በቻይና የፍቅረኛው እጅ በአፉ ውስጥ ገብቶ አልወጣ ያለው ግለሰብ በህክምና እጇ እንዲወጣ ተደረገለት በቻይና ጂሊን ግዛት ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ያሉ ዶክተሮች አስገራሚ የሆነ ክስተት አጋጥሟቸዋል። አንዲት ሴት አስቂኝ ቪዲዮ ለመቅረጽ ስትሞክር እጇን ወደ ወንድ ጓደኛዋ አፍ ውስጥ ትከታለች።በጂሊን ግዛት ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ሲገቡ የሚታዩት ጥንዶች ፎቶዎች በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ታይተዋል።ግለሰቧ ወደ ፍቅረኛዋ አፍ ውስጥ እጇን ካስገባች በኃላ ለማውጣት ስትሞክር የአፉ ጡንቻ ይደነድን እና እጁ ይጣበቃል።
ወጣቷ ከአፉ ላይ እጇን ለማውጣት ደጋግማ ብትሞክርም ባለመቻሏ የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ትወስናለች።ዶክተሮች ታሪካቸውን እስኪሰሙ ድረስ በጥንዶቹ ግራ ተጋብተው እንደነበር ተሰምቷል። የወንድ ጓደኛዋ ፊት ቀስ በቀስ ወደ እየቀላ እጇን ከአፉ ነፃ ለማውጣት የምታደርገው ጥረት ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ተናግራለች። አፉን መዝጋት ባለመቻሉ እና ከጉሮሮው ያለማቋረጥ አስጨናቂ ድምፅ መውጣት ጀመረ። ይባስ ብሎ በጡንቻው መኮማተር ምክንያት ጥርሶቹ እጆቿ ላይ ተጣበቁ።
ጉዳዩን የተከታተሉት ዶክተር ዣንግ ሚንዩአን እንዳሉት የልጅቷ እጅ ተጣብቆ የቀረው የወንድ ጓደኛዋ የመንጋጋ ጡንቻ በመያዙ አፉን እንይከፍት አድርጎታል።ችግሩን ለመቅረፍ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ልዩ አፍ መክፈቻ መሳሪያ ተጠቅመው መንጋጋውን በማስፋት በተወሰነ ቦታ ላይ ጡንቻን የሚያስታግስ መርፌ ተጠቅመዋል። ከ20 ደቂቃ በኋላ የወጣቷ እጅ እንዲወጣ ተደርጓል። አንድ ሰው መንጋጋውን እንዲከፈት ማስገደድ የነርቭ ጉዳት ወይም የመንገጭላ መበታተን ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
🌹@YEHEM_ALE1🌹
🌹@YEHEM_ALE1🌹