𝗣𝗛𝗔𝗥𝗠𝗔 𝗜𝗡𝗙𝗢 𝗣𝗥𝗢


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Медицина


Promote on PHARMA INFO!!!!! ምርትና አገልግሎትዎን ለማስተዋወቅ የሚከተሉትን መገናኛዎች ይጠቀሙ!!!
👉Telephone- +251911919998
👉Telegram- @Endalepharma
👉Email- endale47@hotmail.com
👉Telegram group: https://t.me/ETHIOPHARMAINFO
👉Telegram Channel: @PHARMA39INFO

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Медицина
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Hakim
ማሳሰቢያ
_

በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች የስኳር ህመምን ጨምሮ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች ሃላፊነት በጎደላቸው አካላት እየተለቀቁ ይገኛሉ። ከሰሞኑም ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሰዓታት ውስጥ የስኳር በሽታን ማጥፋት ተችሏል በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ከእዉነት የራቀና አሳሳች ነዉ።

የህክምና ሞያ ሳይኖራቸውና ለሚሠጡት አገልግሎት ህጋዊ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው በማህበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን የሚጎዱ፣ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ተበራክተዋል። ይህ ተግባር ማህበረሰቡን በእጅጉ እየጎዳና ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመዳረግ አልፎ ፈውስ ፈላጊ ዜጎቻችን ላይ ከፍተኛና የተወሳሰበ የጤና ችግር እየፈጠረ ይገኛል።

ስለሆነም በዚህ መሰል ተግባር ላይ ተሰማርታችሁ የምትገኙ አካላት ይህ ተግባር በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትታቀቡ እናሳስባለን።

ማህበረሰቡም ምንጫቸው ካልተረጋገጠ አካላት የሚላኩ መልእክቶችን እንዲመረምር፣ አገልግሎቶችንም ከመጠቀማችን በፊት ጥንቃቄ እንድናደርግ፣ አስፋላጊ ሆኖ ሲገኝም በ"Regulatory.moh@moh.gov.et" ላይ ጥቆማ እንድሰጠን እየጠየቅን ፤ ህዝባችን ሀሰተኛ የጤና መረጃ የሚለቁትን በማጋለጥ ፣የጤና ባለሙያ በማማከር ጤንነቱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ጤና ሚኒስቴር

@HakimEthio


Репост из: Hakim
ብርሃን አይቅበሩ ፤ በብሌን ችግር ምክንያት ለአይነ ስዉርነት የተዳረጉ ወገኖች ብርሃን እንዲያገኙ ምክንያት ይሁኑ!" በሚል መሪ ቃል የዓይን ብሌን ልገሣ ወር ይከበራል።

በዓሉ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚከበር የገለፁት የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው፤ የበዓሉ ዓላማ የተለያዩ የንቅናቄ ሁነቶችን በህዳር ወር ውስጥ በማዘጋጀት ስለዓይን ብሌን ችግሮች፣ ችግሮቹ ስለ ሚያስከትሉት የአይነ ስውርነት ጉዳት ፣ እና ማህበራዊ  ጫናዎች፣  ስለ ዓይን ብሌን ህመሞችና ህክምናቸዉ፣ የአይን ብሌን ልገሳ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች እና እምነቶች፣ እንዲሁም ስለ አይን ብሌን ልገሳ ሂደት ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ይከበራል ብለዋል።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ በበኩላቸው ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች በሃገራችን ከ300ሺህ በላይ የብሌን ጠባሳ ዓይነ ስውራን እንዳሉ የተናገሩ ሲሆን ፤ እነዚህ ወገኖች ብርሃን እንዲያገኙ ለማስቻል የአይን ባንኩ በትኩረት እየሰራ መኖሩን እና ከቀደመው ጊዜ ብዙ መሻሻሎች መታየታቸውን ሆኖም የልገሳ ባህሉን ለማጎልበት ርብርብ እንደሚፈልግ አስረድተዋል።

ዶ/ር አምሣለ ጌታቸው የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የዓይን ባንክ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፤ ስለዓይን ብሌን ችግሮች መነሻ ምክንያትና የመከላከያ መንገዶች ፤ የዓይን ብሌንአሰባሰብ መንዶች እና የዓይን ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ገለፃ አድርገዋል። ማንኛውም ሰው የአይን ብሌን ለጋሽ ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚዋ ከህልፈት በሃላ በሚደረግ የአይን ብሌንልገሣ ሙሉ የአይን ክፍል እንደማይነሣ፡ የለጋሹን የፊት ገፅታ እንደማይቀይር፤ የአይን ብሌን ልገሣ የእድሜ ገደብ እንደሌለውና የልገሣ ሂደቱም አጭር በመሆኑ የቀብር ሥርዓትንእንደ ማያስተጉዋጉል ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ የዓይን ብሌን ልገሣ እዉነታዎችን አብራርተዋል።

በእለቱም የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው ፤ የደምና ሕብረ ህዋስ ባንኩ አምባሣደር አርቲስት ይገረም ደጀኔ ፤ የሶል ጅም የቴኳንዶ አባላትን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከህልፈት በሃላ ለሚደረግየአይን ብሌን ልገሣ ቃል የመግባትና የፊርማ ማኖር ሥነ ሥርዓት የተካሄደ ሲሆን የዓይን ባንክ መስራች የሆኑት ዶ/ር ወንዱ አለማየሁ ወንድም በተከበሩ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የተጻፈ ለአይንባንኩ ድጋፍ የሚውል ብዛቱ 1400 (አንድ ሽህ አራትመቶ) መፅሀፎች በወንድማቸው ዶ/ር ግርማ አለማየሁ በኩል ለደምና ህብረህዋስ ባንክ ምክትል ዋና ዳይሬሃክተር ወ/ሮ ጤናዬ  ደምሴ አስረክበዋል።

መፅሀፉ ለዓይን ባንኩ ማጠናከሪያ  እንድውል ታስቦ በስጦታ እንደተበረከተ  የገለፁትዶ/ር ግርማ ሁሉም ሰው የዓይን ባንኩን በመደገፍ የወገኖችን ብርሃን የመመለስ ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

@HakimEthio


Репост из: Health info & vaccancy news (HIVN)
ማስታወቂያ
______

ጤና ሚኒስቴር ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር በሀገር አቅፍ ደረጃ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ጤና ተቋማትን መረጃ በMFR(Master Facility Registry) ላይ መዝግቦ በመያዝ የተለያዩ አካላት ከጤና ተቋማት ጋር የተያያዙ መርጃዎችን እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም https://mfrv2.moh.gov.et ሊንክ በመጠቀም የተቋማቱን ስም፣ የሚገኙበትን ቦታ እና ሌሎች ተዛማጅ መረጃዎችን ማግኘት የሚችል መሆኑን እየገለጽን የጤና ተቋማትን መረጃ በተመለከተ ጥያቄ ካላችሁ በኢሜል regulatory.moh@moh.ov.et ላይ ሙሉ ስም እና የግል ስልክ ቁጥር በማስገባት መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ጤና ሚኒስቴር


Репост из: Hakim
የሽንት መቅላት ወይም መድማት ችግሮች (Hematuria)  

የሽንት መቅላት በብዙ ምክንያቶች ሊከሰት  ይችላል ፡ የሽንት መድማት ችግር
1- በአይን የሚታይ (Gross Hematuria) ወይም 
2- በሽንት ምርመራ ብቻ የሚታወቅ (Microscopic Hematuria) ሊሆን ይችላል ።

የተለመዱት የሽንት መቅላት ወይም መድማት መንስኤዎቹ የሚከተሉት ናቸው ፡- 
1. ሽንት የሚያቀሉ ምግቦች ለምሳሌ (ቀይ-ስር) ወይም መድሀኒቶች 
2. ከፍተኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለምሳሌ (ረጅም ርቀት ሩጫ) 
3. የኩላሊት ወይንም የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን  
4. የኩላሊት ወይንም የሽንት ፊኛ ጠጠር 
5. የፕሮስቴት እጢ መፋፋት  
6. የፕሮስቴት እጢ ካንሰር 
7. የኩላሊት ብግነት ወይም መቆጣት (Glomerulonephritis) 
8. የሽንት ፊኛ ወይም የኩላሊት ካንሰር 
9. በአደጋ ምክንያት የተከሰተ የኩላሊት ፣ የፊኛ ወይም የሽንት ቱቦ ጉዳት 

የሽንት መድማት ችግር ከቀላል እስከ ካንሰር የመሳሰሉት ከባድ ችግሮች ምልክት ሊሆን ስለሚችል ችግሩ ከተከሰተ ሀኪም ጋር ቢቻል ዮሮሎጂስት ጋር ቀርቦ መሰረታዊ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ። 

ለማንኛውም የኩላሊት ፣ የሽንት ፊኛ ወይም የፕሮስቴት ችግሮች እንዲሁም የወንድ ተዋልዶ ችግሮች በስልክ ቁጥር 0944 724444 የኢትዮስካንዲክ ክሊኒክ ዮሮሎጂስቶችን ማማከር ይችላሉ።

በተጨማሪም በክሊኒካችን በአካል ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ በሚገኘው ክሊኒካችን ሃኪሞቻችን ጋር ቀጠሮ መያዝ  ይችላሉ ።

ለተጨማሪ ምክር እና መረጃዎች የማህበራዊ ድረ ገፆቻችንን ይከታተሉ ፦

TikTok 👉 https://www.tiktok.com/@ethioscanclinic?_t=8rKg1ETBFbD&_r=1

Telegram 👉 https://t.me/ethioscandic

Facebook 👉 https://web.facebook.com/ethioscandicclinic


Репост из: EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Репост из: Hakim
የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አሁናዊ መመሪያዎችና ተስፋ ሰጪ ምርምር ዉጤቶች

የአይነት 1 ስኳር ህመም (type 1 diabetes) ያለበት ልጅ ያላቸው ወላጆች ለልጃቸው ህክምና ተስፋ የሚሰጥ ዜና መፈለግ ያለ ነው። ወላጆች የልጃቸው ህይወት ከኢንሱሊን መርፌ ነፃ እንዲሆን መመኘታቸው ተፈጥሯዊ ነው። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እነዚህ መሬት ያልያዙ ተስፋዎች አሳሳች ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዴም አደገኛ የሆኑ አሳች ዜናዎች የልጅን ህይወት ሊቀጥፉ ይችላሉ።

በዚህ ሳምንት በቲክቶክና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በጣም ሲታይ የነበረ አንድ መረጃ ነበር። ዜናው ‘የአይነት አንድ የስኳር ህመም ስርየት ተገኘለት፣ ከእንግዲህ ኢንሱሊን መርፌ መወጋት እስከወዲያኛው አከተመ እልልልልል አንኳን ደስ አላችሁ’ የሚል ይዘት ያለው የሚያጓጓ ብስራት የያዘ አሳሳች መረጃ ነው። ይህን መረጃ የሰሙ ወላጆች የስኳር ህመም ያለባቸው ልጆቻቸውን ይዘው እኔ ወደምሰራበት የግል ሆስፒታል ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት ልጄን ይሄን ህክምና አዝዙልን አሊያም ወደውጭ ሪፈር አርጉን እያሉ ሲጨነቁ ነበር።

አሁንም ቅድምም በሚናፈሱ ለታይታ የሚሰራጩ አሉባልታዎች በመታለል ኢንሱሊን ህክምናቸውን በማቋረጥ የሚሞቱትን ወገኖቻችንማ ቤት ይቁጠረው።

ይህ ጽሑፍ ሕይወት አድን የሆነውን የኢንሱሊን ሕክምናን አስፈላጊነት በማጉላት አሁን ያሉ የአይነት 1 ስኳር ህክምና እውነታ፣ ወቅታዊ ተስፋ ሰጭ ግኝቶችና ቀጣይ የምርምር አቅጣጫዎችን ግልጽ ለማድረግ ያለመ ነው።

የዓይነት 1 የስኳር ሕክምና አሁናዊ መመሪያዎች ምን ይላሉ?

የቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ የአይነት አንድ ስኳር ህክምና አለም አቀፍ መመሪያዎች እንደሚደነግጉት ኢንሱሊን ውጤታማና አይተኬ አማራጭ ነው። የተሻለ የግሉኮስ ቁጥጥር ለማምጣት እና የስኳር ህመም ተያያዥ የጤና ችግሮችን ለመከላከል አይነተኛ መፍትሄ ኢንሱሊን ነው።
ኢንሱሊን ለአይነት 1 የስኳር ሕክምና የማዕዘን ድንጋይ ነው። ኢንሱሊን እንደዉሃና ኦክስጅን ሁሉ ለሜታቦሊዝም መሳለጥ፣ ለጤናማ እድገትና ሰውነት ግንባታ አስፈልጊ የሆነ ለህልውና ወሳኝ ሆርሞን ነው። ስለሆነም ይህ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ኢንሱሊንን በተፈጥሮ ማመንጨት ስለማይችሉ መደበኛ የኢንሱሊን መርፌ ወይም የኢንሱሊን ፓምፕ መጠቀም ያስፈልጋቸዋል። የኢንሱሊን ሕክምናን ማቆም በጥቂት ቀናት ለሕይወት አስጊ ይሆናል።

በአይነት 1 የስኳር ህክምና ላይ የሚታዩ ያልተሟሉ ጉድለቶች (unmet needs) ምንድን ናቸው?

ዘመኑ የደረሰበት የተሻሻለው የኢንሱሊን ሕክምና እና ክትትል ጥበብ የህመሙ ተጠቂዎችን ጤናና ህይወት በእጅጉ ያሻሻለና ረጅም፣ አምራችና ደስተኛ ህይወት መምራትን ያስቻለ ቢሆንም አሁን ያለው ሕክምና ተግዳሮቶች አለው። ብዙ መስተካካልና የበለጠ መሻሻል ያለባቸው ያልተሟሉ ፍላጎቶች አሉ። ለአብነትም ከ20-25% ታካሚዎች የስኳር ቁጥጥራቸው በሚፈለገው መጠን ግብ አይመታም፤ በርካታ ታካሚዎች ተደጋጋሚና አደገኛ የስኳር ማነስ (hypoglycemia) ያጋጥማቸዋል፤ እንዲሁም ከኢንሱሊን መድሃኒት ጋር የተያያዘ መጠነኛ ክብደት መጨመር አሁን አለም የደረሰብት ህክምና ገደቦች ናቸው።

እነዚህ ያልተሟሉ ፍላጎቶችን ለመሙላት ነው ተመራማሪዎች የተለያዩ የሙከራ መድሃኒቶችን እና ፈውስ ሊሆኑ የሚችሉ መፍትሄዎችን ማሰስ የቀጠሉት። የአዳዲስ ሕክምና አማራጮች ፍለጋ ከተቻለም ፈጽሞ ለማዳንና አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ መፍትሄዎችን ለመፈልሰፍ የተራቀቁ ምርምሮችን ማድረግ እንደቀጠለ ነው። እስካሁንም አስደናቂ እመርታዎች ተመዝግበዋል።

አዳዲስ የአይነት አንድ ስኳር ለማዳን የሚሞከሩ ህክምናዎችና ምርምሮች

1️⃣ የቆሽት ወይም ቤታ ሴል ንቅለ ተከላ (Beta Cell Replacement Therapy: whole pancreas transplantation or Islet Cell Transplantation)

2️⃣ የቆሽት ሕዋስ ማደስ ሕክምና (Beta Cell Regeneration therapy)

3️⃣ የዘረመል አርትዖት (Gene Editing)

ከላይ የጠቀስናቸው በሙከራ ደረጃ ያሉ ህክምናዎች የረጅም ጊዜ ጤና የማሻሻል ትልቅ ተስፋ የሰጡ ሆነዋል።

እነዚህ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ደረጃ ሕክምናዎች ገና ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ አይደሉም። አበረታች ውጤቶችን ቢያሳዩም ገና በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ለሁሉም ታካሚ በሰፊው ከመሰጠታቸው በፊት ብዙ ተጨማሪ ጥብቅ ምርመራ እና ማሻሻያ ያስፈልጋቸዋል።

የጠቀስናቸው እና ሌሎችም የሚያጓጉ ሕክምናዎች እስኪገኙ ድረስ ዓይነት 1 የስኳር ህመምን በኢንሱሊን ማከም ና ስኳርን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። እነዚህን ለዉጦች በተስፋ እየተጠባበቅን አሁን ላይ የተረጋገጡ ተጨባጭ ህክምናዎችን በቁርጠኝነት መቀጠል ይገባል። ስለሆነም አሁን ላይ ያሉትን የሚመከሩ የተረጋገጡ ህክምናዎች መቀጠል አስፈላጊ ነው። የኢንሱሊን ህክምና ፍጹም እንከን የለበትም ባይባልም ሕይወት አድን ነው።

የዚህን ጽሁፍ ሙሉ መረጃ በዶ/ር መላኩ ታዬ ብሎግ https://melakutaye.com/type-1-diabetes-current-treatment-and-future-hopes/ እንዲያነቡና ለሌሎችም እንዲያጋሩ በትህትና እጋብዛለሁ።

ቴሌግራም https://t.me/hakimmelaku
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hakimmelaku
ግብረ መልስ ወይም አስተያየት ለመስጠት https://maps.app.goo.gl/twmS9fq7LiG1eRnq9
WhatsApp/Telegram consults at +251921720381

Dr. Melaku Taye (Endocrinologist, Lipidologist, Health advocate practicing at Tikur Anbessa Specialized Hospital, Addis Ababa University)

Get social with Hakim on Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207

@HakimEthio


Репост из: FBC (Fana Broadcasting Corporate)
በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዜጎች ከስኳር ሕመም ጋር እንደሚኖሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከስኳር ሕመም ጋር እንደሚኖሩ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ዓለም አቀፍ የስኳር ሕመም ቀን በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡ የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሕይወት ሰለሞን (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ስኳር…

https://www.fanabc.com/archives/270461






Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
#መልዕክት❤️

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባ ዶ/ር ዳዊት እሸቱ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ ለወላጆች መልዕክት አስተላልፈዋል።

" በተለይም አራስ ህፃናት ሲጠቡ የሚያልባቸው ፣ የሚደክማቸው ፣ በአጣዳፊ የሚተነፍሱ ፣ ኪሎ አልጨምር የሚሉ ፣ ጉንፋን በቶሎ ቶሎ የሚይዛቸው ፣ እድገታቸው የሚዘገይ ከሆነ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መሄድ ይገባል በዚህም ከበሽታው መታደግ ይቻላል " ብለዋል።

@tikvahethiopia




Репост из: Hakim
‘የስኳር ህመም’ አለብህ/ሽ መባል በብዙዎች ልብ ውስጥ አስፈሪ ስሜት የሚፈጥር ሲሆን በአለም አቀፍና በአገራችን ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ ያለ በሽታ ነው።

በጊዜ በቂ ህክምና ካልተደረገ ለበርካታ የጤና ጠንቆች ይዳርጋል። ሆኖም ግን ከአመት አመት የተሻለ ህክምና እየተገኘለት ስለሆነ የስኳር ህመም በተገቢው መንገድ ከታከመ ታካሚው እንደማንኛውም ሰው ለጅም እድሜ መኖር፣ ጤናማና አምራች ህይወት መኖር ይቻላል።

እኤአ በ1921 ኢንሱሊን የተባለውን የስኳር መድሃኒት ያገኙትን ዶ/ር ባንቲንግ የልደት ቀን ለማዘከር ህዳር 14 ቀን የስኳር ቀን ሆኖ ይከብራል። የህዳር ወርም የስኳር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ሆኖ ይከበራል።

ይህን ምክንያት በማደርግ የዚህ ወር ትኩረቴን በስኳር ዙርያ ግንዛቤን ለማስፋት እና የተሳሳተ መረጃን ለማረቅ የሚደረገውን ሃገራዊ ጥረት በማገዝ የራሴን በጎ አስተዋጾ ለማድረግ በድህረ ገጽና ማህበራዊ ሚዲያዎች በመረጃ የተደገፉና የተረጋገጡ ትምህርታዊ ጽሁፎችን የማጋራ ይሆናል።

ባለፈው አንድ አመት ብቻ ከ50 በላይ ትምህርታዊ ጽሁፎችን በኦንላይና አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ያካፈልኩ ሲሆን በአመዛኙ የሚያበረታታ በጎ ግብረ መልስ አግኝቻለሁ። እነዚህን የጤና ትምህርቶች ማሰራጨት ሰዎች በጤናቸው ላይ የተሻሉ በመረጃ የተደገፉ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ እና ለጤናማ ህይወት አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንደአንድ ግብኣት ይረዳል ብዬ አምናለሁ።

ስለሆነም ድህረ ገጽና ማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቼን በማጋራት እንዲሁም ሌሎችን ወደቻናሌ በመጋበዝ እንዲተባበሩኝ በትህትና እጠይቃለሁ። ማንኛውም የጤና ባለሙያ እነዚህን መረጃዎች ለትምህርታዊ አላማ በማንኛውም መንገድ መጠቀም ይችላል።

ቴሌግራም https://t.me/hakimmelaku
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@hakimmelaku
ፌስቡክ https://web.facebook.com/hakimmelaku
ድህረ ገጽ www.melakutaye.com
ግብረ መልስ ወይም አስተያየት ለመስጠት https://maps.app.goo.gl/twmS9fq7LiG1eRnq9
WhatsApp/Telegram consults at +251921720381

#Quality-Health-Information-For-All-Ethiopians

Dr. Melaku Taye (Endocrinologist, Lipidologist, Health advocate practicing at Tikur Anbessa Specialized Hospital, Addis Ababa University)

Get social with Hakim on Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207

@HakimEthio


Репост из: TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ🚨

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት የጨቅላ ህፃናት እንዳይጠቀሙት የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳስቧል፡፡

ቴግሬቶል የተሰኘ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ (Oral Suspension) መድኃኒት ኖቫርቲስ ፋርማ ሽዌይዝ AG/ Novartis Pharma Schweiz AG በተባለ የገበያ ፍቃድ ባለው የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ የሚመረት ነው።

ቴግሬቶል (ካርባማዜፔይን) 100 mg/5ml Oral Suspension (OS) የተሰኘው መድኃኒት አብዛኛውን ጊዜ አጠቃላይ ለሚጥልና ከፊል መንቀጥቀጥ/ management of generalized tonic clonic and partial seizures ለማከም የሚያገለግል ነው።

ይሁን እንጂ የተጠቀሰው መድኃኒት በውስጡ በሚይዘው ፕሮፓይሊን ግላይኮል (propylene glycol) የሚባል ንጥረ-ነገር መጠን ምክንያት ለጨቅላ ሕፃናት ማለትም ከ4 ሳምንታት በታች ለሆኑ ሕፃናት ወይም በሶስት ወራት የመወለድ ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት ሊወስዱት እንደማይመከር ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

ተቋሙ ፥ በዚህ ምርት ውስጥ ከሚገኙት ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነው ፕሮፓይሊን ግላይኮል ለምግብ እና ትንባሆ ምርቶች እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል እና መዋቢያዎች በአጠቃላይ በአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ ይታወቃል ብሏል።

ይሁንና በዚህ ምርት ውስጥ ያለው መጠን በዚህ የማሳወቂያ መልዕከት ላይ ከተጠቀሱት ለጨቅላ ሕፃናት እና ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ ከደህንነት ገደብ በላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ነው ያለው።

ስለሆነም ይህንን መድኃኒት በጨቅላ ሕፃናት ጊዜያቸው ሳይደርስ ለተወለዱ ሕፃናት እስከ ሦስት ወር ድረስ መጠቀም ጉዳቱ ከጥቅሙ የሚያመዝን በመሆኑ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች መድኃኒቱን ለተጠቀሱት የእድሜ ክልል ከማዘዝ እና ከማከፋፈል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም መድኃኒቱን እንዳይጠቀም መልዕክት አስተለልፏል።

@tikvahethiopia

Показано 14 последних публикаций.