Фильтр публикаций


የኢኮኖሚ እንቆቅልሽ! ! ለጤና አደጋ ሆነው በመንግስት የሚመረቱ!

የብዙ ሀገራት መንግስታት ለህይወት አደጋ የሆኑ ምርቶችን በሀገራቸው እንዳይመረትም ሆነ ዜጎቻቸው እንዳይጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ አያግዱም! ለምን ይመስላችኋል!

በመንግስት ለጤና አደጋ የሆኑ ምርቶች የሚፈጥሩትን ህመምን ለማከም ከፍተኛ የህክምና በጀት ይመደባል!

ለጤና እንደሚጎዳ እየታወቀ በመንግስት ፍቃድ ስለሚመረቱ ምርቶች የሚጠቀሱ ምክያቶችን በምሳሌ እንመልከት!https://youtu.be/UOxmX2rS6RI


በንግድ ጦርነቱ ከማን ጎን መቆም ያዋጣል? ለኢትዮጵያ ከአሜሪካ እና ከቻይና የተሻለ አጋር ማን ይሆናል?

በቅርቡ በአሜሪካ እየተጣለ ያለውን ታሪፍ ተከትሎ ሀገራት የንግድ አጋር ፍለጋ ላይ ናቸው!

ቻይና አልጨበጥ ባለው የአሜሪካ ውሳኔ ምክንያት ወደ ሌሎች የንግድ አጋር ወደሚሆኑ ሀገራት እየዞረች ነው!

ኢትዮጵያ የንግድ ጦርነቱ እየጦዘ ከቀጠለ ከማን ጎን መቆም ያዋጣታል!

በንግድ ጦርነት እንደ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት የሁለቱም ወዳጅ መሆን ከባድ ነው!

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/k_y2IKUymCo


በኢትዮጵያ ኢኖሚያዊ ምክንያት የሌለው ዋጋ ለምን ይፈጠራል?

መንግስት ዋጋን ፍትሃዊ የማድረግ አቅም አለው?

ዜጎች እንዴት መንግስት ከግል ሴክተር ገበያ ፍትሃዊ ዋጋ እንዲፈጠር እንዲያደርግ ይጠብቃሉ?

ትንታኔውን እንመልከት....https://youtu.be/V41xBdFOCeE






#ለመረጃ፡ በዛሬው የዶላር ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 131.4961 ብር ሆኗል! ለጨረታ የቀረበውን 70 ሚሊየን ዶላር 26 ባንኮች እንደተከፋፈሉት ብሔራዊ ባንክ ገልጿል!

የዛሬ 15 ቀን የነበረው ጨረታ አማካይ የጨረታ ዋጋ 131.7095 ብር ነበር!


ዶላር ፈላጊዎች ትንሽ ተረጋጉ!

ብሔራዊ ባንክ ለነገ 70 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ አውጥቷል!

ብሔራዊ ባንክ በየ15 ቀኑ የዶላር ጨረታ አወጣለሁ ባለው መሰረት ቀኑን ጠብቆ 70 ሚሊየን ዶላር ለሽያጭ አውጥቷል!

የባለፈው 15 ቀን ጨረታ ውጤት ብዙ ለወጥ በገበያው ፈጥሯል! በ3ኛ ጨረታ አማካይ ዋጋ መቀነስ አሳይቷል!

ይህ ጨረታ ገበያው ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ይኖረዋል!

የጨረታው ልምምድ የምንዛሬ ገበያውን እንዴት እንደሚወስነው እንመልከት!https://youtu.be/Y0eO6J-yAhQ


#ለመረጃ፡ አሜሪካ በቻይና ላይ የጣለችዉን ቀረጥ ወደ 245% አሳድጋለች።

ወደፊት በድርድር ወደታች ለሚያወርዱት በቀልድ የታሪፍ ተመን ጉልበት እየተፈታተሹብን ነው!


የነገሮች ሁሉ መነሻ እና መድረሻ፡ Game Theory!

12 የተለያዩ ኢኮኖሚስቶች ኖቤል የወሰዱበት ጥልቅ ሃሳብ! Prison's Dilemma!

የግለሰብ፤ የድርጅት፤ የሃገር ጉዳይ ከዚህ ውጪ አይደለም!https://youtu.be/YKAr7ZMYi4k


#ለመረጃ፡ በነዳጅ የሚሠሩ ባለሁለት እግር (ሞተር ሳይክል) እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ኢብራሂም ትራውሬ ቡርኪናፋሶን እያሻገረ ነው!

ECOWAS፤ IMF እና World Bank እየዛቱበት ቢሆንም አስደናቂ ለውጥ እያደረገ ነው!

አሁን ደግሞ ሰልባጅ ልብስ አልቀበልም በማለቱ ከትራምፕ ጋር መዛዛት ጀምሯል!

ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት የለወጥ መነሳሳት ምክንያት የሆነው ወጣቱ ወታደራዊ መሪ እያደረገ ያለውን ድንቅ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እርምጃዎች እንመልከት!

ሀገራቸውን በማይወዱ መሪዎች እየተመሩ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ህዝቦች መቼም ትራውሬን በማየት መቆጨት አለባቸው!

https://youtu.be/zoTfArJTIy4


እንደ አነቃቂ ንግግር አቅራቢዎች ሳይሆን እንደ ኢኮኖሚስት ስለ ገቢ እና የገቢ ምንጭ ማሳደግ እናውራ!

#ስለማታገኙት ገቢ ብትጨነቁ መደበኛ የገቢ/ወጪ ሁኔታ ጭንቀታችሁ ይቀንሳል!

ክርክራችሁን ቀንሱና ምክንያታዊ ሆነን ካወራን ማንም ሰው ገቢ እና የገቢ ምንጩን መለወጥ ይችላል!

https://youtu.be/XzW05IQ83gI


#ለመረጃ፦ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበት 13.6 በመቶ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል።

የምግብ ነክ ዕቃዎች የዋጋ ጭማሪ 11.9% ድርሻ የያዘ ሲሆን፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ የ16.2% የዋጋ ግሽበት ማሳየታቸውን እወቁልኝ ብሏል!


ትራምፕ በቻይና ላይ የተጣለው አጠቃላይ ታሪፍ 145% መሆኑን የገለጹ ሲሆን! ቻይና በምላሹ ከአሜሪካ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የተጣለው ታሪፍ ወደ 125% ከፍ መደረጉን አስታውቃለች!

ማን ዋጋ ይከፍል ይሆናል!
ዝሆኖቹ ወይስ ሳሩ!

በዝርዝር እንመልከተውhttps://youtu.be/lXsjemNSy-4


የንግድ ጦርነቱ በማን አሸናፊነት ይጠናቀቃል?

በቻይና እና አሜሪካ የንግድ ትግል ኢትዮጵያ እንዴት ዋጋ ትከፍላለች?

ጦርነቱን ለማሸነፍ ሀገራት ምን እያደረጉ ነው?

በዝርዝር እንመልከተው https://youtu.be/lXsjemNSy-4


ኢትዮጲያ ውስጥ የባንኮች አክሲዮን ዋጋ ቀንሷል!

ትርፋማ የሆኑ ባንኮች አክሲዮን ዋጋ እንዴት ይቀንሳል?

እጅ ላይ ያለን የባንክ አክሲዮን በርካሽ እንኳን ለመሸጥ ቀላል እየሆነ አይደለም!

በዚህ ወቅት አዋጪው ዋጋቸው የወረደውን የባንኮች አክሲዮን መሸጥ፤ መግዛት ወይስ ገዝቶ ማከማቸት!

ማን ይግዛ? ማን ይሽጥ?https://youtu.be/Sb7Xf8TUUoo




#ለመረጃ፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 711 ደንበኞቹ ያቀረቡትን የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ በመገምገም ለ698 (98%) ለሚሆኑ ደንበኞቹ በድምሩ የ122.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድልድል ማድረጉን ገልጿል።


ትራምፕ ሁሉንም ሀገራትን የሚያካትት ታሪፍ እየሳቁ ጥለዋል!

አሜሪካ ለሁሉም ሀገራት የየድርሻቸውን ታሪፍ በሰበር ዜና መልክ በዝርዝር አሳውቃለች!

ታሪፉ ከዝቅተኛው 10% እስከ 49% የደረሰ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት የተጣለበትን የ10% ታሪፍ በፀጋ መቀበሉን ገልጿል!

ከተጣለው አዲስ ታሪፍ ኢትዮጵያ ልታተርፍ የምትችልበት እድል አለ?

ታሪፉን በፀጋ የተቀበሉ፤ አዲስ የመልስ ህግ ያወጡ እና የዛቱ ሀገራትን እንመልከት....

የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የወደፊት እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል እንመልከት....https://youtu.be/5-D8Vav4H7w


#ለመረጃ፡ በሁሉም ሀገራት ላይ አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ!

Показано 20 последних публикаций.