የታህሳስ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ ማሳሰቡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡