የግብርና ሚኒስቴር ለሴት አርሶ አደሮች የውሃ ፓምፖችን አበረከተ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስቴር በጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴት አርሶ አደሮች 20 የውሃ ፓምፖች አበረከተ።
ግብርና ሚኒስቴር የሴት አርሶ አደሮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን በማስተባበር የተገዙና በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራጩ 100 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለክልሎች እያስረከበ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም በሚኒስቴሩ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በመገኘት በዞኑ ከተለያዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ሴት አርሶ አደሮች 20 የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን አስረክበዋል።
ሴት አርሶ አደሮችን በማበረታታት እና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቅሰው በቀጣይ የሴት አርሶ አደሮችን አቅም ለማሳደግ የሚደረጉ እገዛዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡