#ኢትዮጵያ
በእነ ዳንኤል ዮሐንስ ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ
የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሦሥት ክሶችን መሰረተ፡፡
አቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ አውሮፕላንን አላግባብ በመያዝ፣ በማህበራዊ ሚደያ አማካኝነት በቀጥታ በማስተላለፍ መልካም ስም የሚያጎድፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርአት አማካኝነት በማሰራጨት እና የመንግስት ሰራተኛ ኦፊሻላዊ የስራ ግዴታውን እንዳይፈፅም መቃወም እና አለመታዘዝ የሚሉ ናቸው፡፡
በሁለቱ ወንጀሎች ሁሉም ሲከሰሱ የመዝገቡ መጠሪያ የሆነው በቲክክቶክ የሚታወቀው ዮሀንስ ዳንኤል በሶስቱም ተከሷል፡፡ለሁለት ሰአታት ሙሉ ከአውሮፕላን አንወርድም፤ ይከስከስ በማለት ሌሎችም እንዳይወርዱ በማሳደም በቲክቶክ ቀጥታ በማሰራጨት ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት በቲክቶክ ስሙ ዮኒ ማኛን ቀጥታ በማስገባት የአየር መንገዱ ስም እንዲጎድፍ አድርጓል የሚለውንም አቃቤ ህግ ዘርዝሮበታል፡፡