Ministry Of Education


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


📚ይህ ትክክለኛው የትምህርት ሚኒስትር የተማሪዎች መረጃ ማቀበያ ገፅ ነው
🔵ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት: @STBookbot
🔴ለFreshman : @Freshman_Robot
«Buy Ads» @MoeAds_bot or https://telega.io/c/Tmhrt_minister

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


Grade 12 English Model Exam.pdf
1.1Мб
Grade 12 Maths Model Exam.pdf
1.3Мб
📚English & Maths Model Exam

🔘Grade 12

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ክፍያቸውን ለፈፀሙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት ሳይለቀቅ መዘግየቱይታወቃል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማት ክፍያቸውን ሳያደርጉ በመዘግየታቸው የተፈታኞቹ ውጤት ሳይለቀቅ ቆይቷል።

ተቋማቱ ክፍያውን በመፈፀማቸው የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለየተቋማቱ መለቀቁን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምና እና ጤና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
*******

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምና እና ጤና ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 366 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በማስተርስ እና ፒኤችዲ መርሐ-ግብሮች ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 112ቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሆስፒታሉን 100ኛ ዓመት እና የዩኒቨርሲቲውን 70ኛ ዓመት ምስረታን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት እስከ ነገ ይለቀቃል።

የመውጫ ፈተናውን በግል የወሰዱ ድጋሜ ተፈታኞች ውጤትም ወደየተፈተኑበት ተቋማት ይላካል።

ምንጭ፡ (ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በ35 ፕሮግራሞች 1481 ተማሪዎችን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና አስፈተኖ

👉 በ 13 ፕሮግራሞች 100%
👉 በ 8 ፕሮግራሞች ከ90%-99%
👉 በ 6 ፕሮገራሞች ከ 75%-89%

እንዲሁም እንደ ዩኒቨርሲቲ ካስፈተናቸው አጠቃላይ ተማሪዎች ውስጥ 👉87% የሚሆኑትን ማሳለፍ ችሏል፡፡

ዩንቨርስቲው ለዚህ ዉጤት መሳካት ባለድርሻ አካላትን አመስግኖ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሀገራዊው የ2017 አጋማሽ በተሰጠው ብሔራዊ የመውጫ ፈተና ከተፈተኑ 6 ትምህርት ክፍሎች ሦስቱ (3) 100% በማሰለፍ በኢትዮጵያ ትልቁን #ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጿል።

አጠቃላይ ከተፈተኑ 240 ተመራቂ ተማሪዎች 223 ወይም 93% በከፍተኛ ውጤት አልፈዋል።

እንኳን ደስ ያለን አላችሁ👏👏


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ መደበኛ ተማሪዎቹ መካከል 98 በመቶ ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት (ከ50 በላይ) ማምጣታቸውን ገልጿል፡፡

የኤክስቴንሽን፣ የክረምት እና በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞቹ መካከል ደግሞ 77 በመቶዎቹ የማለፊያ ውጤት ማግኘታቸውን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ውጤት #እንዳልደረሳቸው የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር ገለፀ፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት ለኮሌጆች እንደተላከ ትናንት የተገለፀ ቢሆንም፤ የተፈታኞች ውጤት እስካሁን ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመድረሱን የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር #ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

የተማሪዎች ውጤት ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለመላኩን ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ የግል ትምህርት ተቋማቱ ማረጋገጣቸውን የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር መነጋገራቸውን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ "ቴክኒካል የሆኑ ነገሮችን ጨርሰን እንልካለን" መባላቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ውጤቱ ተጠናቅሮ ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ እስከሚላክ ድረስ የግል ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡


[ይህ ዘገባ የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ወደየትምህርት ክፍላችሁ የተላከ ስለሆነ በየትምህርት ክፍላችሁ በኩል በመሄድ ማየት ትችላላችሁ ሲል ገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም የመውጫ ፈተና ውጤት መመልከት እንደሚቻል አሳውቋል።

👇👇👇
https://eap.ethernet.edu.et.

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


2017 midyear exit exam result Feb 13, 2025 (1).pdf
3.0Мб
#Arbaminch #ExitExam

ዩንቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረግ ጀምረዋል📣

Arba Minch University Office of the registrar and Alumni Directorate 2017 EC Exit Exam Result Reporting Format (Excluding Summer Teachers Result)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

14k 0 31 22 65

#Update #EXITEXAM

ነገ በዩኒቨርሲቲዎቻቹህ በኩል ታያላቹህ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ህብረት ፕሬዝዳንት የሆነው ሃየሎም ስዩም የመውጫ ፈተና ውጤት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሬጅስትራር መላኩንና ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል ነገ ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#Exit_Exam_Result

ተፈታኞች እስካሁን ውጤት ማየት አልቻሉም‼️

በዛሬው ዕለት የ2017ዓ.ም. የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጎ የነበረው ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ለውጤት መመልከቻ ያጋራው ሊንክ ውጤት ይፋ በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መስራት አቁሟል።

ውጤታችሁን በጉጉት በመጠበቅ ላይ ለምትገኙ ተፈታኞች ችግሩ ተቀርፎ ሊንኩ ያለምንም ችግር መስራት ሲጀምር የምናሳውቃቹህ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


የመውጫ ፈተና ውጤት መመልከቻ ሊንኩ እየሰራ እንዳልሆነ አስተውለናል።

ችግሩ ከእስኪቀረፍ በትዕግስት ጠብቁ።


ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


"ከአማራ ክልል ተማሪዎች 60 በመቶ የሚጠጉት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው።" - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

በአማራ ክልል ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ 59.8 በመቶ የሚሆኑት፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን “ከትምህርት ገበታ ውጭ” መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ገልፀዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 32 በመቶ የሚሆኑት ከመማር ማስተማር ተልዕኮዋቸው መስተጓጎላቸውንም በክልሉ ም/ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት “በተጨባጭ በመማር ማስተማር ሂደት እየተሳተፉ” የሚገኙ ተማሪዎች ብዛት 2.78 ሚሊዮን እንደሆኑ ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል በዘንድሮው በጀት ዓመት ለመመዝገብ ታቅዶ የነበረው አጠቃላይ የተማሪዎች ብዛት 7.1 ሚሊዮን እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

በአማራ ክልል በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባራቸውን ያከናወኑ ትምህርት ቤቶች ብዛት 7,444 መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል ያሉት ትምህርት ቤቶች ብዛት 10,983 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 32 በመቶ በሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ተልዕኳቸው ተስተጓጉለው መቆየታቸው ተገልጿል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ትምህርት ሚኒስቴር ጅ ከ Comprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበውን ቅሬታ እያጣራ እንደሚገኝ አስታወቀ።

የዘንድሮ የ Comprehensive Nursing ፈተና ብሉፕሪንት ላይ መሠረት ያላደረገ ነው በሚል በተፈታኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መሰማቱን መዘገባችን ይታወሳል።

ከዚህ ቅሬታ ጋር በተያያዘ ትምህርት ሚኒስቴር የComprehensive Nursing የመውጫ ፈተናን እያጣራ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ህብረት ሰምተናል።

ከ Comprehensive Nursing በተጨማሪም ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ላይ ተመሳሳይ ቅሬታ በብዛት ደርሶናል።

በተደጋጋሚ ከደረሱን ቅሬታዎች መካከል የፊዚክስ የመውጫ ፈተና ይገኝበታል።

የዘንድሮው የፊዚክስ የመውጫ ፈተና Blue print ላይ መሰረት ያላደረገ፣ የጥያቄ እና መልስ ስህተት ያለው እንዲሁም ሁሉንም ኮርሶች ያላማከለ መሆኑን በመጥቀስ ተፈታኞች ፈተናው ይገመገም ዘንድ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ ተፈታኞች በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ፈተና እንዳለፋቸው ገልፀው እስካሁን ላቀረቡት ጥያቄ ምንም ዓይነት ምላሽ እንዳላገኙ ነግረውናል።


ትምህርት ሚኒስቴር በመውጫ ፈተናው የቀረቡ ቅሬታዎችን ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ እናሳውቃቹሃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


የመውጫ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

በርካታ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል የሚል ጥያቄ አድርሰውናል።

👉እስካሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት የመውጫ ፈተና ውጤት #ከሁለት ቀን በኋላ ይፋ ይደረጋል የሚል መረጃ ሰምተናል።

(በተጨማሪ መረጃ እንመለሳለን)

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


ባለፈው ሳምንት ከተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ የ Comprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል፡፡

ፈተናው ከBlue Print ውጪ መዘጋጀቱን እንዲሁም የጥያቄ መደጋገም መኖሩን የገለፁት ተፈታኞቹ፤ ትምህርት ሚኒስትር ቅሬታቸውን በማየት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ከነርሲንግ ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡ ቲክቫህ ጥያቄውን ለሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ያቀረበ ሲሆን፤ የሚሰጡንን ምላሽ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል "ፈተናዎቹ ዘግይተው መሰጠት በመጀመራቸው የሰዓት ዕጥረት እንዲፈጠር ማድረጉ" እንዲሁም "የኔትወርክ እና የመብራት መቆራራጥ ችግሮች" ሌሎች በፈተናው ወቅት የታዩ ችግሮች እንደነበሩ ተፈታኝ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ገልፀዋል፡፡

እንደ ተንቀሳቃሽ ስልክ ያሉ የተከለከሉ ነገሮችን ወደ ፈተና ጣቢያ ይዞ ለመገባት መሞከር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ማጋጠሙን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሞባይል ስልክ ሲጠቀሙ የተያዙ እና በመፈተኛ ክፍሎች ሞባይል ስልኮችን ይዘው የተገኙ 128 ተማሪዎችን ከፈተና ማዕከሉ እንዲሰናበቱ ማድረጉንና ውጤታቸው እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

ምስል፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለ108 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማጎልበቻ ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጥቷል።

ተማሪዎቹ ከአርባ ምንጭ፣ መቐለ እና ድሬዳዋ ከተሞች የተውጣጡ ናቸው።

English Access Scholarship የተሰኘው ፕሮግራሙ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑና ወደፊት የስኮላርሺፕ ዕድሎችን ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።

ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና፣ ዓለም አቀፍ ዜግነት እንዲሁም የአሜሪካ ባህልና ዕሴቶች ላይ ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ስልጠናው የተማሪዎቹን የተግባቦት፣ ትብብር እና መሪነት ክህሎቶች በሚያጎለብት መልኩ ይሰጣል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister

Показано 20 последних публикаций.