Orthodox Mezmur Channel


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✞✞✞ Orthodox Mezmur Channel ✞✞✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙሮችን ያገኛሉ።
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

ለማንኛውም ሀሳብ ፣ ጥቆማ ፣ አስተያየት
👇👇👇
@Orthodox_Mezmurs
@Orthodox_Mezmurs

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций














❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

         ❤ ታኅሣሥ ፲፫ (13) ቀን

ቅዱስ ሩፋኤል

❤ እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ተአምር ላደረገበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለታላቁ አባት ቆቅ ሲመገብ ለነበሩት ለአባ መቃርስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ለገባበት በዓል፣ በስላሞች ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ ለአባ በጽንፍርዮስና ከላይኛው ግብጽ ለሆነ ለቅዱስ አባት ለአብራኮስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ቅድስት ሐና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸነሰቻት የሚሉ አሉ፣ በደብረ ቀልሞን ከሚኖር ከገዳማዊ ከአባ ሚካኤል ዕረፍት፣ ከሰማዕት አብራቂስ፣ ከሐርስፎስ፣ ከመኰንኑ ቆርኔሌዎስ፣ ከወርቅጥጶስና ከአፍሬ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።






አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ | ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

         ❤ ታኅሣሥ ፲፪ (12) ቀን

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን ታላቁ ዋልድባ ገዳምን ላቀኑ ምድራን እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አድርገው ላስባረከ አራዊተ እንስሳ ለሚታዘዝላቸው አንበሳን እንደ ፈረስ ሲያገለግላቸው ለነበረ ለታላቁ አባት ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለዕረፍት በዓል፣ ለዳግማዊ ቂርቆስ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ ብሔረ ብፁዓን ለገባበት መታሰቢያ ቀንና ከአጽማቸው ጠበል ላፈለቁት ለታላቁ አባት ለአቡነ ቶማስ ለዕረፍት በዓልና ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለወራዊው በዓል መታሰቢያና ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለቅዱሳን ለአንቂጦስና ለፎጢኖስ ለዕረፍት በዓል ሰላም አደረሰን። በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ ነድራ፣ ከደብረ እስዋን ከታማኙም ከቅዱስ ዮሐንስ ከመታሰቢያቸው፣ ስለ ቀሲስ ብናጥስ በሮሜ አገር ከተሰበሰብ ከኤጲስ ቆጶሳት፣ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት፣ ከዕረፍታቸው፣ ከቅዱሳን ሰማዕት ከአውሲስና ከእንጦንዮስ፣ ከሮሜው ከአባ መሐር ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። 



















Показано 20 последних публикаций.