Subi Time™ ሱቢ ታይም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Addisababa, Ethiopia🇪🇹

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት
መካከለኛው ምስራቅ እስራኤል ኢራን ለተኮሰችባት 200 ገደማ ባለስቲክ ሚሳይሎች የበቀል እርምጃ ትወስዳልች በሚል ስጋት ውስጥ ገብቷል

"በኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸምን በኋላ አለም ኃያልነታችንን ይረዳል" ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ጋላንት ተናገሩ ።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት በኢራን ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ አለም ያላቸውን ኃያልነት እንደሚረዳ እና ጠላት ትምህርት እንደሚወስድ ለአየር ኃይል አባላት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

እስራኤል፣ቴህራን በስድስት ወራት ውስጥ ከአራት ሳምንታት በፊት ለሁለተኛ ጊዜ በእስራኤል ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ ጥቃት የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅታለች።

"ኢራንን ካጠቃን በኋላ እንዴት ስትዘጋጁ እንደነበር እስራኤል ውስጥ እና በተቀረው አለም መረዳት ይኖራል" ሲሉ ጋላንት ሀትዘሪም በተባለ የጦር ሰፈር በተቀረጸ ቪዲዮ ለአየር ኃይል አባላት ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ጋላንት አክለውም በኤክስ ገለጻቸው "ከእነሱ ጋር በነበረኝ ንግግር ኢራንን ካጠቃን በኋላ ሁለም የእናንተን ኃያልነት፣ ዝግጅታችሁን እና ስልጠናችሁን ይረዳል በሚለው ላይ ትኩረት አድርጌያለሁ" ብለዋል። መካከለኛው ምስራቅ እስራኤል ኢራን ለተኮሰችባት 200 ገደማ ባለስቲክ ሚሳይሎች የበቀል እርምጃ ትወስዳልች በሚል ስጋት ውስጥ ገብቷል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት እስራኤል በፍልስጤሙ ታጣቂ ሀማስ ላይ በጋዛ እና በኢራን በሚደገፈው ሄዝቦላ ላይ በሊባኖስ የምታደርገውን ጥቃት አጠናክራለች።

ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር።

አሜሪካ ግጭቱ አድማሱን እንዳያሰፋ ትፈልጋለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የእስራኤል የበቀል እርምጃ ጦርነቱን ማስፋፋት የለበትም ሲሉ ተናግረዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም ቀደም ሲል እስራኤል ጦርነቱ እንዳይስፋፋ እንድትጠነቀቅ እና በኢራን የኃይል እና የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት እንዳታደርስ ጠይቀዋል።

እስራኤል የሀማስን እና የሂዝቦላ መሪዎችን እና ተተኪዎቻቸውን ብትገድልም፣ ማጥቋተን የምትቀንስ አይመስልም።

እስራኤል በሰሜን በኩል ከሄዝበልላ ጋር የምታደርገው ውጊያ ዋነኛ አላማ በድንበር ላይ ሲካሄድ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ሸሽተው የነበሩ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ወደ ቦታቸው መመለስ ነው።


"በኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸምን በኋላ አለም ኃያልነታችንን ይረዳል"- የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ጋላንት


The U.S. agreed to give Ukraine $800 million in military aid that will go toward manufacturing long-range drones to use against Russian troops, Ukraine’s leader said, fulfilling a longtime Ukrainian goal of getting Washington to buy weapons from manufacturers in Ukraine instead of primarily in America.

#thenewyorktimes
@subitime


በቁጥጥር ስር ውሏል




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
መርካቶ ሸማ ተራ




ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን(CAF) 46ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የሚገኙት የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የጉባኤው ተሳታፊዎችን በዓድዋ ድል መታሰቢያ አቀባበል አድርገውላቸዋል::

የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ እና የጉባኤው ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአቀባበል መርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
subitime





Показано 10 последних публикаций.