የሀዋሳ ከተማ 85% በካሜራ መሸፈኑን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ገለፀ!!!
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ በሃዋሳ ከተማ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ እና የሰላም ማስከበር ሂደት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
ኮማንደር መልካሙ በሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተያዘው የፀጥታ ዘርፍ ሪፎርምን አቅጣጫ መሰረት እንደ መምሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የሆነው የሀዋሳ ከተማን በቴክኖሎጂ የበለፀገ ከተማ ለማድረግ ብሎም በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ማስከበር ሂደት ያላት ከተማ ለማድረግ በተሰራው ስራ የከተማዋን 85% በካሜራ እንዲሸፈን ማድረግ ችለናል ሲሉ ኮማንደር መልካሙ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በዚህ የሪፎርም እቅድ አንድ አካል የሆነውን በህብረተሰብ ተሳትፎ ግንባታዎች ሲሆኑ በዚህም እንደ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ 3 ትላልቅ የፖሊስ ፅ/ቤት እና 40 የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች ግንባታዎች ተጠናቅቀው በከፊል ስራ እየሰሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በዚህም ሰዓት 40 ዘመናዊ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች በሀዋሳ ከተማ ላይ ለ24 ሰዓት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን ላይ የሚገኙ የወንጀል ምርመራ እና የቃል አሰጣጥ ሂደት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና በካሜራ የተደገፉ ሲሆን ይህም የሆነው የተመማሪውን ደህንነት እና መብት መረጋገጥ ለማረጋገጥ ከዛም በተጨማሪም የፋይል መረጃዎችን በማስቀመጥ ቀላል አሰራር እንዲዘረጋ ለማስቻል ሲሆን ይህ አግልግሎት በመላው ከተማችን ፖሊስ ጣቢያ የሚተገበር ነው።
በተጨማሪም 7614 ነፃ የፖሊስ መምሪያው የስልክ መስመር ሲሆን በማንኛውም ቀን እና ሰዓት በዚህ የነፃ መስመር በመደወል መረጃ ለመምሪያው የመረጃ ማዕከል ማድረስ ይችላል ተብላል። የስልክ መስመሩም በአንድ ላይ 5 ደዋዬችን በእኩል ሰዓት ማስተናገድ ስለሚችል ያለ ችግር ለማዕከሉ መረጃ ማድረስ ስለሚቻል ህብረተሰቡ ይህንን የነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀም ኮማንደር መልካሙ የገለፁት።
(Hawassa Engeda) በሚል በከተማችንን አልጋ ቤቶች ጋር በጀመርነው አዲስ Software መሰረት ማንኛውም የአልጋ አግልግሎት የሚጠቀም አካል ሙሉ መረጃ በSoftware አማካኝነት ወደ ተቋማችንን ይመጣል በዚህም በአልጋ ቤቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ ያቀደ የቴክኖሎጂ ትግበራ በከተማች ላይ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ ተግባራዊ አድርገናል።
በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን የሚገኙ ሁሉም የንግድ ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት እንዲጠቀሙ ባስቀመጥነው አስገዳጅ እቅድ መሰረት 583 ተቋምት የድህንነት ካሜራ በጊዜያዊነት የተከሉ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል።
ኮማንደር መልካሙ አየለ አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች በከተማችን ላይ በብዛት እየተሰሩ ሲሆን ፖሊስም ከማህበረሰቡ ጋር በህብረት በመስራት ሰላሙን ያረጋገጠ ከተማ የተገነባ ሲሆን በተጨማሪም 24 ሰዓት ያልተጎደለ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች አግልግሎት የፖትሮል ቅኝት የአባላት ስምሪት በመንደሮች ላይ በማድረግ ሰላማዊ ከተማ ቀጠና መፍጠር መቻሉን ተገልፆል።
ማህበረሰቡ እና ወጣቱ ከፖሊስ ሃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በተገኘው ድል መሰረት የከተማችንን ነዋሪዎች እና ወጣቶች ከልብ አመሰግናለሁ ሲል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።