235 ሰዎችን የሚይዘው አሳንሰር (ሊፍት)
#ቴክኖ_ቅምሻበፊንላንድ ሊፍት ኩባንያ ኮን በ2022 በህንድ ሙምባይ በሚገኘው ጂዮ ወርልድ ሴንተር ህንፃ ውስጥ በዓለማችን የመጀመሪያ የሆነውን 235 ሰዎችን የሚይዘው አሳንሰር (ሊፍት) ገጥሞታል።
ይህ ትልቁ የመንገደኞች ሊፍት የስቲዲዮ አፓርታማ ያክላል የተባለ ሲሆን 16 ቶን የሚመዝንና በ9 የብረት ኬብሎች የተደገፈ ነው፡፡ አሳንሰሩ ሰዎችን ከማጓጓዝ በተጨማሪ ለሰርግና ለአርት ኤግዚብሽን ማሳያ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ሲሆን 25.78 ስኩየር ሜትር ስፋት ያለውና ለተመልካች ውብ የሆነ እይታና የአትክልት ቦታ ያካተተ ነው።
አሳንሰሩ 18 ትላልቅ ፑሊዎች፣ 9 የብረት ኬብሎች እና በብረት ዓምዶች ላይ የተስተካከሉ ሀዲዶችን ባቀፈ አዲስ የፑሊ ጨረር ሲስተም ላይ የተሰራ ነው ተብሏል።
የዓለማችን ትልቁ የመንገደኞች አሳንሰር (ሊፍት) ልዩ ባለ አራት ፓነል የመስታወት በር፣ የመስታወት ግድግዳዎች ፓኖራሚክ እይታዎችን እና ክሪስታል-የተጣበበ ጣሪያን ያሳያል። በአምስት ፎቆች መካከል ብቻ የሚጓዝ ቢሆንም በሴኮንድ 1 ሜትር ፍጥነት በመጓዝ ሪከርድ ሰባሪው ሊፍትም ሆኗል።
ሊፍቱ ውስጥ ተጓዦች ሲደክማቸው አረፍ የሚሉበት 2 ምቹ ሶፋዎችም አሉት፡፡
የኮን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ኢሚት ጎሳይን የዓለማችንን ትልቁን የህዝብ ማመላለሻ አሳንሰር (ሊፍት) ለደንበኞቻችን ችግር ፈች የሆነ ፕሮጀክት በመስራታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡
👇
https://shorturl.at/rT679