ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Эротика


@Tewahdo27
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
“በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። — ዳንኤል 12፥1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Эротика
Статистика
Фильтр публикаций


ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቷል።
1 ቆሮንቶስ 15:20

"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?" ወደ ኢየሱስ መቃብር ለመጡት ሴቶች መላእኩ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ለእኛም የእግዚአብሔር ቃላት ናቸው። ኢየሱስ ተነሥቷል! ይህ ብቻ ሳይሆን ከሙታን በኩራት ነው። እርሱ የእግዚአብሔር ሐሳብ እንደሚጸና እና እኛም ዳግም እንደምንነሣ መተማመኛችን ነው። ሞት በእኛ ላይ ሥልጣን የለውም! እኛ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጆች ነን። ሞት ከእግዚአብሔር መገኘትና ፍቅር ሊነጥለን አይችልም።

https://ortodox_27












Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ፍጥረት አይኳትንም




🙏🙏🙏 ሕማማት🙏🙏🙏

ዕለተ #ረቡዕ
ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕለቱ የምክር ቀን በመባል ይጠራል፡፡

#OrthodoxTewahdo #ኦርቶዶክስ
#profile #timline #post #story

On Telegram👇
         • t.me/ortodox_27
         • t.me/ortodox_27
Share 🙏
https://t.me/ortodox_27












Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


በሰሙነ ህማማት ወቅት የምንሰማቸው እንግዳ ቃላትና ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ በግዕዝም ሆነ በኋላ በአማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የእብራይስጥ፣ የቅብጥና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፦

#ኪራላይሶን ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ < ኪርዬ ኤሌይሶን> ነው #ኪሪያ ማለት እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ ፡፡ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፡፡ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፤ማረን" ማለት ነው።
#እብኖዲ ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው። "እብኖዲ ናይናን" ሲልም " አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።
#ታኦስ ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣አምላክ" ማለት ነው።
#ማስያስ ፦ የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሲህ" ማለት ነው።
#ትስቡጣ ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም "ደግ ገዥ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ- አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግስትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነው።
#አምነስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ " ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግስትከ -የሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን " ማለት ነው።
        ✞✞✞
@Maryam_Maryam2127


☞"ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል።

🌹ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል፡፡ ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው ማቴ.21-23-27

❤️ ህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፡፡ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡ ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው፡፡

ደግሞም ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ "ወይቤሎሙ ኢየሱስ አማን እብለክሙ ከመ መጸብሓውያን ወዘማውያት ይቀድሙክሙ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር፤ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነት እላችኋለሁ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል ሲል አስተምሯል"፡ ማቴ.21-28

በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው፡፡

❤️ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾምና የስግደት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።🙏🏻



Показано 18 последних публикаций.