ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ!
የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የአማራ እናት አምጣ የወለደችው ፋኖ በዱር በገደል "አይደለም መሳሪያቸውን፤ ቀበቶቷቸውን እናስፈታዋለን" ብለው የገቡትን የእነ አብይ አህመድ ቡድንና ጋሻጃግሪዎችን ድባቅ እየመታ ባለፈው አንድ ዓመት ከመንፈቅ አማራዊ አኩሪ ተጋድሎዎችን እያደረገ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ በወሎም አደረጃጀቶቹን እያጠናከራና እያዘመነ በጀግኖች መስዋዕትነት ተጋድሎዎችን እያደረገ ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ በርካታ ስራዎችንም እየሰራ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ በወሎ አካል የሆነው የላስታ ጀነራል አሳምነው ኮር በሚንቀሳቀስበት ላስታ ላሊበላ አካባቢ የገና በዓል በድምቀት እንደሚከበር ይታወቃል። በመሆኑም አገዛዙ ይህንን ደማቅ ሐይማኖታዊ ክብረ በአል የራሱንና የፖለቲካና ወታደራዊ ትርፍ መጠቀሚያ ለማደረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፤ ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዝ ተከታዮችን ጥብቅ ትዕዛዞችንና መምሪያዎችን አውርጃለሁ።
፩. እንግዶቻችን የላሊበላ ኤርፖርትን ጨምሮ በሹምሽሃ ቀበሌ፣ ከሲመኖ ወንዝ ምላሽ ወደ ላሊበላ ከተማ እና ከናዕኩተላብ ከተማ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይቻል።
፪. የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሲቭል አቬሽን ባለስልጣን ከሲቪል መንገደኞች ውጭ አገልግሎት እንዳይሰጥ።
፫. በቀጠናው የሚንቀሳቀሰው የላስታ ጀነራል አሳምነው ኮር በተራ ቁጥር ፩ እና ፪ ያሉትን የመቆጣጠርና የማስከበር ሥራ እንዲሰራ በተጨማሪም አሁን ባለን መረጃ መሰረት ወደ ላስታ የሚያስገቡት በኩልመስክ፣ በጋሸና እና ከሰቆጣ ወደ ላሊበላ ከተማ የሚያስገቡት መስመሮች በድርጅታችን ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የተረዳው አገዛዝ በቅዱስ ላሊበላ ኤርፖርት ሰራዊት ለማራገፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አውቃችሁ፤ የአገዛዙ ሰራዊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይዞ ለመንቀሳቀስ ከተረጋገጠ አየር መንገዱን ጨምሮ አውሮፕላኑ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የመካናይዝድ ኃይሉ ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
ዋርካው ምሬ ወዳጆ
የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ
ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
@Showapress