Natnael Mekonnen


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


ሠውዬውን ለምን እደግፈዋለሁ?

የአብይ ፈተና የጀመረው በመጣ በጥቂት ቀን ውስጥ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር ነበር። ይህ በሆነ በጥቂት ወራት ውስጥ ደግሞ በተቀናጀ ሁኔታ በሚዲያ ከባድ ስሙን የመበከል ተግባር ይፈፀምበት ጀመር።

በአንድ ቡድን Monopoly ተይዞ የነበረውን የደህንነትና የመከላከያ chain of command እንደገና ለማዋቀር ሲሞክር Power vacuum መፈጠሩን ያዩ ጠላቶች ከገዛ ድርጅቱ ባንዳዎች ጋር በፉጨት ተጠራርተው ከ 120 በላይ መፈናቀሎች በሐገሪቱ ላይ በጭካኔ በመፈፀም ሐገሪቱን በአጭር ግዜ ውስጥ በሐገር ውስጥ መፈናቀል ከአለም አንደኛ አድርገው ኢትዮጵያ እየደማች እነሱ ዳር ቆመው ማላገጥ ጀመሩ። ሠውየው ግን ጥርሱን ነክሶ ጉዞውን ቀጠለ። ህዝብ ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ገባ።

ያፈሰሱት ደም ያላረካቸው የጥፋት ኔቶርኮች ሚሊየኖችን ለሚዲያ በመመደብ specifically አብይን ሰይጣናዊ መልክ በመስጠት ከህዝቡ ሊነጥሉት ሠሩ። አነስተኛ መፈንቅለ መንግስት ከመሞከር ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሙከራ እከማቀነባበር እቅድ ነደፉ። ሠውየውን ግን ማቆም የሚችል እቅድና ሴራ ፈፅሞ ሊፈጠር አልቻለም። ጉዞውን ቀጠለ።

አንዱ የኦሮሞ ጠላት አረገው። ሌላው የአማራ ጠላት ነው ብሎ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፈተበት። የገዛ የሚመራትን ሐገር ህዝብ አፈናቀለ የሚል የሞኝ ዘመቻ ተከፈተበት። እኔ በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የሚፈጠሩትን ነገሮች ከቅርብ ሆኜ ታዝቢያለሁ። የሰውዬውን ልፋትና በሱ ላይ የተከፈተውን የማያቋርጥ ዘመቻና የጠላትን ክፋትም አይቻለሁ።

ሁሉ እንዳልተሳካ ያዩ ጠላቶች የመጨረሻ አማራጭ ያሉትን ጦርነት ከፈቱ። የጦርነቱ አስከፊ ጎን መከላከያ ሠራዊታችን የተመታው ውስጡ ባሉ ከሃዲዎች መሆኑ ነበር። ባመነው ተከዳ። ከጀርባ ተወጋ። ግዜ ጠብቀው ጦርነት ከፈቱበት። ነገር ግን ይህ ሁሉ እልቂትና የሚዲያ ዘመቻ ያላሸነፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአብይና ከመከላከያ ጎን ተሰለፈ ሠውየው የአለም አቀፍ ጫናና የዲስኩር ጋጋታ አድርገው ወደአዲስ አበባ ተጠጋን ሲሉ ጭራሽ ወደጦር ሜዳ ሄዶ ፊት ለፊት እንደወንድ ገጠማቸው። ግዙፍ የሚመስለውንና በአውሮፕላን ሳይቀር ከካይሮ መሳሪያ ይላክለት የነበረውን ጎልያድ በፈጣሪ ድጋፍ ድል አደረገ። የሚገርመው ድል ማድረጉ አይደለም። ይህን ሁሉ ያደረገውን አካል ሊያጠፋ ሲችል በድሉ አፋፍ ላይ ቆሞ የይቅርታ እጁን ዘረጋ።

ፈተናው ቀጠለ። የኢትዮጵያ ጠላቶች አልተኙም። የብሔራቸውን ካባ ለብሰው በነፃ አውጪ ስም እዚያም እዚም ተደራጁ። ሐገራቸው ላይ ከግብፅ እስከሶማሊያ ከሐገር ቤት እስከአንታርቲካ የሚዘረጋ የጥፋት ሴራ ይሸርባሉ። ሐገሪቱን እረፍት መንሳትና ሠውየውን የማቆም ዘመቻው ቀጠለ። የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ይታዘባል።

ሠውየውን ማከብረው በፈተኑት ቁጥር ህልሙ ስለሚጨምር ነው። ጦርነት መሀል አባይን ይገነባል። እሳት መሀል ቆሞ ወደብ ያልማል። የትኛውንም አይነት ፈተና ብትደቅንበት ከመርሀግብሩ ፈቀቅ አታደርገውም። ሊያጠፉት የሚያሴሩትን ሳይቀር አሸንፏቸው ሊያጠፋቸው ሲችል ለይቅርታ እጁን ሲዘረጋ ደጋግሜ አይቸዋለሁ።

ባጭሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ታሪክ የትኛውም መሪ ያልገጠመውን ፈተና በስድስት አመት ውስጥ ተፈትኖ ያለፈ። እንደወርቅ በእሳት የነጠረና ኢትዮጵያን ከመፍረስ የታደገ መሪ መሆኑን እኔ ሁሉን ነገር ከቅርብ ሆኜ የተመለከትኩት ናትናኤል መኮንን ህያው ምስክር ነኝ።


#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን እንደሚያግዱ ተነገረ።

ትራምፕ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው ያምናሉ።

ይህን ተከትሎም ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ዘ ታየምስ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።

ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውታል።

ይህን መረጃ ዘ ታይምስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።


ደጃች ዉቤ ሰፈር በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

አራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ዉቤ ሰፈር
በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ ያጋጠመዉን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።


#ትግራይ

“ ‘ ተቀምተናል ‘ የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው “  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ “ የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል “ ብለዋል።

“ ‘ ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ‘ የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ “ ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት “ ተቀምተናል “ የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

“ ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር “ ያሉት ፕሬዜዳንቱ “ ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል “ ሲሉ ገልፀዋል። 

“ ‘ ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ‘ በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው “ ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ “ በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል “ ብለዋብ።

“ ጠላት “ ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው “ መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት “ ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

“ ‘ የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ‘ የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ‘ ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ‘ የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው “ ሲሉም ተናግረዋል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡


ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ

በሰዓት ከ12 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል የተባለው ይህ አዲስ ሚሳኤል ለመምታት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ፡፡

አሜሪካ እና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ ኪቭ ሞስኮን ከሰሞኑ አጥቅታለች፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” በተሰኘ አዲስ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ዩክሬንን መታለች፡፡

እንደ ሩሲያ መከላከያ መግለጫ ከሆነ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው “ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል በዲንፒሮ የሚገኘውን የሚሳኤል ማምረቻ እና የጦር መሳሪያ መጋዝንን አጥቅቷል፡፡ የአሜሪካ ጦር በዚህ ሚሳኤል ዙሪያ እንደገለጸው ሚሳኤሉ አዲስ እና አህጉር አቋራጭ፣ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል ነው ብሏል፡፡

ሩሲያ ሚሳኤሉን የተኮሰችው ለሙከራ ጭምር እንደሆነ ያሳወቀው የአሜሪካ ጦር ሚሳኤሉ በቀጣይ የመሻሻል አቅም እንዳለው እና ሞስኮ ይህንን ሚሳኤል በብዛት ሊኖራት እንደሚችልም ገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሷ ተነገረ የብሪታንያ ጦር በበኩሉ የሩሲያ አዲሱ ሚሳኤል አውሮፓን ኢላማ ለማድረግ ተብሎ የተሰራ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከደቡባዊ ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው ይህ ሚሳኤል ብሪታንያ ለመድረስ 19 ደቂቃ፣ ጀርመን ለመድረስ 14 እንዲሁም ፖላንድ ለመድረስ ስምንት ደቂቃዎች በቂ መሆናቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በ40 ደቂቃዎች ውስጥ በአሜሪካ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡


በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ቢሎ ዞን ልዬ ቦታው ኮንቦልቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዱኛ ጭኮ ሆርዶፋ የተባለ ግለሰብ ከውጭ ሀገር ለሸኔ ሽብር ቡድን አመራር ለሆነው ቦሬ ለተባለው የተላከ ብዛቱ 29,985 ዶላር አቡ ወይም ሮብሰን ከተባለ የቡድኑ ሴል በመቀበል በመኖሪያ ቤቱ በመደበቅ ዶላሩን በህዳር 12/2017 ወደ ቦሬ ለመላክ ዝግጅት ላይ እያለ በተገኘው መረጃ መሰረት ዛሬ ከቀኑ 6:30 በቁጥጥር ስር ውሏል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Good Morning #Ethiopiaዬ : ያራዳ ልጅ አንድ ሰው አእምሮውን ሳተ ለማለት “ጨለለ” ይላል። ራሳቸውን ገግመው ጋዜጠኛ ያደረጉት ወዳጆቻችን አንድ በአንድ እየጨለሉ ነው። ፋሲል የኔአለምም A group of idiots የተባለውን ግሩፕ በይፋ ተቀላቅሏል 😁 ፋሲል የደበዘዘ ጋዜጠኛ ነው። መኖሩንም አለመኖሩንም የማታውቁት አይነት ሠው አለ አይደል? ቢኖር የማይሞላ ባይኖር የማያጎድል አይነት።

ከሶስት ቀን በፊት “ፋኖ ኢሊኮፍተር ጥሏል እመኑኝ” ብሎ እየማለ እየተገዘተ ተናገረና ቆይቶ ደግሞ የሆነች ቀይ የሞተር ሳይክል ስብርባሪ የሚመስል ቆርቆሮ ለጠፈ። ይህን መለጠፉ አይደለም የሚገርመው ተቃውሞ ሲበዛበት እዛው ኮመንት ላይ “የለጠፍኩት ፎቶ የቆየ እንደሆነ ይታወቅልኝ” ብሎን አረፈው 😂 በሶሻል ሚዲያ ታሪክ ራሱን በራሱ ያጋለጠ ቀጣፊ ጋዜጠኛ ተብሎ በቅሌት መዝገብ ላይ ተመዝግቧል 😂🫣


በዳንሻ፣ በሶሮቃና አካባቢው የፅንፈኛው ቡድን አባላት እጅ ሰጥተዋል።

የፅንፈኛው ቡድን አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በዳንሻ፣ በሶሮቃና አካባቢው በስምሪት ላይ ለሚገኘው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት እጅ እየሰጡ ነው።

የኮሩ የሠራዊት አባላት በአካባቢው የፀጥታ መዋቅር በማደራጀት እና በመቀናጀት ባደረጉት ህግ የማስከበር ኦፕሬሽን የፅንፈኛው ቡድን ተበታትኖ እጁን እንዲሰጥ አድርጓል ያሉት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ኮሎኔል መዝገቡ ዘሩ አሁን ላይ በቡድኑ ተፅዕኖ ስር የነበረውን አካባቢ በማፅዳትና አንፃራዊ ሰላም እንዲመዘገብ በማድረግ ህዝቡ የተለመደ ተግባሩን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የተሰጠውን የሰላም አማራጭ እድል በመጠቀም በርካቶች በሰላም እጃቸውን እየሰጡ እንደሆነ የገለፁት ኮሎኔል መዝገቡ ይህን ሳይጠቀም ወደ ለመደው ዘረፋ፣ ግድያ፣ ውድመት ድርጊቱ የገባው ፀረ-ህዝብ ቡድን ላይ ሠራዊቱ እርምጃ መውሠዱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ህዝቡን በመዝረፍና ሰላም በማሳጣት ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን የተናገሩት እጅ የሰጡት የቡድኑ አባላት አሁን በተሰጣቸው የሰላም ምህረት በመጠቀም የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ከመንግስት ጎን ተሰልፈው በሰላም ማስከበር እና በልማት ስራዎች ተሰማርተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።






የፌደራል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጎንደር ከተማ ገቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ከፍተኛ መሪዎቹ ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የሰሜን ምዕራብ እዝ አዛዥ ሌትናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አባት አርበኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደርን ከተማ የውኃ ችግር ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመገጭ ግድብ፣ የአዘዞ አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት እና ጥገና ሥራ፣ የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማትን የመሳሰሉ በከተማዋ እየተገገበሩ የሚገኙ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ።














የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ
 
የአፍሪካ መዲና እና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን በላቀ መስተንግዶ ለመቀበል ልዩ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራችንን በጎ ገፅታ አጉልቶ ለማሳየት መልካም አጋጣሚን በሚፈጥረው በዚህ መርሃግብር ላይ ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር  በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት ይፈልጋል።
 
በመሆኑም የእንግሊዘኛ፣ፈረንሳይኛና ዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የምትችሉ እና ዕድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ለምዝገባ ስትመጡ የትምህርት ማስረጃችሁን እና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንገልፃለን።
 
የአገራት መሪዎች፣የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪውን ያስተላልፋል።
 
ለተጨማሪ መረጃ፡-
 
+251911411045
+251912663737
 
ኑ! ሁሉም ዜጋ ለአገሩ ዲፕሎማት ነው!
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Показано 19 последних публикаций.