Natinael Mekonnen


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Шок-контент


ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
I blog about marketing and sales
Buy ads: https://telega.io/c/NatinaelMekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Шок-контент
Статистика
Фильтр публикаций


ትልቅ ነበር ትልቅ እንሆናለን:: አማን ነው አይደል?!

#EthioSomalia : የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ያደረጉት ጉብኝት


የሶማሊያዉ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ አዲስአበባ ገቡ!

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ለይፋዊ ጉብኝት ዛሬ አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል። የፕሬዝዳንት ሞሐመድ ጽሕፈት ቤት፣ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነትና የጋራ ዓላማዎችን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ አስታውቋል። ዐቢይና ፕሬዝዳንት ሞሐመድ የአንካራውን የባሕር በር ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ በአካል ሲገናኙ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው። ፕሬዝዳንቱ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት፣ ካምፓላ ላይ ዛሬ በተካሄደው የአፍሪካ "ኹሉን ዓቀፍ የግብርና ልማት" አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኋላ ነው። በካምፓላው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ናቸው።


በሎስ አንጀለስ የተከሰተውን እሳት ለመቆጣጠር እስረኞች እንዲሰማሩ የካሊፎርኒያ ግዛት ፈቃድ ሰጥታለች

በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙት እስረኞች መጠነኛ ስልጠና ወስዷው እሳቱን ለመቆጣጠር እያገዙ ነው ተብሏል


የብልፅግና ደሴትና የጉስቁልና ደሴት የሚባል አለ። የብልፅግና ደሴት ነዋሪዎች ከ 60 አመት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ብዙዎችን ባለፀጋ እንደሚያደርግ የተተነበየለት ESX (ካፒታል ማርኬት) በይፋ መርቀው አስጀምረዋል።

የጉስቁልና ደሴት ነዋሪዎች ደግሞ ከስር በምስሉ ላይ እንደምታይዋቸው እየሆኑ ነው 🤓

ደሴትህን ምረጥ ወዳጄ 😄


በሎስ አንጀለስ የተከሰተውን እሳት ለመቆጣጠር እስረኞች እንዲሰማሩ የካሊፎርኒያ ግዛት ፈቃድ ሰጥታለች

በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙት እስረኞች መጠነኛ ስልጠና ወስዷው እሳቱን ለመቆጣጠር እያገዙ ነው ተብሏል


ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ።

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በአምስት አመቱ ተቋማዊ ሪፎርምና በውጪ ጉዳዮች ሰላምና ደህንነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

ከተቋማዊ ለውጡ በመነሳት ተቋሙ ከለውጡ በፊት  የነበረበትን ከፍተኛ የሆነ ችግር በመቅረፍ ሠራዊቱን ከሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ተዋፅኦ እንዲኖረው በማድረግ፣ ሃገራችንን በሚመጥን መልኩ እንደ ኢትዮጵያ እንዲያስብ ተደርጎ እየተገነባ ያለ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልፀዋል።

በአዲሱ ስትራቴጂ ከለውጡ በፊት የነበሩትን መመሪያዎች በመፈተሽ እና እንደ አሥፈላጊነቱ በመቀየር የሠራዊቱን ኑሮና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮች በማሻሻል፣ ሠራዊቱ ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ከሃይማኖትና ከብሄርተኝነት ነፃ የሆነ አስተሳሰብ እንዲኖው የማድረግ ሥራ መሠራቱን አንስተዋል። አየር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና ምድር ሃይልን በማጠናከር ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ሠራዊቱን መገንባት መቻሉንም አሥረድተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሠላም መርጠው በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ እየተሰራ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ሠራዊቱ ልምድ ያለው በመሆኑ ከሀገርም አልፎ በቀጠናው አገራት እንዲከበር አድርጎታል ነው ያሉት።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም ሰፋ ያሉ ጉዳዩች ላይ ሃሳብ አንስተው የተወያዩ ሲሆን አጠቃላይ ስለተደረገላቸው አቀባበልና ሠፊ ገለፃ ምስጋና አቅርበዋል።


በ1 ሰዓት ውስጥ 3 የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ‼️

5 ነጥብ 1 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከኢትዮጵያ ከአዋሽ በስተሰሜን ምዕራብ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአውሮፓ-ሜዲትራኒያን የመሬት መንቀጥቀጥ ማዕከል (EMSC) መመዝገቡን አስታውቋል።

በ1 ሰዓት ውስጥ 3 ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱንም ገልጿል።

ርዕደ መሬቱ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር (ቅዳሜ ጃንዋሪ 11 ቀን 2025) ማለዳ በሀገሪቱ አቆጣጠር ከጠዋቱ 3፡19 (9:19) ሰዓት ላይ በአዋሽ፣ አፋር፣ 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ የደረሰ ነበር።

ይህ ሶስተኛው ነው። ከዛ በፊት በደቂቃዎች ልዩነት 4.9 እና 5.1 በሬክተር ስኬል የተመዘገቡ መንቀጥቀጦችም ደርሰዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) መርቀው ከፍተዋል።

ይኽ ተግባር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በማዘመን ረገድ ዐቢይ ርምጃ ነው። ESX ለዘርፉ ግልፅነትን የተላበሰ የገበያ ስፍራ ይፈጥራል።

በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጥላ ሥርም በኢንቨስትመንት ለሚመራ እድገት በር ይከፍታል።

በመንግሥትም በግልም ዘርፎች የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት የቁጠባ እንቅስቃሴን ማሳደግን ብሎም ኢንቬስተሮችን መጠበቅን ታላሚ አድርጎ ተነስቷል።

ESX በሶስት የገበያ ክፍሎች ላይ ይሰራል። እነዚህም ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግሥት እና ሌሎች ተቋማት የሚያገለግሉ የይዞታ ገበያ፣የቋሚ ገቢ ገበያ እና የገንዘብ ገበያ ናቸው። የሙከራ የገንዘብ ገበያው ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ እንቅስቃሴ ተካሂዶበታል።

ይኽም ገበያው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ለማጠናከር ብሎም ለዘላቂ ልማት የካፒታል አቅም ለማሰባሰብ ያለውን አቅም አሳይቷል።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) ከኖርዲክ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ተቀማጭ ከሆኑ የኖርዲክ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን በዳሰሰው ውይይት የኖርዌይ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ኢትዮጵያ ከኖርዲክ ሀገራት ጋር ረጅም ዓመታት የዘለቀ የፓለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዳላት ያነሱት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ ይህንንም አጠናክራ ለመቀጠል እየሰራች ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በፓለቲካ እና ኢኮኖሚ መስክ እየተተገበሩ ስለሚገኙ የለውጥ ስራዎች ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ፤ ለውጭ ባለሐብቶች እየተፈጠረ ያለው ምቹ ሁኔታን ተጠቅመው የኖርዲክ ሀገራት ኩባንያዎች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የብሔራዊ ምክክር ሂደቱን በአብነት አንስተው ገለፃ አድርገዋል።


ትናንት ምሽት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ የታየው ክስተት...

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸውን አስታውቋል።

ተቋሙ በታዩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመመልከት እንደቻለውም የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አሊያም የሚቲዮር አለቶች እንደሚመስሉ ይፋ አድርጓል።

ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ነው የተመላከተው።

የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራ እንደሚገኝ ተቋሙ ገልጿል።

የተጣራ መረጃ ሲደርስ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

የማጣራት ሥራው እንኪጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ ተቋሙ አሳስቧል።


ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለመንግስት ለማስመለስ ያስችላል የተባለው አዋጅ በፓርላማው ጸደቀ

በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው አዋጅ ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና እንዲሁም ሌሎች ምንጫቸው ባልታወቁ መንገዶች ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ 10 ዓመት ወደኃላ በመሄድ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን የሚያስመልስ የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ያለ አግባብ በግለሰብ፣ በዘመድ አዝማድና ሌሎች ሰዎች ስም የተደበቀ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትና ንብረት ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የነበረውን የህግ ክፍተት አዋጁ እንደሚሞላ ተነግሮለታል፡፡


ዛሬ ምሽት 1:30 አካባቢ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ በርካታ ዞኖች እሳት ያለው ተቀጣጣይ ግዙፍ ነገር ከሰማይ ሲወርድ ታይቷል:: ይህ ግዙፍ ተቀጣጣይ ነገር ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም::


የተሰራውም ለናተው ነው:: ትውልድ እንዲማርበት ሁሉም ነገር ነገ የእናተው ነው::

በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቤተመንግስት ጉብኝት አደረጉ::

Показано 13 последних публикаций.