"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በዘመድ በወገን በገንዘብ በዕውቀት በውበትም እንዳንመካ ማሰተዋልን ይሰጠን የአባ ኪሮሰ አምላክ እግዚአብሔር በዓለም ፍቅር ተጠልፈን እንዳንወድቅ የአባ ኪሮሰ ምልጃ ፀሎት አይለየን!
@Orthodoxtewahdoc

ለንሰሐ ያብቃን አሜን


"ወር በገባ በ8 ፃድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ኪሮስ  ናቸው ።

ካልታሰበ አደጋ ወቶ ከመቅረት ይሰውሩን በቃል ኪዳናቸው ያስምሩን🙏


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌹#የ️አቡነ ኪሮስ ታሪክ ባጭሩ🌹

️ 📌•••በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አሞላክ አሜን እንኻን አደረሳቹ ለአቡነ ኪሮስ ወር በገባ በ8 አቡነ ኪሮስ ናቸው አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
🌿 በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

🌿❤️ ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው ሐምሌ 8 አርፈዋል።
ረድኤት በረከታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
💖🌹

https://t.me/yetwahidolegoche ጆይን እያላችሁ
https://t.me/yetwahidolegoche ጆይን እያላችሁ




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
🌹ወር በገባ በ8 የቅዱስ አባ (ብሶይ) ብሾይ ወርኀዊ መታሰቢያያ በዓላቸው ነው።

#የገዳም ኮከብ ቅዱስ አባ ብሶይ በግብጽ ሼስና በተባለች ቦታ የተወለደ ሲኾን ሰባት ወንድሞች ነበሩት፤ ከዕለታት ባንዳቸው ለእናቱ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልሟ ተገልጾ “ጌታ ከልጆችሽ መኻከል አንዱን እንዲያገለግለኝ ስጪኝ ይልሻል አላት” ርሷም፤ “ጌታ የወደደውን ይውሰድ” ብላ መለሰችለት፤ መልአኩም ቀጭን የነበረውን ሰውነቱም ደካማ የነበረውን የብሶይን እጁን ይዞ “ዝንቱ ውእቱ ወልድ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናይ” (ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይኽ ልጅ ነው” አለ፤ ያን ጊዜ እናቱ “የእኔ ጌታዬን እንዲያገለግለው ጠንካራውን ይውሰድ” በማለት ስትመልስ፤ መልአኩም “ጌታስ የመረጠው ይኽነን ነው” ብሎ መልሶላታል፡፡

ከዚያም በ340 ዓ.ም. ቅዱስ አባ ብሶይ ወደ ሲሐት በረሓ በመኼድ ቅዱስ ዮሐንስ.ሐጺርን ባመነኮሱት በአባ ባውማ እጅ ምንኲስናን ተቀበለ፡፡ አባ ባውማ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና አባ ብሶይ በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ለአባ ብሶይ ተገልጾለት ወደ ገዳም መርቶ አድርሶታል፤ በዚያም ወደ ርሱ ለተሰበሰቡ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ኾኗቸዋል፤ በቅድስና እጅግ የከበረ፤ በፍቅር፣ በደግነት፣ በርኅራኄ የሚታወቁ በተጋድሎም የበረታ ነበረና ዜናው በመታወቁ ቅዱስ ኤፍሬም ወደ አባ ብሶይ መጥቶ አይቶታል፡፡

ጌታችንን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን እያረካ፤ እጅግ ጽኑ የኾነ ተጋድሎን በማድረግ በጾም፣ በጸሎት ይጋደል ነበር፤ ሁሌም ርሱን ለማመስገን ከመሻቱም የተነሣ በምሽት ጸሎት ጊዜ እንቅልፍ እንዳይወስደው ጸጒሩን በገመድ በማሰር ይጸልይ ነበር፤ ዛሬ ድረስ ይኽ ማሰሪያ በዚያው ገዳም አለ፤ በዚኽም ንጽሐ ልቡና መኣርግ ላይ በመድረሱ ጌታችን ደጋግሞ ይገለጽለት ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸውም ጌታ በአምሳለ ነዳይ በእንግድነት ወደ በዓቱ በመጣ ጊዜ በእንግዳ ልማድ ውሃ አቅርቦ ለማጠብ ሲዠምር በምስማር የተወጉ እግሮቹን ዳስሶ በማየቱ ጌታችን እንደኾነ ዐውቋል፡፡ ርሱም በደስታ በመኾን ጌታን ያጠበበትን ውሃ ጠጥቶታል፡፡

ይኽነን ብቃቱን አይተው መነኰሳቱ ጌታችን እንዲገለጽላቸው ይለምንላቸው ዘንድ እጅጉን በዘበዘቡት ጊዜ ወደ ጌታችን አመለከተ፤ ጌታም በተራራው ላይ እንደሚገለጽ ነግሮት ለመነኰሳቱ ኹሉ ነገራቸው፤ እነርሱም በማለዳ ወደ ተራራው ጫፍ ሲገሰግሱ ከተራራው ሥር ጌታን በአምሳለ አረጋዊ ኾኖ በመገለጥ ይዘውት እንዲወጡ ቢጠይቃቸው አንዳቸውም በእንቢተኝነት ጸንተው ወደ ተራራው ይሮጡ ጀመር፡፡ በመጨረሻም አረጋዊዉ አባ ብሶይ ወደ ተራራው ሊወጣ ሲል በአምሳለ አረጋዊ የተገለጸው ጌታችን ዐዝሎት እንዲወጣ ጠየቀው፤ አባ ብሶይም በትሕትና በመኾን ታዝዞ ዐዝሎት ሲወጣ በእጅጉ ከበደው ቀስ እያለ ግን ቀለል ቀለል እያለው መምጣቱን ዐውቆ ጌታችን መኾኑን ተረድቶ ቀና ብሎ ቢያይ ዠርባው ላይ በፍቅር የታዘለው ርሱ ነው፤ ጌታም ስለ ትሕትናው ለርሱ እንደተገጠለት ነግሮት አባ ብሶይን ባርኮታል፤ በመኾኑም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ያዘለበት የአባ ብሶይ ሰውነት ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ብዙ ተአምራትን እያደረገ በገዳሙ አለ፡፡

ቅዱስ አባ ብሶይ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ክዶ የነበረውን በበረሓ የነበረውን ሰው ስለ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ከብሉይ ከሐዲስ በምሳሌ ጭምር በስፋት አስተምሮ እንዲመለስ አድርጓል፤ ቅዱስ አባ ብሶይም ብዙዎች ተጋድሎዎችን ካደረገ በኋላ ሐምሌ 8 በ417 ዓ.ም. በመዐዛ ገነት፣ በይባቤ መላእክት ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፡፡

የቅዱሳኑ በረከት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡

#መጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታደሰ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
✞#አርባዕቱ_እንስሳ ማለት⁉

♨ወር በገባ በ8 ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣
📌እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና። https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
📕#ቅዱስ_ሙሴ_የነብያት_አለቃ📘

❖🌹 ዳግመኛም ወር በገባ በ8 በዚችም ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ደርሶ የዋህ ቅን ጻድቅ የነብያት አለቃ የሙሴ ወርኃዊ መታሰቢያው ነው። ዛሬ መስከረም 8 አመታዊውም ናው።
❖ ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው።

❖ ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም።

❖ እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና፤ በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው።

❖ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊውም ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው፤ በማግሥቱ ደግሞ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ፤ አንዱ ዐመፀኛም ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን አለው።

❖ ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቍጥቋጦ ውስጥም እሳት እየነደደ ራእይን አየ።

❖ አይቶ ሊረዳ በቀረብ ጊዜ ጳጦስ በተባለ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገረው፤ ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲአወጣቸው አዘዘው።

❖ ከዚህን በኋላ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ በግብጻውያን ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን አመጣ፤ መጀመሪያው የወንዙን ውኃ ደም ማድረግ የመጨረሻው የግብጻውያንን የበኵር ልጅ መግደል ነው።

❖ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርዖንና በሠራዊት ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው።

❖ ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር።

❖ እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስለርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል፤ እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላልክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርዘኝ አለው።

❖ ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ፤ የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ ሸፈነ ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሀን ፊቱ በራ።

❖ መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንደጠበቃቸው እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን ለኢያሱ አስረክብ ብሎ አዘዘው።

❖ ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝቡንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስትም እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠለት።

❖ ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በተራራ ውስጥ አረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ፤ የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ።

❖ በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ፤ ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጥላችው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ይሁዳ በጻፈው መጽሐፉ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው የእስራኤል ልጆችም አርባ ቀን አለቀሱለት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                    አርኬ
✍️ ሰላም እብለ ለዘሰገደ ወአስተብረከ፡፡ መልዕልተ ዕፅ ነጺሮ በነደ እሳት መልአከ፡፡ መፈውሰ ቍስል ሙሴ ዘእምደዌ ምድር ተነስከ፡፡ ወእስከ ተሠየመ በላዕለ ፈርዖን አምላከ፡፡ ስብሐተ ቅዱሳን አድምዐ ወዝክረ ብሩከ፡፡  https://t.me/Orthodoxtewahdoc




Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
+ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::+ቅዱስ ሚክያስ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ 1 ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::+ሚክያስ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ሞራት (ሞሬት) ይባላል:: ሚክያስ ማለት "መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው

:: አንድም "መልአከ እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::

+ቅዱሱ ነቢይ ልጅ እያለ መላእክት ያነጋግሩት ነበር:: በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በ3ቱ ነገሥታት (በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ) ዘመንም ትንቢቶችን ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ ገስጿል::

+አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ የዳዊት ከተማ ፈት ሁና: ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት ተናገረላት::
"ወአንቲኒ ቤተ ልሔም ምድረ ኤፍራታ: ኢትቴሐቲ እምነገሥተ ይሁዳ: እስመ እምኔኪ ይወጽዕ ንጉሥ::"
(አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ካንቺ ዘንድ ይወጣልና) አለ::

+ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በሁዋላ ደጉ ዘሩባቤል ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ተወልዶባታል::

+ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: 7 ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹም ቀብረውታል:: ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን ለተፋቅሮ ይበለን: ከበረከታቸውም ይክፈለንና

ጥር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=

1.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ
2.ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ
3.አባ እንድራኒቆስ ሊቀ ዻዻሳት
4.አባ ብንያሚን ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን? +"+ (ሚክ. 6:6)

>


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የዲ/ዮርዳኖስ አበበ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር:
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን:: †††

=>+"+ እንኩዋን ለቅዱሳን አበው "አባ መቃርስ" እና "ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ታላቁ ቅዱስ መቃርስ "*+

=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::

+በ4ኛው መቶ ክ/ዘ አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::

+በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

+ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2 ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::

=>ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ (የሳስዊር) ሰዎች ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ ያደገባት ወላጆቹ (አብርሃምና ሣራ ይባላሉ) የኖሩባት ቦታ ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::

+በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት አደረጉት::

+ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለመቶዎች ዓመታት ተቀመጠ:: በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት (እስላሞች) መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::

+በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ሰውነታቸው ታወከ::

+ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን" ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::

+መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው:: በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::

+ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው በክብር አኑረውታል::

=>ይህቺ ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ስትሆን የተቀደሰችውም በ7ኛው መቶ ክ/ዘ በአባ ብንያሚን እጀ ነው::

+*" ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ "*+

=>ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

+ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27)

+ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ:: ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር:: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ::" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

+ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

+ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ዼጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

+ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት: 4ቱ ዐበይት ነቢያት: 12ቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

=>"15ቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ

*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ
*አብርሃም
*ይስሐቅ
*ያዕቆብ
*ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::

=>"4ቱ ዐበይት ነቢያት"
*ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
*ቅዱስ ኤርምያስ
*ቅዱስ ሕዝቅኤልና
*ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

=>"12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
*ቅዱስ ሆሴዕ
*አሞጽ
*ሚክያስ
*ዮናስ
*ናሆም
*አብድዩ
*ሶፎንያስ
*ሐጌ
*ኢዩኤል
*ዕንባቆም
*ዘካርያስና
*ሚልክያስ ናቸው::

=>"ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስና
*ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

=>ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)ና

*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ:: በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)

*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት):
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::




ነአምን በአብ ወነአምን በወልድ በወልድ/፪/
ወነአምን/፬/ ነአምን በመንፈስ ቅዱስ/፪/
እናምናለን በአብ እናምናለን በወልድ/፪/ /፪/
እናምናለን/፭/ በመንፈስቅዱስ/፪/
✝🌷✝🌷✝🌷✝🌷

እምኲሉ ይኄይስ በሥላሴከ ተአምኖ/፪/
በወላዲትከ/፪/ወበ ወላዲትከ ተማኅጽኖ/፪/

ከሁሉም/፪/ሥላሴን ነው ማመን ማመስገን/፪/
ወልድን በወለደች/፪/ድንግል አማላጃችን በእርስዋ እንማፀን/፪/


💒እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን! ጥር 7⃣ በዚህች ቀን ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው እና ቅዳሴ ቤታቸው ይታሰባል።
****
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር፤ከናምሩድ ክፋት በኋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ፤ ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በኋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው ‹‹ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ፣ በዚያውም አባቶቻችንን በውኃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው›› ተባባሉ፤ ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ፤ ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል፤ ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል፤መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል፤ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው፤ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ በጠፋን ነበር፤ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና፤ይልቁንም ‹‹ኑ እንውረድ ቋንቋቸው እንደባልቀው›› አሉ እንጂ፤በመሆኑም ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቋንቋዎች ተፈጠሩ፤ እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ፤ ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ አድርገው በተኑት፤ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው ‹‹ባቢሎን›› ሲባል ይኖራል። ዛሬም በክፋታችን ምክንያት ተደበላልቀናል አንድነቱን ያምጣልን ። ሁለተኛው ቅዳሴ ቤታቸው። እነዚህን በማሰብ የዛሬውን ቀን እናከብራለን።

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
❤️✝


"ዛሬ ጥር 7 ቅድስት ሥላሴ ናቸው።
"ሀገራችንን ከጥፋት፡ህዝባችንን ከስደት ከሞት ይታደጉልን የቀናውን መንገድ ይምሩን መልካሙን በጎውን ስራ ሰርተን ለንስሀ ለስጋወ ደሙ በቅተን እንድናልፍ ይርዱን።
@Orthodoxtewahdoc

ቅድስት ሥላሴ  በዕለተ ቀናቸው ያላሰብነውን ደስታ ይስጡን፡፡🙏❤


Репост из: "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
መልክአ ቅድስት ሥላሴ

ቅድስት ሥላሴ ሆይ በዕለተ ቀናችሁ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውሩን።🤲🌷
https://t.me/Orthodoxtewahdoc


✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
📗ስንክሳር ዘወርኃ ጥር ፯/7

ወለተ ሥላሴ ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊




" የዚህ ዓለም ኑሮ እንደ እንቅልፍ ነው ። በዚህ ሕይወት የሚሆኑት ሁሉ ሕልም ናቸው ።
በሕልምህ ባለጸጋ ብትሆን ምን ጥቅም አለው? በእንቅልፍ ልብ ሆኖ በቅዠት የሚናገር ሰው ስለ ንግግሩ አይፈረድበትም ። እኛ ግን በዚህ የእንቅልፍ ዘመን የምንናገረው ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ሊያሳጣን ይችላል"

"በድህነት እና በረሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች እንደ ሰለስቱ ደቂቅ ናቸው ። ከድህነት የበለጠ ምን እሳት አለ? ከረሃብስ የሚበልጥ ምን ነበልባል አለ?
ሶስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል ለድሆች ምጽዋትን የሚሰጥ ሰው ደግሞ ሰለስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል!"

"አንድ ሰው እኔ ክርስቲያን ነኝ ሲል በአንድ ቃል ዜግነቱንና ቤተሰቡን ስራውን ጠቅልሎ ተናገረ ማለት ነው  የሚያምን ሰው ከሰማያዊት ኢየሩሳሌም በቀር ምድራዊ ከተማ የለውም "

በትንንሽ ነገሮች ማመስገንን ከለመድህ ትንንሽ ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ሕይወትህ ምስጋና ይሆናል"

            " ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "

Показано 20 последних публикаций.