የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ፈተና በዛሬው ዕለት ሲሰጥ ውሏል።
ተፈታኞች በዛሬው መርሐግብር የአካውንቲንግ እና የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ፈተና ወስደዋል።
የመጀመሪያ ቀን ፈተና አሰጣጡ በርከት ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስኬታማ የነበረ ቢሆንም፤ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ችግሮች እንደነበሩ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደረሱ መረጃዎች ያሳያሉ።
ፈተናው ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት ዘግይቶ መጀመር፣ የቴክኒክ ችግር እንዲሁም የመብራት መቋረጥ ችግር መከሰታቸውን ሰምተናል።
በሌላ በኩል እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ወደ ፈተና ማዕከል ይዘው ለመግባት የሞከሩ ተፈታኞች መያዛቸውም ታይቷል።
እስከ መጪው አርብ ጥር 30/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና፤ በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው
176 ሺህ ተማሪዎች እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
@tikvahuniversity