አንዳንድ ሰው ሲያገኝ አያቅበትም።
ባለሃብት ሲሆን ከአላህም ጋር፣ ከአላህ ፍጡሮችም ጋር የሚጣላ አለ። በተለይ አጥቶ ያገኘ ሰው፤ አላህን ማመስገን ሲገባው የነበረበትን ረስቶ ሌላ ሙድ ውስጥ ይገባል።
እንኳን ሚስኪኖችን እንደ ድልዲይ ሆነው ወንዙን በማሻገር ለዚህ ሰበብ የሆኑትን ሰዎች እንኳ ዘወር ብሎ አያይም። ያኔ አላህን እያለቀሰ ይማፀን እንዳልነበር፤ ዛሬ ግን የታጠረው ሱሪ ይረዘማል፣ ያሳደገው ጺም ይላጫል፣ መስጅድ ለጀማዓህ ሶላት ይመላለስ የነበረው ቤቱ ውስጥ ለመስገድም በግድ ነው… የኩራቱን ነገር'ማ ተውት።
በአጭሩ ምን ልላችሁ ነው፦
አላህን የገንዘብ ሪዝቅ ስንጠይቀው፤ «ገንዘብ ስጠኝ!» ብቻ አንበለው። ይልቁንም ጠቃሚ ገንዘብ እንዲሰጠን፣ ከርሱ የሚያርቀንና እርሱን ከማውሳት ቢዚ የሚያደርገን ሳይሆን ወደርሱ የሚያቃርበን ገንዘብ እንዲሰጠን እንማፀነው።
ከአላህ ከሚያርቅ ባለሃብትነት ይልቅ ወደ አላህ የሚያቃርብ ድህነት የተሻለ ነው።
ዱንያን'ኮ የፈለገ ብንቸገር እንኳ በሞት እንገላገላታለን። አኺራችን ከተበላሸ ግን ምን ማምለጫ አለን? ምን መገላገያ መፍትሄ አለን? መዝገቡ ከታጠፈና ቀለሙ ከደረቀ በኋላ ከቁጭት ውጭ ምን አማራጭ አለን? ምንም!
ሰዎች ቢያስተውሉ ኖሮ፤ ዛሬ ላይ የሚጠፋ የማይመስላቸውና እንኳን ለነርሱ ለዘመድ አዝማድ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ቢከፋፈል የማያልቅ የሚመስላቸው ረብጣ ገንዘብ፤ አላህ ከወሰነ በአንድ ሌሊት እንዳውም በአንድት ቅፅበት ከነርሱ እጅ መውጣት የሚችል ነው።
ትናንት ዘካ አሰልፈው ሲሰጡ የነበሩ፤ ዛሬ ላይ በተራቸው ተሰልፈው ዘካ ለመቀበል የሚቸገሩ ሰዎችን አልታዘብንም ወይ? የነ ቃሩን ታሪክስ ምን ነበር?
ይልቅ አላህ ለዱንያችንም ለአኺራችንም የሚጠቅመንን ሪዝቅ ይለግሰን።
اللهم ارزقني رزقًا واسعًا حلالًا طيبًا من غير كدٍّ.. واستجب دعائي من غير رد.. وأعوذ بك من الفضيحتين: الفقر والدّين، اللهم يا رازق السائلين، يا راحم المساكين، ويا ذا القوة المتين، ويا خير الناصرين، يا ولي المؤمنين، يا غيّاث المستغيثين، إياك نعبد وإيّاك نستعين، اللهم إن كان رزقي في السماء فأنزله، وإن كان رزقي في الأرض فأخرجه، وإن كان بعيدًا فقرّبه، وإن كان قريبًا فيّسره، وإن كان كثيرًا فبارك فيه يا أرحم الراحمين، اللهم صلّ على محمد وآل محمد، واكفني بحلالك عن حرامك، وبطاعتك عن معصيتك، وبفضلك عمّن سواك يا إله العالمين، وصلّى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم።
||
t.me/MuradTadesse