱ ትቺት ትልቅ ሃይልህ ነው። አንተ ራስህ ውስጥ የማታየውን ሰው ሰዎች በፍፁም አንተ ውስጥ ሊመለከቱት አይችሉም። ስላንተ የሚሉህን ሁሉ አትመን፣ ስለአቅምህ የሚነግሩህን በሙሉ አትቀበል። ራስህን ባወቅከው ልክ ራስህን ወደፊት ትገፋለህ፣ በራስህ በተማመንክ መጠን ጥረትህን ትጨምራለህ። በፍፁም ራስህን ዝቅ አድርገህ አትመልከት፣ በፍፁም አቅምህን አታሳንስ። ብዙ ፈታኝ ሁነቶች ይመጣሉ ይሔዳሉ፣ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያት ይመጣሉ ይሔዳሉ አንተ ግን በፈጣሪ ቸርነት እስካሁን አለህ። ሰው ከሚደነቅብህ በላይ በራስህ የምትደነቅበት ጊዜ ያስፈልግሃል፣ ሰው ከሚኮራብህ በላይ በራስህ የምትኮራበት ሰዓት ያስፈልግሃል። ሰውን ለማስደመም አትጣር ይልቅ ራስህን አስደምም፣ ሰው ፊት በግርማሞገስ ለመመላለስ አትድከም ይልቅ የራስህን ግርማሞገስ ራስህ አጣጥም።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


ጊዜህን በርካሽ ዋጋ አትሽጥ ወዳጄ !!

"ሴኔካ አካላዊ ንብረቶቻችንን መጠበቅ ላይ ጥሩ የሆንነውን ያህል፣ አእምሯዊ ድንበሮቻችን ማስመር ላይ ግን ግድ የለሽ መሆናችንን . ያስታውሰናል። ማንም እንዳሻው ድንበራችንን አልፎ ሲገባ አንቃወመውም: ንብረት ተመልሶ ሊገኝ ይችላል፤ እንዲያውም ገና ብዙ የምድር ሃብቶች በሰው አልተነኩም። ጊዜ ግን? ጊዜ ፈጽሞ ሊተካ የማይችል ሀብታችን ነው፤ ተጨማሪ መግዛት አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው በተቻለ መጠን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረግ ብቻ ነው፡፡"

"በሕይወታችን ውስጥ ሌሎች ጣልቃ እንዲገቡ በቀላሉ እንፈቅዳለን፤ የከፋው ነገር ደግሞ በአብዛኛው ጊዜያችንን ሊያጠፉት ለሚችሉት ሰዎች መንገድ የምናመቻች መሆናችን ነው። ማንም ሰው ለአላፊ አግዳሚው ገንዘቡን አይሰጥም፤ ግን እያንዳንዳችን ለምን ያህል ሰዎች ሕይወታችንን ሰጥተናል!ለንብረትና ለገንዘብ እጃችን አይፈታም፣ ሁላችንም እጅግ ስስታሞች መሆን ለሚገባን ለሚባክን ጊዜ ግን የምናስበው እጅግ ትንሽ ነው።”
- ሴኔካ

"የሕይወታችንን ቀናት ልክ እንደ ገንዘባችን አንመለከተም? በትክክል ለምን ያህል ቀናት በሕይወት እንደምንቆይ ስለማናውቅ፣ አንድ ቀን የምንሞት የመሆኑን ሀቅ በቻልነው ሁሉ ላለማሰብ ስለምንሞክር፣ ጊዜያችንን በነጻነት ለማባከን ፍቃድ የተሰጠን ይመስለናል። እዚህ ላይ እኔ በምትኩ የማገኘው ምንድነው?” ብለን እምብዛም ሳንጠይቅ በዚያችው ባለችን ጊዜ ላይ ሰዎችና ክስተቶች ጊዜያችንን እንዲሰርቁን እንፈቅድላቸዋለን፡፡"


"እንዴት እንደምትጠቀምበት ካወቅክ፣
ሕይወት ረጅም ነው ነገሩ፣ ለመኖር ያለን ጊዜ አጭር ስለመሆኑ ሳይሆን ብዙውን ያባከንነው ስለመሆናችን ነው። በደንብ ከተጠቀምንበት ሕይወት በበቂ ሁኔታ ረጅም ነው ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት በበቂ ሁኔታ ተለክቶ የተሰጠ ነው። በድሎትና ችላ በማለት ውስጥ ካባከንነው፣ መልካም ፍጻሜ ለማግኘት ካልሰራን፣ በመጨረሻ ማለፉን እንኳን ከመረዳታትን በፊት አልፎ እናገኘዋለን። ስለዚህ የተቀበልነው ሕይወት አጭር አይደለም፤ አጭር ያደረግነው እኛ
ነን።”
-ሴኔካ

ስለዚህ ዛሬ ራስህን ስትጣደፍ ወይም “በቂ ጊዜ የለኝም፡፡” የሚሉትን ቃላት ስትናገር ብትሰማው፣ ቆም በልና ጥቂት ሰከንዶች ውሰድ፡፡ ይህ እውነት ነው? ወይስ ብዙ አላስፈላጊ ነገሮች በመስራት ተጠምደህ ነው? በእርግጥ ውጤታማ ነህ፣ ወይስ በሕይወትህ ውስጥ ብዙ የባከነ ነገር እንዳለ ትገምታለህ? በህይወታችን አብዛኛውን ጊዜ  የምናባክነው በማይጠቅሙን ሀሳቦች እና በማይረቡ ነገሮች ላይ ነው። እያንዳንዱን ደቂቃ የምንጠቀም ቢሆን ምን ያህል ጊዜ ሊተርፈን እንደሚችል አስቡ!!


"እንዲህም እላለሁ እንዲት ቀንም ቢሆን አልሰጥም - ማንም ቢሆን አንድ ቀኔን ሊመልስልኝ አይችልምና!!

እንዲህም እላለሁ እያንዳንዷ ሰከንድ የእኔ ናት በባለቤትነት እና በስልጣን አስተዳድራታለሁ:: አልፋኝ የምትሄድ ሽርፍራፉ ሰከንድ አትኖርም!!"

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች! 🙏😍
YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/@mikre_aimro2
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪


አይንህን ጣልባቸው!

በሮች ሲዘጉ መስኮቶች ይከፈታሉ፤ ጨለማ ሲውጥህ ትንሽዬ የብረሃን ጭላንጭል ትታይሃለች፤ በእራስህ ስታዝን የሆነ የሚያጓጓህ ነገር ይከሰታል፤ ተስፋ ስታጣ አምላክህ አብሮህ መሆኑን ስታስብ ተስፋ ማድረግ ትጀምራለህ። ህይወት እንዲህ ነች፤ ፅናትህን ትፈልጋለች እንጂ እድሎችን ዘግታ አትዘጋም፤ እምነትህን ትሻለች እንጂ እስከ ወዲያኛው ተስፋ የምታስቆርጥ አይደለችም፤ ብርታትህ ያስፈልጋታል እንጂ እንዲሁ እንደ ቀላል ቆላልፋ አታስቀርህም። ብዙ በሮች ይዘጉብህ፣ አንተ ግን ወደ ተከፈቱት መስኮቶቾ ማማተርህን ቀጥል፤ ጨለማ ይክበብህ፣ አንተ ግን ወደ ትንሿ የብረሃን ጭላንጭል ተጠጋ፤ ተስፋ ማጣት ይፈታተንህ፣ አንተ ግን የመኖርህ ምክንያት፣ የተስፋህ ሚስጥር ወደ ሆነው አምላክህ ቅረብ፤ ተነሳሽነት ይጉደልህ፣ ድካም ይሰማህ አንተ ግን ጠንክረው የሚያጠነክሩህ፣ በርትተው የሚያበረቱህ ላይ አተኩር።

አዎ! ጀግናዬ..! ጨለማውን ለመግፈፍ፣ ህይወትን በተስፋ ለመሙላት፣ የተሻለውን ክስተት ለመፍጠር ተስፋን ወደሚሰንቁት፣ ብረሃን ወደሚያስገቡት የተከፈቱ መስኮቶች አይንህን ጣልባቸው፤ ተስፋ ወደሚሰጥህ አምላክ ተጠጋ፣ የሚያዋጣህን አቅጣጫ ያዝ። ህይወት ላከበዳት ከባድ፣ ላወሳሰባት ውስብስብ፣ ለደከመላት አድካሚ፣ ተስፋ ለቆረጠባት ተስፋ አስቆራጭ ነች። በተቃራኒውም ለተማመነባት ታማኝ፣ ለተደሰተባት አስደሳች፣ ላመሰገነባት አትራፊ፣ ላቀለላት ቀላል፣ ለሚኖራትም በፍቅር የምትኖር ነች። በትግል እደሰታለሁ፣ በውጪው ጫጫታ እረካለሁ፣ በከባቢው እረካለሁ ካልክ መቼም እንደማይሆንልህ አስታውስ። ከውስጥህ የሚወጣ እንጂ ከውጭ የሚመጣ ነገር አያሳርፍህም፤ የሆንከው እንጂ ያስመሰልከው ረፍት አይሰጥህም፤ ለእራስህ የተሰጠው እንጂ የቀማሀው አያስደስትህም።

አዎ! ማንንም ሳትጠብቅ ወደ ውስጥህ መመልከት ከጀመርክ ዙሪያህ በሙሉ ይቀየራል። ሁን ብለህ የምታጠፋው ጥፋት፣ አስበህበት የምትጋፈጠው ውድቀት፣ ፈልገህ የምታጣው ተስፋ የለም። ከእያንዳንዱ ድርጊቶች ጀርባ አስገዳጅና ከባድ ምክንያቶች ይኖሩሃል። ነገር ግን እስካልፈቀድክለት ድረስ የትኛውም ከባድ ነገር መኖርህን ሊያስጠላህ፣ ህይወትህን ሊያጨልም፣ ተስፋህንም ሊያሳጣህ አይችልም። ምንም ውስጥ ብትሆን በህይወት በመኖርህ የምትኮራበት፣ በመተንፈስህ የምታመሰግንበት ጊዜ አታጣም። የመጀመሪያው ሽንፈትህ እስከወዲያኛው ሽንፈትን እያፈራረቀ፣ ውድቀትን እያስከተለ፣ ሃፍረትን እያከናነበ አይቀጥልም።

አዎ! ሽንፈትህን ብቻ ከቆጠርክ ብዙ ተሸንፈሃል፤ ወደፊት እየተሸነፍክ ትቀጥላለህ። አሸናፊነትህን ከቆዘርክ፣ ድልህ ላይ ካተኮርክ፣ የተሻገርካቸውን መሰናክሎች፣ ያለፍካቸውን ፈተናዎች ካስታወስክ የአሁኑን ጨምሮ መጪዎቹን ፈተናዎችና መከራዎች እየተሻገርክ፣ እያሸነፍክ ትቀጥላለህ። ምንም ለማሰብ፣ ምንም ላይ ለማተኮር፣ ምንም ለማድረግ ማንም እጅህን በካቴና አስሮ የሚያስገድድህ አካል የለም። እራስህን የምታስረው፣ ማንነትህን የምታሳንሰው፣ አቅምህን የምትገድበው፣ ሰውንተህን የምትቀብረው አንተ እራስህ ነህ። ትኩረትህን በመቀየር ህይወትህን ቀይር፤ እይታህን በማሻሻል የህይወት አረዳዳህን አሳድግ፤ ክብርህን እያሰብክ፣ ከፍታህን እያስተዋልክ በልኩ ተንቀሳቀስ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪

Показано 20 последних публикаций.