የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ ፀድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።
አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን
አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚያሻሽል ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡
አዋጁ የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።
አዋጁ የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።
የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል “ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ “ ያስገድዳል።
ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለ ነው።
https://t.me/Shields_Law