Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Экономика


የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Экономика
Статистика
Фильтр публикаций


የመንግስት የባለበጀት እና የመንግስት ልማት ድርጅቶች በታክስ ሕግ የተጣለባቸዉ ኃላፊነት በመወጣት ለግሉ ዘርፍ ዓርዓያ መሆን እንደሚጠቅባቸው ተገለፀ

ታህሳስ 10/ 2017 ( ገቢዎች ሚኒስቴር )

የመንግስት የባለበጀት መ/ቤቶች እና የመንግስት ልማት ድርጅቶች በወቅቱ ግብራቸውን በመክፈል እና በግብር አሰባሰብ ላይ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሔደ፡፡

ውይይቱን ያስጀመሩት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ሀገራዊ የገቢ ራዕይን እውን ማድረግ የሚያስችሉ ተከታታይ ሥራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የዚሁ አካል የሆነው የመንግስት የባለበጀት መ/ቤቶች እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች የገቢ አሰባሰብ በግልፅ ለይቶ ለመከታተል እና ለመደገፍ በዋናዉ መ/ቤትና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የመንግስት ድርጅቶች ተቋማት ብቻ የሚያስተናግድ የታክስ አስተዳደር አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመዉ በዚህ አደረጃጀቶችን የመንግስት ተቋማቱ አውቀው በመገልገል እና የሦስተኛ ወገን መረጃ ምንጭ በመሆን በገቢ አሰባሰብ ላይ ሀገራዊ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/EyYrZ


የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ
ግብር ከፋዩ ያለውን የንግድ ሥራ ሀብት እንደ ዓይነቱ እና እንደአገልግሎቱ በመለየት የሚመዘግብበት የንግድ ሥራ ሀብት መዝገብ ሊኖረው የሚገባ ሲሆን የዚህ ዓይነት መዝገብ፡-
👉 እያንዳንዱ የንግድ ሥራ ሀብት የተገዛበት ወይም የተገኘበት ቀን እና ዋጋ፣
👉 በግብር ዘመኑ የንግድ ሥራ ሀብቱን ለማሻሻል የተደረገ ማንኛውም ወጪ ከተጣራ የመዝገብ ዋጋ ሀያ በመቶ በላይ ወይም በታች መሆኑን የሚያሳይ ስሌት የተከናወነበት ሰነድ፣
👉 በዓመቱ መጨረሻ የንግድ ሥራ ሀብቱ ያለውን የተጣራ የመዝገብ ዋጋ፣
👉 የእያንዳንዱ የተጣራቀመ የእርጅና ቅናሽ መጠን የሚያሳይ ስሌት የተከናወነበት ሰነድ የያዘ መሆን አለበት፡፡
👉የኢንቨስትመት የሚካሂድ ግብር ከፋይ የኢንቨስትመንት ሥራው ተጠናቆ የኢንቨስትመንቱ አጠቃላይ ካፒታል እስኪታወቅ ድረስ በየጊዜው የሚወጣው ወጪ ራሱን የቻለ መዝገብ (ledger)ሊኖረው ይገባል፡፡


በሀገር ውስጥ ለሚደረጉ ጉዞዎች የውሎ አበል ከግብር ነጻ የሚደረግበት ሁኔታ

በገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 1/2011 መሰረት

‹‹የውሎ አበል›› ማለት አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ሥራ ለማከናወን መደበኛ የሥራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ በሚሄድበት ጊዜ ለመኝታ፣ ለምግብ፣ ለመጠጥና ተዛማጅ ወጪዎች የሚከፈል ገንዘብ ነው፡፡

በሀገር ውስጥ ለሚደረጉ ጉዞዎች የሚከፈል የውሎ አበል፣
ሀ. አንድ ተቀጣሪ የሚከፈለው የቀን የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 500 ወይም ከደሞዙ 4% ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/2NhiG


ከ330 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ታህሳስ 9/ 2017 ( ገቢዎች ሚንስቴር )

የጉምሩክ ኮሚሽን ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 308.8 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 23.1 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 331.9 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ ምግብ ነክ እቃዎች ፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/CQnXV





Показано 6 последних публикаций.